Master Computer Center

Master Computer Center

Share

The Biggest Online market That Deliver Quality Products without Any Transportation payments. The New page of Our Agency.

11/01/2022

አስደሳች ዜና
ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲሁም ፈተና ወስዳቹ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ለመሄድ ዝግጅት ላይ የምትገኙ ተማሪዎች ማስተር የኮምፒውተር ማሰልጠኛ ተቋም ለናንተ በአይነቱ ለየት ያለ ስልጠና አዘጋጅተንሎታል።
ይህ ስልጠናም University Survival Training የሚባል ሲሆን ወደ ዩኒቨርሲቲ ከመሄዶ በፊት ማዳበር ያለባቹን ችሎታዎች እንዲሁም ማወቅ ያለባቹን ነገሮች በአጭር ጊዜ ስልጠና ልንሰጥ ምዝገባ ጀምረናል።
የምንሰጣቸው ስልጠናዎች
1. ዩኒቨርሲቲ ለይፍን የተመለከቱ ምክሮች እና ታሪኮች
2. የዩኒቨርስቲ ላብራቶሪ ሪፖርቶች አፃፃፍ እና ህግጋቶች
3. የዩኒቨርሲቲ ሪሰርች እና ፕሮፖዛል አፃፃፍ እና ህግጋቶች
4. ከዩኒቨርሲቲ ሊያስባርሩ የሚችሉ ጥፍቶች እና የትምሀርት ዉጤቶች
5. ከዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ማዕረግ ለመመረቅ የሚያግዙ ነጥቦች።

11/01/2022

ምዝገባ ጀምረናል፡፡

አድራሻ ፦ ከበቆጂ ከተማ አስተዳደር ቢሮ ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ።
ስልክ ፦ 0925281976 /0955255999/ 0942426040

11/02/2021

Standard : 12th grade national exams will be held on March 8, 2021. The Ministry of Education announced that the 12th grade national examination will be given on March 8, 2020. He also said that digital ID will be distributed from March 1 to 3, according to the minister of education, Getahun Mekuriya (PhD). Orientation will be given on March 5, and the exams will be held from March 8 to 11. However, the exams that were said to be given online are going to be given on paper because tablets could not be imported to the country. The ministry of education has officially apologized for the delay.

28/12/2020

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅት !

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ገረመው ሁሉቃ ከኢ.ፒ.ድ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሀገር አቀፉን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በተመለከተ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተዋል ፦

• በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኮሮና ምክንያት ፈተና ያልወሰዱ በአጠቃላይ 450 ሺህ የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዘንድሮ ፈተና ይወስዳሉ።

• ለፈተናው ብቻ የሚውል ቪሳት ሌሎች አጋዥ መሳሪያዎች ተገዝተው 1 ሺህ 184 ፈተና ጣቢያዎች ተቋቁመዋል።

• ለ270 ቴክኒሻኖች ስልጠና ተሰጥቷል።

• ለፈታኝ መምህራን 12ሺህ ላፕቶፖች ተዘጋጀቷል።

• 2 ትልልቅ ሰርቨሮችም በተገቢ ቦታ ላይ በመትከል ተማሪዎች እንዲለማመዱ ከ2008 እስከ 2011 ዓ.ም የተሰጡት የ12ኛ ክፍል ፈተናዎችም እዚያው ላይ ተጭነዋል።

• በትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ አማካኝነት በእርዳታ የተገኙ 450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታኅሣሥ 30 ቀን 2013 ዓ/ም ወደ አገር ውስጥ ገብተው ለፈተናው ይውላሉ።

• ፈተናውም ጥር 30 የሚጠናቀቅ ይሆናል።

Education Send a message to learn more

28/12/2020

በአ/አ የ8ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ሆነ።

በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ዛሬ አስታውቋል።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዘግይቶ በ 2013 ዓ/ም በ156 መፈተኛ ጣቢያዎች ለ71,476 ተማሪዎች የተሰጠዉ የ2012 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

ለፈተናው ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 80 % ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል መዛወራቸውን የአ/አ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

የክልላዊ ፈተናዉ ውጤትም ለ10ሩም ክፍለ ከተማዎች ዛሬ ተሰራጭቷል።

ከነገ ማክሰኞ ጀምሮ ተማሪዎች ውጤታቸውን በየትምህርት ቤቶቻችው መመልከት ይችላሉ ተብሏል።

17/12/2020
04/12/2020

University
ከታች በዝርዝሩ ለተገለፃችሁ ለድሬዳዋ
ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ
።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
- የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የሆናችሁ
- የህግ ኮሌጅ አራተኛ ዓመት ተማሪዎች
- የIOT አራተኛ አመት Internship
ተማሪዎች (Civil, Mechanical,
Surveying, Textile and Architecture
Engineering)
- የህክምና (PC-1, C-1, and C-2) ተማሪዎች
ዩኒቨርሲቲያችን በ2013 ዓ.ም የመልሶ ቅበላ
ምዝገባ ይፋ ባደረገው መረሃ ግብር መሰረት
ምዝገባው ታህሳስ 1 እና 2, 2013ዓ.ም
መሆኑን አውቃችሁ በዩኒቨርሲቲው እንድትገኙ
እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
ሁሉም ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ
የCovid-19 መከላከያ ግብአቶችን
እንድታሟሉ እናሳስባለን፡፡
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ
ቅበላ የአካዳሚክ እና አልሙኒ ዳይሬክቶሬት
ዳይሬክቶሬት
===============
=======================
Dire Dawa University
Undergraduate Students Call
።።።።።።፡።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።
To all the students of Dire Dawa
University described below
- 2012 Prospective graduate
student
- Fourth year law students
- Fourth Year IOT Internship
Students (Civil, Mechanical,
Surveying, Textile and Architecture
Engineering)Medical students (PC-1,
C-1, and C-2)
We would like to inform you that
your Registration and reporting
date will be on December 10 and
11, 2020, in accordance with the
program announced by Dire-Dawa
university.
Note:
We recommend that all students
complete the Covid-19 protective
equipment when they arrive at the
University.
Dire-Dawa University
Enrollment, Academic Record and
Alumni Directorate

Photos from Master Computer Center's post 02/12/2020

ለ2012 ዕጩ ተመራቂ ለነበራችሁ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ
ተማሪዎች!
በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ስጋት ምክንያት የተቋረጠው የ2012
ዓ.ም ትምህርት እንዲጀመር መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ
መሰረት በዩኒቨርሲቲያችን በ2012 ዓ.ም ትመረቁ የነበራችሁ
ተማሪዎች ብቻ ከህዳር 29 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም
ድረስ ወደ ዩኒቨርሲቲያችሁ እንድትገቡ ጥሪ እናቀርባለን።
የተመደባችሁበትን የመኝታ ክፍል ባላችሁበት ሆናችሁ
ከዩኒቨርሲቲው ድረ ገፅ http://dormitoryps.hara
maya.edu.et/DormSearch.aspx ወይም
በቴሌግራም@ HU_dorm_placement_bot ሊንክ ማየት
ትችላላችሁ።
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ
ህዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም

01/12/2020

University Students Union - HUSU
BREAKING New's
Sadaasa 29_Muddee 01 guyyaa barattootni
GC yuunibbarsiti Haromaya moraa seenanu
ta'uun ibsaame.
ህዳር 29_ታህሳስ 01 የሐረማያ የዩኒቨርስቲ ተመራቂ
ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ሆኖ ተወስኗል።
December 08-10 G.C is the admission date for
Haremaya University Graduation Students.

29/11/2020

(Fana Broadcasting Corporate
S.C.)
በ2012 ዓ.ም ተመራቂ ለነበሩ ተማሪዎች ከነገ
ጀምሮ ጥሪ ይደረጋል
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)
የተቋረጠዉን መደበኛ የገጽ-ለገጽ ትምህርትና
ሥልጠናም ኮቪዲ-19ን በመከላከልን
የሚከናወንበት ወቅት ላይ መደርሱንም
የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ ለፋና በላከው መግለጫ ÷ከቅርብ
ዓመታት ወዲህ በተለይም ዩኒቨርሲቲዎችን
በየጊዜዉ የዘርና የኃይማኖት ግጭት
የሚቀሰቀስባቸዉ፣ የተማሪዎቻችን ነፍስ
የሚጠፋባቸዉ፣ ልዩ ልዩ ማህበራዊ ጉዳቶች
የሚከሰትባቸዉ እና ነጻና ገለልተኛ መሆን
የሚገባቸዉ ተቋሞች የፖሊቲካዊ ይዘት ያላቸዉ
ጣልቃ ገቢነት የበዛባቸዉ እንዲሆኑና
የዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነታቸዉ ላይ ጫና
የበዛባቸዉ እንዲሆኑ መደረጉን አስታውሷል፡፡
እንዲሁም ሕገ-ወጡ የጁንታ ቡድን ባለፉት
ዓመታት ዩኒቨርሲቲዎችን በጎጥ ከፋፍሎ፤ ህብረ-
ብሔራዊነትና ብዝሃነት እንዳይጎለብት፣
ተማሪዎች እና መምህራን በአከባቢ፤ በዘርና
በኃይማኖት እንዲታጠሩ፤ ከህብረት ይልቅ
መከፋፈሉ እንዲሰፋ በማድረግ ለሁከትና
ለግጭት ብሎም የሰዉ ነፍስ እንዲጠፋ ሰፊ
ሥራ ሰርቷል ብሏል፡፡
የተማሪ ወላጆችም ከራሱ አከባቢ ዉጪ ባሉ
ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪ ምደባ ሲካሄድ
ስጋታቸዉን በተለያዩ መንገድ ሲገልጹ ቆይተዋል
ብሏል ሚኒስቴሩ በመግለጫው፡፡
ይህ የሕገ-ወጡ ጁንታ ተልዕኮና ተግባራት
ዳግም በዩኒቨርሲቲዎች ብሎም በአገራችን
እንዳይከሰቱ ሕግ የማስከበር እርምጃ በጀግናዉ
መከላከያ ሰራዊት እና በጸጥታ መዋቅሮች
እንዲሁም በሕዝባችን ትብብር መወሰዱ ከልብ
አስደስቶናል ያለው ሚኒስቴሩ ን ለዚህም
እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል፡፡
ይህን ተከትሎም የተቋረጠዉን መደበኛ የገጽ-
ለገጽ ትምህርትና ሥልጠና ኮቪዲ-19ን
እየተከላከልን የምናከናወንበትና መንግሥት
ለሚያቀርበዉ የሰብዓዊ ድጋፍ ጥሪ
እንደጀመርነዉ ከልማት ሥራችን ጎን ለጎን
አጠናክረን የምንቀጥልበት ወቅት ላይ ደርሰናል
ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡
በዚህም ቅድሚያ ተማራቂ ተማሪዎችን
በመቀበል የተማዎችን ጥሪ ከህዳር 21 ቀን
2013 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሄድ እና ከአንድ
ሳምንት በኋላ ደግሞ ሌሎች ቀሪ ተማሪዎች
እንዲገቡ እንደሚደረግ ገልጿል፡፡
በመሆኑም ሚኒስቴሩ የ2013 ትምህርትና
ሥልጠና ዘመን የተሳካ እንዲሆን የትምህርት
መህበረሰቡ የተለመደዉን ድጋፍ እንዲያደርግ
ጥሪ አቅርቧል፡፡

Want your university to be the top-listed University in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Bole
Addis Ababa