Cyberigna
ይህ ገጽ ዜጎች ራሳቸዉንና ሃገራቸዉን ከማንኛዉም የሳይበር ጥቃት ሊከላከሉ እንዲችሉ የሚያስችል መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነዉ፡፡
07/10/2022
አለም አቀፍ የሳይበር ወር እና ታሪካዊ ዳራዉ
አለም አቀፍ የሳይበር ወር በወርሃ ጥቅምት በአለምአቀፍ ደረጃ ስለ ሳይበር ደህንነት ግንዛቤን ከፍ ለማድረግ ታስቦ የሚካሄድ የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ መርሃ ግብር ነዉ፡፡
የሳይበር ደህንነት ወር ለመጀመሪያ ጊዜ በዩናይትድ ስቴትስ በ2004 እ.ኤ.አ የዜጎችን የሳይበር እዉቀት ለመጨመርና ንቃተ ህሊናቸዉን ከፍ በማድረግ ደህንነቱ የተጠበቀ የሳይበር አጠቃቀምን እንዲተገብሩ ታስቦ መከበር ጀመረ፡፡
ቀስ በቀስ በአዉሮፓ እና ሌሎች የአለም ሀገራት ተቀባይነቱ እየጨመረ መጥቶ፤ ከዩናይትድ ስቴትስ ቀጥሎ በአዉሮፓ ሀገራት ከ2012 እ.ኤ.አ. ጀምሮ መከበር ጀምሯል፡፡
የተለያዩ ሀገራት ይህን ፕሮግራም ሙሉ ወሩን አልያም ከወሩ ሳምንትን መርጠዉ እንደሚያከብሩት መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡
አዉስትራሊያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለምሳሌ ጋና፣ሳዉዝ አፍሪካ፣ ሞሪሽየስ፣ ኢስዋቲኒ፣ጋምቢያና ሩዋንዳን ጨምሮ ሙሉ ወሩን ባይሆንም ከጥቅምት ወር አንዱን ሳምንት መርጠዉ እንደሚያከብሩት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ በ2012 ዓ/ም የመጀመሪያዉን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በሳምንት ደረጃ በጥቅምት ወር የመጨረሻው ሳምንት “ትኩረት ለሳይበር ደህንነት” በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የሳይበር ደህንነት ንቃተ ህሊና መርሃ ግብሮችን በማካሄድ ማክበር ጀምራለች፡፡
በ2014 ዓ.ም ደግሞ “የሳይበር ደህንነት የጋራ ሃላፊነት፤ እንወቅ፤ እንጠንቀቅ” በሚል መሪ ቃል 2ኛዉን የሳይበር ደህንነት ንቅናቄ በወር ደረጃ ከ ጥቅምት 1 ቀን እስከ 30 በተሳካ ሁኔታ ለአንድ ወር ያክል በኮንፈረንስ፣ በስልጠና ብሎም በተለያዩ የሚዲያ አውታረ መረቦች ንቅናቄዎች ተካሂደዉ ነበር፡፡
3ተኛዉ የሳይበር ወርም እንዲሁ በጥቅምት 2015 አ.ም በተሳካ ሁኔታ ይከበራል፤ የወሩ አላማወች እና ዝርዝር አላማዎችም የሚከተሉት ናቸዉ
የወሩ ግብ
የሳይበር ማህበረሰቡንና የተቋማትን የሳይበር ደህንነት ንቃተ-ህሊና ለማጎልበት የሚያስችል ንቅናቄን በማካሄድ የሃገራችንን የብሄራዊ ጥቅሞችን የማስጠበቅ ተልዕኮን ማገዝ ነዉ፡፡
የወሩ ዝርዝር አላማዎች
• የተቋማትን የሳይበር ደህንነት ጥቃት ተጋላጭነት ለማሻሻል
• የግሉ ዘርፍ የሳይበር ደህንነትን በማስጠበቅ የሚኖረዉን አስተዋዕፆ ማሳደግ
• የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ የሚያስችል የሰዉ ሃብት ልማት ላይ ንቅናቄ መፍጠር ነዉ፡፡
• የማህበረሰቡን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ የሚያሳድግ ንቅናቄ መፍጠር
22/09/2022
የበዓል ሰሞን የሚደርሱ ማጭበርበሮች ወይም ስጋቶች ምን ምን ሊሆኑ ይችላሉ
የገንዘብ ስርቆት፣ የማንነት ስርቆት እና የማጭበርበር ተግባራት
ማህበራዊ ምህንድስና እና ክፍያ ማጭበርበር
የስጦታ ካርድ ማጭበርበሮች/Gift Card Scams
የውሸት ማህበራዊ ሚዲያ ማስተዋወቂያዎች/Fake Social Media Promotions
የውሸት በጎ አድራጎት ድርጅቶች/የበጎ አድራጎት ማጭበርበሮች/Charity Scams
የጥቅል ማቅረቢያ ማጭበርበሮች/Package Delivery Scams
Vishing scams
ሊደረጉ የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች
ማንኛዉንም አይነት ሊንክ ከመክፈቶ በፊት ያስቡ/ከማይታወቁ ላኪዎች በኢሜይሎች ውስጥ አገናኞችን ወይም ዓባሪዎችን አይክፈቱ አታድርጉ።ብዙ አጭበርባሪዎች በመስመር ላይ ተደብቀው በመኖራቸው፣ በዚህ የበዓል ሰሞን የግል መረጃ ከሳይበር ወንጀለኞች ለመጠበቅ የደህንነት ግንዛቤ ቁልፍ ነው። አጥቂዎች የግል መረጃን ለመስረቅ እና ለማታለል ብዙ ጊዜ የኤስኤምኤስ መልዕክቶችን ከአስጋሪ ድህረ ገፆች ጋር ይልካሉ። አንድ ሰው የኤስኤምኤስ መልእክት በውስጡ አገናኝ ከላከለት አይክፈቱት
ደህንነቱ የተጠበቀ አውታረ መረቦችን ይጠቀሙ
ወደ መልዕክት መቀበያ ሳጥኖዎት የሚላክሎትን አጠራጣሪ አገናኞች ፣ አባሪዎች እና ሌሎች መልእክቶችን ከመክፈትዎ በፊት በጥንቃቄ ያጢኑ፡፡
በበዓላት ወቅት የመረጃ ጠላፊዎች ኣጥፊ ተልእኮ ያላቸዉ ሰነዶችን፣ ደረሰኝ፣ ስጦታ፣ ዝመና ወይም የትዕዛዝ መረጋገጫ በማስመሰል ሊልክልዎት ይችላሉ፡ከቻሉ ሁል ጊዜ በክሬዲት ወይም በዴቢት ካርድ ይክፈሉ፣ እንደ ሸማች ተጨማሪ ጥበቃ ይሰጥዎታል።
በኢ-ሜይል ለሚላክልዎት ቅጽ ወይም አገናኝ የይለፍ-ቃልዎን ወይም የፋይናንስ መረጃዎን አያስገቡ፡፡
ስጦታ ሲቀበሉም ሆነ ሲሰጡ ጥንቃቄ ያድርጉ ፤ በዚህ በዓል ቴክኖሎጂ ነክ ስጦታ እየተቀበሉ ወይም እየሰጡ ከሆነ የሚጠቀሙበት ቁስ የዘመነና የቅርብ ጊዜ ሶፍትዌር ያለው መሆኑን ያረጋግጡ
ጊዜያቸው ያለፈባቸው ሶፍትዌሮች ተጋላጭነቶችን የያዙ ሊሆኑ ይችላሉ ፤ ያዘምኑ።
ያገለገለ ቁስ እየተቀበሉ ወይም እየሰጡ ከሆነ ከመስጠትዎ ወይም መጠቀም ከመጀመርዎ በፊት መሳሪያውን ወደ መጀመሪያ የፋብሪካ ምርት ሥርዓት መመለስዎን ያረጋግጡ፡፡
የበይነ መረብ ጋር የተቆራኙ ቁሶችን ደህንነት ለመጠበቅ የሳይበር ደህንነት ማስጠበቂያ እርምጃዎችን ይውሰዱ፡፡
ከበይነ-መረብ ጋር የተቆራኙ ቁሶች ደካማ የሚባል የደህንነት ጥበቃ ሪከርድ ያላቸው በመሆኑ የቁሶችን ደህንነት በአግባቡ አለማስጠበቅ ለአጥፊዎች ይበልጥ ሥራቸውን ቀላል እያደረጉላቸው መሆኑን አይዘንጉ።
22/07/2022
ባለብዙ ደረጃ ማረጋገጫ (multifactor Authentication)
ባለብዙ ደረጃ ማረጋገጫ ማለት ምን ማለት ነው?
ባለብዙ ደረጃ ማረጋገጫ ማለት እንደ አፕሊኬሽን፣ የመስመር ላይ መለያ ወይም ቪፒኤን የመሳሰሉ መገልገያዎችን ለማግኘት ተጠቃሚው ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የማረጋገጫ ሁኔታዎችን እንዲያቀርብ የሚፈልግ የማረጋገጫ ዘዴ ነው።
ባለብዙ-ደረጃ ማረጋገጫ የጠንካራ የማንነት እና ተደራሽነት አስተዳደር ፖሊሲ ዋና አካል ነው። የመጠቀሚያ ስም እና የይለፍ ቃል ብቻ ከመጠየቅ ይልቅ ባለብዙ ደረጃ ማረጋገጥ አንድ ወይም ተጨማሪ የማረጋገጫ ሁኔታዎችን ይፈልጋል፣ ይህም የተሳካ የሳይበር ጥቃት እድልን ይቀንሳል።
ባለብዙ ደረጃ ማረጋገጫ አንድ መለያ ወይም ስርዓት ለመድረስ ከአንድ በላይ መታወቂያ የሚፈልግ የደህንነት መለኪያ ነው ተጠቃሚው መዳረሻ ከመሰጠቱ በፊት ማን ነው የሚሉትን ለማረጋገጥ ከአንድ በላይ ማስረጃዎችን የሚፈልግ ተጨማሪ የደህንነት ሽፋን ነው። የባለብዙ ደረጃ ማረጋገጫን ማከል መለያዎችን ከጠላፊዎች ለመጠበቅ ይረዳል።
የባለብዙ ደረጃ ማረጋገጫ ዋና ዋና ጥቅሞች
የባለብዙ ደረጃ ማረጋገጫ ከሁለት-ደረጃ ማረጋገጫ የበለጠ የደህንነት ንብርብሮችን ይሰጣል።
የተጠቃሚዎችን ማንነት ይበልጥ ያረጋግጣል።
የቁጥጥር ደንቦችን በተሻለ ያሟላል።
ከቀላል አተገባበር ጋር ይመጣል።
ነጠላ መግቢያ (Single sign-on) መፍትሄዎችን ያሟላል።
በርቀትም ቢሆን የሚቀጥለውን ደረጃ ደህንነትን ይጨምራል።
ውጤታማ የሳይበር ደህንነት መፍትሄ ነው።
የባለብዙ ደረጃ ማረጋገጫን ለመተግበር ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸው የማረጋገጫን ዓይነቶች በርካታ ሊሆኑ ይችላሉ ለምሳሌ፦
የኤስኤምኤስ ማረጋገጫ መልክት
የኢሜል ማረጋገጫ መልክት
የሶፍትዌር ማረጋገጫ መልክት
የሃርድዌር ማረጋገጫ መልክት
የስልክ ጥሪ ማረጋገጫ
የባዮሜትሪክ ማረጋገጫ
የደህንነት ጥያቄዎች ማረጋገጫ
በዋናነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
23/06/2022
የትሮጃን ጥቃት
ክፍል 2
o ላለመጠቃት ምን ማድረግ ይገባል
የትሮጃኖች ጥቃት ሰለባ ላለመሆን
• ካልታወቀ ላኪ የሚመጣ ማንኛውንም ከመልዕክቱ ጋር የተያያዘ ፋይል ከመክፈት መቆጠብ
• የማያስፈልጉ ፖርቶችን መዝጋት
• በፈጣን መልዕክት መላላኪያ የሚላኩ መተግበሪያዎችን ከመቀበል መቆጠብ
• ነባሪና የተለመዱ የመተግበሪያዎችን አወቃቀር ማስተካከል፣ ማረምና ደህንነታቸውን ማጠንከር
• በውስጥ ኔትዎርክ ውስጥ የሚኖር ማንኛውንም ግንኙነት በጠንካራ የምስጠራ ዘዴዎች በመጠቀም ማጣንከር እና ትራፊኩን ማመስጠር
• ታማኝ ካልሆኑ የሶፍትዌር ማከማቻ ምንጮች(በተለይ እንደ ቶረንት) አለማወረድና አለመጫን
• ለመተግበሪያዎቹና ለኦፐሬትንግ ሲስተሙ የደህንነት ዝመናዎችንና እድሳቶችን መጫን
• የዳታ ማስቀመጫና መላላክያ ቁሶችን (ለምሳሌ እንደ ፍላሽ) በጸረ ቫይረስ ሶፍትዌር ማስፈተሽ
• የኦፐሬትንግ ሲስተሙን ሙሉ ፈቃድ መገደብ በተለይም ተንኮል አዘል መተግበሪያዎች እንዳይጫኑ
• ኦፐሬትንግ ሲስተሙን መሰረት ያደረገ ጸረ ቫይረስ፣ ፋየርዎልና የጥቃት መለያ መፍትሄዎችን ተግባራዊ ማድረግ
o ከተጠቃን ምን ማድረግ አለብን
በተለያየ መንገድ ተጠቃሚዎች በትሮጃን ተንኮል አዘል መተግበሪያዎች ሊጠቁ ይችላሉ። በጥቃት ወቅትም ፋይል ወይም ዳታ ሳይጠፋ ወይም ሳይበላሽ መመለs የሚቻልባቸው ዘዴዎች ውስጥ/
• የዘመነ አንቲ ቫይረስ ወይም ጸረ ተንኮል አዘል መተግበሪያን በመጫን ሙሉ ኦፐሬቲንግ ሲስተሙን ማሰስና ትሮጃኖችን ማጽዳት
• ሲስተሙን ለጊዜው ከኢንተርኔት ጋር ያለውን ግንኙነት ማቋረጥ
• ለየት ያሉና የማይታወቅ መተግበሪያዎችን ማስወገድ
• ከአቅም በላይ ከሆነ ደግሞ ወደ ኮምፒውተር የደህንነት ባለሙያዎች መውሰድ
21/06/2022
የትሮጃን ጥቃት
ክፍል 1
ትሮጃን ምንድነዉ
ትሮጃኖች በኤሚይል ወይም በሌሎች ዘዴዎች ማለትም በማህበራዊ የትስስር ገጾች ወይም ታማኝ ካልሆኑ የመተግበሪያ ክምችቶች በተጠቃሚዎች የጥንቃቄ ጉድለትና የእውቀት ክፍተት ምክንያት የሚወርዱና የሚጫኑ ሶፍትዌሮች ናቸው። ትሮጃኖች ትክክለኛ ወይም ህጋዊ ሶፍትዌር የሚመስሉ ግን ሌላ ተንኮል አዘል ስራዎችን ወይም ሌላ መተግበሪያዎችን መጫን የሚያስችል አሰራር ያላቸው ማልዌሮች ናቸው።
አጥቂዎች ተጠቃሚውን አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን ተፈጻሚ እንዲያደርግ በመሸወድ እንዲጭን የሚያደርጉ አሰራሮችንም በውስጣቸው ያካተቱ ሲሆን፤ አንድ ጊዜ ከተጫኑ እና ስራ ላይ ከዋሉ በኋላ በውስጣቸው ያለው ተንኮል አዘል ኮድ ራሳቸውን እንዲያነቁ እና ሌሎች ተንኮል አዘል መተግበሪያዎችን በማውረድ መጠነ ሰፊ ጥቃቶችን ወይም ጉዳቶችን ማድረስ እንዲችሉ ያደርጋል። ይህም ገደብ የለሽ የተጠቃሚ ፈቃድን ማግኘት የሚያስችላቸውን ዘዴዎች በመጠቀም ዳታን መቀየር፣ ማጥፋት፣ መስረቅ እንዲሁም የሩቅ መር አሰራርን (ሪሞት ኮንትሮሊንግን) በመፍጠር አጥቂዎች ለስለላና ለመሳሰሉ አይነት የመቆጣጠሪያና የጥቃት ዘዴዎች እንዲጠቀሙባቸው የሚያስችሉ ናቸው።
o ከተጠቃን ምን ሊደርስ ይችላል?
እንደየ ትሮጃን አይነቱ ስራቸውና አላማቸው የተለያየ ሲሆን ብዙውን ጊዜ ግን የሚከተሉትን ምልክቶች ያሳያሉ፤
• የኮምፒውተር ስክሪን ከለር መቀያየርና በትክክል አለመስራት ለምሳሌ ብልጭ ድርግም ማለት፣ መገለባበጥ
• የስክሪን የጀርባ ምስል ወይም የምስል ውቀሮችን መቀያየር
• ኮምፒውተሩ ያለትእዛዝ ዶክመንቶችን ፕሪንት ለማድረግ መሞከር
• ያለተጠቃሚው ትዕዛዝ የድር ጣቢያዎች መከፈት
• የድምጽ መጠን በድንገት መለዋወጥ
• የጸረቫይረስ ፕሮግራሞች ወይም መተግበሪያዎች ማቆም እና የዳታ መቀየር፣ መጥፋት ወይም መበላሸት
• የኮምፒውተሩ የሰዓት እና ቀን መለወጥ
• የማውስ ከርሰር (ወይም ጠቋሚ) በራሱ መንቀሳቀስና የቀኝና የግራ ጠቋሚ አሰራርና ተግባር መለዋወጥ
• የዊንዶውስ የስታርት ቁልፍ(ወይም በተን) መጥፋት
• ፖፕ አፖች (ወይም ብቅ ብቅ የሚሉ የመተግበሪያ ክፍሎች) ግልጽ ካልሆነ መልዕክት ጋር መምጣትና ተጠቃሚውን መረበሽ
• የኬይቦርድና የማውስ ስራ ማቆም
• ተጠቃሚው ግንኙነት ከሌለው አካል የኢሜይል መልዕክት መምጣት
• እንግዳ የሆኑ የጥያቄና የማስጠንቀቂያ የመልዕክት ሳጥኖች ከአዎንታዊና አሉታዊ አማራጮች (በሁሉም አማራጮች ተጠቃሚውን ለሌላ ጥቃት በር መክፈቻነት ሰለባ የሚያደርጉ) ጋር መምጣት
• ባልተለመደ መንገድ የኮምፒውተር የእንደገና መነሳት(ሪስታርቲንግ)
• የታስክ ማናጀር ስራ ማቆም ይህም ለአጥቂው ወይም ለትሮጃኑ ተጠቃሚው ምን ምን ፕሮሰሶች ስራ እየሰሩ እንደሆነ እንዳያውቅ ለማደረግ እና በትሮጃኑ የተጫኑ ፕሮሰሶች ራሳቸውን እንዲደብቁ ለማድረግ
• የሲስተም ፍጥነት ወይም የስራ ሂደት አቅም መገደብ ወይም መቀነስ
• የትክክለኛ መተግበሪያዎች ስራ ማቆም ወይም በትክክል አለመስራት እና መረበሽ
14/04/2022
ሳይበር ሀይጅን
ሳይበርሃይጅንማለትማንኛዉምየኮምፒዉተርወይምመሰልመገልገያዎችተጠቃሚዎችየኮምፒዉተራቸዉንደህንነትአሊያምጤንነትለመጠበቅሲሉየሚያደርጓቸዉጥንቃቄዎችዎይምየሚወስዱዋቸዉእርምጃዎችናቸዉ፡፡በተጨማሪምማንኛዉንምየኢንፎርሜሽንቴክኖሎጂሲስተምእናመገልገያወችንምመጠበቅእንዲሁምየሳይበርደህንነትመልካምተሞክሮዎችንመተግበርመቻልጭምርነዉ፡፡
ምንምእንኳንበዲጂታልአለምዉስጥበርካታስጋቶችናተጋላጭነቶችቢኖሩምየሳይበርሃይጅንቁልፍልምዶችንተግባራዊማድረግየደህንነትስጋቶችንከመቀነስአንፃርእጅግጉልህአስተዋፅኦአለዉ፡፡
• የሳይበርሀይጅንፖሊሲንተግባራዊማድረግዎሳኝነዉይህየሳይበርሀይጅንየሚያካትታቸዉ
የይለፍቃሎችንበየጊዜዉመቀየር ፡ ዉስብስብናሊገመቱየማይችሉየየለፍቃሎችንመጠቀምናበየጊዜዉምመቀያየርየመረጃደህንነትንለማረጋገጥጠቃሚነዉ፡፡
ሶፍትዌሮችንማዘመን ፡ ሁልጊዜምየምንጠቀምባቸዉንሶፍትዌሮችማዘመንናየተሻሻሉትንቅጂዎችመጠቀምየሳይበርሀይጅንዋናተግባርነዉ፡፡
ሃርድዌሮችንማዘመን ፡ ረጅምጊዜአገልግሎትላይየዋሉኮምፒዉተሮችናሌሎችመሰልመገልገያዎችንጭምርማዘመንእናመተካትመቻልየደህንነትስጋቶችንይቀንሳል፡፡
አዲስኢንስቶልየሚደረጉመተግበሪያዎች ፡ ወደመገልገያዎቻችንኢንስቶልየምናደርጋቸዉአዳዲስመተግበሪያዎችበትክክልዶኪመንትሊደረጉናመዘመንመቻልይኖርባቸዋል፡፡
የተጠቃሚዎችንቁጥርመገደብ ፡ በአንድኮምፒዉተርወይምመገልገያላይበጋራየሚጠቀሙተጠቃሚዎችንቁጥርማብዛትተጋላጭነትንከፍየሚያደርግበመሆኑይህእንዳይሆንማድረግተገቢነዉ፡፡
ባክአፕዳታ(መጠባበቂያዳታ) መያዝ ፡ ሁሉንምወሳኝመረጃዎች (ዳታዎች) በሁለተኛአማራጭመጠባበቂያማኖርተገቢነዉይህምከኮምፒዉተራችንበተጨማሪመረጃንበሃርድድራይቮችወይምክላዉድስቶሬጅማከማቸትሊሆንይችላል፡፡
እያንዳንዱንየኦንላይንአንቅስቃሴዎችበጥንቃቄመምራትመቻልተገቢነዉ፡፡
10/03/2022
የመተግበሪያ ደህንነትን እንዴት ማስጠበቅ ይቻላል?
የመተግበሪያ ደህንነት ተጠቃሚዎች፣ ደንበኞች፣ የንግድ አጋሮች እና ሰራተኞችን ጨምሮ በውስጥ እና በውጪ ባለድርሻ አካላት የሚጠቀሙባቸውን ሁሉንም አይነት አፕሊኬሽኖች (እንደ ሌጋሲ፣ ዴስክቶፕ፣ ድር፣ ሞባይል፣ ማይክሮ አገልግሎቶች ያሉ) ድርጅቶች እንዲጠብቁ ያግዛል። ይህም
• አንድ መተግበሪያ ከመመረቱ ጀምሮ በሚኖረው የንድፈ ሃሳብ ደረጃ እና በመመረት ላይ እያለም አስፈላጊውን የፍተሻ ሂደቶችን በመተግበር እና ክፍተቶቹን በመዝጋት፣
• የመተግበሪያውን የስራ ላይ ከባቢ ሁኔታ ደህንነት በመፈተሽ እንዲሁም አስፈላጊውን የደህንነት ግብዓቶችን በተገቢው መንገድ ማመቻቸት፣
• በስራ ላይ ባለበት ጊዜም ወቅታዊ የሆነ የደህንነት ፍተሻና ግምገማ በማካሄድ፣
• በየጊዜው የሚለቀቁትን የመተግበሪያው የደህንነት እድሳት አማራጮችን በተጠንቀቅ በመጠበቅ እና በማዘመን፣
• ምንጫቸው ያልታወቁ መተግበሪያዎችን ባለመጫን፣
• ታማኝ ካልሆኑ የመተግበሪያ ማከማቻ ድሮች መተግበሪያዎችን ባለማውረድ እና ባለመጫን እንዲሁም ታማኝ ያልሆኑ የድር ጣቢያዎችን ወይም ድር መተግበሪያዎችን ከማሰስ በመቆጠብ፣
• እንደ ተቋም ለተጠቃሚዎች ወይም ለሰራተኞች ተገቢውን የደህንነት አጠባበቅ ዘዴዎችን በማስተማር እና ስልጠናዎችን በመስጠት የመተግበሪያ ደህንነትን እንደ ተቋም፣ እንደ ግለሰብ ወይም እንደ ተጠቃሚ ማስጠበቅ እና ከጥቃት ራስን መጠበቅ ይቻላል።
03/03/2022
ወላጆች ልጆቻቸውን በኢንተርኔት አማካኝነት ከሚደርስ አደጋ ለመጠበቅ ምን ማድረግ
ይችላሉ?
ኢንተርኔት ላይ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለመከታተል የልጆቻችን ኮምፒውተር በቤት ውስጥ የሚታይ ቦታ (common Area ) ማስቀመጥ።
የልጃችንን የመረጃ መቃኛ ታሪክ ( Browser History) ደጋግሞ መፈተሽ።
የደህንነት ሶፍትዌር ወይም መሳሪያዎችን መጠቀም።
የግላዊነት ገጽታዎችን(privacy features) የሚደግፉ በመተግበሪያዎ ወይም በኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎ አማካኝነት ያንቀሳቅሱ።
ልጆችዎ የሚጠቀሙባቸውን ሌሎች ኮምፒውተሮችን ወይም መሣሪያዎችን ማወቅ።
የልጆችን የይለፍ ቃል (password)ማወቅ።
በኢንተርኔት አማካኝነት የሳይበር ጉልበተኝነት (cyber bullying) እንደተፈፀመ ወይም የሳይበር ጉልበተኝነት ጥቃት ከሚፈጽም ሰው ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚጠቁሙ የልጆችዎ ባሕርይ ለውጦች ካሉ ማስተዋል
ለልጆቻችሁ ጠንካራ የይለፍ ቃላትን እንዴት ማዘጋጀት እንደሚቻል ፣ እንዲሁም አፕሊኬሽኖችን ማውረድ የሚችሉትና የማይችሉት እነማን ናቸው የሚልቱን ነገሮች ማስተማር ተገቢ ነው
ልጆች የኢንተርኔት ጉልበተኛም ሆነ ማንኛውም ሰው ቢያስቸግሯቸው ሁልጊዜ ወደ እናንተ መምጣት እንደሚችሉ መንገርና መገኘት በጣም አስፈላጊ ነው።
ታዳጊዎች በኢንተርኔት አማካኝነት የሚያገኝዋቸውን እንግዳ ሰዎች እንዳያነጋገሩ አበረታቷቸው።
በተጨማሪም በኢንተርኔት አማካኝነት ያገኟቸውን ሰዎች ማግኘት በጣም አስፈሪ የሆነ አደጋ
ሊያስከትል እንደሚችል ንገሯቸው፤ቢቻል በአካል ከሚያቇቸው ጓደኞቻቸውና ዘመዶቻቸው ጋር ብቻ እንዲነጋገሩ አበረታቷቸው።
ታዳጊዎች የኦንላየን ቴክኖሎጂን በሚጠቀሙበት ጊዜ ሊያጋጥማቸው የሚችሉ ስጋቶች ምንድናቸዉ
1. ተገቢ ያልሆነ ይዘቶች (Inappropriate content)፡ ይህም ሲባል፡-
የወሲባዊ ይዘት ያላቸው (የህፃናት\አዋቂዎች ፖርኖግራፊ፣ ከፊል እርቃን እና \ወይም እርቃን ምስሎች እና ተንቀሳቃሽ ምስሎችን መመልከት
የዓመፅና የስቃይ ምስሎች እና ተንቀሳቃሽ ምስሎች
የጥላቻ ቡድኖችን የሚደግፍ የሚያበረታታ ይዘት ያላቸዉ መረጃዎች
ህገ ወጥ ተግባር የሚያሳዩ ማስታወቂያዎች
ጽንፈኛ ድረገፆች፤ የሽብርተኛ ድርጅቶችን፣ ቦምብ የሚሰሩ ቦታዎችን ወዘተ መረጃዎች
አደገኛ ፀባይን የሚያበረታቱ ድረ ገጾች
ጸያፍ ንግግሮችንና ጸያፍ ድርጊቶችን የሚጠቀሙ ይዘቶችን ያካትታል
2. የቻት ሩም "ጓደኞች" (Chat room “Friends”)
አንዳንድ አዳኞች(predators) ወደ ቻት ሩም ወይም በማኅበራዊ ድረ ገጾች ተጠቅመው ትንንሽ ልጆችን ማግኘት ይችላሉ። በእነሱ ዕድሜ ላይ የሚገኙ መስለው በመቅረብ ጓደኛ ይሆኗቸዋል። አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ እንደዚህ አይነት ሰዎች በአንድ ወቅት በአካል ለማግኘት ይሞክራሉ ብሎም በታዳጊዎች ላይ ተገቢ ያልሆነ ብዝበዛ ሊፈፅሙ ይችላሉ
3. የሳይበር ጉልበተኝነት (Cyber Bullying)
በማህበራዊ ሚዲያ ድረገፆች አማካኝነት የሚደርስ የሳይበር ጉልበትኝነት (cyber bullying):- ህጻናት በማንነታቸዉ ምክንያት የሚደርስባቸዉ ዘለፋ እና ስድብ ነክ ትችት በስነልቦናቸዉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከማድረስ አልፎ ራስን የመጥላት ብሎም ራስን የማጥፋት ስሜት ዉስጥ ሊያስገባቸዉ ይችላል
4. 4. የኦንላይን (መስመር ላይ) ማጭበርበሪያዎች (Online Scams)
ብዙውን ጊዜ በኢንተርኔት ለሚሰነዘሩ ማጭበርበሪያዎች ዋነኛ ዒላማ የሚሆኑት አዋቂ ሰዎች እንደሆኑ ተደርገው ቢቆጠርም ልጆችም ለነዚህ አይነት ማጭበርበሪያዎች በጣም የተጋለጡ ናቸው። ታዳጊዎችን በሚፈልጉት እና ሊያገኙት በሚፈልጉት ነገር ጋር በማያያዝ በሀሰት ሊጭበረበሩና ለከፋ ጉዳ ሊደረጉ ይችላሉ፡፡
28/12/2021
የቴሌግራም አፕ እና የደህንነት ጥንቃቄዎች
የቴሌግራም መተግበሪያ ለአንድሮይድ እና አይኦኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች በተንቀሳቃሽ ስልኮችና እንዲሁም ለዴስክቶፕ በእ.ኤ.አ 2013 ተግባር ላይ የዋለ እና መልዕክቶችን ለመላላክ፣የድምፅ እና የተንቀሳቃሽ ምስል ጥሪዎችን ለማድረግ ብሎም ፋይሎችን ለመጋራት እና ሌሎች ተግባራትን ለማከናዎን ጥቅም ላይ የዋለ መተግበሪያ ነዉ፡፡
ይህ መተግበሪያ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት እና ተወዳጅነትን ያተረፈ መተግበሪያ ሲሆን በርካታ ሰዎችም እየተጠቀሙበት ይገኛሉ በሀገራችንም ተወዳጅ ከሆኑ የመተግበሪያዎች ዝርዝር መሀል አንዱ እንደሆነ ይታመናል፤ ታዲያ ይህ መተግበሪያ እንደማንነኛዉም ሌላ መተግበሪያዎች ሁሉ የሳይበር ጥቃት ሊያስተናግድ ይችላል ባለፈዉ በሰኔ ወር እንኳን በርካታ ቴሌግራም ላይ የተመሰረቱ ጥቃቶች እንደተሰነዘሩ ዘ ሀከርኒዉስ ዘግቧል፡፡
የቴሌግራም መተግበሪያ እንዴት ሊጠቃ ይችላል
o የሶሻል ኢንጅነሪንግ ፡ ይህ ማለት በኢምፐርሶኔሽን ዘዴ ተመሳስልው በሚሰሩ መልእክቶች ሰዎች በቴሌግራም የሚላክላቸውን መልእክት በማመን የሚላኩ ሊንኮችን ሊጫኑ አባሪዎችን ሊከፍቱ እና ለጥቃት ሊጋለጡ ይችላሉ
o ፊሺንግ፡ ይህም ፊሺንጎች ተመሳስለዉ በሚሰሩ የማታለያ መንግዶች የሚትገበሩ ሲሆኑ የቴሌግራም ፊሺንጎችም ህጋዊ እና እዉነተኛ ከሚመስሉ አካዉንቶች የተላኩ በሚመስሉ ሃሰተኛ መልዕክቶች የማጭበርበር እና በመተግበሪያዉ ላይ እና በሌሎችም የመተግበሪያዉ ሲስተሞች ላይ ጭምር ጥቃት ማድረስ ነዉ
o ደህንነታቸዉ ያልተጠበቀ ሌሎች አፕሊኬሽኖከች፡ በመተግበሪያችን ላይ ኢንስቶል የምናደረጋቸዉ መተግበሪያዎች ከታወቁ ምንጮች የተገኙ እና ደህንነታቸዉ የተረጋገጠ መሆናቸዉን ካላረጋገጥን የቴሌግራም አካዉንቶችን ወይም ሌሎችን መተግበሪያዎችን ጭምር የሚሰልሉ ሊሆኑ ይችላሉ
o የምንጠቀምበትን መገልገያ በራሱ አለመዘመን
o የመገልገያ አካላዊ መሰረቅ አሊያም መጥፋት
የቴሌግራምመተግበሪያንስንጠቀምማድረግየሚገባንየደህንነትጥንቃቄወችንእንመልከት፡
o የቴሌግራም መተግበሪያን እንደየሚጠቀሙበት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከ ተገቢዉ የ መተግበሪያ ቋት ማዉረድ ተገቢ ነዉ
o በየጊዜዉ ለሚደረጉ ዝመናዎች ትኩረት መስጠት እና ተከታትሎ ማዘመን ተገቢ ነዉ
o አንቲ ቫይረስ እና አንቲ ማልዌር መጠቀም
o የቴሌግራም ቦቶችን መጠንቀቅ ማለትም ማሊሺየስ የሆኑ አለመሆናቸዉን ማረጋገጥ
o በመተግበሪያዉ የተካተቱ መለያዎች(features) በመጠቀም የደህንነት መለያዎችን መተግበር ለምሳሌ የ2 ፋክተር አዉተንቲኬሽንን መተግበር እንዲሁም የ ቴልገራም ፓስኮድ መለያ መተግበር
o በተቻለ መጠን የቴሌግራምንም ይሁን ሌሎች መተግበሪያዎችን ደህንነቱ በተረጋገጠ የአፕሊኬሽን ሎከር መቆለፍ
o በቴሌግራም የሚላኩ ሊንኮች(አስፈንጣሪዎች) እና አታችመንቶች(አባሪዎች) እንደሌሎች የኦንላይን ተግባራት ሁሉ የ ፊሺንግ መንገዶች ስሚሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ
o የምንጠቀምበትን መገልገያ አካላዊ ደህንነት መጠበቅ
o ሌሎች የደህንነት ጥንቃቄዎችን ተግባራዊ ማድረግ እንዲሁም ቴሌግራማችን የተጠቃ መስሎ ከተሰማን ሌሎች ሴሽኖችን በሙሉ መቋረጥ ብሎም እስከወዲያኛዉ ማጥፋት ተገቢ ነዉ
21/12/2021
ስለ ማልዌር
ክፍል 3
የማልዌር ጥቃት ቢደርስ ሊወሰዱ የሚገባቸዉ ርምጃዎች ምንድናቸዉ
የማልዌር ጥቃት ተጠቂ እንደሆንን ከተረጋገጠ ሊወሰዱ የሚገባቸዉ ርምጃዎችን ለመመልከት ያህል፡-
የኦፍላይን አንቲቫይረስ ስካን ማድረግ
ፈፅሞ ግላዊ ወደሆኑ ሌሎች አካዉንቶችም ይሁን ገንዘብ ነክ የሆኑ አካዉንቶች ሎግ ኢን ከማድረግ መቆጠብ
ያሉትን ፀረቫይረሶች ማዘመን እና ከሌሉም በፍጥነት በማግኘት ስካን ማድረግ
አጠራጣሪ መስለዉ የሚታዩ አፕሊኬሽኖች/ፕሮግራሞችን ማጥፋት
የኦንላይን እርዳታዎችን መጠየቅ አይመከርም
የፀረ ቫይረስን በሴፍ ሞድ ጥቅም ላይ ማዋል ይሄም ቫይረሶች ራሳቸዉን እንዳይደብቁ በማድረግ የፀረ ቫይረሱን ጥቅም የበለጠ ዉጤታማ ያደርጋል
ለሁሉም ግልጋሎቶች ጥቅም ላይ ያሉ የይለፍ ቃሎችን መቀየር
የመገልገያዉን ኢንተርኔት ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ ማቋረጥ
አማራጮችን ሁሉ ጥቅም ላይ አዉሎ መፍተሄ ካልተገኘ መገልገያዉን ሙሉ ለሙሉ ቡት/ ሪስቶር ማድረግ
መገልገያዉን እንደ አዲስ ጥቅም ላይ ሲዉል ሁሉንም የጥንቃቄ ርምጃዎች መከተል
20/12/2021
ስለ ማልዌር
ክፍል 2
የማልዌር ጥቃት ቢደርስብን እንዴት ማወቅ እንችላለን
የማልዌር ጥቃት ሰለባ የሆነ መገልገያ የሚያሳያቸዉ ልዩ ባህሪትን ከተመለከትን የማልዌር ጥቃት ተጠቂ መሆናችንን ማወቅ የሚቻል ሲሆን ከባህሪያቱ አንዱን ጥቂቶቹን አሊያም አብዛኞቹን ባህሪ ሊያሳይ የሚችል ሲሆን ሊታዩ የሚችሉት ባህሪያት የሚከተሉት ናቸዉ፡-
• በድንገት የኮምፒዉተሩ ስራ መንቀርፈፍ፣ትእዛዙ መዘጋት አሊያም ሙሉ ለሙሉ መዘጋት ወይም የትእዛዝ ስህተትነትን የሚገልፅ መልዕክት መመልከት
• ኮምፒዉተሩን ለመዝጋት ወይም እንደገና ለማስጀመር አለመቻል ወይም አለመታዘዝ
• ሶፍትዌርን ለመዝጋት ወይም ለማጥፋት አለመቻል
• ድንገታዊ ያልተጠበቁ ፖፕአፖች ወይም ማስታዎቂያዎች በሌላ ፔጅ ኮንተንት ላይ ብቅ ማለት እና ጣልቃ መግባት
• ትክክለኛ በሆኑ ድረገፆች ላይ ያልተለመዱ እና ወጣ ያለ ይዘት ያላቸዉ ማስታዎቂያዎችን መመልከት
• ያልተለመዱ ቱልባሮች እና አይከኖች በመገልገያዉ ወይም በአሳሾች (ብሮዉዘሮች) ላይ መታየት
• ተጠቃሚዉ ያልፈቀደዉ ዲፎልት አሳሽ ጥቅም ላይ ሲዉል መመልከት ወይም ያልተከፈቱ አሳሶችና ታቦች ተከፍተዉ መመልከት
• ከተለመደዉ ፍጥነት በላይ የባትሪ መጠን መቀነስ እና ማለቅ ወይም መገልገያዉ ሳይታሰብ የመብራትና መጥፋት ሁኔታ መታየት
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
South Africa Street
Addis Ababa
ETH