Raya Vision

Raya Vision

Share

ራያነት ማለት እኮ የፍቅርና የሰላም ተምሳሌት ነው።

Photos from Raya Vision's post 07/06/2026

በቲቤት ሰማይ ላይ የታየው አስደናቂውና አስፈሪው የደመቀ ቀይ ብርሃን

ከሰማይ ወደ መሬት ሳይሆን ከመሬት ወደ ጠፈር የሚተኮሰው ያልተለመደው መብረቅ

ቲቤት በደቡብ ምዕራብ ቻይና የምትገኝ፣ ከኔፓል፣ ህንድ እና ቡታን ጋር የምትካለልና እጅግ ሰፊ በሆነው የኪንግሃይ-ቲቤት እምብርት ላይ ያለች ከፍተኛ ተራራማ ቀጠና ናት። በአማካይ ከባህር ጠለል በላይ ከ4,000 እስከ 5,000 ሜትር ከፍታ ላይ በመገኘቷ "የዓለም ጣሪያ" (Roof of the World) በሚል ስያሜ ትታወቃለች።

ይህ ልዩና እጅግ ከፍተኛ መልክዓ-ምድር አየሩ ቀጭን፣ ሰማዩ ደግሞ እጅግ ንጹህ እንዲሆን ስለሚያደርገው ከምድር በላይ የሚከሰቱ ብርቅዬ የጠፈርና የከባቢ አየር ክስተቶችን ለመመልከት በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ ስፍራዎች አንዷ ያደርጋታል::

በዚሁ ልዩ ስፍራ በቅርቡ በቲቤት ሻናን ክልል በሚገኘውና ከባህር ጠለል በላይ ከ5,000 ሜትር በላይ ከፍታ ባለው ፑማ ዩምኮ ሐይቅ (Lake Puma Yumco) አቅራቢያ በተከሰተ ኃይለኛ የነጎድጓድ ማዕበል ላይ እጅግ አስደናቂ እና አስፈሪ የሆነ የበራ ቀይ የብርሃን ምሰሶ ብልጭታ በቪዲዮ ተቀርጾ ወጥቷል።

የሳይንስ ልብ-ወለድ ፊልም የሚመስለውና "ሬድ ስፕራይትስ" (Red Sprites) በመባል የሚታወቀው ይህ ክስተት፣ ልክ እንደ ግዙፍ የባህር እንስሳ ቅርፅ ያላቸው የብርሃን ዘንጎች ታይተዋል።

07/06/2026

ትግሬ ነህ አማራ የምትሉኝ እኔ ትግሬም አማራም ነኝ
ምክንያቱም የራያ ልጅ ነኝ

06/06/2026

#ሰበር #ዜና
በኮረም ከተማ አሁን ከምሽቱ 2:05 የህወሓት ታጣቂዎች (TDF) ባለው ወቅታዊ ሁኔታዎች እርስ በእርሳቸው የሀሳብ ልዩነት በመፍጠሩ ወደ ግጭት ገብቶዋል ።
በግጭቱ ከ5 በላይ ታጣቂዎች ተጎድቶ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል እስከአሁን ሰዓት ድረስ ቶክስ አልቆመም !!

Photos from Raya Vision's post 06/06/2026

#በትግራይ

በትግራዩ የድሮን ጥቃት ከ30 በላይ የህውሃት ታጣቂዎች መጎዳታቸው ተሰምቷል።

ጠዋት ላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ጥቃቱ ትናንት ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ሌሊት መፈፀሙ የተጠቆመ ሲሆን በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ገምሃሎ አካባቢ፣ መሣሪያና ሎጂስቲክስ ጭኖ ወደ ባደመ ይጓዝ በነበረ የህወሓት ወታደራዊ ኮንቮይ ላይ ያነጣጠረ እንደነበር ተነግሯል።

በጥቃቱ 9 ወታደራዊና የጭነት ተሽከርካሪዎች እና 3 ቀላል (ፒካፕ) መኪኖች ላይ ከፍተኛ ውድመት የደረሰ ሲሆን፣ ከ30 በላይ ታጣቂዎች ህይወታቸው ሳያልፍ እንዳልቀረ ተጠቁሟል።መረጃውን ለዋሱ መሐመድ ያቀበሉት ምንጮች በጥቃቱ ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው እስከ መቀሌ ድረስ ለህክምና መወሰዳቸውን ገልፀዋል። እስካሁን ከፌደራል መንግሥትም ሆነ ከህውሃት የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም።
ህውሃት ከኤርትራ መንግስት ጋር ፅምዶ ብሎ በመሰረተው ጥምረት የፌደራል መንግስቱን ለመውጋት በተደጋጋሚ ሲዝትና ሲዘጋጅ እንደነበር ይታወሳል።

04/06/2026

የንፁሀን እልቂት በቃ ሊባል ይገባል!!

በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በአሰኮ ወረዳ፣ በሺርካ ወረዳ እና ሆንቆሎ ዋቤ ወረዳ ታጣቂዎች ንፁሀን የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮችን በመግደል በርካቶችን ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ይህን ሰይጣናዊ የጥፋት ተግባርም በፅኑ መወገዝ አለበት

በአርሲ በተደጋጋሚ ንፁሀኖችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት እየተበራከተ በየጊዜው ለቅሶ እና ዋይታ ብቻ እየተሰማ ያለ መፍትሄ መቀጠሉ እጅግ ያሳምማል::

ንፁሃን ዜጎች እያለቁ ያለው ከውጪ በመጣ ወራሪ ጠላት ሳይሆን ወንድም ወንድሙ ላይ እየሰነዘረው ባለው አሳዛኝ ከጭካኔ ጥቃት ነው::

በሀገሩ ምድር በድህነት ህይወቱን እየመራ ለሚገኝ ንፁህ ህዝብ ከግራ እና በቀኝ ጠብመንጃ በታጠቁ ሃይሎች በማያውቁት አጀንዳ ለሞት፣ ለእልቂት፣ ለስደት መዳረጉ ልብ ሰባሪ ነው::

ይህ የንፁሀን እልቂት በቃ ሊባል ይገባል!!

ሁሉም ኢትዮጵያዊ የዚህ መሰሉን እልቂት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቆም እጅ ለእጅ ተያይዞ ሊቆም ይገባል::

በአርሲ በተደጋጋሚ እየተፈፀመ በሚገኘው ጥቃት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን ።

ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችንም ቶሎ ያገግሙ ዘንድ እንዲሁም የተፈናቀሉትም ወደቄያቸው ደህንነታቸው ተጠብቆ ባስቸኳይ ይመለሱ ዘንድ ፌደራል መንግስት ቅድሚያ መሰጠት አለበት

Photos from Raya Vision's post 02/06/2026

#አላማጣ አዝናለች
በአባታችን በበርሄ ትኩየ ህልፈት የተሰማኝ ሃዘን ጥልቅ ነው። የታጣቂዎች እጅ ንጹሃን ዜጎችን መቅጠፉን ቀጥሏል፤ ይህ ድርጊት በእጅጉ ያሳዝናል። ለአባታችን ነፍስ እረፍትን፣ ለቤተሰብም ጥንካሬን እመኛለሁ!!

ኣላማጣ💔

01/06/2026

#ራያ የቆንጆዎቹ ማፍለቂያ

Photos from Raya Vision's post 01/06/2026

#ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው።

31/05/2026

🚨በአንድ ጥሪ የጋራ ሰላማችንን እናስከብር!🚨

​የአደጋ ጊዜ ጥሪ 620 መስመራችን 24 ሰዓት ሙሉ ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ነው!

​የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የህዝብን ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የቴክኖሎጂ አቅሙን በማጠናከር ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል።

​ማንኛውንም የወንጀል ድርጊት፣ አጠራጣሪ ሁኔታዎች ወይም አስቸኳይ የጸጥታ እገዛ በሚያስፈልግበት ጊዜ በነጻ የጥሪ መስመራችን 620 ላይ በመደወል ፈጣን ምላሽ ማግኘት ይችላሉ። በተጨማሪም በምስሉ ላይ እና ከታች በተቀመጡት ቀጥታ የስልክ ቁጥሮች ማግኘት እንደሚችሉ እንገልጻለን።

​📞 የድሬደዋ ፖሊስ የድንገተኛ እና የመረጃ ስልክ ቁጥሮች ⬇️
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
​🚨 የዋና መምሪያ እና የድንገተኛ አደጋ ጥሪዎች
• ​📞 አጭር የነፃ ስልክ መስመር ➡️ 620
• ​☎️ ድ/ዳ ፖሊስ ጠ/መምሪያ ➡️ 0251111600 / 0251115211
• ​🚒 ድንገተኛ እሳትና አደጋ ቁጥጥር ➡️ 0251121371

​📍 የከተማው ፖሊስ ጣቢያዎች
• ​🏢 አዲስ ከተማ ➡️ 0251111620
• ​🏢 መጋላ ➡️ 0251110597
• ​🏢 አፈተ-ኢሳ ➡️ 0251111796
• ​🏢 ለገሀሬ ➡️ 0251126110
• ​🏢 ፖሊስ መሬት ➡️ 0251126035
• ​🏢 መልካ ጀብዱ ➡️ 0251160176
• ​🏢 ሳቢያን ➡️ 0251113957
• ​🏢 ጎሮ ➡️ 0251117015
• ​🏢 ሀሎሌ (ጀርባ) ➡️ 0252112324
• ​🏢 ከዚራ ➡️ 0251111713
• ​🏢 ገንደ ቆሬ ➡️ 0251111536

​🌾 የገጠር ፖሊስ ጣቢያዎች
• ​🏡 ቢያዋሌ ➡️ 0258905089
• ​🏡 ዋሂል ➡️ 0258905068
• ​🏡 ቃልቻ ➡️ 0258905054
• ​🏡 ጀልዴሣ ➡️ 0258905083

​🤝 "ለሀገርና ለአካባቢዎ ሰላም መረጋገጥ ለሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ምስጋናችን ከሁሉ የላቀ ነው!"
— የድሬደዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ

Dire Dawa Police
ከትንሿ ድሬ አላማጣ ሁኜ

Want your business to be the top-listed Media Company in Mekelle?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Mekelle