EECMY Tabor Congregation
Tabor Mekaneyesus is a Lutheran church which is part of one of the biggest Lutheran churches in Ethi
10/04/2026
በሚሲዮን ጉዞ እግረ መንገድ የጅማ ከተማ ማስታዎሻ ከተማይቱ ታምራለች ለበለጠ ውቤት እኛም ጸልዬን ወጥተናል እጆለ ጅማ እወዳችኃለን !!! መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንላችሁ!
16/02/2026
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ታቦር ማህበረ ምዕመናን የካቲት 1 እና 8 2018 ዓ.ም በሁለት እሁዶች አምልኮ ላይ በቄስ አመኑ አርሴ የተሰጠ ተከታታይ ትምህርት
ርዕስ፡- ለታላቁ ተልዕኮን ለመፈጸም በመንፈስ ቅዱስ እንመራ (ዮሐ.16፡12-14)
የዮሐንስን ወንጌል ፀሐፊ ዮሐንስ፡- የስሙ ትርጉም “እግዚአብሔር ፀጋ ሰጭ ነው::” ማለት ስሆን እርሱም ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀመዝሙር(ዮሐ.13፡23፣21፡24) ነው፡፡ የተጻፈበት ጊዜ 85-95 AD እንደሆነ ይገመታል፡፡
የዮሐንስ ወንጌል ከሶስቱ ወንጌላት ለየት የሚል ስሆን በታምራት (ምልክቶች)፣ በሚሲዮን እርዝመት እና በሥነ-መለኮት የበለጸገ ነው፡፡
በዚህ ወንጌል ኢየሱስ ራሱን ስባት ጊዜ እኔ (I AM) በማለት ተጠቅሟል፡- “እኔ የህይወት እንጀራ ነኝ”(6፡35፣41፣48፣51)፣“እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” (8፡12፣9፡5)፣ “እኔ የበጐች በር ነኝ” (10፡7፣9)፣ “እኔ መልካም እረኛ ነኝ” (10:11፣14)፣ “እኔ ትንሳኤና ህይወት ነኝ” (11:25)፣ “እኔ መንገድ እውነት ህይወትም ነኝ” (14፡6)፣ “እኔ የወይን ግንድ ነኝ” (15:1፣5)፡፡
እነዚህ አገላለጾች ሁሉ እግዚአብሔር በዘፀአት (3፡14) እኔ/I AM/ በማለት ራሱን ለእስራኤል ህዝብ የገለጠበት ስሆን የኢየሱስ አምላክነት ያሳያሉ፡፡ ሌላው ዮሐንስ የኢየሱስን አምላክነት የገለጠበት መንገድ በመጀመሪያው ቃል የነበረ፣ ቃልም እግዚአብሔር ነበር(1፡1) እና ቃልም ሥጋ የሆነ/Incarenation/ (1፡14) የሚል ነው፡፡
የመንፈስ ቅዱስ ትርጉም
በእብራይስጥ ሩሃ ruach ትንፋሽ፣ ንፋስ ወይም የህይወት እስትንፋስ life-breath (Gen.6:17; Ezek.37:5) የሚል ትርጉም ሲኖረው፡፡በእብራይስጥም ሆነ በከግርኩ ተመሳሳይ ትርጉም አለው፡፡በአዲስ ክዳንም በግርኩ ኑማ/Pneuma የሚለው ቃል ንፋስ፣ ትንፋሽ የሚል ትርጉም ሲኖረው ሁለቱም ቃላት፡- ሩሃ እና ኑማ እንደ (RSV) እስትንፋሰ እግዚአብሔር ወይም የእግዚአብሔር መንፈስ ruach elohim “spirit of God.” የሚል ትርጉም አለው፡፡
ይህ የእግዚአብሔር መንፈስ ruach elohim በብሉይ ክዳን ወደ ሰዎች ለተለየ ተልዕኮ/specific task ይመጣ ነበር: በአዲስ ክዳን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ውስጥ ሊኖር እንደምመጣ በትንብተ (ኢዩኤል 2፡28) ትንብታዊ ተስፋ ተሰጥቶ በ (ሐዋ.2:1-4) ተፈጽሟል፡፡ ስለዚህ በመንፈስ ቅዱስ እንመራ ሲባል በእግዚአብሔር አብ፣በወልድ በመንፈስ ቅዱስ በአንድ አምላክ እንመራ ማለታችን ነው፡፡ በሌላ መልኩ በቃሉ እንመራ ማለት ነው (ዮሐ.1፡1፤1፡14፤6፡63)
1. እግዚአብሔር መንፈስ ነው (ዮሐ.4፡24፤6፡63)
1.1. እግዚአብሔር አብ የተልዕኮ አምላክ ነው
የመፍጠር(ዘፍ 1፡1-31 ፤ዮሐ.1፡3)
የጠፋውን መፈለግ (ዘፍ 3፡9)
ነፃ የማውጣት (ዘፀ.3፡1-8)
1.2. እግዚአብሔር ወልድ የተልዕኮ አምላክ ነው (ገላ 4፡4)
የመፋውን መፈለግ፣እርቅ፣ ማዳን (ሉቃ 19፡1-10፤2ኛ ቆሮ 5፤19-20)
ደቀመዝሙርት የድረግ(ሉቃ.6፡12-16)
የመላክ ተልዕኮ (ማቴ 28፡19-20፤16፡15)
1.3. እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የተልዕኮ አምላክ ነው (ዮሐ.16፡7)
ስለ ኢየሱስ የመመስከር (ዮሐ.15፡26)
ኢየሱስን የማክበር (ዮሐ.16፡13-14)
የማጽናናት (ዮሐ. 16፡7)
ዓለምን የመውቀስ (ዮሐ.16፡8-11)
ቤተክርስቲያን የመምራት (ዮሐ.16፡13፤ሮሜ 8፡14)
2. ቤተክርስቲያን ተልዕኮዋን በመንፈስ ቅዱስ በመመራት መፈጸም አለባት (ማቴ 28፡19-20)
2.1. ሲሉስ የሆነውን አምላክ በማምለክ (ዘፀ.23፡25፤ዮሐ.4፡23-24)
2.2. ስለ ኢየሱስ መመስከር (ዮሐ. 15፡27፤ሐዋ 1፡8)
2.3. የማስታረቅ ተልዕኮ (2ኛ ቆሮ 5፡18፣20)
2.4. ደቀመዝሙር የማደረግ ተልዕኮ (ማቴ 28፡19-20)
2.5. ሚሲዮናውያንን የመላክ ተልዕኮ (ሐዋ. 13፡1-5)
3. ቤተክርስቲያን በተለያዩ ተግዳሮቶች ውስጥ አልፋለች
3.1. የጥንት ቤተክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ በመመራት 5-590
ከውስጥ የስህተት አስተምሮ ከውጭ ስደት
ተቋቁማ ተልዕኮዋን በብቃት ፈጽማለች
3.2. መካከለኛ ክ/ዘመን የጭለማው ዘመን ቤተክርስቲያን
የእግዚአብሔር ቃል ሥፍራ ያጣበት
ወጐችና ልማዶች የእግዚአብሔርን ቃል የተኩበት
ጳጳሱ ከሁሉ በላይ የሆኑበት
3.3. የአሁኗ ቤተክርስትያ በቃል የታደሰች የተሃድሶ ፍሬ ናት በተሃድሶ መንፈስ መቀጠል አለባት
ቃል ብቻ (ሮሜ 10፡17)
እምነት ብቻ (ሮሜ 1፡17፤ኤፊ 2፡8-9)
ፀጋ ብቻ (ኤፈ 2፡8)
ስለዚህ ቤተክርስቲያን ወደ ጭለማ እንዳትገባ ታላቁ ተልዕኮዋን ለመፈጸም በመንፈስ እንመራ ስንል በአብ፣በወልድ፤በመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ እንመራ ማለታችን ሲሆን በሌላ በኩል ቤተክርስቲያን የተሰጣትን ተልዕኮ ለመፈጸም አገልግሎቷና አመራሯ በቃሉ ሊትመራ ይገባል ማለት ነው ። ስለዚህ በቀሪው ዘመናችን ህይወታችንን፣ አገልግሎታችንና የቤተክርስቲያን ተልዕኮበመንፈስ ቅዱስ በመመራት እንድንፈጽመው ጌታ ጸጋውን ያብዛልን ።
JESUS IS LORD!!!
14/02/2026
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ታቦር ማህበረ ምዕመናን አገልጋዮች ከየካቲት 2-7/2018 ዓ.ም አ/አበባ እግዚአብሔር በማህበረ ምዕመናናችን፣ በቤተክርስቲያናችንና በአገራችን በሰራቸው በድንቅ ሥራዎቹ እግዚአብሔርን በማመስገን 2026 አገልግሎት ዘመን ለቤተክርስቲያንና ለአገራችን ሁለተናዊ ስኬት እንድሆንልን በመጸለይና በአ/በባ ድንቅ የልማት ሥራዎችን በመጐብኘት ድንቅ ጊዜ አሳልፈን ተመልሰናል ። ክብር ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ይሁን!!!
22/01/2026
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ታቦር ማህበረ ምዕመና ከታህሳስ 6-12/2018 ዓ.ም የሚሲዮናዊ ሳምት ከሀዋሳ እስከ ወንዶገነት የተደረገ 20,000 በላይ ሰዎች ወንጌልን የሰሙበት ፤117 ነፍሳት ጌታን የተቀበሉበትና 468 ሰዎች ንስሐ የገቡበት የወንጌል ሥርጭት ዘመቻ::
03/12/2025
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ታቦር ማህበረ ምዕመና ከተቋቋመች 28ኛ ዓመቷ ስሆን በእነዚህ ዓመታት 59 ማህበራነ ምዕመናንን አቋቁማለች፣41 የሚሲዮንና 16 ስብከት ጣቢያዎችን በመክፈት ሚሲዮናዊ አገልግሎትን በማገልገል ላይ ትገኛለች ። ከዚህ በተጨማሪ አንድ ሚሲዮናዊ ከሀገር ውጭ አፍርካዊት አገር ጋና ልካለች። ማህበረ ምዕመናኗ በሚሲዮና አገልግሎቷ ባስመዘገበችው ውጤት የኢ/ወ/ቤ/መ/ኢ ካሉ ማህበራነ ምዕመናን መካከል አንደኛ በመሆን የእውቅና ዋንጫ አግኝታለች ። በሆነው ሁሉ ክብሩን እግዚአብሔር ይውሰድ ። በመቀጠል ይንን ታላቁን ተልዕ መላውን ምዕመን በማነሳሳት በተሻለ ትጋት ለማስቀጠል ከታህሳስ 6-12/2018 ዓ.ም ሚሲዮናዊ ሳምንት ሆኖ ሳምንቱን በሙሉ በተለያዩ ፕሮግራሞች ታከብራለች ። በመሆኑም ምዕመናን ሁሉ በእነዚህ ቀናት በሚኖሩን ፕሮግራሞች ላይ በንቃት በመሳተፍ ሚሲዮናዊ ኃላፈነታችሁን እንድት ወጡ በማለት ማህበረ ምዕመናኗ በጌታ ፍቅር ታሳስባለች ።
ኢየሱስ ያድናል!!!
ኢየሱስ ይመጣል!!!
08/11/2025
Big shout out to my newest top fans! 💎
Tariku Tesfaye, Godana Gobena
Drop a comment to welcome them to our community,
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the place of worship
Address
Awassa
Opening Hours
| Tuesday | 08:30 - 17:00 |
| Wednesday | 08:30 - 17:00 |
| Thursday | 08:30 - 17:00 |
| Friday | 08:30 - 17:00 |
| Sunday | 09:00 - 12:00 |