Kemal indiris
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kemal indiris, College & University, Metu.
12/11/2025
21/10/2025
ከቆምን 15 ቀናችን
የተበላሸ ማዳበሪያ ነው
ከጂቡቲ ለደብረ ብርሀን ማዳበሪያ ጭነን ብንደርስም ዩሪያ ማዳበሪያ የተበላሸ ነው አናራግፍም በማለት መፍትሄ የሚሰጠን አካል በማጣት ከቆምን 15ኛ ቀናናችን ሆኗል በማለት መልዕክት አድርሰውናል።
እኛ ከወደብ የጫንነውን ጭነት በሀላፊነት ተረክበን ይዘን ብንደርስም እኛን የማይመለከት ችግር በማንሳት ማዳበሪያ የተበላሸ ስለሆነ አናራግፍም በማለት የባንክ ዕዳ የእቁብ ክፍያ ቤተሰብ የማስተዳደር ሀላፊነት የተጫነበትን መኪና ለ15 ቀን ማቆም የሚያሳዝን ተግባር ነው ብለዋል።
ደብረ ብርሀን ስምሪት ተሰጦን ከጅቡቲ የመጣን 35 መኪኖች ስንሆን እስካሁን መፍትሄ የሚሰጥ ባለመኖሩ ለከፋ ጉዳት ተዳርገናል ብለዋል።
ይህ ማዳበሪያ እየተጫነ ባለበት ወደብ ላይ የጥራት ችግር አለበት ብለን መረጃ ስናጋራ ኬሚስት ነን ምናምን የሚሉ ጭፍኖች መገገሩ ችግር የለውም በማለት ሊዘልፉን የሞከሩ አካላት ነበሩ ጭፍኖች ዛሬስ የት ናችሁ ??
የደብረ ብርሀን ግብርና ቢሮ ማዳበሪያውን አስጭኖ ከላከ አካል ጋር በመነጋገር ችግሩን ሊፈታ ይገባል መኪኖችን በዚህ መልኩ ለ 15 ቀን ማቆም በግለሰብም በሀገርም ላይ ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ማምጣት መሆኑን ልታውቁ ይገባል።
የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ይህንን ልክ ያልሆነ ድርጊት በመመልከት ለ15 ቀናት የቆሙ መኪኖችን መፍትሄ የሚያገኙበት ሁኔታን ሊያመቻች ይገባል።
ብልፅግና "በመስከረም ወር የመንግስት ሰራተኞችን ደሞዝ እንደሚጨምር" ለምን አሳወቀ? ምክንያቱም እየመጣ ያለውን የለውጥ ደመና ስለተገነዘበ ነው።
በመስከረም፦
- የህክምና ባለሙያዎች ለሁለተኛ ዙር ተቃውሞ እየተዘጋጁ ነው፣
- መምህራን ክረምቱን ሲደራጁ ቆይተው ለተቃውሞ ትምህርት ቤት እስኪከፈት እየተጠባበቁ ናቸው፣
- ገበሬው በማዳበሪያ ዋጋ ንረት ሳቢያ እርሻውን ማረስ ስላልቻለ፣ በቁጭት ሞፈሩ ላይ ተደግፎ መልካም አጋጣሚ እየጠበቀ ነው፣
- ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተመረቁ ተማሪዎች ልብሳቸው እላያቸው ላይ እየነተበ፣ በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ፣ በየበረንዳው እያፋሸኩ ይገኛሉ፣
- በየተራራውና ቆላው የሚቃጠለው ወታደር፣ የደሞዝ ማነስ ሳያንሰው ስንቅ በማጣቱ በሽምቅ ታጣቂዎች በየቦታው እየተበተነ ነው።
በአጠቃላይ፣ እያዝገመገመ ያለውን ደመና ዘግይተው ሲረዱ "የደመወዝ ጭማሪ መቼም አይደረግም" የሚለውን አቋማቸውን ለመቀየር ተገደዋል። የደሞዝ ጭማሪው እየመጣ ያለውን ዶፍ ያስቆም ይሆን? አይመስልም። ጠዋት የጠፋውን አህያ ማታ ላይ ጥሪ አይመልሰውም። በጣም እሚንት፣ የዘገየ እርምጃ! (Too little too late!)
ለማስታወስ ያህል:- 50% ፣ 30% ፣ 20%
ለጊዜ መግዣም ቢሆን የደሞዝ ጭማሪው የሚሰነብት መሆን አለበት!
የደሞዝ ማስተካከያ (ጭማሪ አይደለም) በጣም የዘገየ ነው። የመንግስት ሰራተኛ ወደ ህጋዊ ለማኝነት ከተቀየረ ሰነባብቷል። የነበረው ደሞዝ ከወርሃዊ ወጪ 50% እንኳን የማይሸፍን ነው። የPHD ደሞዝ ለደህና የቤት ኪራይ አይበቃም፣ ከወርሃዊ የኮንዶ ኪራይ ዋጋ በታች ነው። አሁንም የተደረገው ማሻሻያ ወርሃዊ ወጪን ሙሉ በሙሉ አይሸፍንም። ቢሆንም የወር ወጪን 80% ቢሸፍን አንድ እርምጃ ነው። ያው 20%ን ምሳ ወይም ቁርስ እየዘለሉ (ሳይፈልጉ መፆም)፣ በእግር እየኳተኑ፣ ሻይ ቡና በመተው፣ አበዳሪ ከተገኘ እየበደሩ፣ ወዘተ. መሞከር ነው።
ደሞዝ ለማስተካከል መሞከሩ ብቻውን ምንም ፋይዳ የለውም። ከዚህ በፊትም ተደጋጋሚ ሙከራ ተደርጎ ከሸፏል። የደሞዝ ማስተካከያ ወሬ ሰሰማ በማግስቱ አከራይ የቤት ኪራይ ይጨምራል፣ ነጋዴው የምግብ ፍጆታን ጣራ ያስገባል ወይም አቅርቦትን ያዛባል፣ ግብር ከፊሉን ይዞት ይሄዳል፣ ግዠበት (inflation) ያብዳል፣ የጥቁር ገበያ የብር የመግዛት አቅምን በሳምንቱ ያዳክማል፣ ሰራተኛው ከወራት በኋላ መልሶ ይቆዛማል።
አሁን የተወሰደው እርምጃ ለሰራተኛው ቅፅበታዊ ጠሩ ስሜት (false pride) ሲሰጣቸው፣ መንግሥት ደግሞ የተቃውሞ ጎራ አጀንዳን ለጊዜው ይቀማበታል፣ ለመጪው ቅርጫ የቀረችውን ፐርሰንታይል ጨምሮ 99% ለመድፈን ይጠቀምበታል። አጀንዳ ለመቀማትም ቢሆን ማሻሻያው ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ይኖርበታል። በደሞዝ ማስተካከያ የመጣው ጊዜያዊ ስሜት ቶሎ ይሟሽሻል። ያ ከሆነ ደግሞ የተበዳይነት ስሜት ዳግም ያገረሻል።
ጊዜያዊ ማስተካከያ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ መዋቅራዊ ለውጥ ካልተደረገ እና በሌሎች ተዛማጅ መፍትሄዎች ካልተደገፈ፣ አለባብሰው ቢሄዱ በአረም ይመለሱ ነው ነገሩ።
Do not celebrate too early; buckle up!
ከመስከረም 2018 ጀምሮ የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ ጭማሪ እንደሚደረግ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ።
ይህ የደመወዝ ማሻሻያ በዜጎች የኑሮ ሁኔታ ላይ መሻሻል ለማምጣት ያለመ ሲሆን፣ በሁሉም የመንግስት የስራ ዘርፎች ላይ እንደሚተገበር ተገልጿል።
በተደረገው ማሻሻያ መሰረት፡-
* ዝቅተኛው ደመወዝ ከ4,760 ብር ወደ 6,000 ብር ከፍ ይላል።
* ከፍተኛው ደመወዝ ከ21,492 ብር ወደ 39,000 ብር ያድጋል።
* የዲግሪ ተመራቂዎች መነሻ ደመወዝ ከ6,940 ብር ወደ 11,500 ብር ከፍ ብሏል።
ይህ የደመወዝ ማስተካከያ ከ160 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት የሚጠይቅ ሲሆን፣ ለመንግስት ሰራተኞች የሚወጣው ዓመታዊ የደመወዝ ወጪ 560 ቢሊዮን ብር እንደሚደርስ ኮሚሽኑ አስታውቋል።
ዘገባዋ የፋና ነው::
🙏🙏🙏
🌴🌴🌴
ህልሜ ጠፋ ተስፋዬም ጨለመ ወይስ እኔ ብቻ ሁለችንም ነን 2011ወደ 2017
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Metu