Merr Queen
''Itoophiyaanota jijjiramaaf onnattan''
በዚህ የመረጃና የመዝናኛ ገፅ አዲስ ?
06/03/2026
"የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የስራ ባልደረቦችን በማግኘቴ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል"
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ
የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የስራ ባልደረቦችን በማግኘቴ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል። የተከበሩ ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና 73 አባላት የያዘውን የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ፤ ለዲሞክራሲ ግንባታ ሂደታችን ላበረከቱት አገልግሎትና አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
ዲሞክራሲያዊ ሂደቶች ከአኅጉራችን ነባራዊ ሁኔታና ተሞክሮ ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ ለማድረግ አፍሪካዊ ተቋማት ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ። የምርጫ ሂደታችንን ለመደገፍ በመላው ሀገሪቱ ታዛቢዎችን በማሰማራት የምርጫ ታዛቢ ልዑኩ ላደረገው ያልተቆጠበ ጥረት እውቅና እና አድናቆት እየሰጠን፣ የምልከታውን የተሟላ ውጤት እንጠብቃለን።
#የምርጫታዛቢ
#የአፍሪካህብረት
#ዲሞክራሲበአፍሪካ
#ኢትዮጵያ
#ዐቢይአሕመድ
06/01/2026
እኔ ዛሬ የሚያሳስበኝ ከመራጩ በላይ ተመራጩ ነው
ጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
ይሄ ህዝብ በቁርጠኝነት የሚሻውን ወስኖ በደምብ ዲሞክራሲያዊ መንገድ ከመረጠ በኋላ የተመረጡ ሰዎች በዚያ ልክ ታምነው እጃቸው ልባቸው ንጹህ ሆነው ደከመን፣ ታከተን ሳይሉ ሰርተው ይሄን አገር ታሪክ ለመቀየር ዝግጁነታቸው ምን ያክል ነው? የሚለው ይበልጥ ያሳስበኛል።ያመንን የታመንን እራሱን የሰጠን ህዝብ እንዴት አገልግሎ ህይወቱን ይነካሉ፣ ይቀይራሉ የሚለው ጉዳይ ይበልጥ ያሳስበኛል።
#ምርጫ2018
#ኢትዮጵያ
#ሰላም
06/01/2026
ልጆቻችን እኛ በምንሄድበት የዳዴ መንገድ እንደማይጓዙ በርግጠኝነት መግለፅ እወዳለሁ
ጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
በኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ ሀገረ መንግስት እንገነባለን፤ ልጆቻችን እኛ በምንሄድበት የዳዴ መንገድ እንደማይጓዙ ዳግም በርግጠኝነት መግለጥ እወዳለሁ።
#ምርጫ2018
#ኢትዮጵያ
#ሰላም
06/01/2026
ኢትዮጵያውያን ከጫፍ እስከ ጫፍ ድምፃቸውን እየሰጡ ነው!
ሐመር ምርጫ ክልል፣ ቆላጃ አንጉዴ ምርጫ ጣቢያ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት በምሥል
#ምርጫ2018
#ኢትዮጵያ
#ሐመር
06/01/2026
የላቀ የዜግነት ቁርጠኝነት ተምሳሌት!
በሰሜን ሽዋ ዞን ሲያደብርና ዋዩ ወረዳ፣ አባያ ቀበሌ (ሳክላ ምርጫ ጣቢያ) እጅግ ልብ የሚነካ እና ታላቅ የዜግነት ሀላፊነት የታየበት ክስተት ተመዝግቧል።
ልጃቸው በሞት የተለየባቸው ቤተሰቦች፣ አስከሬን በቤት አስቀምጠው 7 የቤተሰቡ አባላት በማለዳ ወደ ምርጫ ጣቢያ አምርተዋል። በቦታው የነበረው ማህበረሰብም ለሀዘናቸው ጥልቅ ክብር በመስጠት፤ ሰልፍ ሳይጠብቁ ቅድሚያ ሰጥቷቸው ድምፃቸውን ከሰጡ በኋላ ወደ ለቅሷቸው ተመልሰዋል።
ይህ ተግባር ህዝባችን በምርጫው ሂደት ላይ ያለውን ጽኑ እምነት እና ለሀገሩ ያለውን የላቀ ክብር በተግባር ያረጋገጠበት ህያው ምስክር ነው።
05/31/2026
ኢትዮጵያ ትመርጣለች
05/20/2026
!
ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ የረገጠችው ምዕራፍ ተዓምራዊ በሆኑ የልማት ትሩፋቶች የታጀበ ነው።ይህ የታሪክ ጉዞ ለዘመናት የሀገሪቱን ክብር ሲፈታተን የኖረውን የተረጂነት ቀንበር በፅናት ሰብሮ፣ በራስ አቅም መቆምን የሚያረጋግጥ የሉዓላዊነትና የብልፅግና ማረጋገጫ ነው።ሀገራችን እያንዳንዱን ፈተና ወደ ስኬት መሰላል በመቀየር እና ነገዋን ዛሬ ላይ በመገንባት ሁለንተናዊ ከፍታዋን ማሳለጧ የማይቀሬ እውነት ነው።
05/20/2026
ብልፅግናን በመምረጥ ኢትዮጵያን ከተስፋ ብርሃን ወደ ተጨባጭ ብርሃን እናሸጋግር።
ብልፅግና ፓርቲን ምርጫችን ያደረግነው የተጀመሩ የሀገራዊ እድገትና የብልፅግና ጉዞ እንዳይቋረጡና ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ነው። በሀገራችን የተጀመሩ ትላልቅ ሀገራዊ ሜጋ ፕሮጀክቶች ከሀሳብ ወደ ተግባር ተሻግረው ለሰፊው ህዝብ ጥቅም እንዲውሉ ነው።ብልፅግና ፓርቲን ምርጫችን ያደረግነው የተጀመሩት ሀገራዊ እድገትና ብልፅግና እንዲቀጥል ነው።የተጀመረው የሀገረ መንግስት ግንባታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ነው የተጀመረው ኢትዮጵያዊ አንድነት በፅኑ መሰረት ላይ እንዲቆም ነው።የተጀመሩት የከተሞች ልማትና የመሰረተ ልማት ዘርጋታዎች ተስፋፍተው እንዲቀጥሉ ነው።
05/20/2026
!
ኢትዮጵያ እየተገበረችዉ ያለችዉ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ጉዞ አቅጣጫ የሚቀይሩ ታሪካዊ እርምጃዎች ናቸው።ኢንቨስትመንትን በማበረታታት ለዜጎች የስራ ዕድል ከመፍጠራቸው ባለፈ የኤክስፖርት ዘርፉን በማዘመን የውጭ ምንዛሬ እጥረትን የሚቀርፉና የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት በተግባር የሚያረጋግጡ ጠንካራ ምሶሶዎች ናቸው።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Zambia
Miami, FL