Abyssinia

Abyssinia

Share

Positive thinking, or optimistic attitude, is the practice of focusing on the good in any situation.

06/19/2026

''ኢሰመኮ በአርሲ የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ ያወጣው ሪፖርት ''እውነትን ያድበሰበሰና ፖለቲካዊ ዓላማ ያለው ነው'' ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት''

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በቅርቡ በአርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተ ያወጣው ሪፖርት እውነታውን ያደበሰበሰና የፖለቲካ ዓላማ ያነገበ ነው ሲል ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት በጽኑ ወቀሰ።

ትብብሩ ለኮሚሽኑ በላከው ይፋዊ ደብዳቤ ላይ እንዳመለከተው፣ ኢሰመኮ ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት የሟቾችን ቁጥር ሦስት ብቻ ማድረጉና ጥቃቱ ሃይማኖትን ማዕከል ያላደረገ ነው በማለት የደረሰበት ድምዳሜ ፍጹም ስህተት ነው።

ከተጎጂዎችና ከታማኝ የቦታው ምንጮች አግኝቸዋለሁ ያለው መረጃ እንደሚያሳየው የሟቾች ቁጥር ኮሚሽኑ ከጠቀሰው በአሥር እጥፍ እንደሚበልጥና ''ፍጅቱም'' ጥንታዊ ቤተክርስቲያንን ከማቃጠል ጀምሮ ሃይማኖትና ማንነትን ማዕከል አድርጎ የተቀናጀ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል።

ኮሚሽኑ ለፍጅቱ ተጠያቂው ''ኦነግ ሸኔ'' መሆኑን በፍጥነት ደምድሞ ማለፉ፣ በአካባቢው የመንግሥት መዋቅር እጅ አለበት የሚለውን የሰለባዎች ተደጋጋሚ ቅሬታ ሆን ብሎ ወደ ጎን የተወ አስመስሎታል ብሏል።

ይህ ዓይነቱ አካሄድም በአርሲ ዞን ለሚፈጸመው የተቀናጀ ''ዘር ፍጅት'' በርካታ አካላት የሚሳተፉበት መሆኑ እየታወቀ እውነታውን ለመሸፈን የተደረገ ጥረት ነው ሲል ትብብሩ ከስሷል።

ድርጅቱ አክሎም፣ ኮሚሽኑ ቀደም ሲል በሀገር ውስጥ የሚፈጸሙ ግፎችን ከቦታው በመረጃና ማስረጃ አስደግፎ በማቅረብ ረገድ ያሳይ የነበረው ትጋት አሁን ላይ እየቀነሰ መምጣቱንና እንደ አሰኮ ወረዳ ያሉ ሪፖርቶችም ሕዝብ በኮሚሽኑ ላይ ያለው እምነት እንዲሸረሸር እያደረጉት እንደሚገኝ ገልጿል።

በመጨረሻም የትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ፕሬዝዳንት ተፈርሞ የተላከው ደብዳቤ፣ ኮሚሽኑ ይህንን የተሳሳተ ሪፖርት ማውጣት ያስፈለገበትን መግፍኤ ገልጾ፣ በቦታው እንደገና ጥልቅ ማጣራት በማድረግ የተዛባውን መረጃ ለሕዝብ ማስተካከያ እንዲሰጥበት ጠይቀዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በጥቃቱ ውስጥ ያለውን የመንግሥት መዋቅር ድርሻ በግልጽ በመጥቀስ ተጠያቂነት እንዲሰፍን፣ እንዲሁም ሕዝቡ ተፈጥሯዊ መብቱን ተጠቅሞ ራሱን ሊከላከል የሚችልበትን መፍትሔ ጭምር ኮሚሽኑ እንዲጠቁም በአክብሮት ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

Via:- ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት

የትብብሩን ደብዳቤ እንደት ያዩታል ሀሳብዎን ያካፍሉን?

06/19/2026

የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን አውስትራሊያን በማሸነፍ በዓለም ዋንጫው ሁለተኛ ድሉን አስመዝግቧል!

አሜሪካ 2-0 አውስትራሊያ

በምድብ ዲ (Group D) ሁለተኛ ጨዋታቸውን ያደረጉት የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን አውስትራሊያን 2 ለ 0 ድል ማሳካታቸውን ችለዋል።

ጨዋታው እስከ 96ኛ ደቂቃ (6 ደቂቃ ተጨማሪ ሰዓት) ድረስ በከፍተኛ ፍጥነትና ውጥረት ቢጓዝም፣ የአሜሪካ ተከላካዮች ሳይበገሩ መረባቸውን ሳያስደፍሩ በንጽህና መውጣት ችለዋል። በዚህም ውጤት አሜሪካውያን በምድባቸው ያላቸውን መሪነት ይበልጥ አጠናክረዋል።

ለአሜሪካ ቀዳሚውን ጎል በ 11ኛው ደቂቃ ላይ የአውስትራሊያው ተከላካይ ሲ. በርገስ (C. Burgess) በራሱ መረብ ላይ ባስቆጠረው ጎል (OG) ማግኘት የቻሉ ሲሆን፣ ማጥቃታቸውን በመቀጠል በመጀመሪያው አጋማሽ ማጠናቀቂያ በ 43ኛው ደቂቃ ላይ አሌክስ ፍሪማን (A. Freeman) ሁለተኛዋንና የማሸነፊያዋን ድንቅ ጎል አስቆጥሯል።

በሁለተኛው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ተጭነው ቢጫወቱም ተጨማሪ ጎል ሳይቆጠር ጨዋታው በአዘጋጇ አሜሪካ ፍጹም የበላይነትና አሸናፊነት ተጠናቋል።

⚽️⚽️⚽️

06/19/2026
06/19/2026

Get it

06/18/2026

ለናንተ አደገኛው ማነው?

06/18/2026

«ራበኝ!» ከሰው ልጅ አፍ ሲወጣ እጅግ የሚጨንቅ፣ ሰሚን የሚያደነግጥ ቃል ነው። በተለይ ከጥበብ ባለሙያ ሲሆን.....

«ራበኝ!» ይርብሃል! ሲል የተደመጠው ተዋናይ ዳንኤል አሸናፊ (ዳኒ ጢሞ) ይባላል፤ ላለፉት 30 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ እና በተለያዩ ፊልሞች ላይ ወጣትነቱን እና ሙሉ አቅሙን የሰጠ ባለሙያ ነው።

ሰሞኑን በሰይፉ ፋንታሁን ሾው ላይ ቀርቦ የተናገራት ቃል የብዙ ሰዎችን ልብ ነክቷል፤ ተዋናዩ እንደተቸገረ እና አዲስ አበባ ለመኖር እንደከበደው፣ ከተማ ለቆ ወደ ገጠር እናቱ ጋር ለመሔድ እስከመዘጋጀት የደረሰበትን፣ የኑሮ ውጣ ውረድ ሲናገር ብዙዎችን አስለቅሷል።

«ራበኝ!» ከሰው ልጅ አፍ ሲወጣ እጅግ የሚጨንቅ፣ ሰሚን የሚያደነግጥ ቃል ነው። ይልቁኑ ደግሞ ሌሎችን በኪነጥበብ ሲያዝናና፣ ሲያስተምር እና የህዝብ ድምፅ ሲሆን የኖረ አርቲስት በኑሮ ውድነት ምክንያት ራሱን ማስተዳደር አቅቶት ይህንን ቃል ሲናገረው ስብራቱ ይበልጥ ጥልቅ እና አሳዛኝ ይሆናል።

አርቲስት ማለት የህብረተሰብ መስተዋት ነው። ለሰዎች ሳቅ፣ እውቀት እና መጽናኛን የሚያድል የጥበብ ምንጭ፤ ነገር ግን ዛሬ ያ መስተዋት በገበያው ግሽበት እና በኑሮ ውድነት አለንጋ ተገርፎ ሲሰበር ከጀርባው ያለው ህመም ያስፈራል።

ከአንድ ትልቅ የአርት ባለሙያ ለዓመታት በጭብጨባና በክብር መድረክ ላይ የደመቀ ያ የጥበብ ሰው ዛሬ በኪራይ ቤት መቸገር፣ በዕለታዊ ቀለብ ማጣት እና በብቸኝነት ውስጥ መሆን ሲናገር መስማት ትልቅ ህመም ነው።

ለአርቲስት ከምንም በላይ ክብሩ፣ ስሙ እና ጥበቡ ትልቅ ነው። ረሃብን ደብቆ የውስጥ እንባውን አፍኖ መድረክ ወይም ካሜራ ፊት ፈገግ ማለት ምንኛ ከባድ ስቃይ ነው? "ሰዎችን በስራው ሲመግብ የነበረ፤ እኔ ግን ራበኝ አጣሁ ሲል'' ለሀገሩ ባህልና ጥበብ ህይወቱን ሰጥቶ፣ ሀገሩ ግን ለአንድ ጉሮሮ የሚሆን እንጀራ ነፈገችው።"

ይህ የብዙዎች የውስጥ የለቅሶ ድምፅ ነው። «ራበኝ!» የሚለው ቃል ከአርቲስቱ አፍ የሚወጣው አማራጭ ሲጠፋ፣ ኩራቱ በረሃብ አለንጋ ተሸንፎ መሬት ሲደፋ ብቻ ነው።'' ያኔ ቃሉ ተራ የሆድ መጎድጎድ መግለጫ መሆኑ ቀርቶ የማህበረሰቡ እና የኪነጥበብ መውደቅ ማሳያ ይሆናል።''

የሰውን ልጅ መንፈስ የሚያክሙ የጥበብ ሰዎች በኑሮ ውድነት ተደፍተው «ራበኝ» ሲሉ ጥበብ ራሷ አልቅሳለች ማለት ነው። «ይህ ቃል የርዳታ ጥሪ ብቻ አይደለም የሀገር ስብራት እንጂ!»

ተዋናዩ የደረሰባት ችግር ሰምቶ ከንፈር መምጠጡ እና ማለቀሱ በቂ አይደለም? መርዳት ግደታ ነው።

''ዳንኤል አሸናፊ (ዳኒ ጢሞ) "ያልተዘመረለት የጥበብ ኮከብ" በሚል ርዕስ አድናቂዎቹ የሙያ አጋሮቹ የጥበብ ቤተሰቦች በተገኙበት በክብር ሊመሰገን መሆኑንም ሰምተናል ይበል የሚያሰኝ ነው።''

ለተጨማሪ መረጃ እና ትኬት ለማግኘት
በስልክ ቁጥር:- 0910195041
0910316603

በተጨማሪ ይህን ብርቱ የጥበብ ባለሙያ ለማገዝ

ዳንኤል አሸናፊ
CBE: 1000343965037

ሰላም ለኢትዮጲያ
ሰላም ለህዝባችን
ወሎ አዲስ የህዝብ አድማስ

06/18/2026

“መንግስት ወጣቱን ተስፋ አስቆርጦ መጨረስ ነው ፍላጎቱ” ወጣቷ

06/17/2026

ፍትሕና ነፃነት ልመና አይደሉም፤ የዜግነት መብቶቻችን ናቸው!

አንድን ጋዜጠኛ ማፈን እውነትን ማሰር አይደለም፤ አንድን ድምፅ ማጥፋትም የሕዝብን ጥያቄ ማጥፋት አይችልም። ዛሬ በጋዜጠኛ ሳልሳዊት ባይነሳኝ ላይ የተፈጸመው ሕገ-ወጥ እስር አንድ ሳምንት ሲሞላው፣ ጉዳዩ የአንድ ግለሰብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የመላው ሕዝብ የነፃነትና የፍትሕ ጥያቄ መሆኑን እንደገና አስታውሶናል።

ሳልሳዊት ባይነሳኝ የታሰረችው ወንጀል ፈጽማ ሳይሆን፣ የሕዝብን ጥያቄ በመጠየቋ፣ ሙስናን በማጋለጧ፣ የተበደሉ ዜጎች ድምፅ በመሆኗ ነው ። እውነትን መናገር ወንጀል በሚሆንበት ሀገር፣ ነፃነት በአደጋ ላይ ነው።

ከሳምንት በላይ ያለ ይፋዊ ክስ፣ ያለ ፍርድ ቤት ቀረባ፣ ያለ ግልጽ ሕጋዊ ሂደት አንድ ዜጋን ማቆየት የሕግ የበላይነትን መናቅ እንጂ የፍትሕ ሥርዓት አይደለም። ይህ ድርጊት በአንድ ጋዜጠኛ ላይ ብቻ የተፈጸመ ጫና ሳይሆን ለሁሉም ዜጎች "ዝም በሉ" የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ የሚደረግ ሙከራ ነው።

ነገር ግን ነፃነትን አንለምንም። ፍትሕንም አንማጸንም። እኛ የዚህ ሀገር ባለቤቶች ነን፤ የመናገር መብት፣ የመጻፍ መብት፣ የመጠየቅ መብት፣ የመተቸት መብት የማንም ገዥ ስጦታ ሳይሆን በዜግነታችን የሚገባን መሠረታዊ መብት ነው።

ሀገር የምትገነባው በፍርሃት ሳይሆን በነፃ ሃሳብ ነው፤ ሥልጣን የሚታረምበትም በጥያቄ እንጂ በዝምታ አይደለም። እውነትን የሚናገሩ ድምፆችን ማሰር ታሪክን ማቆም አይችልም፤ የፍትሕ ጥያቄንም ማጥፋት አይችልም።

ዛሬ ለሳልሳዊት የምንቆም ከሆነ፣ ለአንድ ግለሰብ ብቻ አይደለም፤ ለሁላችንም ነው። ምክንያቱም የአንድ ዜጋ ነፃነት ሲገፈፍ የሁላችንም ነፃነት ይጎዳል፤ የአንድ ዜጋ መብት ሲረገጥ የሁላችንም መብት በአደጋ ላይ ይወድቃል።

ፍትሕ ይከበር!
ሕግ ይከበር!
እውነት አትታሰርም!

ነፃነት አይለመንም — የዜጎች የማይደራደር መብት ነው!

#ሀገር #ፍትህ #አዲስአበባ #ዲሞክራሲ #እኩልነት #ነፃነት TikTok

Want your business to be the top-listed Media Company in Virginia Beach?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


Virginia Beach, VA