SNNPR prison adminstration communication

SNNPR prison adminstration communication

Share

south Ethiopian prison (correctional) administration commission post every week or more than posted የ

16/01/2024

የጂንካ ማረሚያ ተቋም ኃላፊ ም/ኩ/ር አስቻለሁ ኔሬሬ መዉሊድ በዓልን አስመልክቶ ለመላው እስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፋ

መላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች የማረሚያ ተቋም ሠራተኞችና የህግ ታራሚዎች እንኳን ለ1498ኛው የነብዩ ሙሃመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!

መውሊድ የታላቁ የእስልምና ነቢይ የነብዩ ሙሐመድ የልደት በዓል ነው፡፡ ከመውሊድም ሰላምን፣ ፍቅርን፣ ትግስትን፣ አንድነትን እንማራለን።

መውሊድ መተባበርና አብሮነት፤ መተዛዘንና መፈቃቀድ በተግባር የሚገለጽበት ነው። ያለው ለሌለው የሚያካፍልበት፣ ማህበራዊ ትስስሩን የሚጠናከርበት፤ በአንድነት አብሮ የሚያሳልፍበት በዓል ነው።

በመሆኑም ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የነብዩ መሐመድን መልካም አስተምህሮቶች ለትዉልዱ በማስተላለፍ ፣ የተቸገሩትን በማሰብ፣ በመረዳዳትና በመደጋገፍ ሊሆን ይገባል።

ስለሆነም እንኳን ለ1ሺህ 498ኛው የነብዩ መሐመድ መውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን እያልኩ፦ በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የአብሮነትና አንድነት እንዲሆን እመኛለሁ።

መልካም በዓል!

Photos from SNNPR prison adminstration communication's post 28/09/2023

በማዕከላዊ #ኢትዮጲያ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በስሩ ከሚገኙ ማረሚያ ተቋማት በጥበቃ ስር የሚገኙ የህግ ታራሚዎች የመስቀል በዓልን እያከበሩ ይገኛሉ።
17/01/2016

በኮሚሽኑ ስር ከሚገኙ ማረሚያ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው
# በዱራሜ ማረሚያ ተቋም
የከንባታ ዞን ምክር ቤት የሀደሮ እና የሽንሽቾ ከተማ በጎ አድራጊ ወገኖች እና ከተቋሙ ጋር በመተባበር በድምሩ ሰባት ሰንጋ በሬ ለክርስቲያን እና ለሙስሊም ታራሚዎች ታርዶላቸው በደማቅ ሁኔታ እንዲያከብሩ የተደረገ ሲሆን ይህን በጎ ተግባር ያደረጉትን ወገኖች በታራሚዎች በኮሚሺኑ እና በተቋሙ ስም እጅግ በጣም እናመሰግናለን
መልካም የመስቀል በአል
መረጃውን የደረሰን የዱራሜ ማረሚያ ተቋም!!

Photos from SNNPR prison adminstration communication's post 27/09/2023

ለሞላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን በሠላም ለብርሀነ መስቀሉ አደረሳችሁ !!

በሀገራችን ክርስቲያኖች ዘንድ መስቀል የድልና የፈተና ምልክት ነው።
መስቀል በአንድ በኩል እስከ ሞት የሚያደርስ መስዋዕትነትና ፈተናን የሚያንፀባርቅ በሌላ በኩል ማንም ሊያስቀረው የማይችለውን ድል አድራጊነትን የሚያሳየን ነው።
ይህም የክርስቶስ ሰላም እና ፍቅር በሁሉም የሰው ልጆች ልብ ውስጥ ስለ አንድነት በጉልህ ከፍ ብሎ ሊታይ ደግሞ ይገባል ብሎ የማረሚያ ኮሚሽናችን ያምናል።
በክልላችን በጉራጌ ዞን ከወትሮ በተለዬ መንገድ የመስቀል ዳመራ በዓል በአደባባይ በድምቀት ይከበራል።
በኮሚሽናችንም በስሩ በሚገኙ፥ ማረሚያ ተቋማት ጠያቂ ዘመዶቻቻውና በተቋማት ተዘጋጅቶ ይከበራል።
በዚህም በእስር ቆይታቸው ወቅት ቤተሰቦቻቸውን እንዳያስቦና እንዳይጨነቁ ይረዳቸዋል።
በመጨረሻም በዚህ መልዕክት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በድጋሚ እንኳን ለዚህ ቀን እና ታላቅ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን ሀገራችንን አንድ በሚያደርግ በሰላም እና በአብሮነት ጉዳይ ልዩነት ሳይኖር እንደተሻገርን ዛሬም እንደ መስቀል ደመራ ተደምረን ለክልላችን ሁሉን አቀፍ ልማት በጋራ ሁላችንም ዘብ እንድንቆም ኮሚሽናችን ጥሪ ያቀርባል።

Photos from የ ጅንካ ማረምያ ተቋም ህዝብ ግንኙነት / Jinka prison Government communication Affairs's post 26/09/2023
Photos from ጨንቻ ማረሚያ ተቋም/ Chencha Prison Institution's post 26/09/2023
26/09/2023

ቀን 15/01/2016 ዓ.ም
በሀገራችን የመስከረም ወር (2016) ዓ.ም መግባቱን ተከትሎ የተለያዩ በዓላት ይከበራሉ ከነዚህም ውስጥ በማዕከላዊ ክልል የሚገኙ ዞኖች የሚከበረው በሀዲያ የያሆዴና በከንባታ መሰላ እንዲሁም በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጋሪዎሮ፣ጊፋታ፣ዮ-መስቀላ፣ሄቦና ጋዜ መስቀላ የመሳሰሉ በዓለት ይከበራሉ፡፡
በነገው እለት የእስልምና እምነት ተከታዮች የመውሊድ በዓል የሚከበር ሲሆን በክርስትና እምነት ተከታዮች የመስቀል በዓል በቀን 17/01/2016 ዓ.ም በተከታታይ ቀናት ይከበራል፡፡
በክልላችን (በሰባቱም) በ7 ማረሚያ ተቃማት ውስጥ የሚገኙ ታራሚዎችም በዓሉን በሉበት ማረሚያ ተቋም ከጠያቂ ዘመዶቻቸውና እርስ በርሳቸው እንኳን አደረሰን በመባባል የሰልፋሎ፡፡
ኮሚሽናችን ለሞላው ሀገራች እና ክልላችን እዝቦች እንዲሁም በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለሚገኙ እህት የማረሚያ ኮሚሽን እና ተቋም አመራሮች እንዲሁም በለሙያዎች ፣በተቋማት ለሚገኙ የህግ ታራሚዎችና ለታራሚ ቤተ-ሰቦች በቀን/16/2016 ዓ.ም 1445 አመተ ሂጅራ ለሚከበረው መውሊድ ወይም የነብዩ መሀመድ (የለህ እዝነትና ሰላም በነብዩ ላይ ይወረድ) ልደት በዓልና በ17 2016 ዓ.ም በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ለሚከበረው መስቀል በዓላት እንኳን አደረሳችሁ እያልን በዓሉ የሰላምና የብልፅግና እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡
ኮሚሽናችን በህግ ስልጣን በተሰጠው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የተላኩ የህግ-ታራሚዎችን አርሞና አንፆ ከማረሚያ ተቋም ሲፈቱ ራሰቸውን እንዲችሉና የበደሉትን መህበረሰብ እንዲኪሱ በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን ሰብዓዊ መብታቸው #ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ በተቀበለቻቸው መርሆች፣ድንጋጌዎችና ህጎች እንዲሁም በህገ-መንግስቱ የተያዙ ሰዎች መብቶችን ለማክበርና ለማስከበር በተቀመጡ ድንጋጌዎች መሰረት ለማስፈጸም ሰፊ ስራዎችን አከናውኗል፡፡
በቅርቡ የህዝብ ጥያቄን መሰረት በማድረግ በተሰጠው ድምፅ መሰረት የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቡችና የመዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መቋቋሙ የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው፡፡
የማከላዊ ክልል ማረሚያ ኮሚሽን ከደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አብሮ የሰራቸውና የፈራቸው የጋራ የአሰራር፣እሴቶች እንዲሁም ለወጦች እጅግ በጣም ከፍታኛ መሆናቸውን ለማየት በቅርቡ የክልሎችና ፊድራል ማረሚያ ኮሚሽኖች በደረጉት ዓመታዊ የጋራ ስብሰባ ላይ ሁለት ተቋማትን በየዓመቱ በሚደረገው የክልሎችና የፊድራል ማረሚያ ኮሚሽኖች የጋራ ስብሰባ እንዲካፈሉና ልመዳቸውን በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲያስተላልፉ ከማስመረጡም በተጨማሪ የቀድሞ ደቡብ ክልል ኮሚሽኑን ጨምሮ ሽልማት ተበርክቶልናል፡፡
ሆኖም በተገኘው ለውጥ መኩራራት ሳይሆን የሚቀሩብን ብዙ ስራዎች እንዳሉ ከግምት ውስጥ በማስገባት በሁለቱም ኮሚሽኖች የተጀመረውን ሁለንተናዊ ለውጥችን ለማስቀጠል በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ መግለጽ ይወዳል፡፡
በዓሉን በምናከብርበት ወቅት እንደወትሮ ሁሉ በመረዳዳትና በመደጋገፍ መንፈስ ሊሆን እንደሚገባው ከወዲሁ አደራ ለማለት ይወዳል፡፡
የማዕከላዊ ክልል ማረሚያ ቤቶች አስታዳደር ኮሚሽን!!

26/09/2023

የእንኳን አደረሳችሁ መልክት
ቀን 15/01/2016 ዓ.ም
በሀገራችን የመስከረም ወር (2016) ዓ.ም መግባቱን ተከትሎ የተለያዩ በዓላት ይከበራሉ ከነዚህም ውስጥ በማዕከላዊ ክልል የሚገኙ ዞኖች የሚከበረው በሀዲያ የያሆዴና በከንባታ መሰላ እንዲሁም በጉራጌ የመስቀል በዓል በደማቅ ሁኔታ የሚከበር ሲሆን በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጋሪዎሮ፣ጊፋታ፣ዮ-መስቀላ፣ሄቦና ጋዜ መስቀላ የመሳሰሉ በዓለት ይከበራሉ፡፡
በነገው እለት የእስልምና እምነት ተከታዮች የመውሊድ በዓል የሚከበር ሲሆን በክርስትና እምነት ተከታዮች የመስቀል በዓል በቀን 17/01/2016 ዓ.ም በተከታታይ ቀናት ይከበራል፡፡
በክልላችን (በሰባቱም) በ7 ማረሚያ ተቃማት ውስጥ የሚገኙ ታራሚዎችም በዓሉን በሉበት ማረሚያ ተቋም ከጠያቂ ዘመዶቻቸውና እርስ በርሳቸው እንኳን አደረሰን በመባባል የሰልፋሎ፡፡
ኮሚሽናችን ለሞላው ሀገራች እና ክልላችን እዝቦች እንዲሁም በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለሚገኙ እህት የማረሚያ ኮሚሽን እና ተቋም አመራሮች እንዲሁም በለሙያዎች ፣በተቋማት ለሚገኙ የህግ ታራሚዎችና ለታራሚ ቤተ-ሰቦች በቀን/16/2016 ዓ.ም 1445 አመተ ሂጅራ ለሚከበረው መውሊድ ወይም የነብዩ መሀመድ (የለህ እዝነትና ሰላም በነብዩ ላይ ይወረድ) ልደት በዓልና በ17 2016 ዓ.ም በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ለሚከበረው መስቀል በዓላት እንኳን አደረሳችሁ እያልን በዓሉ የሰላምና የብልፅግና እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡
ኮሚሽናችን በህግ ስልጣን በተሰጠው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የተላኩ የህግ-ታራሚዎችን አርሞና አንፆ ከማረሚያ ተቋም ሲፈቱ ራሰቸውን እንዲችሉና የበደሉትን መህበረሰብ እንዲኪሱ በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን ሰብዓዊ መብታቸው #ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ በተቀበለቻቸው መርሆች፣ድንጋጌዎችና ህጎች እንዲሁም በህገ-መንግስቱ የተያዙ ሰዎች መብቶችን ለማክበርና ለማስከበር በተቀመጡ ድንጋጌዎች መሰረት ለማስፈጸም ሰፊ ስራዎችን አከናውኗል፡፡
በቅርቡ የህዝብ ጥያቄን መሰረት በማድረግ በተሰጠው ድምፅ መሰረት የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቡችና የመዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መቋቋሙ የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው፡፡
የማከላዊ ክልል ማረሚያ ኮሚሽን ከደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አብሮ የሰራቸውና የፈራቸው የጋራ የአሰራር፣እሴቶች እንዲሁም ለወጦች እጅግ በጣም ከፍታኛ መሆናቸውን ለማየት በቅርቡ የክልሎችና ፊድራል ማረሚያ ኮሚሽኖች በደረጉት ዓመታዊ የጋራ ስብሰባ ላይ ሁለት ተቋማትን በየዓመቱ በሚደረገው የክልሎችና የፊድራል ማረሚያ ኮሚሽኖች የጋራ ስብሰባ እንዲካፈሉና ልመዳቸውን በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲያስተላልፉ ከማስመረጡም በተጨማሪ የቀድሞ ደቡብ ክልል ኮሚሽኑን ጨምሮ ሽልማት ተበርክቶልናል፡፡
ሆኖም በተገኘው ለውጥ መኩራራት ሳይሆን የሚቀሩብን ብዙ ስራዎች እንዳሉ ከግምት ውስጥ በማስገባት በሁለቱም ኮሚሽኖች የተጀመረውን ሁለንተናዊ ለውጥችን ለማስቀጠል በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ መግለጽ ይወዳል፡፡
በዓሉን በምናከብርበት ወቅት እንደወትሮ ሁሉ በመረዳዳትና በመደጋገፍ መንፈስ ሊሆን እንደሚገባው ከወዲሁ አደራ ለማለት ይወዳል፡፡
የማዕከላዊ ክልል ማረሚያ ቤቶች አስታዳደር ኮሚሽን!!

Photos from SNNPR prison adminstration communication's post 25/09/2023
Photos from SNNPR prison adminstration communication's post 09/09/2023

28/01/2015 ዓ.ም
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የማረሚያ ፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም የ34ኛ ዙር የማረሚያ ፖሊስ አባላትን አስመረቀ፡፡
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የማረሚያ ፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም ለ34ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን 921 የፌዴራልና የክልል ማረሚያ ፖሊስ አባላት አስመርቋል፡፡
ሰልጣኝ የማረሚያ ፖሊስ ዕጩዎችን የመረቁት የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ዳመነ ዳሮታ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ባስተላለፉት መልዕክት ማረሚያ ቤት በፍርድ ቤት ውሳኔ የሚመጡ የህግ ታራሚዎችን ተቀብሎ ደህንነታቸውን በመጠበቅ፣ መሰረታዊ ፍላጎታቸውን በማሟላት፣ የታረሙና የታነጹ ፣ህግ አክባሪ እና አምራች ዜጋ ማድረግ ላይ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
ኮሚሽነር ጄኔራል ዳመነ አክለውም በኮሚሽኑ የተጀመረውን የለውጥ ሂደት በማጠናከር ለአገልግሎት ፈላጊዎች ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት የዛሬ ተመራቂ የማረሚያ ፖሊስ አባላት ሚና ከፍተኛ ነው፤ በመሆኑም በምትመደቡበት ቦታ ሁሉ የታራሚዎችን ሰብአዊ መብት ለመጠበቅ እና የተቋሙን መልካም አስተዳደር ለማረጋጥ በትጋት መስራት ይጠበቅባችኋል ብለዋል፡፡
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የፋይናንስ እና ሰው ኃብት ልማት ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ጄኔራል ያረጋል አደመ በበኩላቸው በፌዴራል እና በክልል ደረጃ የሚገኙ የማረሚያ ማዕከላትን በሰለጠነ የሰው ኃይል ለመገንባት ፤የማሰልጠኛ ተቋሙ ከወቅቱ ጋር ተራማጅና በቴክኖሎጅ የታገዙ ስልጠናዎችን ለመስጠት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
በመሆኑም በዛሬው እለት የተመረቁ የማረሚያ ፖሊስ አባላት በማሰልጠኛ ተቋሙ ቆይታቸው የቀሰሙትን እውቀትና ክህሎት በሚመደቡበት ክልል ወይም ማዕከል ችግር ፈቺ ስራዎችን በመስራት በተግባር እንደሚያሳዩ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የማረሚያ ፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም ዳይሬክተር ተወካይ ኢኒስፔክተር ያለምዘውድ ብዙነህ አጠቃላይ የስልጠና ሂደቱን አስመልክተው በአቀረቡት ሪፖርት እንዳመላከቱት ተመራቂ የፖሊስ አባላትን በቂ የመስክ እና የክፍል ስልጠናዎችን ከመስጠት በተጨማሪ በልማትና በበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ተደርጓል ብለዋል፡፡
በዕለቱ የላቀ ውጤት አምጥተው ተሸላሚ በመሆን ከተመረቁ የማረሚያ ፖሊስ አባላት መካከል ኮንስታብል ቢኒያም አቤ እና ኮንስታብል እመቤት አበዋ እንደተናገሩት ፖሊስነት ለህዝብ ደህነነት እና ክብር መቆም ነው፤ በመሆኑም መሰረታዊ የፖሊስ መርሆችን በመስክ እና በክፍል በመከታተል ለዛሬው የምረቃ ቀን በመድረሳቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸው ለወደፊት በሚሰማሩባቸው የስራ መስክ ውጤታማ ተግባራትን ለማከናወን ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

04/09/2023

ነሐሴ 28/2015፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በተለያዩ የመንግስት ሥራ ኃላፊነት ቦታዎች በካብኔ ማዕረግ ለሚያገለግሉ የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ሠጥቷል።

በዚህም መሠረት፦

1. አቶ ሰማን ሺፋ - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ኃላፊ
2. አቶ ንጉሴ አስረስ - በካብኔ ማዕረግ የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ
3. ረዳት ፕሮፌሰር አንተነህ መሉ - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፖሊስ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር
4. ዶክተር ፈለቀች ተክለማሪያም - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፖሊስ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት የዘርፍ ኃላፊ

5. አቶ ሀይረዲን ረዲ - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የህዝብ ግንኙነትና ማህበረሰብ ንቅናቄ ዘርፍ አማካሪ
6. አቶ ኑሪዬ ሱሌ - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የመልካም አስተዳደርና የህግ ጉዳዮች ዋና አማካሪ
7. አቶ ሰብስቤ ተካ - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ፣
8. ወይዘሮ ነኢማ ሙኒር - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ፣
9. አቶ ተስፋዬ ብላቱ - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር
10. አቶ ፀደቀ ሱጌቦ - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ፣
11. አቶ ታረቀኝ ኃይለማሪያም - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የመሠረተ ልማት ዘርፍ አማካሪ
12. አቶ ሙሽተባ አባድር - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የፍትህ አካላት ስልጠና ማዕከል ኃላፊ
13. ኮምሽነር ሉባባ ጀማል - የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኃላፊ
14. ኮሚሽነር ሽመልስ ካሳ - የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር
15. ወ/ሮ ፋዲላ አደም - የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር
16. አቶ ሬድዋን ከድር - የክልሉ ቡናና ቅመማ ቅመም ባልሥልጣን ሥራ አስኪያጅ

17. ዶክተር አክመል መሀመድ - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፖሊስ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ዘርፍ ኃላፊ
18. አቶ ማሞ ቴጋ - በካብኔ ማዕረግ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኩምሽነር
19. አቶ አብዲልባሲጥ አባኮ - በካብኔ ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ጽህፈት ቤት ኃላፊ ልዩ ረዳት
ማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ለጋራ ተጠቃሚነት!!!!

Want your practice to be the top-listed Law Practice in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address

Hwassa
Awassa