HU FM 91.5 RADIO

HU FM 91.5 RADIO

Share

Haramaya University Community Radio Station

Photos from HU FM 91.5 RADIO's post 08/10/2026

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለተቀጠሩ አዲስ መምህራን ሲሰጥ የቆየው የኢንዳክሽን ስልጠና ተጠናቀቀ

በዋናው ግቢ እና በቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት አዲስ ለተቀጠሩና ከትምህርት ለተመለሱ 59 መምህራን ለ 14 ቀን መሰጠቱ ታውቋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የትምህርትና ስነባህሪ ኮሌጅ ዲን ዶክተር ጣሰው መዝገቡ ስልጠናው የትምህርት አሰጣጥ (ፔዳጎጂ) ክህሎት ፣ መማር ማስተማር ፣ የመማሪያ ክፍል ውስጥ አስተዳደርና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን አዲስ ተቀጣሪ መምህራን ክህሎት አግኝተው ወደ ማስተማር ስራ እንዲገቡ ታስቦ ስልጠናው መሰጠቱን ተናግረዋል ።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የከፍተኛ ትምህርት ስነማስተማር ፕሮግራም (PHDP) አስተባባሪ መምህር ዘነበ አቦሰጥ እንዳብራሩት በቴክኖሎጂ ተቋምና በዋናው ጊቢ ስልጠናው መሰጠቱንና 14 ሴቶችና 45 ወንዶች በአጠቃላይ 59 መምህራን መሳተፋቸውን አብራርተዋል።

መምህር ዘነበ አክለውም በተመረቁበት መስክ ያላቸውን ዕውቀት በሚገባ ለተማሪዎች ለማስተላለፍ እንዲችሉ ተማሪ ተኮር የትምህርት አሰጣጥ መስጠት የሚችሉባቸውን የትምህርት አሰጣጥ መንገዶች በተመለከተ ለ14 ቀን ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን ከተከታተሉት መካከል የኤሌክትሪካልና ኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ መምህርት ሰላም እንግዳና ዶክተር ካሳ ባዩ ስልጠናው ቀጥታ ወደ ማስተማር ከመግባታችን በፊት መሰጠቱ ተገቢ መሆኑንና የማስተማር ክህሎት ማግኘታቸውን ጠቁመው ስልጠናው ቀደም ቢልና ለቴክኖሎጂ ሰፋ ያለ ግዜ ቢሰጥ መልካም ነው ብለዋል።

ስልጠናው በዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምሩ መምህራን በሙሉ በትምህርት አሠጣጥ ዙሪያ የማስተማር ስራ ከመጀመራቸው በፊት እንዲወስዱት የሚደረግ መሆኑንና ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በየዓመቱ እየሰጠው የሚገኝ ስልጠና መሆኑ ተገልጿል።

ዘጋቢ፡- ሀብታሙ ኃ/ጊዮርጊስ
ፎቶግራፈር፡- ቴዎድሮስ ሊሻን

08/10/2026
Photos from HU FM 91.5 RADIO's post 07/10/2026

Yuunivarsiitii Haramaayaatti Leenjiin Ijaarsa Dandeeytii Barsiisotaa fi Hoggantoota barnootaa Manneen Barnootaa Sadarkaa 2ffaa Baha Itoophiyaaf kennamaa ture Xumuramee

Itoophiyaatti kenniinsa sirna barnootaa gahumsa irratti bu'uureffate jajjabeessuuf yuunivarsiitii Haramaayaatti kennamaa kan ture leenjiin ijaarsa daandeeytii barsiisotaa fi hoggantoota roga barnootaa manneen barnootaa sadarkaa 2ffaa xumuramuun isaa ibsamee.

Sagantaan leenjii ijaarsa dandeeytii kun deggarsa maallaqqqaa fawundeeshinii Master kard (Master Card) irraa argameen waggoota shaniif kan turu yoo ta'u akka sadarkaa biyyaalessaattiis M/B sadarkaa 2ffaa 700 kessatti qulqullina barnootaa mirkanessuuf kayyeffate kan hojjachaa jiruu dha.

Sagantaa kana dhaabbileen mit-mootummaa Jenevaa Globaal (Geneva Global ), Immajin waan deey (Imagine 1 Day) fi Idukeshinal developmant tirast (Educational Development Trust) M/B kanneen addaan qoddachuun sagantaa leenjii ijaarsa dandeeytii kana hojirra oolchaa jiruu.

Yuunivarsiitii Haramaayaatti hogganaan kolleejii barnootaa fi yaad-qalbii Doktar Xaasaw Mazgabuu akka dubbatanittiis dhaabbatni mit-mootummaa Jeenivaa Globaal (Geneva Global ) kilaastara baha Itoophiyaa jalatti M/B sadarkaa 2ffaa barattoota kutaa 12ffaa gara yuunivarsiitii hin dabarsin kan Godina Harargee Bahaa fi Lixaa, Naannoo Hararii, Bulchiinsa Magaalaa Dirre Dawaa fi Naannoo Soomaalee jiran fi akka biyyaattiis M/B sadarkaa 2ffaa barattoota tokkollee gara yuunivarsiitii hin dabarsin 230 ta'an dabalatee barsiisotaa fi hoggantoota barnootaa isaanii dandeeytii qaban akka gabbifatan xiyyeffannoon hojjatamaa jira jedhan.

Doktar Xaasaw itti dabaluun akka dubbatanittiis leenjiin ijaarsa dandeeytii yuunivarsiitii Haramaayaa waliin ta'uun kenname rakkoowwan qulqulina barnootaa turan furuuf leenjii abdiin guddaan irraa eeggamu ta'uu ibsaniiruu.

Leenjii kana irrattiis Biiroo Barnoota Oromiyaatti Daayirektara sagantaa barnoota M/B sadarkaa 2ffaa kan ta'an Obbo Mangistuu Lataa akka jedhanittiis meeshaaleen deggarsa barnootaa barbaachisan guutamaniis yoo dandeeytiin barsiisotaa hin ijaaramne bu'aan qulqullina barnootaan eegamu akka dhufuu hin dandeenye eeruun leenjiin kun qaama rakkoo isa ijoo ta'e gahumsa barsiisotaa cimsuu keessatti shoora olaanaa taphata jedhaniiruu.

Qindeessaan Jenevaa Globaal (Geneva Global ) sagantaa barnootaa dandeeytii bu'uura godhate kilaastara baha Itoophiyaa Obbo Bashir Abdi Raadiyoo Hawaasa yuunivarsiitii Haramaayaa FM HU 91.5 niif akka ibsanittiis kaayyoon sagantaa leenjii ijaarsa dandeeytii kennamaa jiru kanaa barattoota M/B sadarkaa 2ffaa dhibbentaa 10 gara yuunivarsiitii akka dabran godhuu, dhibbentaan 30 immoo gara dhaabbata leenjii tekniikaa fi oogummaa akka seenan taasisuu fi dhibbentaan 60 gara hojiitti yeroo galan beekumsa Xabboo fi dandeeytii hojii gahoomaa akka qabaatan kan godhu tahuu himaniiruu.

Kilaastara Baha Itoophiyaatti qindeessan sagantaa hoggansa barnootaa Doktar Maaruf Abdallaa akka ibsanitti leenjiin ijaarsa dandeeytii gahooma bu'uura godhate barsiisotaa fi hoggantoonni sirna barnootaa beekumsa leenjicha irraa argataniin mala baruu fi barsiisuu barataa giddu-gala godhate qabatamaan hojiitti kan galchu ta'uu dubbataniiruu.

Kuniis jedhan Doktar Maaruf rakkoowwan qulqullina barnootaa ijoo ta'an bu'uura irraa furuun M/B barattoota tokkollee gara yuunivarsiitii dabarsuu dadhaban leenjiin kun bu'a qabeessa akka isaan godhu addessaniiruu.

Leenjisaa leenjii kanaa kan ta'an yuunivarsiitii Haramaayaatti barsiisaan kolleejii barnootaa fi yaad-qalbii Doktar Mahammad Abdoo Hassan akka ibsanittiis leenjii kanaan mata dureewwan mala guddina oogummaa barsiisotaa itti fufaa ta'e cimsuu, kenniinsa barnootaa gahooma qabu fi beekumsa Xabboo bu'uureffate, madaallii barattootaa fi hirmaannaa dubartootaa cimsuu mata dureewwan jedhanii fi kanneen hafan biroo irrattiis leenjiin kennamuu dubbatan.

Hirmaattoota leenjii dubbifne Harargee bahaa fi lixaa, Naannoo Hararii fi Bulchiinsa Dirre Dawaa irraa barsiisotaa fi hoggantoota barnootaa M/B sadarkaa 2ffaa fi qophaa'inaa akka dubbatanitti beekumsa, dandeeytii fi hubannoo leenjii kana irraa arganne waggoottan dabran hojmaataa fi gufuuwwan barattoota gar yuunivarsiitii dabarsuu dadhabuu turan jijjiiruun bu'aa roga barnootaa foyya'aa ta'e galmessisuuf leenjii nu dandeessisu dha jedhan.

Mastar Kaard ( Master Card) fawundeshiniin Itoophiyaatti foyyaa'insa qulqullina barnootaa fiduuf deggarsa godhaa jiru fi pirojaktiin qulqullina barnootaa hunda galeessa ta'e kun hanga A.L.A 2030 tti cimee kan itti fufu ta'uun bekkameeraa.

Gabaasni kan :- Damooz Yaaqoobi
Ogeesaa Suuraa :- Fu'ad Ahamad Ali
Fuulbana 25/2019

07/10/2026

Second Round Vacancy Announcement

Photos from HU FM 91.5 RADIO's post 06/10/2026

መምህራን የሒሳብ ትምህርትን ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ጋር አያይዘው ሊያስተምሩ ይገባል ተባለ

መምህራን የሒሳብ ትምህርትን ከሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢንጂነሪንግ ጋር አያይዘው ሲያስተምሩ ተማሪዎች የትምህርቱን ተግባራዊ ጠቀሜታ ተረድተው ለዘርፉ ያላቸውን ፍላጎት እንዲያዳብሩ እንደሚያስችላቸው ተገለጸ።

ይህ የተገለጸው በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ተሳትፎና ኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት፣ በማያ ከተማ ከሚገኙ 20 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተወጣጡ የሒሳብ መምህራን በተሰጠ ስልጠና ወቅት ነው።

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግና ሒሳብ ማዕከል አስተባባሪ ዶክተር ሔኖክ ደሳለኝ በስልጠናው ወቅት እንዳሉት፣ እንደ ሀገር ለሳይንስ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።ይህን እየተሰራ ያለውን ስራ ለተማሪዎች በማስተላለፍ የሳይንስ ትምህርት ፍላጎታቸውን ማሳደግ ይገባል ብለዋል።

በተማሪዎች ዘንድ "የሒሳብ ትምህርት ከባድና አስቸጋሪ ነው" የሚለውን የተሳሳተ እሳቤ ለመቀየር ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ ሒሳብን ከዕለት ተዕለት ሕይወታቸው ጋር አያይዘው በተግባር እንዲማሩ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ሒሳብ ለሳይንስ መሰረት መሆኑን የጠቀሱት በዩኒቨርሲቲው የሒሳብ ትምህርት ክፍል መምህር ዶክተር ግርማ ታፈሰ መምህራን ትምህርቱን ከሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢንጂነሪንግ ጋር አያይዘው ሲያስተምሩ ተማሪዎች ሒሳብ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ያለውን ተግባራዊ ጠቀሜታ እንዲገነዘቡና ለሳይንስ ያላቸውን ፍላጎት እንዲያዳብሩ ያስችላቸዋል ብለዋል።

የስልጠናው ተሳታፊ መምህራን በበኩላቸው የተማሪዎችን የሒሳብ ትምህርት መሰረት ለማጠናከር ትምህርቱን ከተግባራዊ ምሳሌዎች ጋር ማያያዝ እንደሚገባ ከስልጠናው መገንዘባቸውን ገልጸው በቀጣይም ያገኙትን ግንዛቤ በተማሪዎቻቸው ዘንድ በተግባር ለመተግበር ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ባሳለፍነው ሳምንት የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፣ በሐረሪ ክልልና በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ 150 መምህራን ብቃትን መሰረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠቱ የሚታወስ ነው።

ዘጋቢ፤ አሸናፊ ከበደ
ፎቶ ግራፈር፤ ቴድሮስ ሊሻን
መስከረም 2019 ዓ.ም.

Photos from HU FM 91.5 RADIO's post 05/10/2026

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የቆየው የምስራቅ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን እና አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ


በኢትዮጵያ ብቃትን መሰረት ያደረገ የትምህርት አሰጣጥ ስርዓትን ለማጠናከር በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የቆየው የምስራቅ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን እና የትምህርት አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ።


ይህ የአቅም ግንባታ ፕሮግራም ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚከናወን ሲሆን በአገር አቀፍ ደረጃ በሚገኙ 700 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያለመ ነው።


ፕሮግራሙን ጄኔቫ ግሎባል (Geneva Global) ፣ ኢማጂን ዋን ዴይ (Imagine 1 Day) እና ኢዱኬሽናል ዲቨሎፕመንት ትረስት (Educational Development Trust) የተሰኙ ግብረሰናይ ድርጅቶች ትምህርት ቤቶችን ተካፍለው በመተግበር ላይ ይገኛሉ።


በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት እና ስነ-ባህሪ ኮሌጅ ዲን ዶክተር ጣሰው መዝገቡ እንደገለጹት ጄኔቫ ግሎባል በምስራቅ ክላስተር ስር የሚገኙ የምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፣ የሐረሪ ክልል፣ የድሬዳዋ አስተዳደር እና የሶማሌ ክልል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ ተማሪዎቻቸውን ወደ ዩኒቨርሲቲ ማሳለፍ ያልቻሉ 231 ትምህርት ቤቶችን በመለየት የመምህራንና አመራሮችን አቅም የመገንባት ስራ እያከናወነ ይገኛል። ዶክተር ጣሰው አክለውም ከዩኒቨርሲቲው ጋር በመተባበር የተሰጠው ይህ ስልጠና በትምህርት ጥራት ላይ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን ለመቅረፍ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት መሆኑን ተናግረዋል።


በስልጠናው ወቅት የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ ለታ በበኩላቸው የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች ባስፈላጊው መጠን ቢሟሉም የመምህራን አቅም ካልጎለበተ የሚፈለገው ውጤት ሊመጣ እንደማይችል ጠቁመው ይህ ስልጠና የችግሩ ዋና አካል የሆነውን የመምህራንን ክፍተት በመሙላት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።


የምስራቅ ክላስተር ጄኔቫ ግሎባል ብቃትን መሰረት ያደረገ የትምህርት ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ በሺር አብዲ ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ሬዲዮ (ሐዩ ኤፍ ኤም 91.5) በሰጡት አስተያየት የፕሮግራሙ ዋና አላማ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎችን 10 በመቶ ወደ ዩኒቨርሲቲ ፣ 30 በመቶ ወደ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት እንዲያልፉ ማድረግ እንዲሁም 60 በመቶ የሚሆኑትን ደግሞ ወደ ስራው አለም ሲቀላቀሉ አገር በቀል እውቀትና ተግባራዊ ክህሎት እንዲኖራቸው ማስቻል እንደሆነ አስረድተዋል።


በኢትዮጵያ የምስራቅ ክላስተር የትምህርት አመራር ፕሮግራም አስተባባሪ ዶክተር ማሩፍ አብደላ እንደገለጹት ብቃትን መሰረት ያደረገው ይህ የአቅም ግንባታ ስልጠና መምህራንና አመራሮች ያገኙትን እውቀት ተማሪን ማዕከል ያደረገ የማስተማር ዘዴ ላይ እንዲያውሉ የሚያስችል ነው። ይህም በትምህርት ጥራት ላይ የሚስተዋሉ መሰረታዊ ችግሮችን በመቅረፍ ከዚህ ቀደም አንድም ተማሪ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ማሳለፍ ያልቻሉ ትምህርት ቤቶችን ውጤታማ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።


የስልጠናው አሰልጣኝ እና በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት እና ስነ-ባህሪ ኮሌጅ መምህር ዶክተር መሐመድ አብዶ ሀሰን እንደተናገሩት ስልጠናው የመምህራንን ቀጣይነት ያለው ሙያዊ እድገት የሚያጎለብቱ የስነ-ዘዴ፣ የብቃትንና አገር በቀል እውቀትን መሰረት ያደረገ ትምህርት አሰጣጥ፣ የተማሪዎች ምዘና እንዲሁም አካታችነትንና የሴቶችን ተሳትፎ የሚያጎለብቱ ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮችን ያካተተ እንደነበር ገልጸዋል።


በስልጠናው ላይ ያናገርናቸው ከምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ከሐረሪ ክልል እና ከድሬዳዋ አስተዳደር የተወጣጡ የመሰናዶና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ከስልጠናው ያገኙት እውቀትና ክህሎት ባለፉት ዓመታት ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርሲቲ ለማሳለፍ እንቅፋት የሆኑ አሰራሮችን በመቀየር የተሻለ የትምህርት ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚረዳቸው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።


ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን በትምህርት ጥራት ማሻሻል ላይ የሚያደርገው ይህ ድጋፍ እና አጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮጀክት እስከ እ.ኤ.አ 2030 ድረስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል።

ዘጋቢ፦ ደሞዝ ያዕቆብ
ፎቶግራፈር፦ ፉአድ አህመድ አሊ
ቀን፦ መስከረም 24/2019 ዓ.ም

Photos from HU FM 91.5 RADIO's post 05/10/2026

በ2019 ዓ.ም አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች

Photos from HU FM 91.5 RADIO's post 03/10/2026

!
!

Yuunivarsiitiin Haramaayaa Baga ayyaana Irreechaaf nagaaan ittiin isin gahe jechuun hawwii gaarii isaa ibsaa.
እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ ዩኒቨርሲቲያችን መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡

Ayyaanichi maatii , firaa fi hawaasa hundaafu kan nagayaa, fayyaa, jaalalaa fi gammachuu isiniif haa ta'uu.
ከመላው ቤተሰብዎና ወዳጅ ዘመድዎ ጋር በዓሉ የሰላም ፣ የጤና ፣ የፍቅርና የአብሮነት ይሁንላችሁ፡፡

Yuunivarsiitii Haramaaaayaa ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ

Ayyaana Gaarii
መልካም በዓል

Photos from HU FM 91.5 RADIO's post 01/10/2026

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ብቃትን መሰረት ያደረገ የትምህርት አሰጣጥ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን መሰጠት ጀመረ

በስልጠናው ተሳታፊ የሆኑት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አንድም ተማሪ ያላሳለፉ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ ዞኖች ፣ በሀረሪ ክልልና በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚያስተምሩ 150 መምህራን ናቸው።

ለትምህርት አመራርና መምህራን የሚሰጠው ስልጠና በትምህርት ቤቶቹ ውስጥ የተሻለ ለውጥ ለማምጣት አሰራራቸውን የሚያሻሽሉበትን ክህሎት የሚያስጨብጥ መሆኑን የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስና ስነቀመር ኮሌጅ ዲንና የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ተወካይ የሆኑት ዶክተር ስለሺ ደሜ ተናግረዋል።

ስልጠናው የመምህራንና የትምህርት አመራሮችን ብቃት በማሻሻል በትምህርት አሰጣጥና ውጤታማነት ላይ ለውጥ ለማስመዝገብ እንዲቻል ስልጠናው መዘጋጀቱን የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የትምህርትና ስነ ባህሪ ኮሌጅ ዲን ዶክተር ጣሰው መዝገቡ ገልፀዋል።

የአቅም ግንባታ ስልጠናው በሀገራችን የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ በተደራጀው የምስራቅ ክላስተር ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ከምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ ዞኖች ፣ ሀረሪ ክልልና ድሬዳዋ አስተዳደር 10 የመሰናዶ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ 150 መምህራን ስልጠና እየሰጡ መሆኑን በኢትዮጵያ የምስራቅ ክላስተር የትምህርት አመራር ፕሮግራም አስተባባሪ ዶክተር ማሩፍ አብደላ ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ሬዲዮ ኤፍ ኤም 91.5 አብራርተዋል።

ዘጋቢ :- ደሞዝ ያዕቆብ
ካሜራ ባለሙያ :- ፉአድ አሀመድ አሊ

Photos from HU FM 91.5 RADIO's post 29/09/2026

ጤናማ እና ተጠያቂ ትውልድ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት በማህበረሰቡ ውስጥ ተሰሚነት ያላቸው አካላት የሚጫወቱትን አዎንታዊ ሚና ለማጠናከር ያለመ የህይወት ክህሎት እና የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ተሳትፎ እና ኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክቶሬት ከሴቶች ፣ ህጻናት እና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ለሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የጸጥታ አካላትና የማህበረሰብ ተወካዮች ነው ስልጠናውን የሰጡት።

በማህበረሰቡ ዘንድ ተሰሚነት ያላቸውን አካላት አቅም በመገንባት አድሎአዊ አመለካከቶችን ለማስወገድና የማህበራዊ ጤና ችግሮችን በመፍታት ረገድ የተጣለባቸውን ሀላፊነት በብቃት እንዲወጡ ለማስቻል ስልጠናው መዘጋጀቱን በዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ ተሳትፎ አስተባባሪ አቶ ኢብሳ አሊይ ገልጸዋል።

ሰልጣኞች ባገኙት ግንዛቤ ወጣቶችንና የማህበረሰብ አባላትን በማስተባበር የኤች. አይ.ቪ ኤድስ ስርጭት በመከላከል እና የአካባቢውን ችግሮች በቅድሚያ በመለየት ዘላቂ መፍትሔ በመፈለግ ረገድ የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ጤና ጣቢያ ባለሙያ የሆኑት አቶ ፈይሳ ፍቃዱ ስልጠናውን ሲሰጡ በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና በሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ዙሪያ የማህበረሰብ ተወካዮችን የግንዛቤ አቅም ማሳደግ የአካባቢውን ማህበረሰብ ጤና በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።

ሌላኛው አሰልጣኝ አቶ ሶኔሳ መርጋ በስልጠናው የሰውን ባህሪ መረዳት ፣ ውሳኔን ማመጣጠን ፣ ወሳኝ አስተሳሰብ (critical thinking)፣ የመደራደር ክህሎት ፣ በራስ መተማመን እና የችግር መፍታት ጥበብ ላይ ያተኮረ ስልጠና መስጠታቸውን ተናግረዋል።

እነዚህን ክህሎቶች ለማህበረሰቡ ማስተማሩ በቀጣይ ዩኒቨርሲቲውን ከሚቀላቀሉ ተማሪዎች ጋር የአካባቢው ማህበረሰብ በመደጋገፍ በጋራ እንዲኖር ትልቅ መሰረት እንደሚጥል አብራርተዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ግንዛቤ ወደ ማህበረሰቡ ለማሸጋገር ዝግጁ መሆናቸውን በመግለጽ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ መሰል አሳታፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ-ግብሮችን በስፋት ማዘጋጀቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ዘጋቢ፡- አሸናፊ ከበደ
ፎቶ ግራፈር፡- ቴዎድሮስ ሊሻን
መስከረም 2019 ዓ.ም

Category

Address


Harar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when HU FM 91.5 RADIO posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Subscribe

We will notify you when anything happens in Harar.