Adane Alaka
Personal
29/11/2024
21/11/2024
28/08/2024
29/07/2024
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሲዳማ ክልል በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ወንሾ ወረዳ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸው ላጡ ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለፁ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሲዳማ ክልል በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ወንሾ ወረዳ በትላንትናው ዕለት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸው ላጡ ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለፁት የክልሉ መንግሥት ከዞን አስተዳደር ጋር በመሆን አደጋ ከደረሰ ሰዓት አንስቶ በዜጎች ላይ ተጨማሪ አደጋ እንዳያደርስ መጠነ ሰፊ ስራ እንደሰራ እንዲሁም ተጎጂ ወገኖች ወዲያው ህክምና እንዲያገኙ እንደተደረገ ገልፀው የክልሉ መንግሥት ተጨማሪ ድጋፎዎችን ለማድረግ የክልሉ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንና የፀጥታ ሀይል ወደ ስፍራው አሰማርቷል ብለዋል።
በሌሎች አከባቢዎችም መሰል ችግሮች ሊፈጠሩ ስለሚችሉ ማህበረሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ርዕሰ መስተዳድሩ ያሳሰቡ ሲሆን በደረሰው አደጋ የሰዎች ህይወት በማለፉ የተሠማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀው፤ ለሟች ቤተሠቦችና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን ተመኝተዋል።
Category
Website
Address
Hawasa
Awassa
Alerts
Be the first to know and let us send you an email when Adane Alaka posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.