EthioTube

EthioTube

Share

Current events, breaking news, entertainment, exclusive interviews, variety shows & much more on Ethiopia. Watch All Things Ethiopia.

06/03/2026

"በምዕመናን ላይ የሚደርሰው ግድያ እያበቃ ሳይሆን እየሰፋ መጥቷል" ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲዎስ

በኦሮሚያ ክልል አርሲ በተለያዩ ወረዳዎች ባለፈው እሁድ ግንቦት 23/2018 ዓ.ም 9 የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መገደላቸውን ተከትሎብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ መግለጫ ሰጥተዋል።

ቅዱስነታቸው ዛሬ ግንቦት 26/ 2018 ዓ.ም. ባስተላለፉት መልዕክት፤ "በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሽርካ፣ በሆንቆሎ፣ በዋቤ እና በሙኔሳ ወረዳዎች በመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ስለደረሰው አሰቃቂ ጥቃት የሰማነው በተሰበረ ልብ ነው" ብለዋል።

በዚህ ጥቃት 280 ምዕመን የተፈናቀለ ሲሆን አብያተ ተቃጥለዋል ሲል የቤተክርስቲያኗ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።

መቶ ዓመታት ያስቆጠረው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉን፣ የካራ ኩፍቴና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን መዘረፋቸውንም ተናግረዋል።

በዚህ ክፉ ቀን፤ በርካታ ምእመናን በግፍ መሰዋታቸውና በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ከቀዬአቸው መፈናቀላቸው ቤተ ክርስቲያናችንን በእጅጉ ያሳዘነ ክስተት መሆኑንም አቡነ ማቲያስ ገልፀዋል።

"በአርሲ ምድር በተደጋጋሚ የሚስተዋለው በደልና ግፍ በሁላችንም ልቡና ውስጥ "እስከ መቼ?" የሚል የቁጭት እና የኀዘን ጥያቄን ፈጥሯል" ብለዋል።

"የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅና ሰላምን የማስፈን አደራ የተጣለባችሁ የጸጥታ አካላትና በየመዋቅሩ ያላችሁ ኃላፊዎች ከምንም በላይ ታሪክ የሚጠይቃችሁ በሥልጣን ዘመናችሁ ለዜጎች ደኅንነት በምትከፍሉት ዋጋ ነውና ይህንን የጥቃት ሰንሰለት በማስቆምና ወንጀለኞችን ለሕግ እንዲቀርቡ" አሳስበዋል ።

Photos from EthioTube's post 06/01/2026

የመንግስት የሚዲያ ተቋማት ምርጫውን አስመልክተው ያሰራጯቸው አነጋጋሪ ምስሎች

- "ከለቅሶ ወደ ምርጫ"
- "ልጅ በወለዱ 2 ሰአት ውስጥ ወደ ምርጫ"
- "በህመም ላይ ሆነው ወደ ምርጫ"

እናንተስ መረጣችሁ?

Photos from EthioTube's post 05/31/2026

ነገ ስለሚካሔደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ በምርጫ ቦርድ የተገለጹ መረጃዎች

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነገ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም. በመላ የሀገሪቱ ክፍሎች ይካሔዳል። ምርጫው በትግራይ ክልል ሙሉ በሙሉ እና በአማራ ክልል በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ እንደማይካሔድ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። በአማራ ክልል ደቡብ እና ምዕራብ ጎንደር፣ ደጋ ዳሞት እና አምባሰል ምርጫ አይደረግባቸውም ተብሏል።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ 54 ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን ቦርዱ መግለጹ አይዘነጋም። በምርጫው የሚሳተፉ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች ተመዝገባዋል። ፓርቲዎቹ ከ 10,000 በላይ እጩዎች ለማስመረጥ አስመዝግበዋል። ከነዚህ ውስጥ 2,080 ለፓርላማ የሚወዳደሩ ይሆናል። 80 እጩዎች በግላቸው የሚወዳደሩ ናቸው።

55 የሀገር ውስጥ ሲቪክ ማኅበራት ምርጫውን የሚታዘቡ ሲሆን እንደ ኢጋድ እና አፍሪካ ኀብረት ያሉ አህጉር አቀፍ ተቋማትም የትዝብት ሥራቸውን ለማከናወን ተወካዮቻቸውን ወደ ኢትዮጵያ ልከዋል።

Photos from EthioTube's post 05/31/2026

ለንደን በመድፈኞቹ እና በደጋፊዎቹ ደመቀች

የ25/26 የፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን የአርሰናል የድል ጉዞ

05/30/2026

ከ20 አመታት በኋላ ዳግም ሽንፈት ለመድፈኞቹ በቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ

ፒኤስጂ 2ኛቸውን የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ በተከታታይ አሸነፈ

05/30/2026

ጨዋታው እንዴት ነው? 🤔

05/30/2026

በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ኃላፊው በታጣቂዎች ተገደሉ

በሰሜን ወሎ ዞን የአንጎት ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ተመስገን ያረጋል በታጣቂዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ።

ወረዳው ባወጣው አጭር መግለጫ አቶ ተመስገን "የተሰጣቸውን የህዝብ አደራ ለመወጣት በስራ ተጠምደው ለእረፍት ትናንት ማታ ወደ ቤታቸው ሊገቡ ሲሉ በሰርጎ ገብ ታጣቂዎች ጥይት ተመተው ገና በ40 ዓመታቸው ህይወታቸው ማለፉን" አሳውቋል።

"አቶ ተመስገን እንደ አንድ የህዝብ አደራ እንደተቀበለ አመራር ወረዳውን በልማት መስክ ለማሰጠቀም፣ የወረዳው ማህበረሰብ ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነቱ እንዲረጋገጥ በከፍተኛ ቁጭት እየሰሩ የሚገኙ አመራር" እንደነበሩ በመግለጫው ላይ ሰፍሯል።

መግለጫው የገዳዮቹን ማንነት "ሰርጎገብ" ከማለት ውጭ በግልፅ አልጠቀሰም።

የአመራሩ ስርዓተ ቀብር በአንጎት ወረዳ አሁን ተገኝ ከተማ በሚገኘው ተከስቴ ቅድስት ስላሴ ቤተ-ክርስቲያን በዛሬው ዕለት ከቀኑ 6 ስዓት ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት መፈፀሙ ተሰምቷል።

05/30/2026

ሰበር:

ሊቨርፑል አሰልጣኙን አርነ ስሎት አሰናበተ

የሊቨርፑል ደጋፊዎች ውሳኔው ተገቢ ነው?

05/30/2026

ቻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ - ዛሬ ማን ያሸንፋል?

አርሰናል ወይስ ፒኤስጂ?

05/29/2026

መንጃ ፈቃድ ያላቸው አሽከርካሪዎች በሙሉ በድጋሚ ሰልጥነው ሊፈተኑ ነው

በሥራ ላይ ያሉ አሽከርካሪዎች በሙሉ በድጋሚ እንዲሰለጥኑና ፈተና ተፈትነው የማሽከርከር ብቃታቸው እንደሚረጋገጥ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ይህን ውሳኔ ያሳወቀው በብቃት ማነስ ምክንያት የሚከሰቱ የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ ሲባል ነው። ለዚህም ይረዳ ዘንድ አጠቃላይ የሰነድ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ተግባር መገባቱን አመልክቷል።

በ15 ቀናት ውስጥ እንደሚጀምር የተዘገበው አዲሱን አሰራር በማይከተል ወይም ሥልጠናውን አጠናቆ ሰርተፍኬት ባልወሰደ አሽከርካሪ ላይ ጥብቅ የቁጥጥር ሥርዓት ይዘረጋል ተብሏል።

Want your business to be the top-listed Media Company in Alexandria?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


4900 Leesburg Pike, Ste 414
Alexandria, VA
22302