Debre Tabor Communication
this page is create to address honest information for society
04/08/2026
በክረምት የምትፈካ ታሪክ፣ተፈጥሮና ባህል የደመቁባት ባለታሪክ ከተማ፤
#ደብረታቦርን #በደብረታቦር!
(ቡሔ፣አሸንድዬ፣አድርሽኝና ደብረታቦር )
👉ደብረታቦርን በደብረታቦር በዓላት በውስጡ ደብረታቦርን፣አሸንድዬን፣ቡሔንና አድርሽኝ መንፈሳዊና ባህላዊ በዓላትን አቅፎ በታሪካዊቷ ደብረታቦር ከተማ ከነሐሴ 13 ጀምሮ የሚከበር በዓል ነው።
👉ይህ በዓል በደብረታቦር ከተማና በሌሎች አካባቢዎች በየአመቱ በድምቀት ይከበራል፡፡
👉የደብረ ታቦር መንፈሳዊ በዓል የተጀመረው የኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን በደብረ ታቦር ተራራ ከመግለጡ ጋር ተያይዞ ነው፡፡
👉የደብረ ታቦር ድምቀት የኾነው ቡሄ ማለት በራ፣ ብርሃን ኾነ፣ ደመቀ የሚል ትርጉም ያለው ነው፡፡
👉በቡሄ በዓል እናቶች ሙልሙል በመጋገር ለሕፃናት እና ለወጣቶች በማደል ያደምቁታል፡፡
👉በቡሄ በዓል በደብረ ታቦር ከተማ ከተገኙ ወጣትና ታዳጊዎች የደስታ ጅራፍ በማጮህ እና በብርሃነ መለኮቱ አምሳል ችቦ በማብራት በሚያሳዩት ትእይንት ይደሰታሉ፡፡
👉ሌላው በቡሄ በዓል በደብረ ታቦር ከሚታዩ ትእይንቶች መካከል እርስ በእርስ መጠያየቅ ሲኾን እናቶች እና አባቶች ለክርስትና ልጆቻቸው ያዘጋጁትን ሙልሙል ዳቦ በመስጠት በዓሉን ያደምቃሉ፡፡
👉ሌሎች የአሸንድዬ በዓል በልጃገረዶች ዘንድ የሚዘወተር የነጻነት በዓል።
👉አድርሽኝም በጎንደር ልዩ ቦታ የሚሰጠው ማህበራዊ ትስስርና መተሳሰብን የሚያጠናክር በዓል ነው።
በደብረ ታቦር ከተማ የቡሄ፣የአሸንድዬና የአድርሽኝ በዓላትን በጋራ እናክብር።
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ሀምሌ 28 ቀን 2018 ዓ/ም
04/08/2026
"በጎነት ለላቀ እህትማማችነት፤ ለኢትዮጵያ ከፍታ!"
በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር የአጼ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት በሚል መሪ መልዕክት በደብረታቦር አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እየታከሙ ለሚገኙ ህሙማን የዓይነት ድጋፍ አካሂዷል።
የተቸገሩትን መደገፍና ለወገን ደራሽ መሆን አያጎድልም፤ መረዳዳትና መደጋገፍ ደግሞ የሴቶች እውነተኛ መገለጫና ውብ እሴት መሆኑንና የብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር በመሆኑ አባላት ሁልጊዜም ለዜጎች ሁለንተናዊ ደህንነትና እድገት ቅድሚያ እንደሚሰጡ በድጋፉ ተገልጿል።
እርስ በእርስ በመረዳዳት፣ በፍቅርና በእህትማማችነት መንፈስ የሚከናወኑ በጎ ተግባራት የማህበራዊ ትስስርን ጥንካሬ ማሳያ በመሆናቸው በስፋት ሊጎለብቱ ይገባልም ተብሏል።
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ሃላፊ ወ/ሮ ቤተልሔም ክበቤን ጨምሮ የአጼ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ አመራሮችና በጎ ፈቃደኛ የሴት ክንፍ አደረጃጀቶች በድጋፍ መርሐ ግብሩ ተገኝተዋል።
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ሀምሌ 28 ቀን 2018 ዓ/ም
04/08/2026
04/08/2026
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዲሱን የደንብ ልብስ በየደረጃው ለሚገኙ የፖሊስ መዋቅርና አባላቶች አስተዋወቀ!
በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠላቅላይ መምሪያ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ''በጀግነት መጠበቅ በሰብአዊነት ማገልገል'' በሚል መሪ ሀሳብ አዲሱን የደንብ ልብስ አስተዋውቋል።
የኢትዮጵያን ብሄራዊ መዝሙር በመዘመርና ሰንደቅ አላማዋን በመስቀል የጀመረው ፕሮግራም የተለያዩ የጎዳና ላይ ትዕይቶችም ተከናውነዋል።
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ያለው ዘለቀ ፖሊስ ከዘመኑ ጋር አሰራሩን እያዘመነ ወቅቱ የሚጠይቀውን ስራ ለመስራት ጥረት እያደረገ እንደሆነ በመግለጽ የደንብ ልብስ አንዱ የተቋሙ የክብር መገለጫ እንደሆነም አንስተዋል።ተቋማዊ ሪፎርሞች በቀጣይ የህዝብና የሀገርን አደራ ለመወጣት አስፈላጊ መሆናቸውን ያነሱት ኮማንደር ያለው ተቋሙ የህዝብ በህዝብና ለህዝብ የሚሰራ በመሆኑ ማህበረሰቡ የተለመደ አጋርነቱን እንዲያስቀጥል አሳስበዋል።
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀይለኢየሱስ ሰለሞን የፖሊስ መዋቅር በየደረጃው ሪፎርሞችን እያከናወነ እንደሚገኝ አንስተዋል።በአለም አቀፍ ደረጃ ወንጀልን ለመከላከልና የዜጎችን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የላቀና የዘመነ የፖሊስ መዋቅርና አደረጃጀት አስፈላጊ መሆኑንም አንስተዋል።የፖሊስ መርህ ለገባው ቃልኪዳንና ለለበሰው ደንብ መሆኑን ያነሱት ምክትል ከንቲባው እንደ ከተማም ወንጀልን በመከላከልና በማክሸፍ ያሉ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል ጎደሎዎችንም ተከታትሎ ማረም እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
እስካሁን የተሻለ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የፖሊስ አባላት የማዕረግ እድገትና እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ሀምሌ 28 ቀን 2018 ዓ/ም
04/08/2026
04/08/2026
"ጽዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ" ሶስተኛ ዙር ሀገር አቀፍ የአካባቢ ብክለት መከላከል ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በጽዳት ዘመቻ በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ተካሂዷል።
ንቅናቄው ለተከታታይ ሶስት ወራት የሚቆይ ንቅናቄ መሆኑን እና ይህ ንቅናቄ ከተሞች የተሻለ ገጽታ እንዲኖራቸው ለማስቻል እንዲሁም ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር ታሳቢ ያደረገ እንደሆነ የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ጽዳትና ውበት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መልሰው ዋለ ተናግረዋል።ሶስቱን የብክለት አይነቶች የሚባሉትን ማለትም ፕላስቲኮችን ማስወገድ፣ የኬሚካል አጠቃቀም ቁጥጥር እና የድምጽ ብክለት መከላከል ሥራ እንደሚሰራ የተናገሩት ሃላፊው በቀጣይም ተከታታይነት ባላቸው የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረኮችና በጽዳት ዘመቻዎች ሞዴል ቀበሌና ክፍለ ከተሞችን ለመፍጠር ጭምር የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የሚሰራ ይሆናል ብለዋል።
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀይለኢየሱስ ሰለሞን እንዳሉት ደብረታቦር ከተማ እንደ ታሪኳ ውብና ጽዱ ለማድረግ ከዘመቻ የጽዳትና የግንዛቤ ስራዎች ባሻገር ባህል አድርጎ መውሰድ እንደሚገባ ተናግረዋል።የፕላስቲክ ምርቶች በቀላሉ የማይበሰብሱና ለትውልድም ጭምር ስጋት ስለሆኑ ማስወገድና ሌሎች ምርቶችን መጠቀም እንደሚገባም አሳስበዋል።
በጽዳት ዘመቻው የከተማ እና የክፍለ ከተማ አመራሮች፣የጽዳትና ውበት ሰራተኞች እንዲሁም የከተማ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች ተገኝተዋል።
ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን ሀምሌ 28 ቀን 2018 ዓ/ም
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Debre Tabor