Teme
No greater wealth than peace oll mind. ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ?
በወታደሮች የተጠበቀው እስረኛ እግናቲዩስ ወደ ሮሜ ከደረሰ በኋላ ብዙ ጊዜ ሳይቆይ ወደ አደባባይ ቲያትር ተወሰደ ። በዚያም ራብ ያጠቃቸው አውሬወች ይጠብቁታል ። አሰፈፈሪውንም ትርእይት ለመመልከት ብዙ ሕዝብ ተሰበስቦአል ። የአረዊት ቤት ተከፍቶ ተለቀቁበት ። በአንድ አፍታም ሰውነቱን ቦጫጭቆው ጨረሱት ። በአደባባዩም መካከል የቀረው ጥቅት የተበታታነ አጥንት ብቻ ነው ። ክርስትያኖች ሰብስበው መታሰብያውን ለማክበር ሲሉ ወደ አንጾክያ የወሰዱት ከዚያም አኖሩት ። እግናቲዩስ በነፍቆት ይጠባብቅ የነበረውን ወደ እየሱስ ክርስቶስ ጋ ሄደ ። ልትቀበልው ያለህን መከራ አትፍራ ። እነሆ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው አሥር ቀንም መከራ ትቀበላላችሁ። እስከ ሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወት አክሊል እሰጣለሁ ። መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ ።
በዚያም በቆየበት ወቅት ለልዩ ልዩ አብያተ ክርስትያናት ደብዳቤ ለመጻፍ ጊዜ አገኘ።ወደ ሮሜ ቤተክርስቲያን መልእክት አስተላልፏል ። ይህ መልዕክት እሰከ ዛሬ ድረስ ተጠብቆአል ።አንድ የሚል ቃል ይገኝበታል ። በሰውነቴም በልበም ኃይል እንዳገኘ ጸልዩልኝ ።በእርግጥም ክርስትያን ሆኖ መገኘት እንጂ በስም ብቻ ክርስትያን መባል አይበቃኝምና በአፍ ብቻ ሳይሆን በእውነት ፈቃደኛ መሆን ያስፈልገኛል። እውነተኛ ክርስትና ብርቱ በመሆን የሚገለጥ ነዉ እንጂ በዝምታ አይደለም ። እናንተ ካልከለከላችሁኝ ለአምላኬ ለመሞት ዝግጁ መሆኔን በሰው ሁሉ ፊት እመሰክራለሁ ። ስለዚህ አለገባብ እንዳታስቡልኝ እለምናችኋለሁ ። ወደ እግዚአብሔር እንደደረሰ የአራዊት ጉርሻ ልሁን ። የእግዚአብሔር የስንዴ ቅንጣት ነኝ ።የአራዊትም ጥርሶች ቢፈጩኝ ለኢየሱስ ክርስቶስ ንጹህ እንጀራ እሆናለሁ። ካንቀላፋሁ በኋላ ለማንም ሰው ሸክም እንዳልሆን ሰውነቴ በሙሉ ይለቅ። አራዊት መቃብሬ እንዲሆኑ ይመጡብኝ ። እንዲይዙኝ እናንተ አነሣሱአቸው ። በመሞቴ በክርስቶስ ነጻነትን አገኛለሁ በእርሱም ነጻ ሆኜ እነሣለሁ ። በጊዜያዊ እስራት የታሰርሁ ሆኜ እገኛለሁ። ስለዚህ አንዳች ምድራዊና አላፊ ነገር መመኘት እንደማያስፈልገኝ ተረድቼያለሁ ። ገና በመንገድም ላይ ሳለሁ በባሕር በየብስም ሌትና ቀን አሁንም ከአራዊት ጋር እየታገልሁ ነኝ ። የዐሥር ነበረች ቁራኛ ነኝ ማለትም ከወታደሮች ጋር ነዉ ያለሁት ። እነርሱም መልካም ነገር ቢያደርጉላቸው የባሰውን ክፋት የሚያሳዩ ናቸው ።ይሁንና በእነርሱ ማጉላላት ልምምድ አገኛለሁ ። በዚህ ግን እጸድቃለው ።ማለቴ አይደለም እውነተኛ ደቀ መዝሙር መሆንን የጀመርሁት አሁን ነው ። የሚታይ ሆነ የማይታይ ማንም ሰው በምቃኝነት ዓይን አይመለከተኝ ። ልድረስ ወደ እየሱስ ክርስቶስ ።እሳት መስቀል የአውረ ብዛት መጨፍጨፍ የአጥንቶቼ መበታተን የብልቶቼ መከባበር የሰውነቴ መጨፍለቅ ሁሉ የሰይጣንሥቃይ ሁሉ ይምጣብኝ ። ወደ እየሱስ ክርስቶስ ልድረስ ። እስከ ሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወት አክሊል እሰጣለሁ ።ራእይ 2:10
....የለኝም በማለት የቄሣርን ተቃውሞ አሳይቶ በነገሩም ተይዞ ተከሰሰው ። ጳጳሱም የሚመጣበትን ነገር ሳይፈራ በግልጽ ክርስቲያን ነኝ ብሎ አመነ ። ትራያኑስም ወደ ሮሜ ተሰድዶ በአንበሶች ተገነጣጥሎ እንዲሞት ፈረደበት ። ወዲያው እጆቹ በሰንሰለት ታስረው በዐሥር ወታደሮች ተጠብቆ በመርከብ ወደ ሮሜ እንዲጓዝ ተገደደ ። መንገድ በሰምርኔስ በኩል ስላለፉ እግናቲዩስ በዚያ ከአንድ ሌላ ስም ጥሩ ክርስቲያን ጋር እንዲገናኝ ተፈቀደለት ። እርሱም ፖሊካርጵ ነዉ ። በወዳጅነት በፍቅር ያደረጉት የዐሳብ መለዋወጥ ሁሉ እግናቲዩስን እንዳጽናናውና እንድበረታታው .....ይቀጥላል
እግናቲዩስ እግናቲዩስ የእግዚአብሔር ቃል በመስበክ ቤተ ክርስትያንን ያገለገላት አንጾኪያ የተባለችው ከተማ ነው። ታማኝ አገልጋይ ከመሆኑም የተነሣ የቤተክርስቲያኒቱ ጳጳስ ሆነ ። 107 ዓ.ም ትራያኑስ ቄሣር ለአገር ጉብኝት ወደ አንጾኪያ መጣ ። በዚያን ጊዜ ለከተማው ሕዝብ ለአማልክት መሥዋዕት ለማቅረብ የማይፈልግ ሁሉ ብርቱ ቅጣት ይደርስበታል ስል ማስታወቂያ አወጣ ። እግናቲዩስ የማስታወቂያውን ቃል ሰምቶ ለአማልክት የምሠዋው ነገር ......ይቀጥላል ጠብቁኝ
10/07/2025
ዛሬም የክብርህ ራብታኛ ነኝ
መዝሙር 42 ዛሬም እነደ ቀድሞ መንፈስህ ከውስጤ ከቶ አይብሬድብኝ ።
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች።
² ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?
10/07/2025
መዝሙር 42 ዛሬም እነደ ቀድሞ መንፈስህ ከውስጤ ከቶ አይብሬድብኝ ።
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች።
² ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?
31/05/2025
“ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።”
— ዮሐንስ 20፥31
31/05/2025
የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል። 1ዮሐ 1:7
“እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።”
— ኢሳይያስ 53፥5
23/03/2025
Bizegeyim bergit yimetal Geta አብሪሐም 25አመት ጠበቀ ፥ ዮሰፍ 13አመት ጠበቀ፥ ሙሴ 40አመት ጠበቀ ። አንተም /ችም ጠብቅ ብዘጌይም በርግጥ ይመጠል ።
The Perethence of God worship time
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Awassa