Eastern Development Initiative

Eastern Development Initiative

Share

Eastern Development Initiative (EDI) is a nationally registered Ethiopian civil society organization, established in 2008 and headquartered in Dire Dawa.

EDI works across peacebuilding, education, health, livelihoods and climate resilience

24/09/2026

የኢስተርን ደቨሎፕመንት ኢኒሽየቲቭ በላይፍ ኤንድ ፒስ ኢኒስቲትዩት ዓለም አቀፍ ድርጅት በተደረገ ድጋፍ በድሬደዋ ከተማ በየወረዳዎች በሚያከናውነው የሰላም ግንባታ ተግባር የተቋቋመውን የአስማሚነት መእከል ከድሬደዋ ብዙን መገናኛ ድርጅት ጋር በመተባበር ለማስተዋወቅ የተላለፈ የሬዲዮ ማስታወቂያ ፡፡

Photos from Eastern Development Initiative's post 21/08/2026

የኢስተርን ደቨሎፕመንት ኢኒሽየቲቭ (EDI) ከላይፍ ኤንድ ፒስ ኢንስቲትዩት ኣለም አቀፍ ድርጅት(LPI) ጋር በመተባበር በ2018 ዓ.ም. በሚያከናውነው የ Cmmunity-led Conflict Transformation Through Participaratory Action Research(PAR) ፕሮጀክት በሰላም ዙሪያ ስላከናወኑት ተግባራት ከሰላም ኮሚቴ አባላት ጋር የሁለተኛ ዙር የውይይት መድረክ (Quarterly review meeting) አካሄደ።
የሰላም ኮሚቴው በየወረዳው ያከናወናቸውን ተግባራት ሪፖርት አቅርበው ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ስላከናወኗቸው ስራዎች፤ ባጋጠማቸው ችግሮች እና ችግሮቹን ለመቅረፍ በተወሰዱ መፍትሄዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡ በቀጣይም ወርሀዊ ሪፖርታቸውን በወቅቱ በማቅረብና ዕቅድ በማውጣት ተጠናክረው በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ቃል በመግባት የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል።

Photos from Eastern Development Initiative's post 13/08/2026

የኢስተርን ደቨሎፕመንት ኢኒሽየቲቭ ( EDI) ከላይፍ ኤንድ ፒስ ዓለም አቀፍ ድርጅት (LPI) ጋር በመተባበር በሰላም ዙሪያ በሚያከናውነው የ PAR) ፕሮጀክት የተቋቋመውን የማህበረሰብ-መር የአሰማሚነት ማዕከልን ከዘጠኙም ወረዳ አስተዳደሮች ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች’፤ከፖሊስ፤ከባለድርሻ አካላትና ጉደዩ ከሚመለከታቸው የተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች ለተውጣጡ ተሳታፊዎች የማስተዋወቅና ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ::
የማህበረሰብ-መር የአሰማሚነት ማዕከሉ የሚመራው በበጎ ፈቃድ ለማገልገል በተመረጡ የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች መሆኑንና በህብረተሰቡ ውስጥ የሚከሰቱ አለመግባባቶችን ፈጣን ቀልጣፋና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ በእርቅና በሰላማዊ መንገድ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም ለመፍታት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው እና በየወረዳው ከአቅም በላይ የሆኑ አለመግባባቶች ሲከሰቱ ባለጉዳዮችን ለማገልገል ማዕከሉ ዝግጁ በመሆኑ ሰፊ የማስተዋወቅ ስራ እንዲሰሩ ለመድረኩ ተሳታፊዎች ማብራሪያና ገለፃ ተደርጎላቸዋል::’
በመድረኩ ላይ በተደረገው ውይይት ያልተግባቡ ሰዎች ተካሰው በፖሊስ ጣቢያና ፍርድ ቤቶች የሚያባክኑትን የስራ ጊዜ ከመቆጠብ በተጨማሪ በማህበራዊ ህይወታቸው ተስማምተውና ተግባብተው እንዲኖሩ ለማስቻል የማህበረሰብ-መር የአሰማሚነት ማዕከሉ የጎላ ጥቅም ስላለው በየወረዳቸው ሲመለሱ ህብረተሰቡ ግንዘቤ እንዲኖረው በመቀስቀስ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ የስብሰባው ተሳታፊዎች ተናግረዋል::
የአስማሚነት ማዕከሉ የሚገኝበት አድራሻ ከድሬደዋ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ፊት ለፊት ሐጂ በክሪ ህንፃ ሁለተኛው ፎቅ ላይ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

Photos from Eastern Development Initiative's post 20/07/2026

በ 2018 ዓ.ም. እየተከናወነ በሚገኘው የ PAR ፕሮጀክት የሴቶች እና የወጣቶች ቡድኖች በየወረዳዎች በሶስተኛው የውይይት ክፍለ-ጊዜ (third session) በሰላም ዙሪያ እያካሄዱ የሚገኙትን የማህበረሰብ ውይይቶችን በከፊል የሚያሳዩ ፎቶግራፎች።

Photos from Eastern Development Initiative's post 09/07/2026

በድሬደዋ ወረዳ ዘጠኝ አስተዳደር ባለፉት ሶስት ዓመታት በሰላም ዙሪያ ሲያካሄዱ የነበረው ማህበረሰብ ውይይት ተሳታፊዎች በፈጠረላቸው ተነሳሽነት ቀጣይነት ያለው ሰላም ለማረጋገጥ ከወረዳው አስተዳደር ጋር በትብብር እየሰሩ ይገኛሉ።
የ Eastern Development Initiative-EDI ከ Life & Peace Institute-LPI ጋር በመተባበር በሰላም ዙሪያ የሚያከናውነው የ PAR ፕሮጀክት ስራ ሲጀመር በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተመድበው ይሰሩ የነበሩ የማህበረሰብ ውይይት ተሳታፊዎች ማህበረሰቡን በማስተባበር፤-
• በየወሩ ስብሰባ በማድረግ በሰላምና በማህበራዊ ችግሮቻቸው ላይ ይወያያሉ።
• ወጣቶች የአካባቢያቸውን ሰላም ለማስከበር በየተራ ሮንድ ይወጣሉ።
• ወጣቱ የአደንዛዥ ዕፅ ተጠቂ እንዳይሆን ውይይትና ምክክር ያደርጋሉ የቁጥጥር ስርዐት ዘርግተው ይሰራሉ።
• ከወረዳው አስተዳደር ጋር በቅንጅት በመስራት ወደፊት ሊከሰቱ በሚችሉ የሰላምና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በቁርጠኝነት እየሰሩ ይገኛሉ።

በወረዳ ዘጠኝ ያለውን የስራ እንቅስቃሴ ለመመልከት አቶ በላይነህ ማዘንጊያው የ LPI Ethiopia Country Manager እና ወ/ሮ ማርታ አበበ የ LPI ክትትልና ግምገማ ከፍተኛ ባለሞያ(MEAL SO) ጉብኝት አድርገው ነበር። የ LPI Ethiopia Country Manager አቶ በላይነህ ማዘንጊያው ለተሰበሰቡት የማህበረሰብ ክፍሎች ባደረጉት ንግግር እያከናወኑ ያሉት ስራዎች በ PAR ፕሮጀክት በሰላም ዙሪያ የተጀመሩ ተግባራትን ቀጣይነት ለማረጋገጥ በመሆኑ መደሰታቸውንና የሰላምና ማህበራዊ ጉዳዮቻቸው ላይ ጠንክረው መስራት እንደሚገባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Photos from Eastern Development Initiative's post 08/07/2026

የማህበረሰብ አስማሚዎችን ተግባራዊ ዕውቀት በማጠናከር ውጤታማ የማስማማት አገልግሎት እንዲሰጡ እና ክህሎታቸውን ማብቃት የሚያስችል ስልጠና ተሰጠ።
ስልጠናው የ Eastern Development Initiative-EDI ከ Life & Peace Institute-LPI ጋር በመተባበር በሰላም ዙሪያ የሚያከናውነው የ PAR ፕሮጀክት አካል ሲሆን በኢትዮጵያ የማስማማት፤ የግልግልና የዳኝነት ማዕከል (Ethiopian Mediation and Arbitration Center-EMAC) አሰልጣኝነት የተካሄደ የሁለት ቀን ስልጠና ነው።
ስልጠናው EDI ባቋቋመው የማህበረሰብ ማስማሚያ ማዕከል (Community Mediation Hub) ውስጥ በበጎ አድራጎት ፈቃደኝነት ለማገልገል የተመረጡ የማህበረሰብ አስማሚዎችን የተግባር ብቃት ለማጠናከር የተዘጋጀ ሲሆን፣ በማህበረሰባቸው ውስጥ የሚከሰቱ አለመግባባቶችን በሙያዊ፣ እና በውጤታማ መንገድ በማስማማት ለማገልገል የሚያስችላቸውን ክህሎት ለማዳበር ያለመ ነበር።
በአቶ በላይነህ ማዘንጊያው የ Life & Peace Institute-LPI Ethiopia Country Manager የተመራ ቡድን የስልጠናውን ሂደት ለማየት ጉብኝት አድርገው ነበር። የ LPI Ethiopia Country Manager አቶ በላይነህ ማዘንጊያው ባደረጉት ንግግር በድሬደዋ የተቋቋመው የአስማሚነት ማዕከል በሌሎች ክልሎች ያልተሰራና የመጀመሪያ በመሆኑ በአርዓያነቱ የሚጠቀስ ስለሆነ ተሞክሮውን ወደ ሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ማስፋት እንዲቻል ለማህበረሰብ አስማሚዎች በተሰጣቸው የክህሎት ስልጠና በመታገዝ ውጤታማ የሆነ የአስማሚነት ተግባራትን የማከናወን ስራዎቻቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በስልጠናው ላይ ለማስማማት ማዕከሉ መደበኛ አሰራር አጋዥ የሆኑ የተለያዩ ቅፃቅፆች ተዘጋጅተው ማብራሪያና ገለፃ ተሰጥቶባቸው እንዲሰሩባቸው የተደረገ ሲሆን ይህም የማዕከሉን አሰራር ቀልጣፋና የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን አስተዋፅኦ ያደርጋል።
ስልጠናው በ EDI የተቋቋመው የማህበረሰብ ማስማሚያ ማዕከል ውስጥ የሚሰጠውን የማስማማት አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት እንዲጠናከር፤የማህበረሰቡ የፍትህ ተደራሽነት እንዲሻሻል እና በማህበረሰቡ ውስጥ ዘላቂ ሰላምና አብሮነት እንዲጠናከር ለማስቻል ወሳኝ አስተዋፅዖ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

Photos from Eastern Development Initiative's post 01/07/2026

የኢስተርን ደቨሎፕመንት ኢኒሽየቲቭ (EDI) ከላይፍ ኤንድ ፒስ ኢኒስቲትዩት ዓለም አቀፍ ድርጅት (LPI)ጋር በመተባበር በሰላም ዙሪያ በሚከናወነው የ( PAR ) ፕሮጀክት ከድሬደዋ ሴክተር መስሪያ ቤቶችና ወረዳ አስተዳደሮች ከተውጣጡ አስፈፃሚ አካላት(Duty bearers ) ጋር ወርክሾፕ አካሄዱ።
በወርክሾፑ ላይ የኢስተርን ደቨሎፕመንት ኢኒሽየቲቭ ፕሮጀክት ኦፊሰር ወ/ሮ መቅደስ ካሳሁን ባቀረቡት ሪፖርት፤-
--ለማህበረሰብ ውይይት አመቻቾች ስልጠና መሰጠቱን
--ሁለት ዙር የማህበረሰብ ውይይት መካሄዱን
--ለትምህርት ቤቶች የሰላም ክበቦች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱን
-- ለሰላም ኮሚቴ ስልጠና መሰጠቱን
--የአስማሚነት ማዕከል ማቋቋም ዋና ዋና ተግባራት መሆናቸውን ካስረዱ በኋላ በየወረዳ አስተዳደሩ በተካሄዱ የማህበረሰብ ውይይቶች የተለዩት ችግሮች ለአስፈፃሚ አካላቱ በዝርዝር ቀርበዋል።
የአስፈፃሚ አካላት(Duty bearers ) ዋነኛ ተግባር በየወረዳ አስተዳደሩ በተካሄዱት የማህበረሰብ ውይይቶች የተለዩ ችግሮችን መፍታትና መፍትሄ ማፈላለግ መሆኑ ተገልፆላቸዋል።
በወርክሾፑ ላይ በቡድን በመከፋፈል ለግጭት መንስዔ የሚሆኑትን ችግሮች ማህበረሰቡ በለየው መሰረት ዕቅድ በማውጣት ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ በቀጣይ የሚያወጡትን ዕቅድ በተግባር ላይ እነደሚያውሉ ቃል በመግባት የዕለቱ ወርክሾፕ ተጠናቋል።

Photos from Life & Peace Institute's post 01/07/2026

Address


Dire Dawa, Dire Mall
Dire Dawa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Eastern Development Initiative posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Subscribe

We will notify you when anything happens in Dire Dawa.