Guada

Guada

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Guada, Public Figure, Addis Ababa.

01/10/2026

በኢንተርኔት የራስን ህመም በራስ የመመርመር አደጋዎች

ከምትገምቱት በላይ በርካታ ሰዎች ለጤና መረጃ ወደ ኢንተርኔት ይዞራል።በርካታ ጥናቶች እንደሚያመለክቱ ስለጤናቸው ስጋት ሲኖራቸው በኢንተርኔ ት ጠቀማሉ። አንዳንዶች መረጃውን ወደ ትክክለኛው የህክምና ሲጠቀሙበት ሌሎች ደግሞ የራሳቸውን ህመም በራሳቸው ለመመርመር እና ለመታከም ይገለገሉበታል።
ዋና ዋና አደጋዎች
1. በልዩ ሁኔታ እርግጠኛ መሆን: በአነበቡት መረጃ ብቻ በመተማመን የባለሙያ ምክሮች አለመቀበል።
2. ያልተገባ ፍርሃት: በትናንሽ ምልክቶችን ከከፋ በሽታ ጋር በማያያ ለባሰ ጭንቀት መዳረግ።
3. ያልተገቡ ምርመራዎች: በማያስፈልጉ የህክምና ምርመራዎች ላይ ጊዜና ከገንዘብን ማባከን
4. አደገኛ ህክምናዎች መውሰድ: በራስ አነሳሽነት ያልተረጋገጡ ባህላዊ መድሀኒቶችን በመውሰድ ለጎንዮሽ ጉዳት መጋለጥ
⏩የኦንላይን መረጃን በኃላፊነት ለመጠቀም

24/09/2026
06/09/2026

Amarelo Honey-አማሪሎ ማር Our aim is to provide pure and organic honey to everyone in Ethiopia and around the world.

03/09/2026

አማሪሎን #በነፃ ይቅመሱ
🗓️ ቅዳሜ ነሀሴ 30 2018
⏰5:30 - 11:00 LT
📍weventurehub, sur construction building, Bole

27/08/2026

ዓይን የነፍስ መስኮት ነው" ይባላል።የእይታ መቀነስ በዕድሜ መጨመር ምክንያት የሚመጣ የማይቀሬ ነገር አይደለም! በቂ ብርሃን ከመጠቀም፣ የኮምፒውተርና ስልክ ስክሪን እይታ ሰዓትን ከመቀነስ፣ የፀሐይ መነፅር ከማድረግ እና የዓይን ጡንቻዎችን ከማንቀሳቀስ ጎን ለጎን ምግብ ለዓይን ጤና ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
ለላቀ የዓይን ጤና በቀን 500 ሚሊግራም ቪታሚን C፣ 400 ኢንተርናሽናል ዩኒት ቪታሚን E፣ 10 ሚሊግራም ሉቲን፣ 2 ሚሊግራም ዚአዛንቲን እና ኮፐር ኦክሳይድ፣ እንዲሁም 80 ሚሊግራም ዚንክ እንዲወሰድ ይመክራል።
🐟 1. ዓሳ እንደ ቱና፣ ሳልመን፣ ትራውት፣ ማኬሬል፣ ሳርዲን፣ አንቾቪ እና ሄሪንግ ያሉ የሰቡ ዓሳዎች ለሬቲና (Retina) በትክክል መስራት አስፈላጊ የሆነው የኦሜጋ-3 ፋቲ አሲድ ምንጭ ናቸው። በተጨማሪም ከዓይን ድርቀት፣ ከዕድሜ ጋር ከተያያዘ የእይታ መቀነስ እና ከሞራ ይከላከላሉ።
🥬 2. አረንጓዴ ቅጠላቅጠሎች፡ እንደ ብሮኮሊ፣ የብራሰልስ በቆሎ (Brussels sprouts)፣ ስፒናች፣ ኬል (Kale) እና ቆስጣ ያሉ ቅጠላቅጠሎች ሉቲን እና ዚአዛንቲን የተሰኙ የዕፅዋት ቀለሞችን ይይዛሉ። እነዚህ አንቲ ኦክሲዳንቶች የዓይን ሕዋሳትን Free radicals ከሚባሉ ጎጂ ሞለኪውሎች በመጠበቅ የሕዋሳት ውድመትን ይከላከላሉ። በተጨማሪም ቪታሚን A፣ C፣ E እና ቤታ ካሮቲን በውስጣቸው ይገኛሉ።
🥕 3. ካሮት በቪታሚን A እና በቤታ ካሮቲን የበለፀገ ነው። ቤታ ካሮቲን ሮዶፕሲን (Rhodopsin) የተባለ ፕሮቲን እንዲመረት ይረዳል፤ ይህም ሬቲና ብርሃንን እንዲቀበልና ከጨለማ ጋር እንዲላመድ ያደርጋል።
🫘 4. የጥራጥሬ እህሎች እንደ ኪድኒ ቢንስ፣ ሽምብራ፣ ምስር፣ ለውዝ እና አተር ያሉ ጥራጥሬዎች በዚንክ የበለፀጉ በመሆናቸው ሬቲናን የመጠበቅ እንዲሁም የሞራ እና የእይታ መቀነስ ሥጋትን የመቀነስ አቅም አላቸው።
🌻 5. የሱፍ ፍሬ አንድ ኦንስ (28 ግራም ያህል) የሱፍ ፍሬ በዩኤስዲኤ (USDA) ከተመከረው የዕለት ቪታሚን E ግማሹን ይዟል። በተጨማሪም ጥሩ የዚንክ ምንጭ በመሆኑ የእይታ መቀነስን እና የሞራ በሽታን ለመከላከልና ሂደቱን ለማዘግየት ይረዳል።
🥚 6. እንቁላል፡ የእንቁላል አስኳል በዕድሜ ምክንያት የሚመጣን የእይታ መጎዳት የሚከላከሉ የሉቲን እና ዚአዛንቲን ምንጭ ነው። ቢጫ-ብርትኳናማ ቀለማቸው ሬቲናን ሊጎዳ የሚችል ጎጂ ሰማያዊ ብርሃንን ይከላከልላታል። በተጨማሪም እንቁላል ለሌሊት ዓይነ ስውርነት እና ለዓይን ድርቀት የሚረዱ ቪታሚን A፣ C፣ E እና ዚንክን ይዟል።
🍠 7. ስኳር ድንች፡ ለሌሊት እይታ በሚረዳ ቤታ ካሮቲን የበለፀገ ነው። በተጨማሪም አንድ ስኳር ድንች በቀን ከሚያስፈልገው የቪታሚን C መጠን ከግማሽ በላይ ይይዛል። እንዲሁም የዓይን ሕዋሳት ውድመትን የሚከላከሉ አነስተኛ የቪታሚን E መጠኖችን ይዟል።
🍊 8. የብርቱካን አስተኔ ፍራፍሬዎች (Citrus fruits) ብርቱካን፣ ግሬፕፍሩት፣ ሎሚ (እና ቤሪዎች) ከዕድሜ ጋር የተያያዘ የእይታ መጎዳትን የሚታገለው የቪታሚን C ከፍተኛ ምንጭ ናቸው።
🎃 9. ዱባ (Squash) የበጋ ዱባ (Summer squash) ቪታሚን C እና ዚንክን የሚይዝ ሲሆን፣ የክረምት ዱባ (Winter squash) ደግሞ ቪታሚን A፣ C እና ኦሜጋ-3 ይዟል። ሁለቱም ዓይነት ዱባዎች ሉቲን እና ዚአዛንቲን በመያዛቸው ዓመቱን ሙሉ ለዓይን ጤና ተስማሚ ናቸው።
💧 10. ውሃ፡ ውሃ የሕይወት መሠረት ነው! ስለዚህ ለዓይን ጤናም አስፈላጊ ነው። በቂ ውሃ መጠጣት የሰውነት ድርቀትን በመከላከል የዓይን ድርቀት ስሜትን እና ፅናቱን ይቀንሳል።
✨ የእይታ መቀነስ በዕድሜ መጨመር ምክንያት የሚመጣ የማይቀሬ ነገር አይደለም። ለዓይን ጤና ጠቃሚ በሆኑ ንጥረ ነገሮች የበለፀገ ምግብ መመገብ የዓይን በሽታዎችን ለመከላከል ወይም ለማዘግየት እንዲሁም ዕድሜ ልክ ሙሉ የዓይን ጤና እንዲኖርዎ ይረዳዎታል!

Category

Website

Address


Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Guada posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Subscribe

We will notify you when anything happens in Addis Ababa.