RAYN Trading PLC
RAYN Trading plc is established to serve the global community in the area of real estate development Telegram channel
https://t.me/raynmarketing
የልጆች አዕምሮ ፈጣን እድገት እንዲኖረው የሚያደርጉ 7 ምግቦች!
➖〰️➖🧠〰️➖〰️🧠🧠➖〰️➖🧠〰️➖〰️
የልጆች አዕምሮ ፈጣን እድገት እንዲኖረው የሚያደርጉ ሰባት ምግቦች የሚከተሉት ናቸው:-
1️⃣ እርጎ 🥤🥛
አእምሮ ላይ መልዕክት በተገቢው እንዲላክና እንዲቀበል ይረዳል፤ ቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ አለው፤ ይህ ደግሞ የአእምሮ ህብረ ህዋሶችና መልእክት አስተላላፊዎች በተገቢው እንዲያድጉ ይጠቅማል።
2️⃣ አትክልቶች 🥬🥕🥒🥗
አትክልቶች አንቲ ኦክሲደንትነት አላቸው፤ ይህ ደግሞ የአዕምሮ ህዋሶች ጤናማ እንዲሆኑ ይረዳል። ለምሳሌ እንደ ስኳር ድንች፣ ዱባ፣ ካሮት ያሉትን መስጠት እንደባሮ ሽንኩርት፣ እስፒናች፣ ቆስጣ ያሉት ደግሞ በፎሌት የበለፀጉ ስለሆኑ ልጆችን ከመርሳት በሽታ ይከላከላሉ።
3️⃣ ብሮኮሊ 🥦🥦
ካንሰር ተከላካይነት ባህሪ አለው በተጨማሪም የነርቭ ስርዐት በተገቢው የተያያዘ እንዲሆን ያግዛል።
4️⃣ አቦካዶ 🥑🥑
አስፈላጊ ቅባት አለው፤ ይህም በቂ ደም ወደ ጭንቅላት እንዲዘዋወር ይረዳል። ኦሊክ አሲድ በመያዙ ምክንያት ማይሊን የተባለውን የአዕምሮ ክፍል ከመጥፎ ነገር ይከላከለዋል(ማይሊን በሰዐት በ200 ማይል ፍጥነት መልዕክት እንዲተላለፍ ያደርጋል)። በቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ የበለፀገ መሆኑ ልጆች በግፊት የመያዝ እድላቸውን ይቀንሳል።
5️⃣ አሳ 🐠🐟
አሳዎች በኦሜጋ 3 የበለፀጉ በመሆናቸው የልጆች አእምሮ ፈጣን እድገት እንዲኖረው ይረዳሉ።
6️⃣ እንቁላል 🥚🥚
የተለያዩ ንጥረ ነገሮች አሉት፤ ለምሳሌ ኦሜጋ 3፣ ዚንክ፣ ኮሊን(አሴታይል ኮሊን) እንዲመረት የሚረዳ ሲሆን የማስታወስ ችሎታን ለማዳበር ያግዛል።
7️⃣ የተፈጨ አጃ 🌾🌾
በተለይ ለቁርስ ብንመግባቸው ጥሩ የማስታወስ ችሎታ እንዲኖራቸው ይረዳል፤ በተጨማሪም በቫይታሚን ኢ፣ ዚንክ፣ ቫይታሚን ቢ ኮምፕሌክስ የበለፀገ ነው። ከፍተኛ ፉይበርነት ስላለው ኃይልን እንዲያገኙም ያደርጋል።
መልካም ጤንነት!!
ምንጭ፦ fb Chef Ermias Tadese(ሄልዝላይን)
መስከረም 23/2016 ዓ.ም
ህይወትን በመነቃቃት መንፈስ እንደገና ለመጀመር የሚረዱ 10 የዶ/ር ወዳጄነህ ማህረነ ምክሮች!
በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ዕለት ተዕለት በሚኖራችሁ ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ፤ ምንም ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ ያውቃል?
እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን 10 ነጥቦች ይተግብሯቸው፡፡
1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምክንያት ስላልሆነ ለእኛ በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡ ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል፤ ጊዜ መድኃኒት ነው ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”
3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና የውድቀትን ካርድ ልንመዝባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው፡፡
4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዎች ጠንክረው ላለመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው ትልቁ ምክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡
5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡ በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡
6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡
7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሯችንንና ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታችን በከንቱ ይባክናል፡፡
8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡
9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡
10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችን ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ቢሆን እንኳን የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን መውደድ አለብን።
ምንጭ፦ fb የስኬት ፍልስፍና(ከአንቂ መፅሀፍት ገፆች)
መስከረም 21/2016 ዓ.ም
27/07/2023
life skill Amharic.ppt life skill Amharic.ppt - Download as a PDF or view online for free
ለግንቦት 2015 ዓ.ም ለሽያጭ/ለኪራይ የቀረቡ ቤቶች
ራይን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር ለግንቦት ወር 2015 ዓ.ም ለሽያጭ/ኪራይ ያቀረባቸው ቤቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
ስለቤቶቹ ተጨማሪ መረጃና መግዛት/መከራየት ከፈለጉ በ0991656565 ወይም 0983353530 ይደውሉ!!!
ሀ. ኮንዶሚኒየም ቤቶች
1ኛ. ባለ1 መኝታ ~ቱሉዲምቱ ~2ኛ ፎቅ ላይ ~53.22ካሬ ~ ዋጋው ብር 3.2 ሚሊዮን
2ኛ. ባለ2 መኝታ ~ ቱሉዲምቱ ~1ኛ ፎቅ ላይ ~ 74 ካሬ ~ ዋጋው ብር 3.75 ሚሊዮን
3ኛ. ባለ2 መኝታ ~ ቱሉዲምቱ ~3ኛ ፎቅ ላይ ~ 71 ካሬ ~ ዋጋው ብር 3.7 ሚሊዮን
4ኛ. ባለ2 መኝታ ~ ጀሞ 2 ~ 4ኛ ፎቅ ላይ ~ 73 ካሬ ~ ዋጋው ብር 4.2 ሚሊዮን
5ኛ. ሰቱዲዮ ~ ኮዬ ፈጬ ~ መሬት ላይ ~ 42 ካሬ ~ ዋጋው ብር 2.3 ሚሊዮን
ለ. አፓርታማ/ሪልስቴት ቤቶች
6ኛ. ባለ3 መኝታ ~ፍየል ቤት(ሲኤምሲ) ~ 1ኛ ፎቅ ላይ ~ 116 ካሬ ~ ዋጋው ብር 12.9 ሚሊዮን
7ኛ. ባለ3 መኝታ ~ፍየል ቤት(ሲኤምሲ) ~ 1ኛ ፎቅ ላይ ~ 116 ካሬ ~ ዋጋው ብር 12.9 ሚሊዮን
8ኛ. ባለ2 መኝታ ~24(መገናኛ) ~ 4ኛ ፎቅ ላይ ~146 ካሬ ~ ዋጋው ብር 19 ሚሊዮን(ሪልስቴት ነው)
ሐ. ፈራሽ ቤቶች/ለአዲስ ግንባታ የሚሆኑ ቦታዎች
9ኛ. ከ1ዐ ክፍል በላይ ፈራሽ ቤቶች ~አዳማ(ናዝሬት)~ በይዞታ 1895ካሬ፤ በካርታ ደግሞ 1300ካሬ ~ ዋጋው ብር 42 ሚሊዮን
❤ ሁሉም ዋጋዎች የተወሰነ መደራደሪያ አላቸው!
መ. የሚከራዩ ቤቶች
10ኛ. ባለ1 መኝታ ኮንዶሚኒየም ~ቱሉዲምቱ ~2ኛ ፎቅ ላይ ~ 54 ካሬ ~ ወርሃዊ የኪራይ ዋጋ 7,800 ብር
11ኛ. ባለ2 መኝታ ሪልስቴት ~24(መገናኛ) ~7ኛ ፎቅ ላይ ~ 141 ካሬ ~ ወርሃዊ የኪራይ ዋጋ 80,000 ብር
ስለቤቶቹ ተጨማሪ መረጃና መግዛት/መከራየት ከፈለጉ በ0991656565 ወይም 0983353530 ይደውሉ!!!
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል!
03/10/2021
Please join our telegram channel
raynmarketing የራይን አላማ የላቀ የደንበኞች አገልግሎት በተለይ በግብይት ዘርፍ ላይ ትኩረት በመስጠት በሰው ልጆች አኗኗር ዘዬ ላይ ትርጉም ያለው አዎንታዊ ለውጥ ማምጣት ነው።
18/09/2021
Call for more by:
+251991767676 or +251991656565
10/09/2021
RAYN Trading plc wishes all Ethiopians a happy, peaceful and prosperous new year.
The office sales person is responsible for the day to day activity of the company including controlling the accounting system, writing letters as required, closing sale, briefing customers about our products and so on. Applicants who are positive thinker and visionary with a minimum of BA degree in accounting and atleast with one year experience suites this position.
This post is available for 10 consecutive days from the date of announcement
The real estate sales person is responsible to prospect home buyers, generate qualified leads, follow up customers, make site visit with customers and close the sale. Ideally it is preferred the sales person is positive thinker and visionary. Applicants with network marketing background are encouraged to apply. Sales person with salary mentality doesn't suite this position.
#5 sales persons are required for this post with a minimum qualification of 12th graduate.
This post is available for 10 consecutive days from the date of announcement.
06/09/2021
ቡልጋርያ አፍሪካ ህብረት ሳይት፤በካሬ 46000 ብር ጀምሮ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ልዩ ቅናሽ።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Alfoz Plaza
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 09:00 - 17:00 |
| Tuesday | 09:00 - 17:00 |
| Wednesday | 09:00 - 17:00 |
| Thursday | 09:00 - 17:00 |
| Friday | 09:00 - 17:00 |
| Saturday | 09:00 - 12:00 |