AyzoNet

AyzoNet

Share

We are delighted to announce the launch of the Ethiopian Social Media platform called AyzoNet.

10/01/2024

[የእናትና የልጅ ፍቅር በቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ]
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (መስከረም ፳፩| በእመቤታችን በዓል በረከቷን በመሻት የተለጠፈ)
💥 ጌታ ሆይ ከንፈሮችኽ የሕይወትን በጎ መዐዛ ይመግባሉ (ያስገኛሉ) (መሓ ፬፥፲፩)፤ ከጣቶችኽ ጫፍ በጎ መዐዛ ያለው ከርቤ ይንጠባጠባል (መሓ ፭፥፭)፤ ዐይኖችኽ የአንተን ዕይታ በተራበችው በእናትኽ በቅድስት ድንግል ማርያም ላይ በፍቅር ተተክለዋል፤ የቤተ ክርስቲያን የጸጋ ልጆች (ምእመናን) በአንተ ፍቅር የተራቡ ናቸው፡፡

💥 ሱራፌልም “ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ” ብለው ጮኹ፤ ኪሩቤልና ሰራዊቱ ፍጹም ምስጋናን ለባሕርይ አምላክ ለአንተ ምስጋናቸውን አቀረቡ፤ በረቂቅ አካላቸውም ግርግሙን ሸፈኑ፤ ከሱራፌልም አስፈሪ ክንፎች እና ከግርማ ሞገሳዊ ነጐድጓዳዊ ድምፆቻቸው የተነሣ እመቤታችን ማርያምና ዮሴፍ በረአድ ቆሙ (ሉቃ ፪፥፲፫-፲፰)

💥 አንተን የሚወስን ማን ነው? ማንስ ሊይዝኽ ይችላል? አንተን ማን ሊመረምርኽ ይችላል? ያንተን ልደት ምስጢር ለማውጣጣት ማንስ ሊደፍር ይችላል? ... ብሉየ መዋዕል ቀዳማዊዉን ርሱም ተሸክማ ወተትን የምትሰጠው ድንግል እነኋት፤ ኹለቱንም እረኛም ጠቦትም የኾነውም እነሆ (ዮሐ ፲፥፲፩፤ ራእ ፯፥፲፬)። ካህንም መሥዋዕትም ኹለቱንም የኾነው እነሆ (ዕብ ፱፥፲፩-፲፪)፤ ሐሊበ ድንግልናን የሚጠባ ጠቦት ሆይ በባሕርይኽ ክቡር ነኽ!፡፡

💥 ጌታ ሆይ እናትኽ በደስታ ተመልታለች፣ ዮሴፍም በደስታ ተመልቷል፤ አንተም ወኃቤ ፍሥሐ ነኽ፤ የፋሲካ ደስታ ጠቦት የኾንኽ ሆይ! (፩ኛ ቆሮ ፭፥፯) አንተን የወለደች ድንግል ማርያም አንተን ስትስምኽ ደስ ይላታል!

💥 ቀበሮ የተባለ ሰነፍ ንጉሥ የነበረው ሄሮድስ በድምፁ የሚርበተበትበት የአንበሳ ደቦል ነኽ (ዘፍ ፵፱፥፱፤ ማቴ ፪፥፫) አገዛዙን አበቃኽለት በርሱ ቁጥጥር ሥር የነበረው የራስኽን አገዛዝ ተረከብኽ (ማቴ ፪፥፳)፤ አንተ ንጉሥና የነገሥታት ኹሉ ንጉሥ ነኽ (ራእ ፲፯፥፲፬)፡፡

💥 አዳምን ከዐቧራ ፈጥረኸዋል (ዘፍ ፪፥፯) የራስኽንም እናት ፈጥረኻል (ሉቃ ፩፥፴፰)፤ ቀዳማዊ ልደትኽ ከአብ የኾነ ሆይ የአንተ ፈቃድ የአንተን ኲለንታ ትስብዕት በማሕፀነ ድንግል ቀረጸ፤ መለኮታዊ አኗኗርኽ ሊታወቅ አይቻልም አንተ ጥንት የለኽምና (ዮሐ ፩፥፩)፤ አንተ ስለፈቀድኽ ራስኽን በማሕፀነ ማርያም ውስጥ አኖርኽ፡፡

♥ እዚያም እናትኽ፣ ምርጥኽ፣ የእጅኽ ሥራና አገልጋይኽ ድንግል ማርያም ተንበርክካ አንተን ወልዳለች (ሉቃ ፪፥፯)፤ አንተን ስትወልድኽ፣ ዕቅፍ አድርጋ ስትስምኽ በምስጋናና በጸሎት ታመሰግንኻለች፤ አንተን ስታቅፍኽ ወተቷን ታጠባኻለች ለአንተ በመዘመርና በሕፃንነትኽ መንገድ ፈገግ በማለት፣ አንተ ወተቷን እየጠባኽ በደስታ ስትመላ፣ አንተን የወለደችኽ ለአንተ ወተት ያጠባችኽ በአድናቆት ትዋጣለች፤ አንተ የፈጠርኻት ድንግል ማርያም እጅግ ተደንቃለች።

💥 ወልድ ሆይ በአንተም አማካይነት የእናትኽ አእምሮ በአንክሮ በአርምሞ ይኹን፤ የእናቱ አስተማሪ፣ የእናቱ አምላክ፣ የእናቱ ጌታ፣ ከእናቱ ብላቴናም አረጋዊም የኾነ፣ እስከአኹንም ድረስ በአድናቆት የመላኸኝ አንተ ነኽ (ሉቃ ፪፥፲፱)፤ የአንተ ጥበብ ያስጨንቀኛል፤ በአንተ ላይ ዐይኑን ሊያሳርፍና በአንተ መዐዛ ሊተነፍስ የማይችል ማን አለ? በሕፃንነትኽ ድክ ድክ ስትል ተመልካቾች ኹሉ ይደነቃሉ (ሉቃ ፪፥፵፮-፶፩)።

💥 የአንተ መገለጽ ኹናቴ ዐዋቂዎችን ፍጥረታትን ያስገርማል፤ ታስደንቃለኽም፣ በሕፃንነትኽ ታናናሾች እጆችኽ ያጨበጭባሉ፣ እግሮችም ይመታሉ፤ በማንኛውም መንገድ እንዴት ተፈቃሪ ነኽ፤ የአንደበትኽ ጒርምርምታ እንኳን ስለአባትኽ ይናገራል (ሉቃ ፪፥፵፱)፡፡

💥 ውበትኽ ምን ያኽል ታላቅ ነው (መዝ ፵፬፥፪)፤ ብላቴና የኾንኸው እግዚአብሔር ሆይ፣ አፍኽ እንደ ማር ወለላ በጣም ጣፋጭ ነው! ከአፍኽ የሚወጣው ኀይል የሰማያት አካላት እንዲርዱ ያደርጋል፤ በአንተ አንድ ድምፅ ይኽ ኹሉ ፍጥረት እንዴት ይሸበራልን? ብላ ድንግል ማርያም ተደንቃ ትቆማለች (ሉቃ ፪፥፲፲፱)፤ አንተ ጸጋኽን ለኹለቱም ዓለማት የምትሰጥ ስትኾን ከፈጠርካት እናትኽ ግን ወተቷን ትጠባለኽ፡፡

💥 ያንተን ልደት በመዝሙር እንድናገር ላበቃኸኝ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ ምስጋና ይግባኽ፤ ለእኔ ጒድለት ራራ ይቅር በል፤ ለአንተ ለጌታዬ ምስጋና ላቀርብና ላመስግንኽ። በአንተ ስጦታ የተነሣ ምስጋናኽን እዘምራለኊ፤ በተወለድኽበት ቀን ኀጢአታችንን ይቅር በል፣ እናም በቸርነትኽ ለተበላሸው ሕይወታችን ፈውስን አምጣልን፤ ሰላም ይኹን ጌታዬ፤ በሕዝብኽና በቤተ ክርስቲያንኽ ላይ ግዛ፤ በጣም ክቡር የባሕርይ አምላክ ለኾንኸው አምላክ በአንተ የበዓል ቀን ጌታ ምስጋና ይግባኽ!)”

[ሙሉውን ከነገረ ማርያም በሊቃውንት መጽሐፌ አንብቡ]
✍ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
(የእመቤታችን በረከቷ ረድኤቷ ፍቅሯ ጣዕመ ፍቅሯ ይደርብን)

ሊኒክስ ኮማንድ የመጀመሪያ ከልፍ -cli CLI commands Introductory - Linux Part 3 06/12/2022

https://youtu.be/JAb4BGDailo

ሊኒክስ ኮማንድ የመጀመሪያ ከልፍ -cli CLI commands Introductory - Linux Part 3 ይሄ ከአለፈው ለሊኒክስ ኮማንድ ኢንተርፌስ ቪድዮ የቀጠለ ነው (Continuation of the previous CLI commands Introductory video) በሊኒክስ ላይ ግን ሶስተኛ ቪድዮ ሲሆን ፡ ትምህርቱን በደንብ ለመከታተል እና ተጠቃ.....

የኮምፒዩተር ኔትወርኪንግ ፕሮቶኮልስ DNS, DHCP, SMTP, FTP እና ሌላም - Computer Networking Part 6 05/22/2022

https://youtu.be/19-jWNjnEa4

የኮምፒዩተር ኔትወርኪንግ ፕሮቶኮልስ DNS, DHCP, SMTP, FTP እና ሌላም - Computer Networking Part 6 ይሄ ቪድዮ ከአለፈው ሳምንት ቪድዮ የቀጠለ፡ እና የኮምፒዩተር ፕሮቶኮልስን ለምሳሌ DNS, DHCP, SMTP, FTP ... በዝርዝር እናያለን፡ for Student's in Ethiopia የአንድ ሺህ ብር የሚያሸልም ጥያቄም አል።

ኮምፒዩተር ኔትወርኪንግ ክፍል 5 - Computer Networking Part 5 - Protocols - Traceroute - ከአለፈው የቀጠለ ... 05/15/2022

https://youtu.be/QsjrL8ut1Jo

ኮምፒዩተር ኔትወርኪንግ ክፍል 5 - Computer Networking Part 5 - Protocols - Traceroute - ከአለፈው የቀጠለ ... በዚህ ቪድዮ፡ ከአለፈው የቀጠለ routing table እና route tracing, እንዲሁምፕሮቶኮልስን እናያለን - What are protocols in Computer Networking የሚለውን በዝርዝር እናያለንStudent's in Ethiopia የ 1...

ኮምፒዩተር Networking ክፍል 4 - Routing table, LAN, VLAN, VLAN ID, ምንነት እና ግልጋሎት 05/07/2022

https://youtu.be/Jd-hiCslbuk

ኮምፒዩተር Networking ክፍል 4 - Routing table, LAN, VLAN, VLAN ID, ምንነት እና ግልጋሎት Computer Networking Part 4በዚህ ቪድዮ መልክት (packet) በኔትወርክ ውስጥ እንዴት እንደሚጉዋዝ፡ ወይም ራውተር እንዴት መልክትን በመቀባበል ለእግኛ እንደሚያደርስልን እናያለን፡ እንዲሁም VLAN and VLAN I...

ዊንዶው ሰርቨር Active Directory አጭር ኮርስ - Window Server Active Directory Step by Step Training 04/30/2022

https://youtu.be/i4qZcAO_MYI

ዊንዶው ሰርቨር Active Directory አጭር ኮርስ - Window Server Active Directory Step by Step Training ይህ ቪድዮ ከአለፉት ሁለት የዊንዶው ሰርቨር ተከታታይ ቪድዮዎች የቀጠለ ነው። ዛሬ ለ Window Server Administrator or Window System Administrator ስራ መስክ በጣም አስፈላጊ የሆነውን የዊንዶው ሰርቨር Role AD DS...

ሊኒክስ ኦፕሬትይንግ ስይስተም አጭር ኮርስ እና Linux Lab create ማድረግ 04/22/2022

https://youtu.be/WCotomxkSK8

ሊኒክስ ኦፕሬትይንግ ስይስተም አጭር ኮርስ እና Linux Lab create ማድረግ በዚህ ቪድዮ Linux ን እንመለከታለን. የ $1000 ብር የሚያሸልም ጥያቄ for Students in Ethiopia.What is Linux? What is it used for? Step-by-step instructions to build a Linux com...

04/20/2022
ዊንዶ ሰርቨር ቨርችዋል ማሽንን ከኢንተርኔት ጋር ማገናኘት .. Window Server VM configuration - Part 2 04/15/2022

https://youtu.be/IlsmoVfqRVY

ዊንዶ ሰርቨር ቨርችዋል ማሽንን ከኢንተርኔት ጋር ማገናኘት .. Window Server VM configuration - Part 2 In this video, we go over .. configuring the Window Server Virtual Machine we start creating in the previous video...$1000 birr question for Students in Ethi...

የራስችን I.T LAB መስራት - Window Server Virtual Machine - Building our own Home I.T. Lab Virtualization 04/07/2022

https://youtu.be/BThSaRued6o

የራስችን I.T LAB መስራት - Window Server Virtual Machine - Building our own Home I.T. Lab Virtualization $1000 Ethiopian Birr Question for Students in Ethiopia.Building Our own I.T. Lab using Virtualization - step by step instruction.

ሳይበር ሰኪዩሪቲ የስራ ዘርፍ Cybersecurity Job opportunity, Salary, certifications 04/01/2022

https://youtu.be/CYuJ7dNuU6U

ሳይበር ሰኪዩሪቲ የስራ ዘርፍ Cybersecurity Job opportunity, Salary, certifications Cybersecurity Job opportunity, Salary, certifications የሳይበር ሰኪዩሪቲ የስራ ዘርፍ፡ ደሞዝ እና የትምህርት እንዲሁም ሰርተፍኬት ዝግጁነት

Want your business to be the top-listed Media Company in Richardson?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


5417 Palace Drive
Richardson, TX
75087