Injibara Communication

Injibara Communication

Share

Injibara communication

Photos from Injibara Communication's post 07/10/2026

"​ዕዙ ተልዕኮውን በድል እየተወጣ ነዉ" የ11ኛ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ

​በደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላምና አካባቢው በግዳጅ ላይ የተሰማራው የ11ኛ ዕዝ ከአካባቢው የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት የጽንፈኛውን ቡድን የጥፋት ሴራ በማክሸፍ ሰላምን እያረጋገጠ እንደሚገኝ የዕዙ የኦፕሬሽን ምክትል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ ተናገሩ።

​የዕዙ ሠራዊት በቁርጠኝነትና በጽናት በመካነ ሰላምና አካባቢው ተደብቆ የሕዝብን ሰላም ለማደናቀፍ በሚጥረው ጽንፈኛ ቡድን ላይ አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ ላይ እንደሚገኝ ምክትል አዛዡ ገልጸዋል።

​ከምሥራቅና ምዕራብ ጎጃም የተወጣጣው ጽንፈኛ ቡድን የባንዳነት ተልዕኮዉን ለመፈጸም ወደ ደቡብ ወሎ ሠርጎ ለመግባት የሞከረበት ዋና ዓላማ የተለመደውን የዘረፋ ተግባር ለመፈጸም እንደሆነም አስረድተዋል።

​ጽንፈኛው ቡድን ከአባቱ ከወያኔ ተልዕኮ ተቀብሎ በጎጃምና በወሎ አዋሳኝ አካባቢዎች ሰላምን ለማደፍረስ የሚያደርገውን ጥረት ሕብረተሰቡ በሚገባ የተረዳው መሆኑን የገለጹት ሜጀር ጄኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ፤ ሕዝቡ ከሠራዊቱና ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር መረጃ በመስጠትና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

​የሠራዊቱን ምት መቋቋም ያልቻለው ይህ የጽንፈኛ ቡድን የሰላም እጁን እስካልዘረጋ ድረስ የትም ይግባ የት ሠራዊቱ ተከታትሎ የመምታትና ሰላምን የማረጋገጥ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የዕዙ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ አረጋግጠዋል።

​በመጨረሻም የደቡብ ወሎ ዞን የመካነ ሰላምና የአካባቢው ሕዝብ ለዕዙ ሠራዊትና ለጸጥታ ኃይሉ እያደረጉ ላሉት ድጋፍ ምክትል አዛዡ ምስጋና አቅርበዋል። ዘገባው የዕዙ የሠራዊት ሥነ-ልቦና ግንባታ ነው።

አማራ ኮሙኒኬሽን

07/10/2026

ኤርትራን ጨምሮ ሌሎች ባእዳን ሀይሎች ከኢትዮጵያ ድንበር በአስቸኳይ እንዲወጡ ኢትዮጵያ አሳሰበች

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ ከብልምበርግ ጋር ባደረጉት ቆይታ ኤርትራ የኢትዮጵያ ግዛት መውረሯን ገልፀዋል።

የአካባቢ ባለሥልጣናትና ነዋሪዎች ለAFP እንደተናገሩት፣ የኤርትራ ወታደሮች በአዲግራት አካባቢ ታይተዋል፤ ከዚያም ወደ ደቡብ፣ ወደ መቀሌ አቅጣጫ ሲንቀሳቀሱ መታየታቸው ተዘግቧል።ከባድ መሣሪያዎችን የያዙ ተሽከርካሪዎችም
ታይተዋል።
በሰሜን ኢትዮጵያ አዲግራት ከተማ ውስጥ የኤርትራ ወታደሮች ሲንቀሳቀሱ መታየታቸውንም የአካባቢ ነዋሪዎችን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።

በትግራይ ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ያሉ የኤርትራ ወታደሮች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ግዛት በአስቸኳይ መውጣት አለባቸው ሲሉ ሚንስተሯ አሳስበዋል።

Photos from Injibara Communication's post 07/10/2026

የመንግስትን የሰላም አማራጭ ጥሪ የተቀበሉ ሀይሎች እጃቸውን ሰጡ።
******,****//**********
በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በዚገም ወረዳ በተሳሳተ መንገድ ተደራጅተው በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው እጃቸውን ሰጠዋል።

የዚገም ወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት እና የሀገር ሽማግሌዎች ባልተገባ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አካላት የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው እጃቸውን በመስጠታቸው አቀባበል አድርጎላቸዋል።

የዚገም ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን በሪሁን ይህን የሰላም አማራጭ ጥሪ የዚገም ወረዳ አስተዳደር ምክርቤቱ መላ አመራሩ ጋር የሀገር ሽማግሌው በየደረጃው ያለው የፀጥታ አካሉ በሰላም ዙሪያ በሰራ ጠንካራ ስራ የመጣ ውጤት መሆኑን ጠቁመው መንግስት አሁንም በተሳሳተ መንገድ የሚንቀሳቀሱ አካላትን ለመቀበል በሩ ክፍት በመሆኑ ሌሎች አካላትም እጅ በመስጠት ለህዝባችን ዘላቂ ሰላምና ልማት የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት አለባችሁ ብለዋል።

አቶ ጥላሁን አያይዘውም የአካባቢውን ፀጋ መሠረት ባደረገ መንገድ የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚ በማድረግ ህይወታቸውን እንዲመሩ መንግስት በትኩረት እንደሚሰራም አስገንዝበዋል።

የመከላከያ ሰራዊት አዛዥ መቶ አለቃ ሃይማኖት አያሌው በበኩላቸው በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ወደ አልሆነ ቦታ ወጥተው የነበሩ አካላት መንግስት ችግሮችን በጠረጴዛ ዙሪያ በውይይት በመፍታት በሀገሪቱ ሰላም ማስፈን አለብን ብሎ ባስቀመጠው መሠረት የሰላም ተዋናይ ሁነው የመጡ አካላትን አመስግነዋል።

ዛሬ ላይ የሰላም አማራጭ የተቀበላችሁ አካላት ከፀጥታ መዋቅሩና ከአመራሩ ጎን ሁናችሁ አሁንም ያልተመለሱ ወንድሞቻችሁን በመምከር እንድትመልሱ ትልቅ አደራ አለባችሁ ሲሉ መቶ አለቃ ሃይማኖት አሳስበዋል።

የሀገር ሽማግሌዎችም ግጭት በውይይት እንጅ በጦርነት እንደማይፈታ ጠቁመው በይቅርታ ወደ ሰላም መንገድ የመጡ አካላትን ከልብ አመስግነዋል።

እጅ የሰጡ አካላትም በማወቅም ባለማወቅም የበደልነውን ህዝብ ይቅርታ እየጠየቁ እንደሚክሱም ቃል ገብተዋል። በቀጣይም በየትኛውም መንገድ ከመንግስት ጎን በመሆን ለመስራት ዝግጁ ነን ሲሉም ገልፀዋል።
Zigem communication

Photos from Injibara Communication's post 07/10/2026

🔔 የሰላም ጥሪው ደወል ቀጥሏል፤ ለሰላም የተዘረጉ እጆች አኹንም አልታጠፉም 🕊️

በአማራ ክልል የተከሰተውን ግጭት እና የሰላም መደፍረስ በውይይት እና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት፣ ዘላቂ ሰላምንም ለማጽናት መንግሥት የሰላም በሩን ክፍት አድርጎ ቆይቷል።

ይህን የሰላም ጥሪ በመቀበል የክልሉን እና የሀገርን ሰላም አስቀድመው የጦርነትን መንገድ የተሰናበቱ በርካታ የቀድሞ ታጣቂዎች በአሁኑ ወቅት የተረጋጋ ሕይወት ከመምራት ባለፈ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እየኾኑ ይገኛሉ።

በውይይት እና በድርድር ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የቀረበው ጥሪ አሁንም አልተቋረጠም።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በመደመር መንግሥት ምሥረታ ላይ ባደረጉት ንግግር ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት ያላት፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነቷ የጸና፣ የአዲስ ሥልጣኔ ባለቤት እና ፈር ቀዳጅ የኾነች አይበገሬ ኢትዮጵያን መገንባት እንደሚገባ ገልጸዋል።

ይህም የሚሳካው ችግሮችን በውይይት እና በንግግር መፍታት ሲቻል እንደኾነ አንስተዋል። "በጫካ ያላችሁ እና ያኮረፋችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖች ወደ ሰላማዊ መንገድ ኑ፤ የይቅርታን መንፈስ ተላብሳችሁ በሀገር ግንባታ ተሳተፉ፤ ሀገርንም አስቀጥሉ" ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በአማራ ክልል የመንግሥት ምሥረታ ባደረጉት ንግግር ክልሉ ላለፉት ሦሥት ዓመታት ከተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች እና ግጭቶች ካለፈ በኋላ የተገኘው ትምህርት "በጠላትነት እና በግጭት አሸናፊ አለመኖሩን ነው" ብለዋል።

በጦር መሣሪያ ድምጽ የሰዎች መረበሽ፣ የሕይወት መጥፋት፣ የንብረት ውድመት እና የሕዝብ መፈናቀል የትኛውንም ያህል ምክንያት ቢቀርብለት ዘላቂ መፍትሔ ሊኾን እንደማይችል አንስተዋል።

ግጭት ተስፋን የሚያስቆርጥ፣ የዕድገት እና የመለወጥ ዕድሎችን የሚዘጋ፣ እናቶችን በሐዘን የሚያመሰቃቅል፣ የክልሉን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መሠረት የሚያፈርስ መኾኑን የገለጹት ርእሰ መሥተዳድሩ በክልሉ እየተካሄደ ያለው ግጭት እና ደም መፋሰስ በአስቸኳይ እንዲቆምም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በተለይም በጫካ ኾነው መሣሪያ ያነሱ አካላት የሕዝብን ሰላም ማስቀደም እንዳለባቸው እና ከሀገር ጠላቶች ጋር መተባበር በታሪክ ፊት የሚያዋርድ ተግባር መኾኑን አሳስበዋል።

በውስጥ ቅሬታ እና ጥያቄዎች ቢኖሩም ዘላቂ መፍትሔ የሚያገኙት በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ ውይይት ብቻ እንደኾነ ጠቅሰዋል። ወጣቶች የነገዋን ሀገር የሚገነባ አቅም መኾን እንጂ የግጭት ሰለባ መኾን እንደሌለባቸው ገልጸዋል።

መንግሥት እና ማኅበረሰቡ ለሰላም የዘረጉትን የድርድር፣ የውይይት እና የሰላም ጥሪ በመገንዘብ ሁሉም አካላት ከእንደዚህ ዓይነት ድርጊቶች ሊቆጠቡ ይገባል። ኅብረተሰቡም ከመምከር እስከ መገሠጽ፣ ከማሸማገል እስከ ማደራደር ያለውን ሚና እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ሀገርን ማጽናት እና ለባዕዳን አሳልፎ አለመስጠት ታላቋን ኢትዮጵያ ለመገንባት መሠረት እንደኾነም ተመላክቷል።

!

!🇪🇹



የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Photos from Injibara Communication's post 07/10/2026

የተፈጥሮ ማዳበሪያ ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ ባሻገር የአፈር ለምነትን ለመጨመር ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ ።
መስከረም 27/2019 ዓ/ም( አዊ ኮሙኒኬሽን )በ2019 ዓ/ም 5 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሜትር ኩብ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ኮምፖስት ለማዘጋጀት አቅዶ እየሰራ መሆኑን የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ግብርና መምሪያ አስታውቃ ።

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ቤዛዊት ጌታሁን በሰጡት መግላጫ በየደረጃው የሚገኙ
የግብርና ተቋም አመራሮችና ሠራተኞች
ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ አርሶ አደሮች የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግና የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ አቅደው እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል ።

በብሔረሰብ አስተዳደሩ ተፈጥሮን በተፈጥሮ ለማከም በተያዘው በጀት ዓመት 5 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሜትር ኩብ የተፈጥሮ ማዳበሪያ እና 25 ሺህ ኩንታል ቨርሚ ኮምፖስት ለማዘጋጀት ታቅዶ እስከ አሁን 2 ነጥብ 57 ሚሊዮን የተፈጥሮና 9 ሺህ 170 ኩንታል ቨርሚ ኮምፖስት ማዘጋጀት መቻላቸውን
መምሪያ ኃላፊዋ ገልፀዋል ።

አሲዳማ መሬትን ለማከምና ምርትን ለመጨመር የብሔረሰቡ አስተዳደር አርሶአደሮች የተፈጥሮ ማዳበሪያ በስፋትና በጥራት አዘጋጅተው እንዲጠቀሙ በሁሉም ወረዳዎች የግንዛቤ ትምህርት ተሰጥቶ ወደ ተግባር መግባታቸውን የገለፁት ወ/ሮ ቤዛዊት ቨርሚ ኮምፖስትን በስፋት ለማዘጋጀት የግብርና ቢሮ በገነባላቸው ማዕከላት 25 ሺህ ኩንታል ለማዘጋጀት አቅደው እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል ።

የበጋ መስኖ በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በስፋት የሚለማ በመሆኑ በየደረጃው የሚገኙ የግብርና ባለሙያዎች ሁሉም አርሶአደሮች የተፈጥሮ ማዳበሪያ ኮምፖስት በጥራት አዘጋጅተው እንዲጠቀሙ ድጋፍና ክትትል እንዲያደርጉ መምሪያ ኃላፊዋ ጥሪ አስተላልፈዋል ።
Awi communication

Photos from Injibara Communication's post 07/10/2026

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ወቅታዊ የፀጥታና የልማት ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ።

የውይይት መድረኩን ከአማራ ክልል የመጡ ደጋፊ አመራሮች አቶ አዲሱ በየነና አቶ ደሳለኝ አለምነህ መርተውታል።

የውይይት መድረኩ እንደ ሀገር ያገጠመውን ጦርነት በድል ለማጠናቀቅና ልማቱ ሳይስተጓጎል ለማስቀጠል ዓላማ ያለዉ ነው፡ ፡

የውስጥ ባንዳዎችና የውጭ ባዳዎች በማቀናጀት የከፈቱትን ጦርነት ከመላ ኢትዮጵዊያን ጋር በአንድነት ለመደምሰስና በድል ለማጠናቀቅ የጋራ ተደርጓል።

የብሔረሰብ አስተዳደሩ ህዝብ የጋራ ጠላቶችን ለመደምሰስ ከሀገር መከላከያ ሠራዊትና ከፀጥታ አካላት ጎን መሆንና በአይነት፣ በገንዘብና አቅም በፈቃዳቸው ሁሉ ድጋፍ እንዲያደረጉ ማስገንዘብ እንደሚገብ የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

ሁሉንም አከባቢዎች ከፅንፈኖች ነፃ በማደረግ ሁሉም የመንግስት ተቋማት ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡና በሁሉም ትምህርት ቤቶች መማር ማስተማር ማካሄድ እንዳሚገባ በውይይቱ ተነስቶል።

በየአካባቢው የሚስተዋሉ ሌብነትንና ብልሹ አሰራሮችን መከላከል፣ ማረምና ተጠያቂ እንዲሆኑ በህግ ማጋለጥ እንደሚገባ ውይይት ተካሂዷል።

በየደረጃው የሚፈጠሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታትና ዜጎችን የሚያረካ ጥራት ያለው ፣ ፈጣንና ቀልጠፋ አገልሎት መስጠት እንዳለበት ተገልፆል።

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ አየን ብርሃን በብሔረሰብ አስተዳደሩ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈንና ልማትን ለማፋጠን ቀን ከሌት እንደሚሰሩ አንስተው ህዝቡ ልማት ወዳድ፣ ህግ አክበሪና ለመንግስት ታማኝ በመሆኑ ተገቢዉን አገልሎት ለመስጠት ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ልማትን ለማፋጠንና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የህዝብ መድረክ ቀጣይ ለመፍጠር እቅድ እንዳላቸው የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው ነፍጥ አንግበው ጫካ ከሚገኙት ወገኖች ጋር ዘላቂ ሰላሞን ለመፍጠርና ችግሮችን በውይይት ለመፍታት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በብሔረሰብ አስተዳደሩ በአዲስ የተደራጃውን ከፍተኛ አመራርሮች ወደ ስራ እንዲገቡ አመራሩና ህዝቡ በማገዝና በመደገፍ ሰላምን ማስፈንና ልማትን ማስቀጠል የሚያስችል የቀጣይ አቅጣጫ በመስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል።
Awi communication

Photos from Injibara Communication's post 06/10/2026

ዜጎችን ከድህነት አዙሪት አላቆ በዘላቂነት ራሳቸውን የቻሉ ማድረግ የትኩረታችን ማዕከል ነው! ወ/ሮ ልዩ ወርቅ ጌታሁን
የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ምግብ ዋስትናና ሴፍቲኔት ጽ/ቤት የ1ኛ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀሙን ከቴክኒክ ኮሚቴ አባላት እና አጋር ተቋማት ጋር በመሆን ገመገመ! በዚሁ መድረክ ላይ በ1ኛ ዙር ተመርቀው የወጡ የአካባቢ ልማት የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎችን የኑሮ ደረጃ ለመገምገም የተደረገ የዳሰሳ ጥናት ውጤት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ልዩ ወርቅ ጌታሁን እንደተናገሩት፤ የሴፍቲኔት መርሐ-ግብር ዜጎች በዕለት ተዕለት ድጋፍ ብቻ ተወስነው እንዲቀሩ የሚያደርግ ሳይሆን፣ በሂደት አቅማቸውን ገንብተው ከድህነት እንዲላቀቁ እና በራሳቸው እግር እንዲቆሙ የሚያስችል ትልቅ ሀገራዊ ራዕይ ያለው ስራ መሆኑን ገልጸዋል።

የእንጅባራከተማ ከተማና መሠረተ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ የቆዬ ጥላሁን እንደተናገሩት፤ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎችን አቅም ማጎልበት እና ከድህነት ወጥተው የኢኮኖሚ ባለቤት እንዲሆኑ ማድረግ የሚቻለው በተቀናጀ የባለድርሻ አካላት ስራ እና በክህሎት ልማት ላይ ትኩረት ሲደረግ መሆኑን ጠቁመው፣ መምሪያው ከጽ/ቤቱ ጋር በመቀናጀት የሚጠበቅበትን ድርሻ እንደሚወጣ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ዋና ከንቲባ አቶ ኑርልኝ ሰውነት እንደገለፁት፤ ከተማችንን ከምግብ ዋስትና እጦት ነፃ ለማውጣት እና የነዋሪዎቻችንን ኑሮ በዘላቂነት ለማሻሻል በሚደረጉ ጥረቶች የሴፍቲኔት ስራዎች የማይተካ ሚና አላቸው። ከድህነት ተመርቀው የወጡ ዜጎች በዘላቂነት ጸንተው እንዲቆሙ ከተማ አስተዳደሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት የሩብ ዓመቱ አፈፃፀም ላይ የታዩ ጠንካራ ጎኖች ተጠናክረው፣ ክፍተቶች እንዲስተካከሉ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል!

Photos from Injibara Communication's post 06/10/2026

የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅና የምክር ቤት ውይይት ተካሄደ።
እንጅባራ መስከረም 26/01/2019ዓ/ም (እንጅባራ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን)
የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም መነሻ በማድረግ፣ የ2019 በጀት ዓመት ዋና ዋና የሥራ ዕድል ፈጠራ ግቦችንና መመሪያዎችን መሠረት ያደረገ ሰፊ የዕቅድ ኦሬንቴሽን ለከተማውና በቀበሌ ደረጃ ለሚገኙ አመራሮች ሰጥቷል።

ይህ ከፍተኛ አመራሮችና የምክር ቤት አባላት የተሳተፉበት የምክር ቤት ውይይት በከተማው ዋና ከንቲባ የተመራ ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱ ሊከናወኑ በሚገባቸው ዋና ዋና አቅጣጫዎች ላይ ቁልፍ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።

የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አመለወርቅ አናጋው እንደገለጹት፤ ይህ የዕቅድ ትውውቅ መድረክ የ2019 በጀት ዓመትን የእንጅባራ ከተማ ወጣቶች የሥራና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥበት ዓመት ለማድረግ ትልቅ መነቃቃትን የፈጠረ ነው ብለዋል።

የከተማው ዋና ከንቲባ አቶ ኑርልኝ ሰውነት በሰጡት ማጠቃለያ አቅጣጫ፤ በከተማችን ውስጥ የሚፈጠሩ ማናቸውም የሥራ እድሎችና አዳዲስ የኢኮኖሚ ዘርፎች ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊደገፉ እንደሚገባ አሳስበው፤በያዝነው የ2019 በጀት ዓመት በቋሚነት ለ6,505 እንዲሁም በጊዜያዊነት ለ1,626 በድምሩ ለ8,131 ሥራ ፈላጊ ወጣቶችና ዜጎች አስተማማኝ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የተቀናጀ ርብርብ ይደረጋል ብለዋል።

አያይዘውም ዋና ከንቲባው ሁሉም የመንግሥትና አጋር ተቋማት በተሰጣቸው ግልጽ ዕቅድ መሠረት የሥራ ዕድል የመፍጠር ድርሻቸውን በውጤታማነት የመወጣት ግዴታ አለባቸው ብለዋል።

በመጨረሻም በእንጅባራ ከተማና አካባቢዋ የሚገኙ ተፈጥሯዊና ኢኮኖሚያዊ ጸጋዎችን አጣጥሞ በመጠቀም ለወጣቶች የሥራ ዕድል ማስፊያ ማድረግ ይገባል ሲሉ በኦፅዕኖት ተናግረዋል።

የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ስራ ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ታፈረ ከበደ እንደተናገሩት ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴና ዕድገት በሚያመጡ ዋና ዋና የሥራ ዘርፎች ላይ አትኩሮ ይሰራል ብለው፤ለተለያዩ የሥራ እድሎች የተዘጋጁ የማስሪያና መሸጫ ቦታዎች (ሼዶች) ለተመደበላቸውና ለተሰጣቸው ትክክለኛ አገልግሎት ብቻ እንዲውሉ ጥብቅ ክትትል ይደረጋል ብለዋል።
የውይይት ሰነዱን የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ም/ኃላፊው አቅርበዋል።

Photos from Injibara Communication's post 05/10/2026

የእንጅባራ ከተማ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሹመት አፀደቀ።
የእንጅባራ ከተማ ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛዙር 47ኛ መደበኛ ጉባኤ አቶ መሃሪ የኔትን የከተማው ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ ሾመ ።
እንጅባራ መስከረም 25/2019ዓ/ም (እንጅባራ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን)

Photos from Injibara Communication's post 05/10/2026

የእንጅባራ ከተማ ምክር ቤት የ2019 በጀት ዓመት አጠቃላይ የስራ ማስኬጃ እና የልማት በጀት ሰነድ በመመርመር ድምር 1 ቢሊዮን 573 ሚሊዮን 849 ሺህ 496 ብር አፅድቋል።

የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ተስፋሁን ዋሴ በበኩሉ፦ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የጸደቀው በጀት ከተማዋን የንግድና የልማት ማዕከል ለማድረግ ያላት አቅም እያደገ መምጣቱን የሚያሳይ በመሆኑ፣ የተመደበውን በጀት ፍትሃዊና ግልጽ በሆነ አሰራር በመጠቀም ህዝብን በታማኝነት ለማገልገል ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።

ጽ/ቤቱ ኃላፊው አያይዘውም፣ የውስጥ ገቢ አሰባሰብ አቅምን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማሳደግ የከተማዋን የራስ አገዝ አቅም ማጠናከር እና የተጀመሩ ሁለገብ የልማት ስራዎችን ጥራታቸውን ጠብቀው በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ ማድረግ የትኩረት አቅጣጫቸው እንደሆነ አስገንዝቧል።

Telephone

Website

Address


Awi Zone Injibara
Injibara

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Injibara Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Subscribe

We will notify you when anything happens in Injibara.