Intelligent Group
To promotion
04/30/2026
እንኳን ለዚህ ክብር አበቃችሁ
የማህበራችን አባል ከሆኑት መካከል ወጣት ቸርነት ባንድራ እና ስጦታ ብላቱ የፊታችን እሁድ ይሞሸራሉ።💍
መልካም ጋብቻ!
The Date 25/08/2018
04/22/2026
እንኳን ለዚህ ክብር አበቃችሁ
የማህበራችን አባል ከሆኑት መካከል ወጣት ፋሲካ አብርሃም እና ሊል ነገሶ የፊታችን እሁድ ይሞሸራሉ።💍
መልካም ጋብቻ!
The Date 18/08/2018
10/21/2025
እንኳን ለዚህ ክብር አበቃችሁ
የማህበራችን አባል ከሆኑት መካከል ወጣት ኢሳያስ እንድሪያስ እና ሮሪታ አዲሱ የፊታችን እሁድ ይሞሸራሉ።💍
መልካም ጋብቻ
the date 16/02/18
09/14/2025
የIntelligent Group 3ኛ ዓመት ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ አካሂደናል።
በዓመታዊ ጉባኤው የማህበራችን የ2017 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ከመገምገም ባሻገር የኦዲት ሪፖርት በማዳመጥ ሰፋ ያለ ሀሳብ በማንሸራሸር አቅጣጫዎችን ያስቀመጥን ሲሆን በቀጣይ 2018 ዓ.ም እቅድ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት በማድረግ የማህበሩን ጠንካራ ጎን ለማስቀጠል እና ካፒታላችንን ለማሳደግ ከስምምነት የደረስን ሲሆን ከማህበሩ የተሻለ አፈጻጸም ያሳዩ አባላትን በመሸለም የእለቱን ስብሰባ አጠናቀናል።
በስራ ምክንያት በተለያዩ የሀገራችን ክፍል ሆናችሁ የዛሬውን ጠቅላላ ጉባኤ ያልተካፈላችሁ አባላት በቀጣይ ዓመት እንደሚትገኙ እምነታችን የጸና ነው።
የዓመት ሰው ይበለን።
📷 Kibru Gizachew
01/28/2025
እንኳን ለዚህ ክብር አበቃችሁ
የማህበራችን አባል ከሆኑት መካከል ወጣት ሰለሞን ሳሙኤል እና ነጻነት መርሳ የፊታችን እሁድ ይሞሸራሉ።💍
መልካም ጋብቻ
25/05/17 መቅረት አይቻልም::
12/03/2024
ከ Intelligent group አባላት የተወጣጣው
ከበጎ አድራጎት ስራዎች ባሻገር የተለያዩ ዘግጅቶችን ማድመቅ ከፈለጉ አያሳስብዎ እኛን ያናግሩን ይሎታል!
እንደስማችን ምስክር ነው ስራችን! 🦅
ለበለጠ መረጃ
☎️ +251946026564
☎️+251925744937
11/25/2024
አክልሉ ገመቹ
እንኳን ደሰ አለህ
የማህበራችን አባል ከሆኑት መካከል ወጣት አክሊሉ ገመቹ የፊታችን እሁድ ይሞሸራል።
ፈጣሪ እንኳን ለዚህ ክብር አበቃህ💍
መልካም ጋብቻ
22/03/2017 መቅረት አይቻልም::
04/12/2024
!
ገና በልጅነታቸዉ በደረሰባቸው ፆታዊ ጥቃት የተጎዱ እህቶቻችንን እየደገፈችና ስነልቦናዊ ጉዳት የደረሰባቸውን እየመከረች ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመሆን ፆታዊ ጥቃት ይቁም ብላ ለብዙ ሕፃናት፣ሴቶች ዘብ የቆመች እና የተቸገሩትን እየረዳች ለሌሎች የሚትኖር አንዲት ጀግና እናት እናስተዋውቃችሁ፡፡
ወ/ሮ ታየች ብርሃኑ ይባላሉ የሚ ኖሩት በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ምስራቅ ክ/ ከተማ ሲሆን በሀዋሳ ከተማ እና ከተለያዩ ቦታዎች የሚመጡ ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች እና ህጻናትን በጉያቸው በማስጠለልና ድምፅ የሚሆናቸውን ላጡ ተጎጂዎች ድምፃቸውን እያሰሙ ጥቃት አድራሾቹ በህግ እንዲጠየቁ ከተጎጂዎች ጎን በመቆም ከመንግስት እና ግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር እየሰሩ ይገኛሉ።
እኛም ከእናታችን ጋር በነበረን ቆይታ ብዙ ጠቃሚ ትምህርትና ምክር ወስደን ተመልሰናል።በሌላ በኩል ከእድሜ አንጻር ከሚመጣ ድካም የተነሳ እናታችን ይህንን ስራ የሚደግፋቸውንና ተተኪ ሆኖ የሚያስቀጥልላቸውን ሰው እንደሚፈልጉ አጫውተውናል።
ማህበራችንም አቅሙ በፈቀደው መጠን ለስራቸው ያግዛቸዋል ብሎ ያሰበውን የንፅህና መጠበቂያ የሚሆኑ ቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ሌሎቻችንም በተቻለን መጠን እናታችንን እየጎበኘን የሚሰሩትን መልካም ስራ እናበረታታ ፣ እንደግፋቸው መልእክታችን ነዉ ።
ስም ወ/ሮ ታየች ብርሃኑ ስ.ቁ 0953760388
አድራሻ ምስራቅ ክ/ከተማ
ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው!!!
ኢንተሊጀንት ግሩፕ በጎ አድራጎት ማህበር።
03/31/2024
ኢንተሊጀንት ግሩፕ በጎ አድራጎት ማህበር ለአንዲት እህት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
******************************
ኢንተሊጀንት ግሩፕ መጋቢት 22/07 /2016 ዓ. ም ሐዋሳ
ኢንተሊጀንት ግሩፕ በጎ አድራጎት ማህበር በትላንትናው እለት በይርጋዓለም ከተማ 05 ቀበሌ ለአንዲት እህት የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። ማህበሩ ከተቋቋመ ወዲህ የመጀመሪያውን ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በቀጣይም መጠነ ሰፊ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ለመስራት በይፋ ወደ ተጠናከረ እንቅስቃሴ መግባት ችሏል።
በትላንትናው እለት ወደ ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን በመሄድ ድጋፍ ያደረግንላት እህታችን ትርፌ ኢሳይያስ የምትባል ሲሆን ባለቤቷ ልጅ ከወለደች በኋላ እቤት ያለውን እቃ ሽጦ ጥሏት እንደጠፋና በአራስነት ጊዜዋ ብዙ አይነት ችግር እንደተፈራረቅባት ለራሷና ለልጇ የእለት ጉርስ እና ቤት ኪራይ ስትል የቀን ስራ እስከመስራት ደርሳ እንደነበር አጫውተናለች በዚህም ወቅት ስራው ከብዷት መታመሟንና በብዙ ስቃይ ውስጥ እንዳሳለፈች ከአንደበቷ መስማት ችለናል።
በአሁኑ ወቅት ደጋግ ቤተሰቦች በረንዳቸውን ተጠቅማ ሻይ ቡና አስጀምረዋት በመስራት ላይ ትገኛለች።
ማህበራችን ባለው አቅም ለሻይ ቡና መሰረታዊ የሆኑ ቁሳቁሶችን በድጋፍ መልክ የለገሳት ቢሆንም ይህ በቂ ባለመሆኑ ደጋግ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እንዲያደርጉላት ማህበራችን ጥሪውን እያስተላለፈ ለጊዜው ለሻይ ቡና እንትድትጀምር የተፈቀደላት የሰው በረንዳ ከመሆኑም ባሻገር ቦታው የሰው እንቅስቃሴ የማይኖርበት መሆኑን ተከትሎ ወደተሻለ ቦታ እንዲትቀይር የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲታረጉላት እንማጸናለን።
#ለጊዜው በአዋሽ ባንክ የተከፈተ አካውንት አያይዘን አስቀምጠናል።
ስም ትርፌ ኢሳያስ 013561322627500 Awash Bank
ስልክ 0944353542
አድራሻ ይርጋዓለም 05 ቀበሌ ጋሽ ዛላ ጊቢ ፊትለፊት።
በተጨማሪም በማህበሩ አስተባባሪዎች በኩል እህታችንን ለመርዳት ከፈለጉ 0913657098/0946556549/ 0916407479/0926967865/0916551797
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Southern Pines, NC