Dani Computer Solution Center
Am working for ur interest
23/04/2022
✴️ ኮምፒውተራችን እንዴት በቀላሉ ከፕሪንተር ጋር ማስተዋወቅ እንችላለን
🔆 ኮምፒውተራችንን ከፕሪንተር ጋር ለማስተዋወቅ የሚጠቅሙ ብዙ ሶፍትዌሮች እንዳሉ ይታወቃል እንዲሁም ተመሳሳይ wifi በመጠቀምም በዋየርለስ ወይም ያለ ኬብል ፕሪንተራችንን ከኮምፒውተራችን ጋርም ማስተዋወቅ እንችላለን።
🔆 እኔ ግን ዛሬ ይዤላችሁ የቀረብኩት ያለምንም wifi እና software ኮምፒውተራችንን ከፕሪንተር ጋር እንዴት ማስተዋወቅ እንደምንችል ነው።
🔆 ኮምፒውተራችንን እንዴት ከፕሪንተራችን ጋር ማስተዋወቅ እንችላለን።
1⃣ control panel ውስጥ በመግባት device printer እንመርጣለን ወይም start ን በመንካት search box ላይ device and printer ብለን እንፅፋለን።
ኮምፒውተራችንን ከፕሪንተር ጋር ማያያዙን እንዳንረሳ።
2⃣ በመቀጠል add printerን እንመርጣለን ።search እስኪጨርስ እንጠብቃለን።
3⃣ add alocal printer የሚለውን መርጠን next እንለዋለን።
4⃣ በመቀጠል ፕሪንተራችንን ያያዝነው በኬብ ስለሆነ ከሚመጣልን ምርጫ የመጀመሪያውን USB portን እንመርጣለን።next እንለዋለን
5⃣ አሁን ከሚመጡልን ዝርዝሮች ውስጥ የፕሪንተራችንን ስም በመፈለግ መርጠን next ቀጥሎም next እንለዋለን።
6⃣ በመጨረሻም print a test page የሚል ይመጣልናል click አርገን test እናደርግና finish ብለን እንጨርሳለን።
ለወዳጆ ያጋሩ
እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።
✅✅✅ #ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!✅✅✅
የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
ቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology
02/09/2021
29/08/2021
ስለጉግል 10 ሊያስገርምዎ የሚችሉ መረጃዎች እነሆ ። 👇👇👇👇
✅ ስያሜው
ግን ጉግል ምን ማለት ነው? ጉግል ስያሜውን ያገኘው በስህተት ነው።
በእንግሊዝኛው 'googol' ማለት በሂሳብ ቀመር 1 እና መቶ ዜሮዎች ማለት ነው።
እና ተሜው ተሳስቶ ስያሜውን ጉጎል ወደ ጉግል አመጣው፤ የጉግል ፈጣሪዎችም ይህንን ቃል ለመጠቀም መረጡ።
✅ የጀርባ ማሻ
የጉግል ፈጣሪዎች ላሪ ፔጅ እና ሰርጌይ ብሪን ለጉግል የሰጡት የቀድሞ ስም በእንግሊዝኛው 'Backrub' ወይም የጀርባ ማሻ የሚል ትርጓሜ ሊሰጠው የሚችል ቃል ነበር።
ምክንያቱም ሰዎች ፈልገው የሚያገኙት መረጃ ጉግል ላይ ከሰፈሩ ሌሎች ድረ ገፆች ስለሆነ። ኋላ ላይ ስሙን ሊቀይሩት ተገደዱ እንጂ።
✅ የተንጋደደ
ጉግል ንግድ እና ጠንከር ያሉ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆኑ ጨዋታዎችም ይገኛሉ።
እንደማሳያ እስቲ ወደ ጉግል ይሂዱና ይህችን "askew" የእንግሊዝኛ ቃል መፈለጊያው ላይ ይፃፉት።
✅ ፍየሎች
ጉግል አረጓንዴ ምድርን እደግፋለሁ ይላል፤ ለዚህም ነው የመሥሪያ ቤቱን ሳር ማጨጃ ማሽኖች በፍየሎች የተካው። አሜሪካ ካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት የሚገኘው የጉግል ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ 200 ያህል ፍየሎች ወዲያ ወዲህ ሲሉ ተመልክተው የየትኛው አርብቶ አደር ዘመናይ ግቢ ነው ብለው እንዳይደናገሩ። ፍየሎቹ የጉግል ናቸውና።
✅ እየተመነደገ የሚገኝ 'ቢዝነስ'
ጂሜይል፣ ጉግል ማፕ፣ ጉግል ድራይቭ፣ ጉግል ክሮም ከተሰኙት በተጨማሪ ከፈረንጆቹ 2010 ጀምሮ ጉግል በየጊዜው የተለያዩ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን የግሉ ሲያደርግ ቆይቷል።
ሊያውቁትም ላያውቁትም ይችላሉ ግን እኛ እንንገርዎ፤ አንድሮይድ፣ ዩትዩብ፣ እንዲሁም አድሲን የተሰኙት ቴክኖሎጂዎች የጉግል ንበረቶች ናቸው።
ከሌሎች 70 ያክል ኩባንያዎች በተጨማሪ ማለት ነው።
✅ ዱድል
ዱድል የተሰኘው የጉግል ውድድር መድረክ አሜሪካ የሚገኙ ተማሪዎች የድርጅቱን ምልክት ፈጠራቸውን ተጠቅመው እንደአዲስ እንዲቀርፁት የሚያበረታታ ነው።
ይህ ውድድር ከተጀመረ ወዲህ የጉግል አርማ በየቀኑ ሲቀያየር ይስተዋላል።
አንዳንዴም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበሩ ቀናት በማስመልከት የጉግል መለያ ይለዋወጣል።
✅ ለሌሎች ያመለጠ ዕድል
በፈረንጆቹ 1999 ላሪ እና ሰርጌይ «ኧረ ጉግልን በአንድ ሚሊዮን ዶላር የሚገዛን» እያሉ ቢወትወቱ የሚሰሙ ጠፋ።
ዋጋው ላይ መደራደር ይቻላል ቢሉም ምንም ምላሽ አልተገኘም።
አሁን የጉግል ዋጋ ከ300 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሆኗል፤ ሚሊዮን አላልንም፤ ልብ ያርጉ ቢሊዮን ነው።
✅ መሪ ቃላት
'ከይሲ አይሁኑ' ከድርጅቱ ቀደምት መሪ ቃላት አንዱ ነበር።
'ምን አገባው' የሚሉ ብዙዎች ቢኖሩም ድርጅቱ ይህን መሪ ቃል አልተውም ብሎ ሙጥኝ ብሏል።
✅ ምግብማ ግድ ነው
ከጉግል ባለቤቶች አንዱ የሆነው ሰርጌይ ብሪን ነው አሉ ማንኛውም የጉግል ቢሮ አካባቢ ምግብ የሚገኝበት አማራጭ መኖር አለበት ብሎ ያዘዘው፤ በቢዛ 60 ሜትር ርቀት ላይ።
የጉግል ኩባንያ ሠራተኞች ቢሯቸው እጅግ ያሸበረቀና ምግብ ባሰኛቸው ጊዜ ወጣ ብለው ሊመገቡበት የሚችሉበት እንደሆነም ይነገራል።
✅ የጉግል ባልንጀራ
የጉግል ኩባንያ ሠራተኞች ውሾቻቸውን ወደ ሥራ ቦታቸው ይዘው መምጣት ይፈቅዳለቸዋል።
ውሾቹም ከቢሮው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ራሳቸውን እንዲያመቻቹ ሥልጠና ይሰጣቸዋል።
ምንጭ፦BBC AMAHARIC
29/08/2021
ኮምፒዉተር የሚዘጋበት ወይም ክራሽ የሚያደርግበት 5 ምክንያቶች
1. የሀርድዌር መቃረን
ለ Windows ክራሽ የማድረግ ዋነኛው ምክንያት Hardware መቃረን ነው፡፡እያንዳንዱ Hardware ክፍሎች ለመግባባት IRQ(interrupt request channel) ያስፈልጋቸዋል፡፡
እነዚህ IRQ ለየሀርድዌሩ የተለዩ ወይም የተነጠሉ መሆን
አለባቸው፡፡ ለምሳሌ አንድ ፕሪንተር IRQ 7 ሲኖረው ኪቦርድ ደግሞ IRQ 1፡፡እያንዳንዱ ሀርድዌር የራሱ የሆን IRQ ለመያዝ ጥረት ያደርጋል፡፡ ግን ብዙ የሀርድዌር እቃዎች ስንጠቀም ወይም የሀርድዌሩ ሶፍትዌር በስርዓት ካልተጫነ ሁለት ሀርድዌሮች ተመሳሳይ IRQ ሊጋሩ ይችላሉ፡፡
በዚህም ሰዓት ሁለት የሀርድዌር ዕቃዎች በተመሳሳይ ሰዓት ለመጠቀም ስንሞክር ክራሽ ሊያደርግ ይችላል፡፡
🈴 2. የተበላሸ ራም
ራም Ram (random-access memory) ችግሮች ዋናው የብሉ እስክሪን ኦፍ ዴዝ (blue screen of death) ዋና መንስኤ ሲሆን የሚያሳየው መልእክት ፋታል ኤክሰብሽን ኢረር ( Fatal Exception Error) የሚል ነው፡፡ ፋታል ኢረር
የሚነግረን አሳሳቢ የሀርድዌር ችግር አለ ማለት ነው፡፡ አንዳንዴ የሀርድዌር ክፍል ስለተጎዳ መቀየር እንዳለበት ይናገራል፡፡ በራም የሚመጡ ችግሮች ብዙ ግዜ የራሙ ከኮምፒዉተሩ ጋር ሳይጣጣም ሲቀር ነው፡፡ ይህም ማለት
ለኮምፒዉተር የራም ስሎት ጋር ሳይመጣጠን ሲቀር ፤ የራሱ ያልሆነ ሞዴል ስንጠቀም እና የተለያየ አይነት ራም በአንድ Computer ውስጥ ስንጠቀም ነው፡፡ለምሳሌ 70ns ለይ 60ns ራም ስንጠቀም ኮምፒተሩን ፍጥነት ይቀንሳል፡፡ይሄ ደግሞ ራሙን ከአቅሙ በላይ ይጫነዋል።
በዚህ ግዜ window ክራሽ ያደርጋል፡፡
🈴3.ባዮስ ሴቲንግ( BIOS settings)
እያንዳንዱ ማዘር ቦርድ ሲመረት የራሱ የሆነ የተለያዩ ቺፕሴት ሴቲንግ አብሮት ይጫናል፡፡
እነዚህን ሴቲንግ ለመጠቀም በኮምፒውተራችን ኪቦርድ ላይ F2 ወይም F10 (እንደ ኮምፒዉተሩ ይለያያል) ኮምፒዉተሩ ስንከፍት ከጥቂት ሰከንድ በኻላ በመንካት ሴቲንጉን አክሰስ
ማድረግ ይቻላል፡፡ ነገር ግን አንዴ ባዮስ ዉስጥ ከገባን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡
ማንኛውንም ሴቲንግ ከመቀየራችን በፊት ፎቶ ወይም ወረቀት ለይ ሴቲንጎቹን ማኖር አንድ ያበላሸነው ነገር ካለ በቀላሉ መቀየር ያስችለናል፡፡ብዙን ግዜ የባዮስ ችግር የራም ላተንሲ ችግር ነው፡፡ የድሮ ኮምፒዉተር ራም ላተንሲ 3 ሲሆን የቅርብ ግዜ ራሞች ደግሞ ላተንሲ 2 ናቸው፡፡
ይሄንን ሴቲንግ በምንቀይርበት ጊዜ ኮምፒዉተሩ ክራሽ ያደርጋል ወይም ፍሪዝ ይሆናል፡፡
🈴 4.ቫይረስ
ቫይረሶች የኮምፒዉተር ፕሮግራም ሲሆኑ እራሳችውን በማብዝት ወይም ኮምፒዉተር ፋይሎች
ላይ በማጣበቅ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ ቫይረሶች
የትእዛዞች ስብስብ ሆኖ እራሱን በሌላ የኮምፒዉተር ፕሮግራም ያጣብቃሉ(ብዙ ግዜ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን)፡፡ ኮምፒዉተራችን ውስጥ ቫይረስ ሲያጠቃ የኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ፋይል የመቀየር ሀይል ስላለው ኮምፒዉተሩን
ክራሽ ወይም ፍሪዚ ሊያረግ ይችላል፡፡
🈴5.መጋል
በኮምፒዉተራችን ዉስጥ ካሉ ሀርድዌሮች በጣም አስፈላጊው እና ዋናው ሲፒዩ ነው፡፡ ሲፒዩ በኤሌትሪክ ሃይል የሚሰራ ሲሆን ካለው ውስብስብ የትራዚስተር ብዛት አማካኝነት የሚፈጥረው ከፍተኛ ሙቀት ሲፒዩን ሊያበላሸው ወይም ከጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ሲፒዩ ብዙ
ጊዜ ከማቀዝቀዣ ቬንትሌተር ከኮምፒዉተራችን አንድ ላይ
ይመጣል፡፡ እነዚህ ቬንትሌተሮች ከተበላሹ ወይም ሲፒዩ ካረጀ የኮምፒዉተራችን ሲፒዩ መጋል ይጀምራል፡፡ ይህ ደግሞ በኮምፒዉተራችን ላይ የከርንል ኢረር ያ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Jimma Ethiopia (around JU " Kolober")
Jimma