SCS - Soddo Catholic Secretariat
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from SCS - Soddo Catholic Secretariat, Catholic Church, Ethiopia, Wolaita Soddo, Sodo.
26/09/2026
#የመስቀል በዓልን አስመልክቶ ከብጹዕ አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ የሶዶ ሀገረስብከት ጳጳስ የተላከ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት:-
✝️ በስመ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ። አሜን።✝️
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
“የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ነው፤ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው”
(1ኛ ቆሮ 1፥18)
የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰብ፤
እግዚአብሔር በቸርነቱና በምሕረቱ ዘመናትን አሻግሮ፣ ለብርሃነ መስቀሉ በዓል በሰላም፣ በጤናና በበረከት እንኳን ለከበረውና ለተቀደሰው የመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን።
መስቀል ለእኛ የእንጨት ምልክት ብቻ አይደለም፤ የመዳናችን ምሥጢር፣ የእግዚአብሔር ፍቅር የተገለጠበት፣ የሞት ኃይል የተሰበረበት፣ የሰው ልጅም ከጨለማ ወደ ብርሃን የተመለሰበት የመድኃኒታችን የድኅነት ምልክት ነው።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች በጻፈው መልእክት ስለ መስቀል ትርጉም ጥልቀት ሲናገር “ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር የምመካበት ምንም ነገር የለኝም” በማለት ይመሰክራል። ገላ 6፡14። ስለዚህ እኛም በመስቀሉ እንመካለን፤ በመስቀሉ እንታመናለን፤ በመስቀሉም የተገለጠውን የክርስቶስን ፍቅር እናከብራለን።
ጌታችንም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሙሴ በምድረ በዳ እባቡን እንደሰቀለው፣ እንዲሁ የሰው ልጅ ሊሰቀል ይገባል” ብሎ ተናግሯል። እንደዚሁም የመስቀሉን ምሥጢር እግዚአብሔር ለዓለም ካለው ፍቅር ጋር አያይዞ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ እንዳይጠፋ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው” እንደሆነ ገልጦልናል። (ዮሐንስ 3፥14–16)። ስለዚህ የመስቀል በዓል ስናከብር፣ በመስቀል ላይ የተሰቀለውን ጌታችንን እናስታውስ። እኛን ለማዳን ራሱን የሰጠውን፣ በደሙ ያነጻንን፣ በፍቅሩ ያቀረበንን፣ በሞቱም ሞታችንን ድል ያደረገውን መድኃኒታችንን በመስቀሉ እናስባለን።
የመስቀል በዓል የሚያስታውሰን የታሪክ ክስተትም አለው። ንግሥት እሌኒ እውነተኛውን የጌታችንን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ለመፈለግ በጸሎት ከፍተኛ ጥረት እንዳደረገችና በመጨረሻም ደመራ አስደምራ እንዲቃጠል በማድረግ ጌታችን የተሰቀለበት ሳይቃጠል መትረፍ ብቻ ሳይሆን ተአምራቶችም እንደተፈጸሙበት በታሪክ ይገለጻል። ስለሆነም እኛም ደመራ በማቀጣጠል ደስታችንን በዝማሬ እና በተለያዩ ዝግጅቶች በየዓመቱ የምናስታውስበት ነው።
ዛሬም ደመራ ስናቀጣጥል የእሳቱን ብርሃን ብቻ አንመልከት፤ በልባችን የክርስቶስ ብርሃን ይብራ። የመስቀሉ ምልክት በግንባራችን ብቻ ሳይሆን በሕይወታችን ይጻፍ። የመስቀሉን ፍቅር ተቀብለን ይቅር እንባባል፤ በሰላም እንኑር፤ የተቸገረውን እንርዳ፤ የወደቀውን እናንሳ፤ እርስ በርሳችንም በፍቅር እንተሳሰብ።
ክቡራን ምዕመናን፣ በውጪም በሀገር ውስጥ ያላችሁ፡ የመስቀል በዓል ለእያንዳንዳችን የእምነት መታደስ፣ የንስሐ መንፈስ፣ የፍቅር መብዛትና የተስፋ መጽናት ይሁን። በመስቀሉ የተገለጠው የክርስቶስ ፍቅር በቤተሰቦቻችን እና በሕይወታችን ይብዛ። የመስቀሉ ብርሃን ጨለማችንን ያርቅ፤ የመስቀሉ ኃይል ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን፤ የመስቀሉ ጸጋ ለመንግሥተ ሰማያት ያብቃን። በመስቀሉ ኃይል ሰላሙን ለምንወዳት ሀገራችን እንዲሁም ለዓለማችን ያውርድልን።መስቀሉ ኃይላችን፣ ተስፋችንና መድኃኒታችን ይሁንልን። አሜን
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በዓል አደረሳችሁ!
✝️ አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ
(የሶዶ ሀገረ ስብከት ጳጳስ )
23/09/2026
የጨረታ ማስታወቂያ
21/09/2026
🕊️ “There is no true peace without fairness, truth, justice and solidarity.”
Pope St. John Paul II
His words remind us that peace is not simply the absence of conflict it is built through justice, truth, fairness and solidarity. As we celebrate the International Day of Peace, let us continue to invest in peace for everyone, everywhere, every day.
Happy International Day of Peace! 🕊️
10/09/2026
የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት 2🌼19
ከ ብጹዕ አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ በኢትዮጲያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የሶዶ ሀገረስብከት ጳጳስ 🌼🙏🏽
06/09/2026
🙏🏽
✝️ «ብርሃናችሁ ይብራ!» (ማቴ 5:16)
በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በሶዶ ሀገረስብከት ለተከታታይ ሶስት ቀናት (ከነሐሴ 21 - 23)
ሲካሄድ የቆየው የወጣቶች ፌስቲቫል በታላቅ ድምቀት ተጠናቀቀ !!!
**oDiocese
30/08/2026
✝️ «ብርሃናችሁ ይብራ!» (ማቴ 5:16)
በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በሶዶ ሀገረስብከት ለተከታታይ ሶስት ቀናት (ከነሐሴ 21 - 23)
ሲካሄድ የቆየው የወጣቶች ፌስቲቫል በታላቅ የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎትና በረከት ተጠናቀቀ።
ከ1,200 በላይ ወጣቶች በተሳተፉበት በዚህ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ 📖 ቃለ-እግዚአብሄርን ክቡር አባ አለማየሁ ፎላ ያካፈሉ ሲሆን «ካቶሊካዊነታችንን እንመስክር» በማለት ጥልቅ መልዕክትን አስተላልፈዋል።
መስዋዕተ ቅዳሴውን የመሩት ብፁዕ አቡነ ደጀኔ ሂዶቶ የሶዶ ሀገረ ስብከት ጳጳስ በመዝጊያው ላይ የሚከተለውን አባታዊ መልዕክት ለወጣቶች አስተላልፈዋል፦
ወጣቶች ሆይ ከፌስቲቫሉ ያገኛችሁትን ትምህርት በፎቶና ቪዲዮ ከማስቀረት ባለፈ በልባችሁና በሕይወታችሁ እንዲቀር ጣሩ፤ ሕይወታችሁ ምስክር ይሁን። የወንበር ወጣቶች ባለመሆን ፤ የመፍትሄና የአገልግሎት ሰው ሁኑ ፣ ቤተክርስቲያን የናንተን ፈጠራ፣ ድፍረትና ተስፋ ትፈልጋለች ስለዚህ ወደ ቁምስናችሁ ስትመለሱ እምነታችሁን አትደብቁ፤መስክሩ እራሳችሁንም ሁኑ።
ይህን እንድታደርጉ ሀይል የሚሰጣችሁን የእግዚአብሔርን ቃል አንብቡ፤ በቅዱስ ቁርባን ስግደት ተጠናከሩ፤ ንስሀንም አትዘንጉ።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ያስተላለፉትን መልዕክት በማስታወስ እኔም እንዲህ እላችኃለሁ ቴክኖሎጂንና ሰው-ሠራሽ አስተውሎትን (AI) ለበጎ ነገር ተጠቀሙበት፤ በዲጂታሉ ዓለም የክርስቶስ ምስክሮች ሁኑ።
በመጨረሻም እንደ ቅዱስ ፍራንቺስኮስ “ጌታ ሆይ ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” በማለት ራሳችሁን ጠይቁ፤ ጌታ የሚመልስላችሁንም መልስ የሕይወት ጥሪ አድርጋችሁ ያዙ። በማለት ጥልቅ መልዕክትን አስተላልፈዋል።
#በስተመጨረሻም ፌስቲቫሉ በላቀ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላደረጉት ለሀገረ ስብከቱ የወጣቶች አስተባባሪ ለክቡር አባ አበበ ሜጋ፣ ለሐዋርያዊ አስተባባሪ ለክቡር አባ ማቴዎስ ተገኝ፣ ወጣቶችን በእግዚአብሔር ቃል ሲያንጹ ለቆዩት ለክቡር አባ አለማየሁ ፎላ እና አባ ታዴዎስ አያኖ ፣ በመስዋዕተ ቅዳሴ ላገለገሉ ክቡራን አባቶች፣ ለሲስተሮችና ደናግላን ፣በዝማሬ ላገለገሉት ዘማሪ ቢንያም አፈወርቅና ለፊሶን አባላት፣ ኢያሱ ኮላሶ፣ አማኑኤል አርጃ፣ ለአስተባባሪዎችና ንቁ ተሳትፎ ላደረጉት ወጣቶች በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋና አቅርበዋል።
**oDiocese
⛪️ታላቅ የወጣቶች ፌስቲቫል!!
በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በሶዶ ሀገረስብከት በርካታ የሀገረስብከቱ ወጣቶች የተሳተፉበት ታላቅ የወጣቶች ፌስቲቫል "ብርሃናችሁ ይብራ" በሚል መሪ ቃል በዑደት ፣መቁጠሪያ ፀሎት እና በቅዱስ ቁርባን ስግደት ዛሬ ተጀመረ።
ፌስቲቫሉ እስከ ነሐሴ 24/2018 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ መንፈሳዊ መርሀግብሮች ይቀጥላል።
ይህ የወጣቶች ፌሲቲቫል በሀገረስብከት ደረጃ በየአመቱ የሚዘጋጅ ሲሆን በመርሀግብሩ
🙏🏽 መንፈሳዊ ትምህርት በተጋባዥ ካህናት
🙏🏽 መዝሙር በተጋባዥ ዘማሪያን
🙏🏽 ጸሎት እና ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ዝግጅቶች ያካትታል።
ታላቅ የወጣቶች ፌስቲቫል!!
በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በሶዶ ሀገረስብከት በርካታ የሀገረስብከቱ ወጣቶች የተሳተፉበት ታላቅ የወጣቶች ፌስቲቫል "ብርሃናችሁ ይብራ" በሚል መሪ ቃል በዑደት ፣መቁጠሪያ ፀሎት እና በቅዱስ ቁርባን ስግደት ዛሬ ተጀመረ።
ፌስቲቫሉ እስከ ነሐሴ 24/2018 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ መንፈሳዊ መርሀግብሮች ይቀጥላል።
ይህ የወጣቶች ፌሲቲቫል በሀገረስብከት ደረጃ በየአመቱ የሚዘጋጅ ሲሆን በመርሀግብሩ
🙏🏽 መንፈሳዊ ትምህርት በተጋባዥ ካህናት
🙏🏽 መዝሙር በተጋባዥ ዘማሪያን
🙏🏽 ጸሎት እና ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ዝግጅቶች ያካትታል።
Category
Contact the place of worship
Website
Address
Ethiopia, Wolaita Soddo
S**o
Opening Hours
| Monday | 08:00 - 18:00 |
| Tuesday | 08:00 - 18:00 |
| Wednesday | 08:00 - 18:00 |
| Thursday | 08:00 - 18:00 |
| Friday | 08:00 - 18:00 |
Alerts
Be the first to know and let us send you an email when SCS - Soddo Catholic Secretariat posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.