Bisrat Promotion
በአካል ጉዳተኝነት እና ጉዳተኞች ላይ የሚሰራ…እያዝናናን እ? A Multimedia Initiative Focused on Raising Disability Awareness!
14/11/2024
ፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ እድገት ውስንነት ብሄራዊ ማህበር የተመሰረተበትን 30ኛ አመት በስካይ ላይት ሆቴል እያከበረ ይገኛል
በፕሮግራሙ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ :የአካል ጉዳተኛ ማህበራት አመራሮች :የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ልጆች ወላጆች:የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ልጆች እንዲሁም በጎ ፈቃደኞች ተገኝተዋል ።
የፍቅር ኢትዮጵያ የአእምሮ እድገት ውስንነት ብሄራዊ ማህበር ፕሬዝዳንት የሆኑት ወ/ሮ ምህረት ንጉሴ እንዳሉት ስኬቶቻችንን ስናከብር ብዙ የሚቀሩ ስራዎች እንዳሉም እንገነዘባለን። በየቤቱ በሰንሰለት የታሰሩ የፀሀይ ብርሃን የሚናፍቁ ወገኖቻችንን በልባችን ይዘን፤ ይህ በዓል ጥረቶቻችንና ተልእኳችን እንደሚቀጥል ለማስታወስ ይሁን።
የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ዜጎችንና ቤተሰቦቻቸውን መብት፣ ብቃት፣ ሙሉ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለመደገፍ ቁርጠኞች ነን። በጋራ ጥንካሬያችን፣ ገደቦችንና እንቅፋቶችን መግፋታችንን እንቀጥላለን በዚህም ለሁሉም ብሩህ፣ እኩልና አካታች ዓለም ወደፊት እንፈጥራለn
31/08/2024
በ17ኛው የፓራሊምፒክ ጨዋታዎች አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ በ1500 ሴቶች የጭላንጭል (T-13) ፍጻሜ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች።
80 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው የስታድ ደ ፍራንስ ብሔራዊ ስታዲየም በተደረገው ውድድር አትሌት ትዕግስት 4 ደቂቃ ከ22 ሴኮንድ ከ39 ማይክሮ ሴኮንድ አሸንፋለች።
አትሌት ትዕግስት እ.አ.አ በ2021 በቶኪዮ በተካሄደው 16ኛው የፓራሊምፒክ ጨዋታዎች በተመሳሳይ ርቀት ተሳትፋ በውድድሩ ታሪክ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ማምጣቷ የሚታወስ ነው።
ሞሮኮዋዊቷ አትሌት ፋጡማ ኢዝሃራና አሜሪካዊቷ አትሌት ሊዛ ኮርሶ ሁለተኛና ሶስተኛ በመውጣት የብርና የነሐስ ሜዳሊያ አግኝተዋል።
በውድድሩ ላይ 11 አትሌቶች ተሳትፈዋል።
በተያያዘም ዛሬ ቀን ላይ በተካሄደ የወንዶች 1500 ሜትር የእጅ ጉዳት (T-46 ምድብ) የፍጻሜ አትሌት ገመቹ አመኑ ስምንተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
29/08/2024
ነፍስ ይማር🙏💔
ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ አረፉ 😭😭
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዝዳት ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ነሐኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ማረፋቸውን አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከደቂቃዎች በፊት አስታውቋል።
ፕሮፈሰር እንድሪያስ እሸቴ አካል ጉዳተኛ ለሆኑ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በስራ ዘመናቸው ከፍተኛ አገልግሎት የሰጡ ግለሰብ ናቸው
28/07/2024
አቢሲኒያ ሽልማት🏅
👏👏
"ትጉኋንን እንሸልማለን" በሚለው መርሀ ግብር
በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል
የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ሴቶች ብሄራዊ ማህበር ዛሬ 21/11/2016 ዓ.ም ተሸልማለች።
እንኳን ደስ አላችሁ 👏🤟🥇
27/07/2024
በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ ውድ ህይወታቸውን ባጡ ወገኖቻችን ምክኒያት ብሄራዊ ሀዘን ታውጇል ስለሆነም የጣፍጭ መዝናኛ ዝግጅት ክፍል ዛሬ የሚተላለፈውን ፕሮግራም አጥፎል
ውድ ህይወታቸው ላጡ ወገኖቻችን ቤተሰቦች መፅናናትን እየተመኘን በሚቀጥለው ሳምንት መደበኛ ፕሮግራማችን የሚቀጥል መሆኑን እንገልፃለን ።
24/07/2024
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት ናዳ ምክንያት የዜጎቻችን ህይወት በመቀጠፉ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እገልፃለሁ።
በተከሰተው ድንገተኛ አደጋ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖችና ለተጎጂ ቤተሰቦች ወዳጅ ወመዶች ሁሉ መፅናናትን እንመኛለን ።
21/06/2024
ለአካል ጉዳተኞች የሚሆኑ የተለያዩ እቃዎችን ከፈለጉ ከብስራት ፕሮሞሽን ያገኛሉ
በ +251115577357 ይደውሉ
ከምንሸጣቸው እቃዎች መካከል በጥቂቱ
Talking watch
Hearing aid
Wheelchair
braille watch
Crutch
Talking calculator and other
14/06/2024
የአካል ጉዳተኞችን ለማገዝ ዊልቸር በነፃ የምትሰጠው ኢትዮጵያዊት
ገና በልጅነቷ ባጋጠማት የፖሊዮ ህመም ምክንያት የቀኝ እግሯን እንደፈለገች አታዘውም፡፡ ቆማ መሄድ ባለባት የልጅነት አድሜዋ ቆማ እንድትሄድ አላስቻላትም ነበር፡፡ ነገር ግን ጠንካራ እና የተሻለ የኑሮ ደረጃ ያላቸው ቤተሰቦች ነበሯት፡፡ ስለሆነም ብዙ ወጥተውና ወርደው ብዙ ወጪም አውጥተው በ5 ዓመቷ መራመድ እንድትችል አደረጓት፡፡ ሳባ ተክለማርቆስን፡፡
ሳባ ተክለማርቆስ የአጋፔ ሞቢሊቲ ኢትዮጵያ መስራች ነች፡፡ አጋፔ ለአካል ጉዳተኞች በነጻ ዊልቸሮችን የሚሰጥ ድርጅት ነው፡፡ ሳባ በመላው ዓለም የሚገኙ በጎ አድራጊዎችን አሰባስባ ይህን መልካም ተግባር ታደርጋለች፡፡ ማንም አካል ጉዳተኛ መሬት መንፏቀቅ የለበትም ብላ በማመን የዛሬ አራት ዓመት ይህንን ጉዞ እንደጀመረች ከአዲስ ዋልታ ጋር ባደረገችው ቆይታ ገልጻለች፡፡
በ14 ዓመት እድሜዋ ወደ አሜሪካ ያቀናችው ሳባ ትምህርቷን የጨረሰችውም ሆነ ቤተሰብ የመሰረተችው በዛው በአሜሪካ ነው፡፡ ከ20 ዓመታት ቆይታ በኋላ ለእረፍት ወደ ትውልድ ሀገሯ ስትመለስ የተመለከተችው ነገር አንድ ውሳኔ እንድትወስን አስገደዳት፡፡
ከብዙ ዓመታት በኋላ ስትመለስ ብዙ ነገር ረስታ እንደነበርና ቤተክርስትያን አካባቢ መሬት ላይ እየተንፏቀቁ ምጽዋት የሚጠይቁ በርካታ አካል ጉዳተኞች ስትመለከት ደነገጠች፡፡ አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ ብላም ወሰነች፡፡ ለዚህም ወደ አሜሪካ ተመልሳ አጋፔ ሞቢሊቲ ኢትዮጵያን ከአራት ዓመት በፊት አቋቋመች፡፡
በአጋፔ የሚሰሩ የበጎ አድራጎት ሰራተኞች ሳባ በአሜሪካ ከልጇቿና ቤተሰቦቿ ጋር ተመችቷት መኖር ስትችል በየክፍለሀገሩ እየዞረች በጣም ለተጎዱ አካል ጉዳተኞች እና ረጂ ለሌላቸው በነጻ ዊል ቸር ትሰጣለች ሲሉ ደግነቷን ይገልጻሉ፡፡
አጋፔ ሞቢሊቲ ኢትዮጵያ በሁሉም ክልል እየሄደ በየአካባቢው ያሉ አካል ጉዳተኞችን ይደግፋል፡፡ ከየአካባቢው ፎቶና የተለያዩ መረጃዎች ይላካሉ፡፡ ነገር ግን አንድ የዊል ቼር አይነት ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች አይሆንም፡፡ ስለሆነም እንደየጉዳቱ የተለያየ ዊል ቼር ያስፈልጋል፡፡ እንደየአስፈላጊነቱና እንደጉዳታቸው አይነት ዊል ቼርም የሳባ ድርጅት በነጻ ይሰጣል፡፡
ሳባ በመጨረሻም ማንም አካል ጉዳተኛ መሬት ላይ በመንፏቀቅ ሲሄድ ማየት አልፈልግም ስትል ምኞቷን ገልጻለች፡፡
20/03/2024
የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን ከኢትዮ ቴሌ ኮም ጋር በመተባበር 500 ለሚሆኑ የተለያየ አካል ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች ድጋፍ አደረገ።
ደጋፍ ለተደረገላቸው ተማሪዎች በአካል ድጋፍ እና የቴክኖሎጂ መርጃ ቁሳቁስ እጦት ምክንያት ትምህርታቸውን እንዳያቆርጡ የዊልቸር፣ የክራንች፣ የነጭ በትር እና የጆሮ ማዳመጫ ናቸው ።
ድጋፉ በአዲስ አበባ ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች የተከናወነ ሲሆን በሌሎች ክልሎችም የሚቀጥል መሆኑን የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን ዋና ዳይሬክተር አባይነህ ጉጆ ተናገረዋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ኮሚንኬሽን ኦፊሰር መሳይ ወብሸት ኩባንያው ያደረገው ድጋፍ ማህበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት ያደረገው መሆኑን ተናግረዋል።
26/02/2024
ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ‹‹ለተሻለ ነገ እናንብብ ››የሁለተኛ ቀን መራጭ ደራሲ ዘነበ ወላ ነው፡፡ደራሲው የማንበብ ልምዱን እንዲህ አጋርቷል፡፡
‹‹እኔ 24 ሰዓታት ስራዬ ብዬ የማነብበት ጊዜ አለ፤ ጠዋት ከእንቅልፌ ከመነሳቴ በፊት አነባበለሁ፡፡ ስተኛም እንደዛው፤ በቦርሳዬ ውስጥ የማነበውን ነገር ይዤ ነው የምንቀሳቀሰው፡፡ 24 ሰዓታት ማንንም በስልክ ሳላናግር ልቆይ፤ ሁለት እና ሶስት ቀን አልፎም ሳምንት ከቤት ሳልወጣ ላነብ እችላለሁ፡፡ ››
ደራሲ ዘነበ ወላ ህዝቡ ቢያነባቸው ደስ የሚለኝ የምንግዜም ምርጥ መፅሃፍት ምርጫዎቼ በማለት የሚከተሉትን ዘርዝሯል፡፡
1 ፍቅር እስከ መቃብር፡- ሀዲስ አለማየሁ
2 ከአድማስ ባሻገር ፡- በዓሉ ግርማ
3 የታንጉት ምሥጢር፡- ብርሃኑ ዘርይሁን
እንደተወዳጁ ደራሲ ዘነበ የማንበብ ትልቁ ጥቅሙ አንብበህ የራስህን ሃሳብ ማሰብ እንድትችል ማድረጉ ነው፡፡ ስታነብ ደስታን ትገበያለህ፤ ቋንቋህ ያድጋል በሃሳብ ትመጥቃለህ፤ በአንድ ጉዳይ በአንድ አቅጣጫ ብቻ ከማሰብ ትወጣለህ፤ እውነትህን በእራስህ እምነት ልክ ብቻ ከማየት መላቀቅ የምትችለው ስታነብ ነው ይላል፡፡
እርስዎም የራስዎን ምርጥ 3 መፅህፋት መርጠው ያጋሩ
14/02/2024
15ኛው አለም አቀፍ የምልክት ቋንቋ ጉባኤ በ2017 ዓም በኢትዮጵያ እንደሚካሄድ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በቀጣዩ አመት ዓለም አቀፍ የምልክት ቋንቋ ጉባኤን ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ለማዘጋጀት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ጉባኤው ከጥር 6 እስከ 9 ቀን 2017 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።
ስምምነቱን የተፈራረሙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ትብብሩ ጉባኤውን በተሳካ መልኩ ለማካሄድ የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰዋል።
በዚሁ ወቅት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ የዓለም የምልክት ቋንቋ ጉባኤ በቀጣይ አመት ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ እንደሚካሄድ ተናግረዋል።
ይህንን ተከትሎ ሚኒስቴሩ ጉባኤውን ከብሔራዊ መስማት ከተሳናቸው ማህበርና ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለማካሄድ ዝግጅት መጀመሩን ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው የኢትዮጵያን ስም ከፍ የሚያደርጉና የአገራትን ትስስር ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራትን ዩኒቨርሲቲው እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህ ረገድ ጉባኤው በኢትዮጵያ እንዲካሄድ የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።
የዩኒቨርሲቲው ምሁራን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በመተባበር ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን የሚጠበቅባቸውን ሚና ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
10/02/2024
የኢቢሲ ጋዜጠኛ ኢያሱ ፈጠነ ከዚህ አለም በሞት ተለየ
**************
ለረጅም አመታት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ያገለገለው ጋዜጠኛ ኢያሱ ፈጠነ ከዚህ አለም በሞት ተለየ።
ጋዜጠኛ ኢያሱ ፈጠነ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ በኢቢሲ ከሪፖርተርነት እስከ ከፍተኛ ኤዲተርነት አገልግሏል።
በ1975 ዓ.ም ሰኔ 12 ቀን በወንጂ ሸዋ የተወለደው ኢያሱ በተወለደ በ41 አመቱ በድንገተኛ አደጋ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነ ጽሑፍ በመጀመሪያ ድግሪ የተመረቀው ጋዜጠኛ ኢያሱ ህይወቱ እስካለፈችበት ቀን ድረስ ላለፉት 17 አመታት በሞያው ሀገሩን ሲያገለግል ቆይቷል።
ጋዜጠኛ ኢያሱ ፈጠነ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባትም ነበር።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በጋዜጠኛ ኢያሱ ፈጠነ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለፀ፤ ለቤተሰቦቹ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለስራ ባልደረቦቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
27526