ANRS Disaster Risk Management Commission

ANRS Disaster Risk Management Commission

Share

ለአደጋ የማይበገርና የምግብ ዋስትናው የተረጋገጠ ማህበረሰብ ለመፍጠር ተግተን እንሰራለን!

Photos from ANRS Disaster Risk Management Commission's post 03/06/2026

በኤፍራታ ግድም ወረዳ በ14.8 ሚሊዮን ብር የሚገነባው የመስኖ ካናል ፕሮጀክት አፈጻጸም 65 በመቶ ደረሰ

ባህር ዳር፦ ግንቦት 27/2018 ዓ.ም (አስስአኮ)

​ በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ ግድም ወረዳ ፈረዶ ቀበሌ በአብክመ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን "ያልተማከለ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ስራ አመራርን ማጠናከር ፕሮጀክት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እየተገነባ የሚገኘው የመስኖ ካናል ግንባታ አፈጻጸም 65 በመቶ መድረሱ ተገልጿል። ከክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጋር በመተባበር እየተከናወነ ለሚገኘው ለዚሁ ፕሮጀክት 14.8 ሚሊዮን ብር በጀት መመደቡ ታውቋል።

​የአካባቢውን አምራች ኃይል ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የሚጠበቀው ይህ የመስኖ ልማት ስራ በአሁኑ ወቅት በጥሩ አፈጻጸም ላይ የሚገኝ ሲሆን፥ እስካሁን ባለው ሂደት 1.5 ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ መንገድ ጠረጋ ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል። በተጨማሪም 183 ሜትር ኩብ የድንጋይ ግድብ ስራ እና 190 ሜትር ኩብ የድንጋይ ማቅረብ ተግባር በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል።

​ለግንባታው የሚያስፈልገው 250 ኩንታል ሲሚንቶ ቀድሞ በቦታው እንዲደርስ የተደረገ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅት የ100 ሜትር የካናል ቁፋሮ እና የስትራክቸር ግንባታ ስራዎች በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

​ይህ የመስኖ ካናል ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ በአካባቢው የሚገኘውን ማህበረሰብ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥና የአደጋ ስጋትን ለመቀነስ የጎላ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል።
​ #ተግባራችን #የመስኖልማት #ኤፍራታግድም #የአደጋስጋትስራአመራር
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት
Like,Shares & Comment ያድርጉ

📌 ድረ-ገጽ፦ Web:-https://anrsdpfsc.org.et
***
📌 ፌስቡክ:-www.facebook.com/profile.php?id=100067131507069
***
📌 ዩቲዩብ፦https://youtube.com/
***
📌 ቲክቶክ፦ tiktok.com/
***
📌 ቴሌግራም፦ https://t.me/ADRMC_1
***
📌 ቲዊተር /x አካውንት፦ https://x.com/disaster_food_1
***
📌 ኢንስታግራም፡- https://www.instagram.com/drmc_1
***
📌 ዋትስአፕ፦https://whatsapp.com/channel/0029VbCXynhJuyAF8GRYmW1N
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Photos from South Gondar Disaster Risk Managment's post 03/06/2026
Photos from Central Gondar Zone Disaster Risk  Management Office's post 03/06/2026
01/06/2026

እ.ኤ.አ ከጁን 1 እስከ 10/2026 (ግንቦት 24 እስከ ሰኔ 3/2018 ዓ.ም) የሚኖረው የአየር ሁኔታ በውሃ ዘርፍ ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተፅዕኖ
//////////
በሚቀትሉት የጁን የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ ተፋሰሶች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው የገጸምድር የውሃ ፍሰት እንደሚኖራቸው ይጠበቃል።

በመሆኑም ከሚጠበቀው የአየር ሁኔታ ጋር ተያይዞ የሚኖሩ መልካም አጋጣሚዎችን ለመጠቀምና የሚጠበቁ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ለመቀነስ ከታች የቀረቡትን ቦታ ተኮር የውሃ ሚቲዎሮሎጂ ምክረ ሀሳብ ከወዲሁ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

01/06/2026

እ.ኤ.አ ከጁን 1 እስከ 10/2026 (ግንቦት 24 እሰከ ሰኔ 3/2018 ዓ.ም) የሚኖረው የአየር ሁኔታ አዝማሚያ
=============

በጁን የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት ለዝናብ መፈጠር አስዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በተለይም በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘም እርጥበታማው የአየር ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየተስፋፋ ከመሄዱ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸዉ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

በሚቀጥሉት ቀናቶች ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች እና የደቡብ እና የደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ ከባድ (ከ1-30 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ በውሃ አካላትና በከባቢ አየር ውስጥ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በመካከለኛወ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በጁን የመጀመሪያው አስር ቀናት ከሚኖረው ከፍተኛ የፀሐይ ሀይል ጋር በተያያዘ በተለይም የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት በአፋር ክልል፣ በሰሜንና በደቡም ምዕራብ የሀገሪቱ ሥፍራዎች ሊይ ከ32 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ ትንበያዎች ያመላክታሉ፡፡

Photos from ANRS Disaster Risk Management Commission's post 01/06/2026

እ.ኤ.አ ከጁን 1 እስከ 10/2026 (ግንቦት 24 እስከ ሰኔ 3/2018 ዓ.ም) የሚኖረው የአየር ሁኔታ በግብርናው ሥራ እንቅስቃሴ ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተፅዕኖ
=============

በሚቀጥሉት የጁን ወር የመጀመሪያዉ አስር ቀናት ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው እርጥበት በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በመካከለኛዉ የመኸር ሰብል አብቃይና የበልግ ሰብል ተጠቃሚ በሆኑት አካባቢዎች ላይ እንደሚያገኙ ይጠበቃል።

በመሆኑም የሚኖሩ መልካም አጋጣሚዎችን ለመጠቀምና የሚጠበቁ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ለመቀነስ ከታች የቀረቡትን ቦታ ተኮር የግብርና ሚቲዎሮሎጂ ምክረ ሀሳብ ከወዲሁ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

30/05/2026
Photos from የምዕ/ጎጃም ዞን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ተ/ጽ/ቤት  West Gojjam Zone Disaster Risk Mgtoffice's post 29/05/2026
Photos from የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ ስጋት ሥራ አመራር  ጽ/ቤት's post 29/05/2026
Want your organization to be the top-listed Government Service in Bahir Dar?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Bahir Dar