Hawassa Polytechnic College
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hawassa Polytechnic College, College & University, Hawassa, Awassa.
Hawassa polytechnic is public TVET College established in 1990 E.C to offer technical and vocational education and training for the local community through both formal and non-formal programs aimed to provide morally up right and competent work force for
21/04/2026
የሚመረቱ ቴክኖሎጂዎች የአከባቢን ፍላጎት መነሻ በማድረግ ለገበያዉ የማቅረብ ሥራ ላይ ትኩረት ሰጥተዉ እየሰሩ እንደሚገኙ የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን ገለጹ።
ኮሌጁ የሰራዉን የፕላስቲክ ሪሳይክልና ፕሮሰስ ቴክኖሎጂን በሀዋሳ ከተማ ተደራጅቶ እየሰራ ለሚገኝ ዉበት ሀዋሳ ኢንተርፕራይዝ በ1.2 ሚሊየን ብር ግዢ በመፈጸም ርክክብ አድርጓል ።
የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ መልካሙ በራሳ በኮሌጃቸዉ የሚመረቱ ቴክኖሎጂዎች የአከባቢን ፍላጎት መነሻ በማድረግ ችግር ፈቺ አዋጪ ቴክኖሎጂ በመስራት ለአብዢ ኢንተርፕራይዞች የማሸጋገርና በተቋም በማምረት ለገበያዉ የማቅረብ ሥራ ላይ ትኩረት ሰጥተዉ እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
በኮሌጃቸዉ ተሰርቶ በዛሬዉ ዕለት ለርክክብ የበቃዉ ቴክኖሎጂ የፕላስቲክ ሪሳይክል ፕሮሰስ ቴክኖሎጂ መሆንና የፕላስቲክ ዉጤቶችን የሚፈጭ ፣ የሚያጥብና የሚያደርቅ ቴክኖሎጂ መሆኑን የተናገሩት የኮሌጁ ዲን የሀዋሳ ከተማ ለተጀመረዉን ስማርት ሲቲ ትልቅ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑን ተናግረዋል።
በኮሌጁ የተመረተዉ ይህ ቴክኖሎጂ ከዉጪ የሚገቡ የቴክኖሎጂ ዉጤቶች ሊተካ የሚችል ቴክኖሎጂ መሆኑን የተናገሩት የኮሌጁ ዲን ለአከባቢ ጥበቃ አበርክቶ ሚናዉ ከፍተኛ መሆንን ተናግረዋል።
የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምክትል ዲንና የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢ/ኤ ዋና አስተባባሪ ወ/ሮ ከበብሽ ተሰማ ይህ የተመረተዉ ቴክኖሎጂን እሴት ሰንሰለት ትንተናን መነሻ በማድረግ የተሰራ ቴክኖሎጂ በማንፋክቸሪንግ ዲፖርትመነት የአከባቢን ብክለት ችግር መነሻ ተደርጎ የተሰራ መሆኑንና ቴክኖሎጂውን ሰርቶ ለማጠናቀቅ የሁለት ዓመት ጊዜ መዉሰዱን ተናግረዋል።
ቴክኖሎጂው ሲሰራ አካል ጉዳተኞችን እና ሴቶችን ታሳቢ ተደርጎ መሆኑን እንዲሁም የሚሰሩ ማንኛዉም ስራዎች ከእጅ ንኪኪ ነጻ መሆኑን ከምክትል ዲኗ ገለጻ ለመረዳት ችለናል።
የዉበት ሀዋሳ ኢንተርፕራይዝ ማናጀር አቶ አልታየ የቦ በቀላሉ ሊበሰብስ የማይችል ሀይላንድዶችን የመፍጨት የማጠብ ስራዎችን የሚሰራ ቴክኖሎጂ በመሆኑ ይህንን ቴክኖሎጂ በአግባብ በመጠቀም የማህበራቸዉን የዉስጥ ገቢያቸዉን ለማሳደግ ትልቅ አበርክቶ እንዳለዉ ተናግረዋል።
11/04/2026
****** የኮሌጃችን ማህበረስብ በሙሉ*********
እንኳን ለጌታችንና ለመዲኃንታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን! በዓሉን ስናከብር አቅም ያጡና አዛውንቶችን በማስታወስ፤ ጌታችን የእኛ በደል ይቅር ለማለት በመስቀል እርቃኑን ተሰቅሎ ፍቅርንና ይቅርታን እንዳስተማረን እኛም እርስ በእርሳችን ይቅር በመባባል በፍቅሩ ተዋደን አንድ ሆነን ማክበር ይኖርብናል።
በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የጤና እንዲሆንልን እምኛለው።
*****ሀዋሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ********
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ(ገና) በዓል በሰላም
አደረሳችሁ/አደረሰን!!
🌲🌲🌲🌲ታህሳስ 28/2018 ዓ/ም🌲🌲🌲🌲
ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት መታሰቢያ(ገና) በዓል በሰላም
አደረሳችሁ/አደረሰን: በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣የብልጽግና፣የአብሮነትና የመተሳሰብ እንዲሆን የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ መልካሙ በራሳ የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፏል!!!!
🌲🌲🌲🌲🌲ታህሳስ/2018 ዓ/ም🌲🌲🌲🌲
🌲🌲🌲🌲🌲ሀዋሳ ፓሊ ቴክንክ ኮሌጅ🌲🌲🌲
02/11/2025
በሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 2018 ስልጠና ዘመን የገበያ ፍላጎት ቅድሜ ጥናትና Validation እና የኢንድስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ የልምድ ልውውጥ ህደት የመገመበትን Workshop አካሄደ ።
ኮሌጁ በ2018 ሥልጠና ዘመን ገበያው/ ኢንድስትሪው ዬትኛውን ሙያ እና ደረጃ የሠለጠነ የሰው ኃይል ይፈልጋል የሚለውን የጥናት ሪፓርት ባቀረበበት መድረክ
✅የኢንዱስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ አባላት
✅የኢንዱስትሪ ባለቤቶች
✅የሥራና ክህሎት ቢሮ የ2ቱ ዘርፍ ዳይረክተሮይቶች
✅የሀሳ ዩንቨርስቲ የጥናትና ምርምር ምሁራን
✅የኮሌጁ የ2ቱም ዘርፍ ባለሙያዎች
✅የኮሌጁ የየዲፓርትመንት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የውይይት መድረኩን የመሩት የኮሌጅ ም/ዲን እና የሠልጣኝ አሠልጣኝ ልማት ዋና ሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ኢዩኤል ዮኔ እንደ ሀገር የተቀመጡ የሪፎርም አጀንዳዎችን ለማሳካት ኢንድስትሪውን ፍላጎት መነሻ አድርጎ በማሠልጠን የበቃ ዜጋን ለገበያው ለማቅረብ ብቸኛው መንድ የኢንዱስትሪውን የሰው ኃይል ፍላጎት በጥናት መለየት ነው ስሉ አሳባቸውን ገልፀዋል ።
በዚሁ መድረክ የቀረበው ሌላኛው ርዕሰ ጉዳይ የሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቦርድ አባላት የልምድ ልውውጥ ህደትና ግኝቶች ላይ ሲሆን
የኮሌጁ የኢንዱስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ አባላቱ
👉በELSE Addis/Rider textile factory
👉በMNS textile manufacturing company
👉በFederal Tvet Institute/ በተለይም ምን እንደሚመስል ሰፊ ጉብኝትና ከኢንዱስትሪ ባለቤቶች ጋር ጋር በቂ ውይይት ማድረጋቸውን በኮሌጁ IAB ሰብሳቢ አቶ ወሌ አበጋዝ አንስተዋል።
በዕለቱ የኢንዱስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ እና የኮሌጁ አመራሮች ትኩረት ሰጥቶ የተነጋገሩበት ሌላኛውና ዋነኛው ጉዳይ የሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አዲሱ የTextile and Garment _Factory_Autonomous ሆኖ ወይንም በከፊል ነፃ ሆኖ እራሱን ችሎ ለማሠልጠንና ለማምረት እንድሁም አገልግሎት ለመሥጠት ወደ ሥራ እንድገባ አድቫይዘሪ ቦርዱ በልዩ ትኩረት እየሠራ መሆኑንም የኮሌጁ ዲን አቶ መልካሙ በራሣ አንስቷል።
የኮሌጁ ዲን በገለፃው በልምድ ልውውጥ ካየናቸው የTextile Manufacturing ኩባኒያዎች አንፃር ስታይ የቁጥር ብዛት ልዩነቶች ይኑሩ እንጅ የሀዋሳ ፓሊ አዲሱ Training Factory ሁሉንም ለማሠልጠንና ለማምረት ብቁ የሆኑ ዘመኑ የሚፈልገው ትላልቅ ማሽነሪዎች ያሟላና በአሁን ሰዓት ወደ ስራ ለመግባት የምቸግረው የግብት ችግር አለመኖሩንም አረጋግጠዋል ።
በመጨረሻም የኢንድስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ በኮሌጁ ከሌለው ጊዜ በማካፈል ፣ በዕቀት ፣ በሀሳብና በተለያዩ እያሳየ ላለው አብሮነትና ድጋፍ የኮሌጁ ዲን አመሥግነው የዕለቱን ውይይት አጠቃለዋል ።
ሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም
25/10/2025
/Mastercard Foundation መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የተማሪውን የትምህርትና አስፈላጊ ወዎችን ሙሉ በመሸፈን Scholarship_ዕድል ይዞላችሁ መተዋል ።
FAWE መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ከሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር 2017 ዓ.ም ከሲዳማ ክልል ከሁሉም ወረዳዎች የተመለመሉ በርካታ ተማሪዎችን የ Scholarship ዕድል በመስጠት ለተማሪዎች
✅ የቤት ክራይ
✅ የተሟላ የቤት መገልገያ ቁሳቁስ
✅የትምርት ቤት ክፍያ
✅ ለቀለብ የሚሆን ወጪ
✅ የትራንስፖርት ወጪ
✅ የህክምና ወጪ
✅ የተማሪውን ወላጅ ይደገፋል
✅ የትምርት ቁሳቁስ እና ሌሎች ወጪዎችን ሸፍኖ ወይም አሟልቶ እያሠለጠነ የቆየ ሲሆን
ዘንድሮም በ2018 ሥልጠና ዘመን (Phase II) ለ2ኛ ዙር ሠልጣኞችን በተመሣሣይ መልኩ ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቀዋል ፣ በመሆኑም የዕድሉ ተጠቃሚ የሚሆኑ ሠልጣኞች ማሟላት ያለባቸው ዝቅተኛ መስፈርት
1ኛ. በ2016 እና 2017 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በመውሰድ በቴክኒክና ሙያ ሙያ ለደረጃ 3, 4እና 5 የሚያስገባ ውጤት ያላቸው
2ኛ. በክህሎት ዘርፍ ማለትም በሙያ ነክ ስልጠና ዘርፍ የመሠልጠን ፍላጎት ያላቸው።
3ኛ. "STEM" ትምርት በጣም ጎበዚ ሆኖ ግን በኢኮኖሚ ችግር በTVET ገብቶ መሰልጠን የማይችል/ትችል
4ኛ. የአካል ጉዳት ያለባቸውም በዚህ ፕሮጀክት እንድሳተፉ የሚበረታቱ ሲሆን አካል ጉዳተኛ የሆን የአንድ ዓመት ጭማር ተደርጎ በ2015 የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ የዛን ዓመት የደረጃ 3,4እና5 ያላቸው የዕድሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
5ኛ. የዕድሉ ተጠቃሚ 80% ሴቶች ሲሆኑ 20% ወንዶች ይሆናሉ ።
በመሆኑም ፕሮጀክቱ ዜጎችን ብዙ መንገድ ተጠቃሚ የሚያደርግ ለክልላችን ታላቅ ዕድል ይዞ የመጣ በመሆኑ ተማሪዎች ከፊታችን 17-21 አርብ ድረስ ብቻ የሚሆን ሲሆን በሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር -2 ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ ስንል በትህትና እናሳውቃለን ።
:-
1. በ2017 እና በ2016 ያጠናቀቃችሁ የ12 ክፍል ውጤት
2. የ10ኛ እና የ11ኛ ክፍል Transcript
3. የ 8 ክፍል ካርድ
4. አንድ 3*4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ
5. ለውድድሩ ይጠቅመኛል የሚትሉትን አስፈላጊ ማስረጃዎችና ሰነዶችን ኮፕ በመያዝ በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ ።
ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም
27/07/2025
Anga tidhitinonna buqqeensa bowirsidhino qansoota kalaqate Tekiniketenna Ogummate qajeelshi kolleejja qeechi luphiimaho. Dukko Hageretsiyoon Abbebe.
==================
Sidaamu Qoqqowi Loosunna Dandoote Biiro Hawaasi Pooli Tekinikete Kolleejje 26kki Yannara Deerra 2, deerra 4nninna deerra 5ni Qajeelsiissino 600 Qajeelaano Maassiissu.
Maassote aana leeltinoti Sidaamu qoqqowi loosunna dandoote biiro sooreette dukko Hageretsiyoon Abbebeti, Anga tidhitinonna buqqeensa bowirsidhino qansoota kalaqate Tekiniketenna Ogummate qajeelshi kolleejja qeechi luphiima ikkasi xawissino.
Sooreette leddeno konni handaarinni qajeeltanno qansooti dandootenni ikkadda ikkitinohura uminsa looso kalaqidhannorenna gobbateno sae kalqete dandootenni heewisamaano ikkitannore ikkansa qummi assitino.
Konninni handaaraho illacha uyine loonsoonnihunni gumaammu qansooti kalaqama dandiitino yitinoti sooreette Kolleejje qoqqowohono ikko gobbate deerrinni albisa ikkasenni qajeelsite ogimmatenni haammata qansoota gobbatenna kalqete deerrinni heewisame horaameeyye ikkanno gede assitinota kulte techo maassamaano afidhino egenno loosu widira soorratenni umonsa soorritanno gede xawisse hawalle hagiidhitini yitino.
Kolleejjennihu qaru diine kalaa Melkaamu Baraasihu isiwidoonni, kolleejje sai 27 diro islancho qajeelsha aatenni ogimmatenna dandootenni ikkadda qansoota kalaqqanni nootanna gobbateno ikko soojjaati Afirikira islancho qajeelsha aatenni heewisamaancho ikkase xawisino.
Techo 600 ikkitanno qajeelaano addi addi ogimmanni deerra 2, deerra 4nninna deera 5ni qajeeltinori maassamansa huwachishino.
Taxeha Maassote amanyoote baxxannoha assannosihu kolleejje ISO21:2018EOMS Tophiyunni umikkita ikkite serifikeetete baraarancho ikkasenna rosu finote kaarti soorrami kawa umikki yannara 12kki kifile rosse guddino qajeelaano adhite qajeelsite maasiisansa kolleeje baxxinoha aassanoseta kalaa Melkaamu lede xawisino.
እጃቸውን የተፊታቱና ብሩህ አዕምሮ ያለቸውን ዘጎች ለማፍራት የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ሚና ከፍተኛ ነው ። ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ
ሀዋሳ ፖ/ቴ/ኮ
22/07/2025
.
:-
==============================
የሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዬ ሙያ ዘርፍ ከደረጃ 2-5 ያሰለጠናቸውን ከ600 በላይ ሠልጣኞችን ሐምሌ 20/2017ዓ.ም በልዪ ድምቀት ያስመርቃል ።
ይህ ታላቅ የምረቃ ፕሮግራም የፊታችን እሁድ ከጧቱ 2:00 ጀምሮ ስለሚካሄድ ውድ ተጋባዥ እንግዶቻችን፣ የተከበራችሁ ሠልጣኞቻችን ፣ የተከበራችሁ የተመራቂ ሠልጣኝ ወላጆች እንድሁም አጠቃላይ የኮሌጃችን ማህበረሰቦች በሰዓቱ በሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጥቅር ግቢ ተገኝታችሁ የምረቃ ፕሮግራም ተካፋይ እንድትሆኑ እንጋብዝዎታለን ።
እንኳን አደረሳችሁ! እንኳን ደስ አላችሁ!
ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ!
ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም
ሀዋሳ ሲዳማ ኢትዮጵያ
03/05/2025
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሀዋሳ ፖሊ የቴክኒክ ኮሌጅን ጎበኙ
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ዜጎች መንግስት ባመቻቸላቸው ዕድል አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅመው የመፍጠርና ማምረት ክህሎቶችን እያጎለበቱ መሆኑን በቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ባደረጉት ምልከታ አረጋግጠዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስልጠናና ማምረቻ ማዕከልን ጨምሮ ሌሎች ማዕከላትን የጎበኙ ሲሆን በክልሉ ያሉ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በቂ አቅም አጎልብተው ከራሳቸው አልፈው ለሀገር የሚተርፉ አሰልጣኞችንና ሠልጣኞችን በማፍራት ውጤታማ እንዲሆኑ ከዚህ በፊት በተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።
በቅርቡ በዓለም ባንክ የተገነባው በሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስር የሚተዳደር የጨርቃጨርቅና አልባሳት ማምረቻ ፋብሪካና የሥልጠና ማዕከል የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆቻችን ውጤቶች አንዱ ማሳያ መሆኑን ገልጸዉ፤ ይህ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ቀጠናዊ ትስስር ለማጠናከርም ጉልህ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
የክልሉ መንግስት የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች ሙያና ክህሎትን ለማሳደግ እንዲሁም ለስልጠና አስፈላጊ የሆኑ ማሽኖችን ከሟሟላት አኳያ በትኩረት መስራቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ባለፉት ጊዜያት በኢትዮጵያና በአፍሪካ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን መቻሉ የሚያበረታታን ነው ብለዋል።
አክለውም ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከሆቴልና ቱሪዝም ሙያ በተጨማሪ በተለያዩ ሙያዎች በርካቶችን አሰልጥኖ ብቁ በማድረግ በተለያዩ ተቋማት ተቀጥረው ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማቅረብ እየሰራ የሚገኘውን ስራ አድንቀው በሚቀጥሉት ጊዜያት በሀገር ደረጃ ተወዳዳሪ አሰልጣኞች እና ሰልጣኞች በማፍራት የስራ ትስስርም ለመፍጠር ሰፊ ርብርብ ይደረጋል ብለዋል።
እንደ ክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ ኮሌጆቹ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ሥራዎችን እየሠሩ እንደሚገኙ አሳስበው ዜጎች ጠንካራ ሥልጠና ወስደው በውጪ ሀገራት ተወዳዳሪ ሆነው የሥራ ዕድል አግኝተው እንዲሰሩ በተደረገው ርብርብ መደሰታቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም የሥራነና ክህሎት ኢንተርፕራይዞች ቢሮ እየሠራ ላለው ሥራ ምስጋና የሚቸረው መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።
ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ዓላማችን ብቁ ተወዳዳሪ ዜጎችን ማፍራት ነው !
ISO21001:2018 Certified
29/04/2025
/አለን 🎆
የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በሲዳማ ክልል ደረጃ በ2017 ሥልጠና ዘመን በመንግስት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆችና በኢንዱስትሪያል ኮሌጆች መካከል በ2 ዓመት አንዴ የሚካሄደውን የቴክኖሎጂ ፣ የክህሎና ተግባራዊ ጥናት ውድድር በአጠቃላይ 29 ሜዳሊያወችን በማሸነፍ አንደኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀ።
ባለፋት ቀናቶች በክልሉ ሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ አዘጋጅነት በሠልጣኝ ፣ በአሠልጣኝ እና በኢንተርፕራይዞች ደረጃ ሲያካድ የነበረው የቴክኖሎጂ፣ የክህሎትና የተግባራዊ ጥናት ውድድር ተጠናቋል ።
በክልሉ ደረጃ በ5 ፖሊ ቴክኒክና በ6 ኢንዱስትሪያ ኮሌጆች በአጠቃላይ በ11 የመንግስት ተቋማት መካከል ለ4 ተከታታይ ቀናት ውድድር የተደረገ ሲሆን
በውድድሩም የሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአጠቅላላ ውድድር አይነት
ወርቅ🥇=16
ብር 🥈=7
ነሃስ 🥉=6
በድምሩ =29🥇🥈🥉🏆 ሜዳሊያዎችን በበላይነት በማሸነፍ በክልሉ ውድድር 1ኛ በመሆን አጠናቋል ።
ድሉን አስመልክተው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፋት የኮሌጁ ዲን አቶ መልካሙ በራሳ አጠቃላይ ይህ ውጤት እንድመጣ ክብርት የክልሉ ሥራ ክህሎት ቢሮ ኃላፊዋ ፣ ክቡር የዘርፉ ኃላፊ እና ክቡራን የቢሮ ማናጅመንት አባላት፣ የኮሌጁ ማነጅመንት ፣ የድፓርትመንት ተጠሪዎች ፣ የዘርፉ ኤክስፔርቶች እንድሁም ተወዳዳሪዎቻችን፣ ሁሉም ሠልጣኞችና አጠቃላይ ማህበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን ስል መልዕክቱን አስተላልፏል ።
ውጤቱ የመጣው በግባር ቀደም አሠልጣኞች በምሰጠው ጥራት ያለው ስልጠና መነሻ መሆኑን ጠቅሶ አሠልጣኝ መምህራኖችን በተለዬ ሁኔታ እንኳን ደስ አላችሁ ይህ የእናንተ የልፋታችሁ ውጤት ነው ስል ልዩ ምስጋናውን አቅርበዋል።
በመቀጠልም ለፈደራል ውድድር ከኮኮሌጁ የሲዳማን ክልል በመወከል 1ኛ የወጡ 16 ተወዳዳሪዎች የሚቀርቡ ስለሆነ ክልላችንን አሸናፊ ለማድረግ እንድሁም የኮሌጃችንን ከፍታ ለማረጋገጥ የተሻሉ ስራወችን በመስራትና ተወዳዳሪዎቻችንን በማበረታት የተለመደውን ድል እንድናስመዘግብ ድጋፋችሁ እንቅጠናከር ስል ለአሠልጣኞች መልዕክቱን አስተላልፏል ።
በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን ፥
ድሉ ይቀጥላል !
ዓላማችን ብቁ ተወዳዳሪ ዜጋን ማፍራት ነው!!
የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ISO21001:2018 Certified
ሚያዝያ 21/2017 ዓ.ም
24/04/2025
እንኳን ደስ አላችሁ
የኢንስቲትዩቱ ሀዋሳ ካምፓስ ራሱን ችሎ ISO 900፡2015 የጥራት ሽልማት ተሸላሚ ሆነ።
ቀደም ሲል የደቡብ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በመባል ይታወቅ የነበረውና ከ2016 በጀት ዓመት ጀምሮ ተጠሪነቱ ለኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የሆነው ተቋም በሰራው የጥራት ሥራ አመራር መሰረት ተገቢውን የኦዲት ሂደት አልፎ ተሻላሚ ሆኗል።
የኢንስቲትዩታችን ማኔጅመንት ለካምፓሱ የሥራ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞችና በሂደቱ አስተዋፆኦ ለነበራቸው ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋናው ግቢ በ2016 ዓ/ም መሰል ሽልማት መሸለሙ የሚታወስ ነው።
ዌብሳይት http://www.ftveti.edu.et/
ዩቲዩብ http://www.youtube.com/fdretvtinstitute
ፌስቡክ https://www.facebook.com/TVTI.EDU.ET
ቴሌግራም https://t.me/fdretvtinstitute
ቲክቶክ www.tiktok.com/
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the university
Telephone
Website
Address
Hawassa
Awassa