Genet Computers
አዳዲስ እና ያገለገሉ ላፕቶፖች በቅርብ ቀን በብዛት
HEY friends ICT exibition will began tomorrow upto wednsday and also sofia will be their
27/03/2017
ፍላሽ ዲስክ ቡታብል ለማድረግ የሚጠቅመን ሶፍትዌርና ስቴፖቹ! Create Bootable USB Drives to Install (Almost) Any OS ፍላሽ ዲስክ ቡታብል ለማድረግ የሚጠቅመን ሶፍትዌርና ስቴፖቹ! Create Bootable USB Drives to Install (Almost) Any OS
23/03/2017
VPN ምንድን ነው?VPNን መጠቀም ጥሩነቱ ምኑ ላይ ነው?What is a VPN? - VPN stands for Virtual Private Network VPN stands for Virtual Private Network. But what is it? What can a VPN do for you and do you need a VPN? Let's take a look....
22/03/2017
ትወርክ ትራብልሹት!Network Connection doesn't have a valid IP configuration-Fixed Easily ትወርክ ትራብልሹት
21/03/2017
የኔትዎርክ የትውስትድ ፔር ገመድ/ ኬበል/ ከለር ኮዶች!How to make Ethernet Cable - Straight Through & Crossover Ethernet Crimp Tool Set:How to make CAT5 Ethernet Cable - Straight Through & Crossover (HD) ================================= EIA 568A PIN WIRE 1 ...
20/03/2017
የዳታ ማስቀመጫ ክፍልፋዮች ፊደል ከA እስከ Z መቀየር (Reassigning Drive Letters)
በኮምፒውተር ውስጥ ያሉ የHard Disc ክፍልፋዮች፣ USB flash, ሲዲ/ዲቪዲ እና ፊሎፒ ዲስክ ማጫዎቻ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ ሲጫን በራሱ በዲፎልት የተሰየሙበትን ፊደሎች C፣ D፣E፣ F በምንፈልገው ፊደል ከA እስከ Z መቀየር እንችላለን፡፡ ይሄም የሚጠቅመን የኮምፒውተር ቫይረሶች ፕሮግራም ሲፃፍ/ሲሰሩ የዳታ ማስቀመጫውን Hard Disc ፊደል በራሱ ዲፎልት ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ የሰጠውን ብዙዎች ቫይረስ የሚሰሩ ግለሰቦች ስሊያውቁት ይሄን መሰረት አድርገው የቫይረስ ፕሮግራሞች የሚያዘጋጁ በመሆኑ የኮምፒውተሩን የዲስኮች ፊደል መቀየር አንዱ ጥቅም ነው፡፡
ለምሳሌ የሲዲ ማጫዎቻ የተሰየመበትን ፊደል ለመቀየር
1. Computer→ Right-Click→Manage
2. Computer Management
3. Disc Management
4. በቀኝ በኩል CD-Rom የሚለው ላይ Right-Click→Chage Drive Latter and Paths የሚለውን እንምረጥ ወይም ከማውጫው ላይ Action በሚለው ስር All tasks→Change Drive Latter and Paths
5. የሲዲ ማጫዎቻውን ፊደል የሚያሳየን ገጽ ላይ Change የሚለውን ቁልፍ እንምረጥ
6. በሌሎች ዲስኮች ያልተያዘ የምንፈልገው ፊደል ከA እስከ Z እንምረጥና Ok
7. ፊደሉን ለመቀየራችን ማረጋገጫ መልክት ይመጣል Yes
20/03/2017
32 ቢት እና 64 ቢት ሲፒዮ ልዩነት
እንደምናችሁ ወዳጆቼ ዛሬ በ32ቢት እና በ64 ቢት ፕሮሰሰር መሃል ያለውን ልዩነት ይዘ ቀርቤለሁ ይህ ጽሁፍ ኮምፒውተር ለምትገዙ፤ የምትጠቀሙበትን ኮምፒውተር/ላፕቶፕ የተጫነበትን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ከፍ(አብግሬድ) ለማድረግ እንዲሁም የምትጭኑትን ሶፍትወዌር ለመወሰን ያግዛል፡፡
የኮምፒውተር ሲፒዩ በሁለት አይነት 32 እና 64 ቢት በሚል የሚከፈል ሲሆን የፕሮሰሱ አይነት በኮምፒውተር ላይ ምንም አይነት እክል የማይፈጥር ቢሆንም የምንጭናቸው ኦፕሬቲንግ ሲስተምና ሶፍትዌሮች ይወስኑታል፡፡
32 ቢት ፕሮሰሰር
32 ቢት ፕሮሰሰር ከ1990 ጀምሮ በሁሉም ኮምፒውተሮች ላይ የምገኘው ሲሆን የፕሮሰሰር አምራች የሆኑት ኢንቴል እና ኤኤምዲ እየሰሩ ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ ፡፡
ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌር የሚሰሩ ድርጂቶች 32 ቢት ፕሮሰሰርን መሰረት በማድረግ ሲሰሩ ከነዚህም ውስጥ ማክሮሶፍ ዊንዶ 95፣ 98 እና ኤክስፒን ሁሉም 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ተደርገው የተሰሩ ናቸው፡፡
32 ቢት ፕሮሰሰር የሆነ ኮምፒውተር 64 ቢት የሆነ ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የማንችል ሲሆን ምንጊዜም 32 ቢት ፕሮሰሰር መጫን የሚችለው 32 ቢት የሆነ ኦፕሬቲን ሲስተም እና ሶፍትዌሮች ብቻ ነው፡፡
64 ቢት ፕሮሰሰር
64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በ1961 አካባቢ አይቢኤም IBM 7030 Stretch supercomputer የሚባል የሰራ ቢሆንም እስከ 2000 ድረስ ለቤት መጠቀሚያ ተብለው በሚሰሩ ኮምፒውተሮች ላይ አልነበረም በማክሮሶፍት 64 ቢት ፕሮሰሰርን የሚጠቀም 64 ቢት ዊንዶ ኤክስፒ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ አቀረበ በመቀጠል ዊንዶ ቪስታ፣ ዊንዶ 7፣ ዊንዶ 8 እና ዊንዶ 10 64 ቢት ፕሮሰሰር የሚጠቀሙ ባለ 64 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ ቀርበዋል፡፡
64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር 64 ቢት እና 32 ቢት ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጫን የሚችል ሲሆን 32 ቢት ፕሮሰሰር 64 ቢት የሆነን ኦፕሬቲን ሲስተም መጫን አይችልም፡፡
ማስታወሻ
64 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር 16 ቢት ተብለው የተሰሩ ፕሮግራሞችን/ሶፍትዌሮች የማይሰራ ሲሆን ብዙ 32 ቢት የሆኑ ፕሮግራሞች/ሶፍትዌሮች 64 ቢት ፕሮሰሰር እና ኦፕሬቲን ሲስተም ላይ የሚሰሩ ሲሆን አንዳንድ የድሮ ወይም የቆዩ 32 ቢት ፕሮግራሞች/ሶፍትዌሮች በትክክል አይሰሩም (compatibil አይደሉም)
32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ የሆነ ልዩነት ያላቸው ሲሆን አንድን ስራ በኮምፒውተር ላይ ስንሰራ ፕሮሰሰሩ ያለው ፍጥነት አንዱ ልዩነታቸው ሲሆን 64 ቢት ፕሮሰሰር ትልቅ ፍጥነት አለው፡፡ 64 ቢት ፕሮሰሰር ለገበያ ተሰርቶ የሚመጣው በdual core፣ በquad core፣ በsix core እና በeight core ቨርዥን በሆኑ ኮምፒውተሮች ላይ ነው፡፡
32 ቢት እና 64 ቢት ፕሮሰሰር አንዱ ሌላው ልዩነታቸው በኮምፒውተሩ ላይ የሚያስፈልገው የሚሞሪ(ራም) መጠን ሲሆን 32 ቢት ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር በጠቅላላ 4GB የሆነ ራም ብቻ መጠቀም የሚያስችል ሲሆን 64 ቢት የሆነ ፕሮሰሰር ያለው ኮምፒውተር ከ4GB በላይ የሆነ ራም መጠቀም ያስችላል ይሄም ግራፊክስ ዲዛይን፣ ኢንጂነሪንግ እና ቪዲዮ ኤዲቲንግ ለሆኑ ሶፍዌሮች በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
በአሁን ጊዜ በርካታ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች እና ሶፍትዌሮች 64 ቢት እየሆኑ የመጡ በመሆኑ ተጠቃሚዎች ኮምፒውተሮቻቸው 64 ቢት እንዲሆኑ የተገደዱ ሲሆን ይሄም የፕሮሰሰር አምራቾች 64 ቢት ፕሮሰሰር በስፋት ወደገበያ እያቀረቡ ነው፡፡
ድጋፈችሁ አይለየን like፣ invite፣ comment፣ share በማድረግ በየጊዜው አዳዲስ ነገርን እንድናቀርብ አበረታቱን እንወዳችሁዋለን
Share your knowledge free for millions
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Addisu Gebeya
Addis Ababa