John yosef
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from John yosef, Awassa.
08/07/2023
He’s feeling sad 😞 because no one appreciates his hardwork ♥
29/07/2021
በወንዶ ገነት ከተማ ያለውን የተፈጥሮ ሀብት ባለሀብቶች እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀረበ
****************
(ኢ.ፕ.ድ)
የወንዶ ገነት ከተማ ለሆቴል፣ ሎጅ እና ንግድ ሥራ ከፍተኛ አቅም ያላት በመሆኗ ባለሃብቶች በከተማዋ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የከተማዋ ከንቲባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የወንዶ ገነት ከተማ ከንቲባ አቶ እርዳቸው ኤሊያስ በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ ወንዶገነት በፍል ውሃ የታደለች ከተማ በመሆኗ ባለሀብቶች ይህንን ሀብት አልምተው ቢጠቀሙ ራሳቸውንም ከተማዋንም አትራፊ ያደርጋሉ።
እንደ ከንቲባው ገለፃ፤ እንደ ቡና፣ አትክልትና ፍራፍሬና ያሉ ምርቶች በከተማዋ በከፍተኛ መጠን ግብይት ይፈጸማል። ከዚህ ግብይትም ከተማዋ በቀን ከ500 ሺ ብር በላይ ገቢ ትሰበስባለች።
ወንዶገነት ከኢትዮጵያ በርካታ ከተሞች ለየት የሚያደርጋት ዓመቱን ሙሉ ግብይት የሚፈፀምባት ከመሆኑም በተጨማሪ 50 ሺ ነዋሪ በማይሞላባት ከተማ ከግማሽ ሚሊዮን ብር የሚልቅ ገቢ የሚሰበሰብባት መሆኗ ነው ብለዋል።
በከተማዋ በአስፈላጊ የሚባሉ መሰረት ልማቶች በሚፈለገው ልክ አልተሟላላትም ያሉት ከንቲባው፤ በዚህም ምክንያት ህብረተሰቡ በሚገባን ልክ እንልማ በገቢያችን መጠን ትኩረት ይሰጠን የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ እያቀረብ ነው ብለዋል።
የክልሉ መንግስትም ጉዳዩ በመገንዘቡ እያጤነው መሆኑን ከንቲባው ጠቁማዋል፡፡
በክፍለዮሀንስ አንበርብር
Click here to claim your Sponsored Listing.