MesfinPage

MesfinPage

Share

pc maintner. I Believed Jesus Chrisg

05/01/2026

“በሚስት ታስረህ እንደ ሆንህ መፋታትን አትሻ፤ በሚስት አልታሰርህ እንደ ሆንህ ሚስትን አትሻ።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 7፥27

30/12/2025

#የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የተሳሳተ ውሳኔ .....

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ተማሪ የሆነችው ወጣት፣ በማህበራዊ ሚዲያ (ቲክቶክ) ባጋራችው ቪዲዮ ምክንያት ለአንድ ዓመት ከትምህርቷ እንድትታገድ መወሰኑ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

ተማሪዋ በቪዲዮዋ ላይ "መምህራን ለ3ዐ ደቂቃ ያህል ካስተማሩ በኋላ የተማሪዎች የመስማትና የመረዳት አቅም ስለሚቀንስ የምታስተምሩን አይገባንም" የሚል ይዘት ያለው መልዕክት ማስተላለፏ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ የዩኒቨርሲቲው ዲሲፕሊን ኮሚቴ ይህ ድርጊት መምህራንን የሚያንቋሽሽና የዩኒቨርሲቲውን ክብር የሚነካ ነው በሚል ተማሪዋ ለአንድ ዓመት ከትምህርት ገበታዋ እንድትታገድ ወስኗል።

ይህን ጥያቄ ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ላቅርብ
1ኛ) ተማሪዋ ያጋራችው ሐሳብ በሳይንስ እና በምርምር የተረጋገጠ አይደለምን????? ወይስ አታውቁትም
2ኛ) የተማሪዋ ሐሳብ የመምህራንን ክብር ዝቅ ያደረገው የቱ ጋር ነው ? እውነቱ ስለተነገረ????
3ኛ) ትምህርት አይጠቅምም ብሎ የሚያወራ ባለስልጣን (ትምህርት ሚኒስትር) ባለበት ሐገር ???? የእርሷ ጥፋት የቱ ጋር ነው?????

ስለሆነም ተማሪዋ ላይ የተወሰነው ኢፍታዊ ውሳኔ ከእንደገና በሰከነ መንፈስ ታይቶ ተማሪዋን የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ወደ ትምህርት ገበታዋ ይመልሳት ዘንድ በአንክሮ እጠይቃለሁ።
ፍትህ በግፍ ከትምህርት ገበታዋ ለታገደችው እህታችን::

30/12/2025

“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሰው የሚታመን ሥጋ ለባሹንም ክንዱ የሚያደርግ ልቡም ከእግዚአብሔር የሚመለስ ሰው ርጉም ነው።”
— ኤርምያስ 17፥5

26/12/2025

የማይንቀሳቀሰውን ፣ የሚንቀሳቀሰውን ንብረትን ልትዘርፍ ትጥር ይሆናል። ግን የአዕምሮዊ ንብረትኖ መንጠቅ ፈፅሞ አትችልም።

23/12/2025

“አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤”
— ኤፌሶን 4፥5

22/12/2025

የኢትዮጵያ ጥንታዊ የሹመት ማዕረጎችና የዘመኑ አመራር ምን ይመስል ነበር?

​ኢትዮጵያ የረቀቀና የሰለጠነ የመንግሥት መዋቅር ባለቤት ለመሆኗ አንዱ ትልቁ ማረጋገጫ፣ ጥንታዊ የሹመት ማዕረጎቿ ናቸው። ይህ በምስሉ ላይ የምታዩት ዝርዝር ዝም ብሎ የስሞች ስብስብ አይደለም፤ ይልቁንም የኢትዮጵያን የሥራ ክፍፍል፣ የኃላፊነት ተዋረድ (Hierarchy) እና የማኅበራዊ መስተጋብር ጥበብ የሚያሳይ የታሪክ ሰነድ ነው።

​በዘመናዊው የቢዝነስ ዓለም "Leadership" እና "Organisational Structure" (ተቋማዊ መዋቅር) የምንላቸው ጽንሰ-ሀሳቦች በሀገራችን ከዘመናት በፊት ሥር የሰደዱ ነበሩ።

​ጥቂት ማሳያዎችን ለመጥቀስ ያህል....

➤ ​ቢትወደድ፦ የንጉሡ የቅርብ አማካሪና የሕዝብ ጉዳዮች መሪ። በዘመናዊው አጠራር "Chief Advisor" ወይም "Vice President" ሊባል ይችላል።

➤ ​ፊትአውራሪ፦ በጦር ግንባርም ሆነ በአስተዳደር ስልት ቀዳሚ ሆኖ የሚመራ፤ ዛሬ የምንጠራው "Visionary Leader" ነው።

➤ ​ጸሐፌ ትእዛዝ፦ የመንግሥትን ሕግጋትና ታሪክ በጽሁፍ የመመዝገብና የማስተላለፍ ኃላፊነት የነበረው፤ የኢትዮጵያ "Chief of Staff" ነው።

​የሴቶች ድርሻ፦ እቴጌ፣ ንግሥት፣ ልዕልት እና ወይዘሮ የሚሉት ስያሜዎች ጥንት ትልቅ የሥልጣንና የክብር ደረጃን የሚወክሉ ነበሩ። ዛሬ እነዚህን የሚተካ ክብደት ያለው ስም ማጣት የባህል መክሰማችን ማሳያ ነው።

​መንፈሳዊ መዋቅር፦ ከሊቀ ጳጳስ, ንቡረ እድ,...ቀኝ ጌታ... ያሉት ስሞች የቤተክርስቲያን የማዕረግ ስሞች ምን ያህል የጠበቀ እንደነበር ያሳያሉ።

የታሪክ ምሁራን እንደሚስማሙት፣ እነዚህ ኩሩ ስያሜዎች መዳከም የጀመሩት በሁለት ዋና ምክንያቶች ነው ይላሉ።

1. ​የ1966ቱ አብዮት (ደርግ)፦ የዘውዱ ሥርዓት ሲወገድ፣ እነዚህ ማዕረጎች "ፊውዳላዊ" ተብለው ታገዱ። በምትካቸውም የሶሻሊስት ተፅዕኖ ያረፈባቸው ወታደራዊ ስያሜዎች (ሌተናል ኮሎኔል፣ ሜጀር ጄኔራል) ነገሡ።

2. ​የምዕራባውያን ተፅዕኖ (ግሎባላይዜሽን)፦ በባህልና በቋንቋ ተገዢነት ምክንያት የራሳችንን ጥለን "ሚኒስትር፣ ዳይሬክተር፣ ፕሬዝዳንት" የሚሉትን ስያሜዎች በፈቃደኝነት ተቀበልን። ዛሬ "ሻለቃ" ወይም "ባሻ" እንኳ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸዋል።

- 'ራስ'ን የመሰለ ስም በእኛ ትውልድ አልታደልንም።

ወደ ኋላ የምንመለከተው ለመቆዘም ሳይሆን፣ ወደ ፊት የምንሄድበትን ጽኑ መሠረት ፍለጋ ነው። በቴክኖሎጂ፣ በፋይናንስና በቢዝነስ ዓለም የምንሰማራው ኢትዮጵያውያን፣ የራሳችንን ታሪክና የአደረጃጀት ጥበብ ስናውቅ ዓለም አቀፋዊ ዕውቀትን ከሀገራዊ እሴት ጋር አዋህደን ትልቅ ለውጥ ማምጣት እንችላለን ይላሉ የታሪክ ሙህራን።

​ማንነታችንን ማወቅ የባርነትን ሰንሰለት ሰብሮ፣ በፈቃደኝነት የወደቅንበትን የታሪክ መዘንጋት ያድነናል። ዛሬ ላይ ቆመን የትናንቱን ውበት ስንመለከት፣ ለነገው ትውልድ የምናስተላልፈው የራሳችን የሆነ "Brand" እንዳለን እናረጋግጣለን።
ሰላም ለሀገራችን 💙🙏

21/12/2025
07/12/2025

ሰዎች ራሳቸውን እንዲወዱ ካደረክ፣ አንተንም ይወዱሃል።

27/11/2025

ከሆንክለት ይልቅ የሆንክበትን መርሳት አብዝቶ ይቀለናል ያ ነው አብሮ የኖረ ወዳጅነትን የሚያሳጣን!

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Awassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


Awassa