EYOB.
Contact our real estate company to make a better decision about your new property.
10/01/2024
🏡 Introducing AL-SAM APARTMENTS #2! 🌟 Your next home destination awaits.
02/09/2023
06/08/2023
ከቅዳሜ ሃምሌ 29 ጀምረው በወሰን ብሬክስ ህንፃ በመገኘት በፍጥነት እና በጥራት የተገነባዉን ባለ 2 እና ባለ 3 መኝታ ቤት ዘመናዊ አፓርትመንቶች በVR ቴክኖሎጂ ታግዘው እንዲጎበኙ ተጋብዘዋል!
በ60% ቅድመ ክፍያ የራሶ ያድርጉ ጎራ ብለው የግንባታ ጥራት እና ውበቱን አድንቀው ዘመን ተሻጋሪ ቅርስ የግሎ ያድርጉ!
ለበለጠ መረጃ
📲0975777879
03/08/2023
ተመስገን 🙏 በክረምት ⛈ መንከራተት ቀረ 😊
የመረጡትን ሪል እስቴት ካሉበት ሆነዉ በስልክዎ📱አሊያም በኮምፒዩተሮ👨💻 ይጎብኙ!
🏙 ኮፊ ፕላዛ
ኮፊ ፕላዛ በመሀል ከተማ ካሳንችስ ላይ ቅንጡ አፓርትመንቶችን በ30% ቅድመ ክፍያ ለገበያ አቅርቧል::
የግንባታ ሂደቱ 65% ደርሷል::
ሳይቱ በባለ ኮከብ ሆቴሎች(ኢንተርሌግዠሪ:ሀያትሪኤጀንሲ:ማርዮት ወ.ዘ.ተ)፣ አለም አቀፍ ድርጅቶች (ECA:IOI e.t.c)፣ አለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች (ግሪክ ክለብ: ቅዱስ ዮሴፍ ወ.ዘ.ተ)፣ መንግስታዊ ተቋማት(ቂርቆስ ክ/ከ አስተዳደር:ዉልናማስረጃ ወ.ዘ.ተ) እና በወንዝ ዳር ፕሮጀክት የተከበበ ነዉ::
የመኖሪያ አፓርትመንቶቹ ስፋት:-
🛌ባለ 1 መኝታ፡ 66 ካሬ ሜ
🛌ባለ 3 መኝታ፡ 176 ካሬ ሜ
🛌ባለ 3 መኝታ፡ 204 ካሬ ሜ
ስለ ሪል እስቴቱ | አፓርታማዉ በጥቂቱ:-
🟢 በወለል (በፍሎር) 3 ቤቶች ብቻ ያሉት
🟢 ሁሉም አፓርትመት ጥሩ እይታ (ቪው) ያላቸው እና ሁሉም የመጠቀሚያ ክፍሎቻቸዉ በቂ አየር እና ብርሃን የሚያገኙበት
🟢 ለኤሌክትሪክ መኪናዎች ቻርጂንግ ስቴሽን ያለው
🟢 ድምጽን በአስተማማኝ ሁኔታ የማያስገቡ መስታወቶች የሚገጠሙለት
🟢 በአውሮፖ ስታንዳርድ እና ቴክኖሎጂ የተመረቱ የሳኒተሪ መስመር የሚዘረጋለት
🟢 በየወለሉ የቆሻሻ ማግለያ ልዩ ቦታ(ክፍል) የተዘጋጀላቸው
🟢 ያልተሰሰተበት አንዱ ቤት ከሌላኛው ቤት በሁለት ግድግዳ የተለያየ (ድምጽ የማያስተላልፍ)
🟢 ቢገዟቸው ለውጭ ሀገር ዜጎች ለኪራይ ተመራጭ እንዲሆኑ ታስበው የተገነቡ
🟢 ደረጃቸውን የጠበቁ ሰፋፊ ሊፍቶች
የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች ( ፓርኪንግ)
🟢 24 ሰዓት አስተማማኝ ጥበቃ ያለው
🟢 በሳምንት ለ7 ቀናት በቀን ለ24 ሠዓት የማይቋረጥ የውሃ አቅርቦት እንዲኖረው የከርሰ ምድር ውሀ አቅርቦት የሚሟላለት
🟢 ለህንፃው ውበትን ያላበሱ እና ነዋሪዎች አየር የሚወስዱባቸው ባልኮኒዎች ያሉት
🟢 የኤሌክትሪክ ሀይል መቆራረጥ እንዳያጋጥም አውቶማቲክ ጀነሬተር የሚገጠምለት
🟢 የቤቱን ዋጋ 30% ብቻ ቅድመ ክፍያ ከፍለው ቀሪውን 70% በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ ዘና ብለው የሚከፍሉት
🟢 ግንባታው ከ65% በላይ የተጠናቀቀ እና በፍጥነት በመሰራት ላይ የሚገኝ
የመረጡትን አፓርትመንት የራስዎ ካደረጉ በሁዋላ ማከራየት ቢፈልጉ እኛ በነፃ እናከራይሎታለን::
የሚጎበኙበት ሊንክ:-
🔗https://rb.gy/6c2v0
ለመመካከር:-
📞0975777879
01/08/2023
#በቅድመክፍያ ቤቶችን የሚገዙ ቤት ገዢዎች ሊጠነቀቁባቸው የሚገቡ ጉዳዮች
🏠💸
➡️በቅድመ ክፍያ በተለያየ ሁኔታ የቤት ገዢዎች በተከፋፈለና ረዘም ባለ ሁኔታ በግንባታ ላይ ያሉ ቤቶችን መሸጥ (presales) የሪል እስቴት ግብይት ውስጥ አልሚዎች እንደ ፕሮጀክት ማስኬጃ የገንዘብ ምንጭ (project finance) የሚጠቀሙበት ለቤት ገዢዎችም በተራዘመ የክፍያ ሂደት ቀስ በቀስ እየከፈሉ ቤት እንዲገዙ የሚያስችል አስቻይ የክፍያ አማራጭም ነው።
➡️ይህ አይነት ግብይት ውስጥ አልሚዎችም ሆነ ገዢዎች ጥንቃቄን ካላደረጉ ለኪሳራ የሚዳርግ ነው።
ከአልሚዎች የተያያዘውን አቆይተነው ከቤት ገዢዎች ጋር የተያያዘውን እንደሚመለከተው ለማቅረብ እንሞክራለን:-
1️⃣ ከፕሮጀክት መዘግየት ጋር የተያያዘ:-
ፕሮጀክቶች በተለያዩ ምክንያቶች ይዘገያሉ::ብዙ ግብይቶች በዶላር ምንዛሪ እኩሌታ ተሰልቶ እንዲከፍሉ ስለሚደረግ ፕሮጀክቶች በዘገዩ ቁጥር የገንዘብ ምንጫቸው ከሀገር ውስጥ ያደረጉ የቤት ገዢዎች ለተጨማሪ የክፍያ ወጪ ይዳረጋሉ። ከክፍያ ባሻገር ፕሮጀክቶች በመዘግየታቸው ከፕሮግራማቸው ውጪ ለቤት ኪራይ እየከፈሉ መኖር መቀጠላቸው ከፍተኛ ጫና ይፈጥርባቸዋል።
2️⃣ የዲዛይን እና የጥራት ችግር:-
በቅድመ ክፍያ የሚገዙ ቤቶች ግብይት በማስታወቂያ ላይ በሚለቀቁ የማርኬቲን ምስሎች እና በወረቀት ላይ ባሉ መረጃዎች ስለሚከናወኑ በግንባታ ሂደት በሚኖር ትግበራ በሚኖር የአሰራር ችግር፣ የማጠናቀቂያ ቁሶች ደረጃ መውረድ ወይም የዲዛይን ክለሳ የተነሳ ገዢዎች የጠበቁትን ላያገኙ ይችላሉ ።
3️⃣ ከገንዘብ አቅርቦት ጋር ያሉ ተያያዥ ጉዳዮች:- የቤቶች ግብይትን አስቻይ ለማድረግ የተወሰነ ክፍያ ከባንኮች ጋር ተያይዞ እንዲከፈል ሊደረግ ይችላል። ይህም በተራዘመ ሂደት ባንኮች ለሚያወጡት የተለያዩ የወለድ ጭማሪዎች ሊዳርግ ይችላል። ደንበኞች በራሳቸው ምንጭ በሚሸፍኑት የክፍያ ሂደት ውስጥ ክፍያ እንዲከፍሉ የሚሰጣቸው ጊዜ አጭር በመሆኑና ከክፍያ መዘግየት ጋር በአልሚዎች የሚቀመጡት ቅጣቶች ከፍ ያሉና ውልን እስከማቋረጥ የሚደርሱ መሆናቸው ። ጥቂት የማይባሉ ተለምነው የገዙ የቤት ገዢዎች በክፍያ ማዘግየት ሰበብ በቅጣት ጭምር ውላቸው ተቋርጦ ገንዘባቸውም ተቆራርጦ ያውም የከፊሉበት ቤት ለሌላ ተሸጦ እንዲከፈላቸው መደረጉ አክሳሪ ይሆንባቸዋልና አስተማማኝ የገቢ ምንጭ እንዳላቸው ሳያረጋግጡ በአነስተኛ ቅድመ ክፍያ ተታልለው እንዲገዙ አይመከርም።
4️⃣ ከአልሚዎች ብቃትና ታማኝነት ጋር በተያያዘ:- የሀገራችን የሪል እስቴት ዘርፍ ግብይት ወጥ የሆነ የግብይት መመሪያ ስለሌለ ግብይቱ በአብዛኛው በመተማማመን ላይ የተመሰረተ ስኬቱም በአልሚዎቹ አቅም ታማኝነትና ያለፈ የስኬት ታሪክና ስም ጋር የተያያዘ ነው ። የቤት ገዢዎች በቅድመ ክፍያ ቤት የመግዛት ሂደት ወስጥ ከመግባታቸው በፊት የአልሚውን ህጋዊነት፣ የፕሮጀክቱን ህጋዊነት፣ ፕሮጀክቱ የደረሰበትን ደረጃ፣ የአልሚውን የፋይናንስ አቅም ፣ የቀደሙ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም፣ ስምና ዝና፣ ታማኝነት ፣ ወቅታዊ የአልሚው አቅም ፣ የበፊት ደንበኞቻቸውን ምስክርነት ማድመጥ ይመከራል።
5️⃣ ከገበያ ሁኔታ ጋር በተያያዘ:-
የሪል እስቴት ግብይት ቶሎ ቶሎ ተለዋዋጭ (dynamic) የሚባል ሲሆን በሀገራችን እስከአሁን እንዳለው ሁሌ እያደገ የሚሄድ ግን አይደለም። ተለዋዋጭነቱ ከቤት አቅርቦት ብዛትና እጥረት ጋር ብቻ ሳይሆን ከ ሀገር ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ፣ በየጊዜው ከሚወጡ ፖሊሲዎች ጋርም የሚያያዝ ስለሆነ ከተራዘመ የክፍያ አማራጭነቱ ባሻገር የክፍያውን መጠን ከኢኮኖሚ ሁኔታዎች ፣ ከገበያው አካሄድ ጋር ማገናዘብ ይፈልጋል።
⚠️
ሲጠቃለል ቤት ገዢዎች በቅድመ ክፍያ ቤት ለመግዛት ከመወሰናቸው በፊት የሪል እስቴት ግብይት ባለሙያዎችን እንዲያማክሩ፣ የሚገቡበትን ውል ከህግ አማካሪ ጋር እንዲመክሩ፣ በተስማሙበት የክፍያ ሁኔታ መሰረት ሊከፍሉበት የሚችል አስተማማኝ የገቢ ምንጭ እንዳላቸው እንዲያረጋግጡ፣ የቤት ግብይት ፋይናንስን በተመለከተ እውቀት ያላቸው የባንክ ባለሙያዎችን እንዲያማክሩ፣ ስለ አልሚዎቹ እና ፕሮጀክቱ ጥናት እንዲያደርጉ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን እንዲገመግሙ ይመከራል።
❗️ ከፈንጅ አምካኝ ቀጥሎ ከስህተት ሊማሩበት የማይቻለው የቤቶች ግብይት ነው ይባላል። ይህም በምክንያት ነው ። ቤት እገዛለሁ ብሎ ስህተት ውስጥ የገባና ጥሪቱን ያሟጠጠ ተመልሶ ቤት የመግዛት አቅም ማዳበሩ ከባድ ነውና በእውቀትና በጥንቃቄ እንገበያይ።
ስለ ሪል እስቴት ብቻ የበለጠ ምክር ለማግኘት እና ከባለሙያዎች ጋርም ለመመካከር ከፈለጉ የቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ::
23/07/2023
⚠️ በሪል እስቴት ግብይት ውስጥ ጥንቃቄ የሚያሻው አንቀፅ
#የክፍያአንቀጽ
በዚህ ወቅት በሀገራችን በቅድመ ክፍያ በሚገዙ የሪል እስቴት ግብይት ውል ውስጥ ከባዱ አንቀጽ ከክፍያ ጋር የተያያዘው ነው።
በግንባታ ሂደት በተከፋፈለ ክፍያ በተራዘመ ሂደት ግንባታ ሂደትን ታሳቢ ያደረገ ግብይት (pre sales) አንዱ ቤት ገዢዎች ቤት እንዲገዙ የሚያስችል አካሄድ ሲሆን አልሚዎችም ለግንባታ የሚሆን ፋይናንስ የሚያገኙበት አንዱ መንገድ ነው።
የሪል እስቴት ግብይት የሚመራበት ወጥ መመሪያ አለመኖርና ዘርፉን በሃላፊነት የሚመራ ተቋም ባለመኖሩ ግብይቱ በዋናነት የሚከናወነው በአልሚዎች በኩል በሚዘጋጅ የግብይት ውል ነው።
ከውሉ ውስጥ አንዱ ከሌላው የሚለይበት የክፍያ አንቀጽ ነው። የተለያየ የአከፋፈል ሁኔታዎች ስላሉ በዚህ ወቅት ቤት የሚገዙ ሊጠነቀቁበት የሚገባው የአከፋፈል ሁኔታ progress payment የሚባለውን አይነት ነው።
በprogress payment ውስጥ ብዙዎች ግንባታው ቀስ ብሎ ይከናወናል ብሎ በማሰብ ብዙም ሳያቅማሙ ውሉን ተቀብለው የመጀመሪያ የሚባለውን አነስተኛ ክፍያ (15-20%) ከፍለው ፈርመው ግብይቱን ይፈጽማሉ።
አልሚዎችም ግንባታውን ከሚጠበቀው ፍጥነት በላይ አፋጥነው በመገንባት ገዢዎችን ሁለተኛም ሆነ ሶስተኛ ክፍያ እንዲከፍሉ ይጠይቃሉ።
ይህ የግብር ማፍጠን ተዘጋጅቶ ለተቀመጠ ወይም የተጠራቀመ አቅም ላለው ተዘጋጅቶ ለተቀመጠ ጥሩና አበረታች ሲሆን ሰርቶ ቆጥቦ ያለውን አገላብጦ ሰርቶ ለሚከፍል አብዛኛው ገዢ ግን ፈተና እየሆነ ነው።
ለገዢዎች ክፍያውን ለመክፈል የሚሰጣቸው ጊዜ በአብዛኛው ከአንድ ወር አይበልጥም ብዙዎቹ ጋር እንደውም ያነሰ በቀናት የሚቆጠር ነው።
ገዢዎች በተጠቀሰው ጊዜ መክፈል ካልቻሉ ማስጠንቀቂያና ቅጣት ተደማምረው ከግብይት ውጭ እንዲሆኑ እየሆኑ ከከፈሉት ቅድመ ክፍያ ላይ እስከ 20% ተቀንሶባቸው ውላቸው ተቋርጦ የከፈሉበት ቤት ለሌላ ገዢ ከፍ ባለ ዋጋ እንዲሸጥ ይደረግና ዙሩም ይቀጥላል።
ስለዚህ ቤት ገዢዎች ውል ሲዋዋሉ አቅማቸውን ገምግመው የገበያውን አሰራር ተረድተው ቢሆን ተመካሪ ነው ። በተጨማሪም ውላቸው ላይ ከ ግንባታ ሂደት በተጨማሪ የጊዜ ሰሌዳ እንዲቀመጥላቸው ቢያደርጉ ወይም እንደዚያ የሚያመቻቹ አልሚዎችን ምርጫቸው ቢያደርጉ መልካም ነው
ጥቂት የማይባሉ በዚህ ሂደት ተጎጂ እየሆኑ መሆኑ ይህ የግብይት ውል አንቀጽ ቀጣዩ የዘርፉ ፈተና እንዲሆን ያሰጋል።
እየተጠነቀቅን እየተሳሰብን እንገበያይ።
📝 ስለ ሪል እስቴት ብቻ የበለጠ ለመወያየት ከስር ያለዉን ሊንክ ተጭነው ይቀላቀሉን
22/07/2023
ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ቤት ሲገዙ የሚያገኟቸው ጥቅሞችና ጥንቃቄ ሊያደርጉባቸው የሚገቡ ጉዳዮች 📂
በሃገራችን የቤቶች ግብይት ውስጥ ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተሻለ ተጠቃሚ የሚያደርጓቸው በርካታ ሁኔታዎች በመኖራቸው የተነሳ በግብይቱ ዋና ተዋናይ ሆነው ይታያሉ።
ቤት በሀገር ቤት ሲገዙ ያሏቸው ጥቅሞች🔑
ሀ) ከሀገራቸው ጋር ያላቸው ትስስር ይጨምራል
ለ) በሀገራቸው ቋሚ ንብረት አፍርተው ቤተሰቦቻቸውን ለመጦር ይችላሉ። ለእነሱም የማረፊያና በጡረታ ወቅት መጠቀሚያ ይሆናቸዋል።
ሐ) በዲያስፖራ ፋይናንሲስግ ለቤት መግዢያ እስከ አስር በመቶ ድረስ ብቻ በውጭ ምንዛሪ ከፍለው ቀሪውን 90% ብድር ከባንኮች ለማግኘት መቻላቸው
መ) በተመረጡና ቦታዎች ላይ በተጠና መንገድ ቤቶችን በመግዛት የቤት ቁስ በሟሟላት በጥሩ ዋጋ በማከራየት ጥሩ ገቢ ያገኙበታል
ሠ) በተከፋፈለ የአከፋፈል ሁኔታ በብር በሚደረግ ክፍያ ውል ገብተው ከሚገነቡ ሪል እስቴት አልሚዎች ሲገዙ በየእለቱ ከሚወርደው የብር ምንዛሪ ተጠቃሚ ይሆናሉ።በውጭ ምንዛሪ ስሌት በብር የሚከፈል ግብይት ውስጥም ተጠቃሚነታቸው ላቅ ያለ ነው።
ረ) እንደ ኢንቨስትመንት ለሚያስቡትም ከርቀት ሆኖ የሚሰራ ቀላል እና አዋጭ የስራ ዘርፍ ነው። ዛሬ የተገዛ ቤት ከሁለት አመት በኋላ ሁለት ከአራት አመታት በኋላ ጥቂት እየተጨመረበት አራትና አምስት እየሆነ ሊበዛ የሚችል ነው።
ሊጠነቀቁባቸው የሚገቡ ጉዳዮች 🆘
ሀ) ገበያውን በደንብ ያጥኑ:- ብዙ አማራጮች ስላሉ ከመወሰናቸው በፊት በርካታ አማራጮችን እንዲመለከቱና ጥቅሞቻቸውን አስልተው አቅማቸውንም አይተው ገምግመው እንዲገዙ ይመከራል።
ለ) የግብይት ባለሙያዎችን መጠቀም:- በሪል እስቴት ዘርፍ ግብይት ውስጥ ጥሩ ሙያና እውቀት ያላቸውን የግብይት ባለሙያዎችን እገዛና ምክር መጠቀም
ሐ) ህጋዊ ጉዳዮችን መለየት:- የሪል እስቴት ግብይት ከፍ ያለ ነዋይ የሚፈስበት በመሆኑና በሀገራችን ወጥ የሆነ የግብይት መመሪያ ስለሌለ በአልሚዎች የሚዘጋጁ የግብይት ውሎች ብዙ ልዩነት ስላላቸው የግብይቱን ሂደት እና የሚዋዋሉትን ውል በህግ አማካሪ ወይም በግብይቱ ልምድ ባለው የማርኬቲንግ አማካሪ እንዲጠቀሙ ይመከራል
መ) የፋይናንስ አማራጮችን መለየት:- ገዢዎች ቤት ከመግዛታቸው በፊት ግብይቱ የሚጠይቀውን ክፍያ በሚፈለገው ጊዜ ሊያገኙበት የሚችሉት እና የተሻሉ የባንክ ብድር እና ከክፍያ ጋር የተያያዙ ቅናሾችን ለይቶ መጠቀምን ታሳቢ ያድርጉ
ሠ) ጉብኝት ማድረግ:- የሚገዙትን ቤት ውሳኔ ከመወሰናቸው በፊት ጊዜያቸውን አተካክለው ወደ ሀገርቤት መጥተው በአካል አማራጮችን ቤቶቹ የሚገኙበትን አካባቢም ቢመለከቱ ካልታሰበ ኪሳራ ይዳርጋቸዋል
ረ) መሰረተ ልማትን መመልከት:- ቤት ብቻውን ቢያምር ዲዛይኑም ማራኪ ቢሆን ግንባታውም ቢጠናቀቅ መሰረተልማት ካልተሟላለት የታለመለትን የመኖሪዬነትም ሆነ የኢንቭስትመንት ዓላማ ስለማያሳካ መሰረተ ልማትን መሟላት አለመሟላቱን ለማሟላት ቀላል ወይም ከባድ መሆኑን ተስፋውንም መገምገም ይገባል።
☀️ ☀️ ☀️
ሲጠቃለል ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከርቀት ሆነው ለሚያደርጉት የቤት ግብይት ትኩረት ሰጥተው፣ በባለሙያ ታግዘው፣ ጥቅማቸውን አስልተው፣ አማራጮችን ተመልክተው አመዛዝነው ፣መርጠው፣ የግብይት ውሎችን መርምረው ፣ አስቻይ የአከፋፈል ስርዓቶችን ለይተው ቢሆን ይመከራል።
ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቤት ገዢዎችን ከየትኛውም አልሚ ቢገዙ ነጻ የማማከር አገልግሎት እንሰጣለን።
17/07/2023
🏫 አቡቀለምሲስ የሪል እስቴት ማሰልጠኛ ተቋም
ተቋማችን አቡቀለምሲስ በ16 ዙሮች ከአራት መቶ በላይ የሪል እስቴት ሽያጭ ባለሙያዎችን አሰልጥኖ በዘርፉ እንዲሰማሩ አድርጓል።
17ኛና 18ኛ ዙር ስልጠና በታዳሽ ኢንዱስትሪ ስፖንሰር አድራጊነት ስልጠና ጀምረዋል።
በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ለሚመዘገቡ ሁለት ዙር ስልጠናዎች በታዳሽ ኢንዱስትሪ (ታዳሽ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ ማህበር) ስፖንሰርሺፕ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ።
በርካታ የሪል እስቴት አልሚዎችና የማርኬቲንግ ስራ የሚሰሩ ኤጀንቶች ከተቋማችን ለሚወጡ ሰልጣኞች የስራ እድል አመቻችተዋል።
በዚህ እድል ለመጠቀም የምትፈልጉና ከታች የተቀመጠውን መስፈርት የምታሟሉ በተያያዘው ፎርም ላይ እንድትመዘገቡ እንጠይቃለን
🟢 በማንኛውም ዘርፍ ቢያንስ በዲፕሎማ የተመረቁ
🟢 ስራ የሌላቸው
🟢 ለስልጠናው በቂ ጊዜ ያላቸው
🟢 በዘርፉ ተሰማርተው ለመስራት ፍላጎቱና ዝግጅቱ ያላቸው
🟢 ለመጸሃፍ ፣ ሰርተፍኬት እና ብቃት ማረጋገጫ 900ብር መክፈል የሚችሉ
ለመመዝገብ 👇
https://forms.gle/MvhYebY3kcAtXb5i9
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮቻችን 0951040404 | 0930100191 ይደውሉ ወይም ቢሯችን ብቅ ይበሉ።
መመዝገብያ ፎርም በታዳሽ ትሬዲንግ እስፖንሰርነት የቀረበ በሪል እስቴት ሽያጭ ዘርፍ ለ100 ተማሪዎች የቀረበ ስልጠና
17/07/2023
13/07/2023
Attention real estate investors!
We have the perfect apartment for your portfolio. With its modern design
convenient location and strong rental potential this property ticks all the boxes.
Secure your investment today! 🏢💼
Armonium Real Estate | F6-01 📍Building code : F6-01 ➖Type: Appartment (3 bedrooms)➖Area(Sq.m): 129➖Status: Fully Finished➖Title deed: Yes ➖Price: 13,878,000 Birr➖Location: Addis Ababa, ...
04/07/2023
🏫 አቡቀለምሲስ የሪል እስቴት ማሰልጠኛ ተቋም
ተቋማችን በ16 ዙሮች ከአራት መቶ በላይ የሪል እስቴት ሽያጭ ባለሙያዎችን አሰልጥኖ በዘርፉ እንዲሰማሩ አድርጓል።
በቀጣይ ሁለት ወራት በታዳሽ ኢንዱስትሪ (ታዳሽ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ ማህበር) ስፖንሰር አድራጊነት ለአንድ መቶ ሰልጣኞች ልዩ ስልጠና አዘጋጅቷል።
በርካታ የሪል እስቴት አልሚዎችና የማርኬቲንግ ስራ የሚሰሩ ኤጀንቶች ከተቋማችን ለሚወጡ ሰልጣኞች የስራ እድል አመቻችተዋል።
በዚህ እድል ለመጠቀም የምትፈልጉና ከታች የተቀመጠውን መስፈርት የምታሟሉ በተያያዘው ፎርም ላይ እንድትመዘገቡ እንጠይቃለን
1) በማንኛውም ዘርፍ ቢያንስ በዲፕሎማ የተመረቁ
2) ስራ የሌላቸው
3) ለስልጠናው በቂ ጊዜ ያላቸው
4) በዘርፉ ተሰማርተው ለመስራት ፍላጎቱና ዝግጅቱ ያላቸው
5) ለመጸሃፍ ፣ ሰርተፍኬት እና ብቃት ማረጋገጫ 900ብር መክፈል የሚችሉ
6) እድሜ ከ20-35 የሆኑ
ለመመዝገብ 👇
https://forms.gle/MvhYebY3kcAtXb5i9
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮቻችን 0951040404 | 0930100191 ይደውሉ ወይም ቢሯችን ብቅ ይበሉ።
መመዝገብያ ፎርም በታዳሽ ትሬዲንግ እስፖንሰርነት የቀረበ በሪል እስቴት ሽያጭ ዘርፍ ለ100 ተማሪዎች የቀረበ ስልጠና
Coffee Plaza (ኮፊ ፕላዛ )
በመሀል ካዛንቺስ ግንባታው 65% የተጠናቀቀለት መኖሪያ ቤት በ30% ብቻ ቅድመ ክፍያ ቀሪውን 70% በሁለት አመት ጊዜ በ6ዙር ማጠናቀቅ ይቻላል ::
ለበለጠ መረጃ /ሳይት ለመጎብኘት 097 577 7879 ይደውሉ :: ከሰኞ እስከ እሁድ ለማስተናገድ ዝግጁ ነን!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Lideta
Addis Ababa