Biruk Design
Director cinematographer & Design with Art directing
14/06/2026
"ዛሬ 4 ዓመት ሆነው እንደ ቀልድ..." — ተወዳጁ ድምፃዊ ዳዊት ነጋ በታላቅ ክብር ተዘከረ
ታዋቂው እና በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈው የትግርኛ ሙዚቃ ፈርጥ ድምፃዊ ዳዊት ነጋ (ዴቭ) ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ ሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. ልክ 4 ዓመታት ተቆጥረዋል።
ይህንኑ አራተኛ ዓመት የሙት ዓመት ዕለት በማስመልከት፣ የቅርብ ወዳጆቹ፣ ቤተሰቦቹ እና አድናቂዎቹ ድምፃዊው በሚገኝበት የቀብር ስፍራ በመገኘት የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ በክብር እና ናፍቆት አስበውታል።
በ1980 ዓ.ም. የተወለደውና ባለትዳር እንዲሁም የአንድ ልጅ አባት የነበረው ድምፃዊ ዳዊት ነጋ፣ ባሳለፈው አጭር የሕይወት ዘመኑ ለትግርኛ ኪነ-ጥበብ ዕድገት፣ ዘመናዊነት እና ስርጭት የማይረሳ፣ አሻራው የማይጠፋ ከፍ ያለ አስተዋፅኦ ማበርከቱ ይታወሳል።
ድምፃዊው ባህላዊ የትግርኛ ዜማዎችን ከዘመናዊ የሙዚቃ ስልቶች ጋር በማዋሃድ ለአድማጮች በማቅረብ ረገድ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ድንቅ የጥበብ ሰው ነበር።
ያለ ዕድሜው የተቀጠፈው የፈገግተኛው እና ተሰጥኦው የዴቭ ሕልፈት ዛሬም እንደ ቀልድ 4 ዓመታት ቢሞላውም፣ ባበረከታቸው ድንቅ የሙዚቃ ሥራዎቹ፣ በፈገግታው እና በሕዝብ ልብ ውስጥ ባለው መልካም ስሙ ሁሌም ሲታወስ ይኖራል።
ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለአድናቂዎቹ በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን። ነፍስህ በሰላም ትረፍ ዴቭ!
📷 Frewoini / ጉርሻ Page
ለከርስ ተብሎ የአናት ቅቤ አይበላም።
ሰዉ ሲሞት ለማዘን ከየትኛዉም ብሔር
ከየትኛዉ ሐይማኖት መፈጠር አይጠበቅብህም
ሰዉ መሆን ብቻ በቂ ነዉ።
28/05/2026
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Sodo
SODO