Wolaita Post
we are in community visit our page
22/01/2026
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የ2018 የውድድር ዘመን ምድቦች
Ethiopian Football Federation
20/01/2026
የካዎ ጦና መታሰቢያ ሐውልት ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በይፋ ይመረቃል።
18/01/2026
ሴኔጋል የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ሆነች
ጥር 10 2018 በ35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አስተናጋጇን ሞሮኮ በማሸነፍ ሴኔጋል ዋንጫውን አንስታለች።
ምሽት 4 ሰዓት ላይ በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ሴኔጋል በተጨማሪ ሰዓት ባስቆጠረችው ብቸኛ ግብ የዋንጫ ባለቤት ሆናለች።
የሴኔጋልን የድል ግብ ፓፔ ጉዬ ከመረብ አሳርፏል።
18/01/2026
🚨 𝗕𝗥𝗘𝗔𝗞𝗜𝗡𝗚: በአፍሪካ ዋንጫ ታምር ተከስቷል!
👉በአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ጫወታ ሴኔጋል ጎል አስቆጥራ ዳኛው ፋውል ነው ብሎ ሽሮ በ98ኛው ደቂቃ ዳኛው ለሞሮኮ የፍጹም ቅጣት ምት በመስጠቱ የሴኔጋል ተጫዋቾች የዳኛውን ውሳኔ ተቃውመው ሜዳውን ለቀው የወጡ ቢሆንም #በማኔ ጉትጎታ ተመልሶ ወደሜዳ በመግባት የሴኔጋል በረኛ የፍጹም ቅጣት ምት መልሷል። በዚህ ሰዓት ሴኔጋል ሞሮኮን 1 ለ 0 እየመራች ነው።
18/01/2026
#የወላይታ ንጉሥ የነበሩ የካዎ ጦና ሐውልት መጪው ማክሰኞ ዕለት ጥር 12/2018 ዓ.ም ይመረቃል።
18/01/2026
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገበታ ለትውልድ የመጀመሪያውን መዳረሻ ደንቢ ኢኮ ሎጅን በይፋ መረቁ
📍በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የተገነባው ይህ ሎጅ በ36.7 ሄክታር ጥብቅ ደን ላይ ያረፈ ነው፡፡
🔊 የደንቢ ኢኮ ሎጅ የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት፤ ከገበታ ለሸገር እና ገበታ ለሀገር መርኃ-ግብሮች የቀጠለ እና ሥራዎቹን ወደ አዳዲስ አካባቢዎች የወሰደ ነው ተብሏል፡፡
💬 “ሥራው ከአካባቢው በተገኙ የግንባታ ቁሳቁሶች እና በአካባቢ አቅም የተገነባ በመሆኑ ዘላቂነትን እና ባለቤትነትን ያንፀባርቃል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናግረዋል።
18/01/2026
የተወዳጁ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ የአስከሬን ሽኝት ሥነ-ሥርዓት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተካሄደ ነው
***************
ከትናንት በስቲያ ድንገተኛ ኅልፈቱ የተሰማው ተወዳጁ የኪነ-ጥበብ ባለሙያ ነጻነት ወርቅነህ የአስከሬን ሽኝት ሥነ-ሥርዓት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተካሄደ ይገኛል።
በፊልም እና ቴአትር ተዋናይነት፣ በቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢነት እና በሌሎች የጥበብ ሥራዎቹ ስመጥር የሆነው ነጻነት ወርቅነህ ባደረበት ሕመም ጥር 8 ቀን 2018 ዓ.ም በድንገት ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል።
የተወዳጁ አርቲስት የአስከሬን ሽኝት ሥነ-ሥርዓት ቤተሰቦቹ፣ ወዳጆቹ፣ የሙያ ባልደረቦቹ፣ አድናቂዎቹ፣ የሃይማኖት አባቶች እና ካህናት፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እየተካሄደ ይገኛል።
16/01/2026
ዜና ዕረፍት
ተወዳጁ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
ተወዳጁ የኪነ-ጥበብ ባለሙያ ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
በፊልም እና ቲያትር ተዋናይነት፣ በቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢነት እና በሌሎች የጥበብ ስራዎች ውስጥ ስመጥር እና ተወዳጅ ከሆኑ የጥበብ ሰዎች አንዱ የሆነው ነጻነት ወርቅነህ ባደረበት ህመም በድንገት ህይወቱ ማለፉ ነው የተገለፀው።
ለበርካታ ዓመታት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን የሚተላለፈው የቤተሰብ ጨዋታ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ የሆነው ነጻነት ወርቅነህ ባለትዳርና የ3 ልጆች አባት እንደነበር ከኢቢስ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
15/01/2026
ቦዲቲ ካምፓስ!!
በወላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ አስተዳደር ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ቦዲቲ ካምፓስ አዲስ ለተመደቡ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች ደማቅ አቀባበል እየተደረገ ነው።
ውድ ተማሪዎቻችን እንኳን የሰላም እና የአብሮነት ተምሳሌት ወደሆነው ቦዲቲ ከተማ አስተዳደር እና ቦዲቲ ካምፓስ እንኳን በሰላም መጣችሁ!!
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
«እውቀትን በተግባር!!»
08/01/2026
ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2018 18ኛ እና 19ኛ ሳምንት የውድድር ቦታ ማሻሻያ!
የ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ10ኛ እስከ 19ኛ ሳምንት ውድድር በአዲስ አበባ፣ አዳማ እና ሀዋሳ ከተማ እንሚካሄድ መገለፁ ይታወቃል። 18ኛ እና 19ኛ ሳምንት በሃዋሳ ከተማ የታሰበው ውድድር በአዳማ ከተማ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም እንደሚካሄድ እያሳወቅን የውድድር ቦታ እና የሰዓት ማሻሻያ የተደረገበትን መርሐግብር አያይዘናል ።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር
05/01/2026
ማንቼስተር ዩናይትድ ሩበን አሞሪምን አሰናበተ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪምን አሰናብቷል፡፡
ዩናይትድ ለ14 ወራት ክለቡን የመሩትን ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ማሰናበቱን አስታውቋል፡፡
05/01/2026
ከወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ የአድራሻ ለውጥ ማሳሰቢያ!!
የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት፣የወላይታ ሶዶ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት እና በከተማ አስተዳደር ግቢ የሚገኙ መምሪያዎች በሙሉ በአዲሱ የከተማ አስተዳደር ህንጻ ግንባታ ምክንያት ከዚህ በፊት ለክቡራን ተገልጋዮች አገልግሎት ሲሰጥ የቆየበትን የአድራሻ ከታህሳስ 27/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዋዱ ተብሎ በሚታወቀው ሠፈር ከእንያት ሆስፒታል ወረድ ብሎ ታፍ የነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት በሚገኘው ህንፃ አገልግሎት እንደሚሰጥ አሳውቋል ።
በመሆኑም አገልግሎት ፈላጊዎች በሙሉ በተጠቀሰው ቦታ ተገኝተው መስተናገድ የሚችሉ መሆኑን ገልጿል ።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Gununo
S**o