Sofia Shibabaw

Sofia Shibabaw

Share

Gospel Singer,Founder and CEO of Sofi’s Design,
Actress

06/12/2026

አንድ ባለሀብት ስሜን በሀሰት አጥፍታለች ብለዉ የከሰሷት ቲክቶከር 22,000 የኖርዌይ ገንዘብ እንድትከፍላቸዉና በሌሎችም ከባድ ቅጣቶች ተፈረደባት መባሉን ስንሰማ፡
ለካ የኛም ስም በከንቱ የጠፋዉ የወደፊት በረከታችን እየተጋገረልን ስለሆነ ነዉ።ለበጎ ነዉ ማለት ይሄኔ ነዉ።
አሁን ያሳሰበኝ ስሜ በሀሰት የጠፋበት ቪዲዎዎች ከሚዲያዉ እንዳይነሱ ነዉ።
ቢያንስ ከነዚህ ስራ ጠል አምቶ አዳሪዎች እየተቀበልን ለሀገራችን ድሆች እንሰጣለን።በጣም አበረታች ነገር ነዉ ባለሀብቱ የወሰዱት እርምጃ።

06/09/2026

ዳንኤልንም ከአንበሶች አፍ አድኖታል
ዳንኤል 6:27

06/06/2026

ስለዚህ ልቤን ደስ አለው ምላሴም ሐሴት አደረገች፤ ሥጋዬም ደግሞ በተስፋ ታድራለች፤
ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በፊቴ አየዋለሁ፤ በቀኜ ነውና አልታወክም።
መዝሙር 16:8

06/03/2026

በአርሲ በኦርቶዶክሳዉያን ክርስቲያኖች ላይ የሚደረግ ተደጋጋሚ ጥቃት ማንም ያድርገዉ ማን ይህ ነገር ሊቆም ይገባል። ይህንን ድርጊት የሚፈፅሙትን ሀይላት መንግስት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ወደ ህግ በማቅረብ ህዝቡ በሰላም የመኖር መብቱ ሊከበርለት ይገባል።
አሁን በሀገራችን የሚሰራዉ ልማትና ለዉጥ እጅግ የሚደነቅ ቢሆንም ዋናዉ አንገብጋቢዉ ጉዳይ ግን የህዝብ ደህንነት ሊሆን ይገባል። ህዝብ በነፃነት መዉጣት መግባት ካልቻለ ሁሉም ትርጉም ያጣል።መንግት የህዝብን ደህንነት ሊያስቀድም ይገባል!

06/03/2026

እኔ የአርሰናል ደጋፊ ነኝ። አንዳንድ ጓደኞቼ ደግሞ የማንቸስተር ዩናይትድና የማንቸስተር ሲቲ ደጋፊዎች ናቸው። በባለፈው የቻምፒየንስ ሊግ ፍጻሜ ላይ አርሰናልን ከመጥላታቸው የተነሳ ሁሉም በአንድ ድምፅ የPSG ደጋፊ ሆነው ተገኙ።

እኔም “አርሰናል ብዙ ጠላቶች አሉት፤ ይህን ዋንጫ ቢያነሳ ደስ ይለኛል” ብዬ ለመጸለይ ተንበረከኩ። ነገር ግን ሰው እንደ ቅጠል በሚረግፍባት፣ ብዙ መከራና ችግር በሞላባት ሀገር ተወልጄ ለእግር ኳስ ለመጸለይ ማሰቤ ራሴን ታዘብኩትና የአርሰናልን ጉዳይ ትቼ ለሀገሬና ለሕዝቤ ጸልዬ ተነሳሁ።

በመጨረሻ አርሰናል በፔናልቲ ምቶች ተሸነፈ። ጓደኞቼም ማብሸቃቸዉን ጀመሩ። እኔም እውነት ለመናገር ትንሽ ቅር ብሎኝ ነበር። ነገር ግን ቆይቼ ሳስበው፣ “እኮ ከጥቂት ቀናት በፊት ፕሪሚየር ሊጉን አሸንፈዋል! ለምን በአንድ ሽንፈት ከማዝን በዚያ ታላቅ ድል አልደሰትም?” ብዬ ራሴን ጠየቅሁ።

ያኔ ድብርቴ በአንድ ጊዜ ተነሳ፤ በደስታና በድል መንፈስ ተሞላሁ።

በሕይወትም እንዲሁ ነው። ትናንት እግዚአብሔር የሰጠንን ብዙ ድሎች እየረሳን፣ ዛሬ ባልተሳካልን አንድ ነገር ላይ እናዝናለን። ወደ ኋላ ተመልሰን የሕይወታችንን ገጾች ብንገላብጥ ግን፣ እግዚአብሔር የሰጠን ተቆጥረው የማያልቁ በረከቶች፣ ድሎችና ምህረቶች እናገኛለን።

ስለዚህ ዛሬ ያልተሳካውን ከመቁጠር ይልቅ ፣ ትናንት የተሰጠንን ድል እናስታውስ። ምክንያቱም ምስጋና የሚጀምረው ያጣነውን በመቁጠር ሳይሆን፣ የተሰጠንን በማስታወስ ነው።
Arsenal 🏆

05/25/2026

የኢየሱስ ነኝ።

05/24/2026

እግዚአብሔር ያክብርልኝ ወንድሜ ገጣሚ አቤል አይላ 🙏 አሜን 🙏 ክብር ሁሉ ለክብር ባለቤት ለእግዚአብሔር ይሁን🙏

የሶፊያ ዜማ... የሰማይ ማህተም

​ከሰማዩ ድንኳን ከኪሩቤል መንደር፣
ላንቺ የተሰጠዉ የመረጋጋት ምስጢር፤

እነሱማ .......

ሰዎችማ ምን አላቸው? መሸረብ ነው ስራቸው፣
የቆመውን ጥለው መውደቅ ነው ምርጫቸው።

ብርሃኑን ሸፍነው ጨለማ ሊያሳዩሽ፣
በቃላት አሜኬላ ከፍታሽን ሊቀንሱሽ፤

ጥበብን አጡና በቅናት ታዉረዋል
ቅኔሽን ሊቀሙ ማልደዉ ተነስተዋል።

​ነገር ግን...

ከሰማይ የመጣዉ የቅኔሽ ማዕበል፣
የምድር አሉባልታ ሊያግደዉ አይችል

በተንኮል በሸር ክብርትሽ አይረክስም፣
የጸናዉ እምነትሽ ለአፍታም አይረታም።

05/24/2026

ወንድሜ ገጣሚ መሳይ ጊዜ ወስደህ ስለ እኔ ህይወት ያስተዋልከዉን ቁምነገርና የታዘብከዉን ሁሉ በግጥም ስለገለፅክልኝ ከልቤ አመሰግናለሁ!! እግዚአብሔር ያክብርልኝ!እጅግ ጠጣም ድንቅ ግጥም ነዉ🙏

ሰላምሽ ከላይ ነው

ሰላምሽ ከላይ ነው ከላይ ከፀባኦት ከልዕለ ሰብ ሀገር
የደህንነትሽ ስር የረፍትሽ ቁም ነገር
እዚህ ሰባሪ እንጂ አና'ፂ ሰው የለም
ደህና እደሪ ያለ ደህና አደርሽ አይልም
አንቺ እጅግ ውድ ሴት ለዚያዉም ውድ እንቁ
ወደው ከቀረቡሽ ከስርሽ አይርቁ
የዚህ አለም ግሳንግስ ገፍቶሽ ከፍቅር ሀገር
የሰው አሉባልታ ጋርዶብሽ ቁምነገር
ከፀጋው ባለቤት ሊያርቁሽ ቢጥሩ
አውርደው ሊጥሉሽ ተግተው ቢታትሩ
አምላክሽ ነውና ምርኩዝ መደገፊያሽ
እምነት ተስፋ ፍቅር ይሁን መጠለያሽ

05/23/2026

ኢትዮጵያዊነት

05/23/2026
Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Silver Spring?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address


1400 East West Highway
Silver Spring, MD
20910