Golden Oil Ministries
Sharing the life of Christ!
05/05/2026
የፍርድ እና የተግሳፅ ዓላማ:- በምን ላይ እንፍረድ? በምንስ ላይ አንፍረድ | ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን | Evangelist Yared Tilahun | Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
03/20/2026
እንደ ይሳኮር ልጆች የዘመኑን የሰዓት እምቢልታ ለይቶ ማወቅ፣ በዚህ ግራ በተጋባ ዓለም ውስጥ የሚገባውን ለማድረግ የሚረዳ ሰማያዊ ጥበብ ነው። በተለይም ዛሬ በምድራችን ላይ የሚታዩትን አስገራሚ የመንፈሳዊ ጸጋ እንቅስቃሴዎች በጭፍን ከመቃወም ወይም ያለ አንዳች ማጣሪያ ከመቀበል ይልቅ፣ መጽሐፍ ቅዱስን እንደ መነጽር በመጠቀም የእግዚአብሔርን እውነተኛ አሻራ መለየት ይገባል። እግዚአብሔር ለካህኑ ለአሮን በደረቱ ላይ እንዲያደርገው የሰጠውና "ብርሃንና እውነት" የተባሉት ኡሪምና ቱሚም፣ ግራ በሚያጋቡ የሕይወት አውድማዎች ላይ መለኮታዊውን ፍርድና ውሳኔ ለመለየት የተሰጡ ሰማያዊ መሣሪያዎች ነበሩ።
ይሁን እንጂ፣ በአዲስ ኪዳን ይህ መለኮታዊ ፍርድና መለያ የሚገኘው ተራራ በመቧጠጥ ወይም አገልጋይ ፍለጋ በመባዘን ሳይሆን፣ በአእምሮ መታደስ በሚገኝ የክርስቶስ ልብ (Mind of Christ) ነው። ይህም የዚህን ዓለም የተሳሳተ የአስተሳሰብ ቀመር በማፍረስ፣ የሰማዩን አዲስ ሕይወት የሚያስተናግድ ንቃተ-ህሊና በመላበስ የሚገኝ የበሰለ ማንነት ነው።
ሆኖም ግን፣ እግዚአብሔር ፈቃዱን እንዲያውቁበት የሰጣቸውን ይህንኑ ቅዱስ ኤፉድ፣ ጌዲዮን ከድል በኋላ ከወርቅ አቅልጦ በሠራውና በራሱ ከተማ ባቆመው ምስል እንደታየው፣ ዛሬም የጸጋ ስጦታዎችና መገለጦች ከባለቤቱ ከእግዚአብሔር ይልቅ ትኩረት ተሰጥቷቸው የሕዝቡ ማሰናከያ "ጣዖት" ሊሆኑ ይችላሉ። ይህም ለአገልጋዩም ሆነ ለቤተሰቡ የማይወጡበት ወጥመድ እና የመንፈሳዊ ምንዝርና ምክንያት የመሆን አደጋ አለው።
ስለዚህ፦
✅ መጽሐፍ ቅዱስ የሚታይ መጽሐፍ ብቻ ሳይሆን፣ ዓለምንና መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎችን የምናይበት "መነጽር" እንደሆነ ተገንዝበን፤
✅ ኡሪምና ቱሚም በእኛ ሕይወት ውስጥ "የታደሰ አእምሮ" ሆነው እንደሚገለጡ በማሰብ፤
✅ የጸጋ ስጦታዎችና መገለጦች እግዚአብሔርን ማሳያ መሆናቸው ቀርቶ የሰው ክብር መገለጫ ሲሆኑ ወደ ጣዖትነት እንደሚለወጡ በማወቅ፤
✅ ታላቅ መንፈሳዊ ድል ካመጣን በኋላም፣ በሠራነው "ኤፉድ" (የስኬት መታሰቢያ) ስውር ወጥመድ እንዳንጠመድ መጠንቀቅ እንደሚገባን እያሰብን፤
በዚህ በመጀመሪያው ክፍል፣ ከቃሉ አገልጋይ ከወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን ጋር ሆነው ይህንን የእግዚአብሔርን ቃል አብረው ይማሩ::
ለሌሎች ማጋራትን አይርሱ 😇
ኡሪምና ቱሚም፦ የዘመኑን መጋረጃ የሚገፍ የእውነት ብርሃን | ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን |By Evangelist Yared Tilahun | እንደ ይሳኮር ልጆች የዘመኑን የሰዓት እምቢልታ ለይቶ ማወቅ፣ በዚህ ግራ በተጋባ ዓለም ውስጥ የሚገባውን ለማድረግ የሚረዳ ሰማያዊ ጥበብ ነው። በተለይም ዛሬ በምድራችን ላይ የሚታዩትን ...
03/06/2026
እግዚአብሔርን መምሰል| ክፍል 3| ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን| By Evangelist Yared Tilahun| Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
03/02/2026
እግዚአብሔርን መምሰል ማለት ከውጪ የሚጫን ሃይማኖታዊ ስርአት ሳይሆን፣ ዓለም ሳይፈጠር የታቀደውና በክርስቶስ በኩል ለሰው ልጆች የተሰጠው መለኮታዊ ህይወት ከውስጥ ወደ ውጭ የሚፈስበት የቅድስና ኑሮ ነው፤ ይህም አንድ መንፈስ ለሁላችን በጋራ ተሰጥቶ እንደ አንድ አካል ብልቶች የሚያስተሳስረን የህይወት ትስስር በመሆኑ፣ በግል ተነጥሎ የሚወሰድ ሳይሆን በጋራ የሚካፈልና ክርስቶስ በስጋ ተገልጦ እንደመጣ ሁሉ እኛም በስጋችን የእርሱን ማንነት የምንገልጥበት ሰማያዊ ጥበብ ነው። እውነተኛ መንፈሳዊነት ውስጡ በምኞት እየተቃጠለ በውጭ ግን መጋባትንና መብልን በመከልከል የሚታይ የግብዝነት ድራማ ሳይሆን፣ የውስጥ ማንነትና የውጭ ገጽታ ተስማምተው የሚታዩበትና ሰውን ከባዶ ተስፋና ከስህተት ትምህርት ነፃ አውጥቶ በህያው አምላክ ተስፋ ወደሚገኝበት እውነተኛ ህይወት የሚያደርስ የእምነት ጉዞ ነው።
ተባረኩበት 😇😇😇
ለሌሎችም ያጋሩት
እግዚአብሔርን መምሰል | ክፍል 2 | በወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን | By EVANGELIST YARED TILAHUN እግዚአብሔርን መምሰል ማለት ከውጪ የሚጫን ሃይማኖታዊ ስርአት ሳይሆን፣ ዓለም ሳይፈጠር የታቀደውና በክርስቶስ በኩል ለሰው ልጆች የተሰጠው መለኮታዊ ህይወት ከውስጥ ወደ ውጭ የሚፈስበ...
02/25/2026
እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።
ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:28-29
ሕያው ድንጋዮች በባለሙያው እጅ | የማይመስለውን የማስወገድ ጥበብ | ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን | ²⁸ እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።²⁹ ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እ....
02/20/2026
የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ፣ ሞትና ሲኦልን ያሸነፈበት መለኮታዊ ጥበብ በገጠር ኢትዮጵያ አውሬን ለማጥመድ እንደሚቀቀል ቀንድ ሁሉ ድንቅ ነው። ሲኦል የክርስቶስን ደካማ ስጋ ዋጥኩ ብላ ብትፈነጥዝም፣ በውስጧ ግን የቀለጠው ቀንድ ቀዝቅዞ ወደ ቀድሞ ጥንካሬው እንደሚመለስ፣ የትንሳኤው ኃይል የሞትን ሆድ ቀዶ በድል ወጥቷል። የሰው ልጅ ውድቀት ከፈጣሪው የተገነጠለበትና "እራሴን በራሴ እመራለሁ" ብሎ ያወጀበት የጥፋት መንገድ ቢሆንም፣ እግዚአብሔር ግን በምህረቱ ሰው በኃጢአቱ ለዘላለም ተጎሳቁሎ እንዳይኖር በሞት ውስጥ ቤዛነትን ሰጠው። ይህም የትንሳኤ ምስጢር በኖህ መርከብ ከጥፋት ውሃ በላይ መነሳት፣ በሙሴ የማይቃጠል ቁጥቋጦ ውስጥ በሚታየው የስጋና የመለኮት መዋሃድ፣ እንዲሁም በአብርሃም የሙት ማህፀን ውስጥ በተገለጠው አዲስ ህይወት በጥላነት ተስሏል። ዛሬም ወንጌል የትንሳኤ ተስፋ ነው፤ እኛም አማኞች የዛሬውን የባህሪ ለውጥና የነገውን የትንሳኤ ክብር ተሸክመን የምንመላለስ፣ ከሞት ፍርሃት ነፃ የወጣን የእግዚአብሔር የኃይል ማዕከላት ነን።
ፀጋ ይብዛላችሁ ተባረኩበት 😇
ለሌሎችም ያጋሩት 😇
የወንጌል ኃይል| ክፍል 2 | ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን | BY EVANGELIST YARED TILAHUN Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
02/10/2026
ውስጥ ተኮር የሚያደርገን፣ ወደ እውነተኛ ደቀመዝሙርትነት የሚያደርሰን፣ የገባንበትን መንግስት ምስጢር እንድናውቅና በመንግስቱ ውስጥ እንድንከብር የሚያስችለን ሕይወት ለዋጭ ትምህርት።
ድርጊቱ ወይንስ ማድረጊያው| Motive | | ክፍል 3| Evangelist Yared Tilahun | ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን |
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the place of worship
Telephone
Website
Address
United States Of America
Silver Spring, MD
20906
02/07/2026