Awi Zone Environmental Protection
Creating awareness around environmental protection and its benefits over community
21/08/2026
ቃልን በተግባር! በርቱልን የተፈለገውም የአካባቢ ጽዳት ሥርዓት ሆኖ እንዲቀጥል ነው፡፡
20/08/2026
የኮሪደር ልማት ስራን አስመልክቶ የሚጋሩ ማራኪ መልዕክቶች፡
የከተማችን አዲስ ገጽታና የዕድገት ማሳያ፦ በኃላፊነትና በትጋት በተከናወነ የተቀናጀ ስራ የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር የኮሪደር ልማት 96% መድረሱ፣ ከተማችን ወደ ላቀ የውበትና የዘመናዊነት ደረጃ እየተሸጋገረች መሆኗን በተግባር ያረጋገጠ ኩሩ ስኬት ነው!
የህብረተሰብ ትብብርና የጽናት ውጤት፦ ይህ የውበትና የልማት ምዕራፍ የነዋሪዎች፣ የአመራሩና የባለሙያው የጋራ ጥረት ውጤት በመሆኑ፣ የቀረውን ጥቂት ስራ በተመሳሳይ የውድድርና የትጋት መንፈስ በማጠናቀቅ እንጅባራን ለሁሉም ምቹና ጽዱ ከተማ እናደርጋታለን!
በኃላፊነትና በትጋት በተከናወነ የተቀናጀ ስራ የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር የኮሪደር ልማት 96% መድረሱ፣ ከተማችን ወደ ላቀ የውበትና የዘመናዊነት ደረጃ እየተሸጋገረች መሆኗን በተግባር ያረጋገጠ ስኬት ነው!
19/08/2026
ሁላችንም የበኩላችንን በመወጣት ጽዱና ዉብ አካባቢን እንፍጠር!
19/08/2026
ነሀሴ 13/2018 ዓ.ም
ንጹህ ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ !
የ3ኛው ዙር "ጽዱ ኢትዮጵያ" ንቅናቄ በደማቅ ሁኔታ ከተካሄደ በኋላ፣ በርካታ ተቋማት የተጣለባቸውን አደራ በመወጣት የራሳቸውንና የአካባቢያቸውን ግቢ የማጽዳት ስራ በከፍተኛ ተነሳሽነት መጀመራቸው አበረታች ውጤት እያሳየ ይገኛል!
ይህ አበረታች ጅምር የንቅናቄ መድረኩ ወደ ተግባር መተርጎሙንና ለውጥ ማምጣቱን በግልጽ የሚያሳይ ነው።
📢 ጥሪና ማሳሰቢያ ለሁሉም ተቋማት፡
• ጽዳት የጀመራችሁ ተቋማትን በሙሉ እያመሰገንን፣ ይህንን በጎ ተግባር አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ እናሳስባለን።
• እስካሁን ግቢያችሁን ማጽዳት ያልጀመራችሁ ሌሎች ተቋማትም ይህንን መልካም አርአያነት በመከተል ግቢያችሁንና አካባቢያችሁን የማጽዳት ስራ እንድታከናውኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!
• ከማስጀመሪያ የጽዳት ዘመቻ እና ከንቅናቄ መድረክ በኃላ በጽዳት ዘመቻ የተሳተፉ ለአብነት፡-
- እንጅባራ ከተማ የሴቶች፣የጤናና የግብርና ተቋማት፤
- እንጅባራ ከተማ 01 እና 03 ቀበሌዎች፣
- ዳንግላ ከተማ ግብርናና ስቪል ሰርቪስ ፑል፣
- በባንጃ ወረዳ በዲካራ ከተማ
- ቻግኒ ከተማን መጥቀስ ይቻላል፡፡
ጽዳት ከራሳችንና ከተቋማችን ይጀምራል! ሁላችንም የበኩላችንን በመወጣት ለጽዱና ለዉብ ኢትዮጵያ እንትጋ!
#ጽዱኢትዮጵያ #የጽዳትዘመቻ #ጽዱ ተቋም
18/08/2026
ነሀሴ 12/2018 ዓ.ም
ደረቅ ቆሻሻ(Solid Wsate)
የደረቅ ቆሻሻ ባልተገባ መንገድ መወገድ የሚያስከትለው ጉዳት:-
• የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን በመድፈን ለጎርፍ መጋበዝ።
• የከተሞችን ውበትና ጽዳት ማበላሸት።
• የበሽታ አስተላላፊ ተባዮች (እንደ አይጥና ዝንብ) መራቢያ መሆን።
• የመሬትና የከርሰ-ምድር ውሃ መበከል።
ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ መርሆዎች (The 4 Rs)
1. Reduce (መቀነስ): የሚመረተውን ቆሻሻ መጠን ከምንጩ መቀነስ።
2. Reuse (ደግም መጠቀም): ቁሳቁሶችን ሳይለወጡ ደጋግሞ መጠቀም።
3. Recycle (ለውጦ መጠቀም): ቆሻሻን ወደ አዲስ ምርት መቀየር።
4. Recovery (ማበስበስ):-ምሳሌ የተፈጥሮ ቆሻሻዎችን ወደ ማዳበሪያነት መቀየር (Composting)
"ህግን በማከበር እና በትብብር በመስራት አካባቢያችንን እንጠብቅ!"
14/08/2026
Voluntary Community Cleaning Campaign in Chagni Town Administration
14/08/2026
"ጽዱ ኢትዮጵያ ለመጪው ትውልድ" በዘመቻ ብቻ የሚወሰን ሣይሆን ይህን ንቅናቄ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሥርዓት ልናደርገው ይገባል፡፡
11/08/2026
የፅዳትን ጉዳይ የዘወትር ተግባር ልናደርገው ይገባል!
11/08/2026
ነሃሴ 05/2018 ዓም
በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ተጠሪ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪነት «ፅዱ ኢትዮጵያን ለመጭው ትውልድ እናስተላልፍ» በሚል መሪ ቃል ዞናዊ የንቅናቄ መድረክ መካሄዱን ተከተሎ፣ በጓንጓ ወረዳ አካባቢ ጥበቃ ጽሕፈት ቤት እና በቻግኒ ከተማ አስተዳደር ቅንጅት ሰፊ የፅዳት ዘመቻ ተካሂዷል።
ይህ የፅዳት ዘመቻ ለነዋሪዎች ምቹ የመኖሪያና የስራ አካባቢን ለመፍጠር ያለመ ሲሆን፣ በከተማው ውስጥ የሚገኙ ልዩ ልዩ ቦታዎችና የተቋማት አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ከቆሻሻ እንዲያጸዱ ተደርጓል።
በዚሁ ህዝባዊ የንቅናቄ ዘመቻ ላይ የዞን አካባቢ ጥበቃ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የጓንጓ ወረዳና የቻግኒ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ የወረዳው የመንግስት ሰራተኞች እንዲሁም በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በንቃት ተሳታፊ ሆነዋል። ይህ የፅዳት ዘመቻ አካባቢን በመጠበቅና የከተማን ውበት በማሳደግ ረገድ የህብረተሰቡን ተሳትፎ የሚያጎለብት ሲሆን፣ መሰል የበጎ አድራጎትና የልማት ስራዎች በተጠናከረ መልኩ ተገቢውን ትኩረት አግኝተው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።
10/08/2026
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the organization
Website
Address
Amhara Region
Injibara