Adi Entertainment

Adi Entertainment

Share

This is Adi Entertainment Page which deals with Art works and Ethiopianism contents.

27/02/2026

ዛሬ የዉስጤን ላጋራችሁ ወደድኩ
ebsታሌቭዥን ሀገራችን ኢትዮጵያ ካሏት ቀዳሚዉና ትልቁ የግል ሚዲያ መሆኑን ይታወቃል። የዚህም ጣብያ መስራችና ስራ አስፈጻሚ አ/ቶ አማን ፍሰሃጽዮ ነበሩ ካጣናቸዉ ቀናቶች ተቆጥረዋል አዳየነዉ አደሰማነዉ እጅግ የሚደነቁ፣ የሚወደዱ፣ የሚከበሩ፣ የሚናፈቁ፣ የማይረሱ፣ የሚመሰገኑ ድንቅ እና ልዩ ሰዉ ነበሩ!! አ/ቶ አማን ዘርተዉት የሄዱት ዘር በበለጠ አፍርቶ እደሳቸዉ ጊዜ ወገንን፣ ሀገርን የማስጠራና የሚጠቅም ፍሬ እደሚሆን አልጠራጠርም! ይህንንም ዘር ተከባክቦ ጠብቆ እዳፈራ የማደርጉት ከፈጣሪ ቀጥሎ ታታሪዋ፣ ጽኑዋ፣ ጀግነዋ ውድ ባለቤታቸዉ ወ/ሮ ማክዳ ፍሰሃጽዮን ይሆናሉ። ወ/ሮ ማክዳ በደረሰበዋት ከባድ ሀዘን ፈጣሪ እስከመላዉ ቤተሰቦዋት ጽናቱን ይስጠዋ። የሚጽናኑትም ከባለቤቶት ጋ በጋራ ያቆማችሁትን ትልቅ ተቋም(ሚዲያ) በጽናት እደትላንትናዉ ከፍ አድርገዉ ወደፊት ሲጋዙ ነዉ አደማደርጉትም ሙሉ እምነቴ ነዉ!

EBS Television is known as one of the first and largest private media outlets in our country, Ethiopia.
Its founder and CEO, Aman Fissehazion, has been gone from us for some days now. We have seen and heard about him—he was truly an admirable, beloved, respected, deeply missed, unforgettable, and praiseworthy person. He was an extraordinary and unique individual.
I have no doubt that the seed he planted will bear even greater fruit, becoming a source of pride and benefit for our people and our country in the days ahead. Protecting and nurturing this seed so that it flourishes will, next to God, be carried forward by his hardworking, strong, and courageous beloved wife, Makda Fissehazion.
May God grant strength and comfort to Mrs. Makda and her entire family during this time of great sorrow. I firmly believe that the greatest comfort will come as she continues, with resilience, to elevate and move forward the great institution (media organization) that you both built together.
#ኢትዮጵያ 💚💛❤

29/01/2026

#ማርታአሻጋሪ ሁሌም እጅግ አድርጌ የማከብርሽ፣ የማደንቅሽ፣ የምወድሽ! ባለዉለታዬ በኔ ልብ ዉስጥ ትልቅ ቦታ አለሽ!! ምንግዜም የማይቀየር! ፈጣሪ እረጅም እድሜ ከጤና ጋ ይስጥልኝ! ዘመንሽ ሁሉ ይባረክ 🙏❣️❣️
Marta Ashagari #ኢትዮጵያ

27/01/2026

#አስቴርአወቀ የሙዚቃ ልኳ የዜማና የግጥም ደራሲ የሙዚቃ ቅንብር ባለጸጋ እጅግ ድንቅ ድምጻዊት❗️ የመድረክ ንግስት❗️የሀገር አልባሳት አበሳደር! የሙያ ጽናት አስተማሪ❗️
ስለሀገርሽ እና ስለ ፍቅር አብዝተሽ በጥበብ አዋዝተሽ የነገርሽን ብቸኛዋ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ንግስት አስቴር አወቀ ላመሰግንሽ እወዳለሁ! አንቺን የማደንቅበት፣ የምወድበት ፣ የማከብርበት እጅግ ብዙ! ብዙ! ምክናቶች አሉኝ! እንኳንም የሀገሬ የ #ኢትዮጵያ ልጅ ሆንሽ! ፈጣሪ የጥበብ አምላክ ዘመንሽን ይባርክ! #እወድሻለሁ ❗️❣️❣️❣️❣️❣️
#ኢትዮጵያ

22/12/2025

#ነጻነትመለሰ #አስራት #ኦርቶዶክስተዋህዶ #ኢትዮጵያ
💚💛❤

21/12/2025

#አስቴርአወቀ የኢትዮጵያን ሙዚቃ በፍቅር፣ በክብር፣ በጽናት ይዘሽ የተጋዝሽ ድንቅ ባለሙያነሽ!! አንቺን የማከብርበትና የማደንቅበት ምክናቶቼ ብዙ ብዙ ናቸዉ! መድረክንም አንቺ አክብራት። 💚💛❤
#ኢትዮጵያ #አስቴርአወቀ❣️❣️
#ኢትዮጵያሙዚቃ

30/11/2025

#ሳያትደምሴፀ❣️❣️

‎ሳያት ውበቷ ትጋቷ፣
‎ሳያት ውበቷ ነው ብርታቷ

| ‎በዚኽ ዐውድ፣ ስለ ሳያት ደምሴ መጠነኛ ማስታወሻ ለማስፈር ወደድኹ፡፡ መነሻዬ፣ በተለይ፣ የማኀበራዊ ብዙኀን መገናኛው የጭቃ ጅራፍ ነው። መቼም፣ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች የታደልነው ማኅበራዊ በጎ የሚካድ አይደለም።

በአኳያውም፣ የታሰበውን ኹሉ በዐፈሣ በሚዋረሱበት ሜዳዊ ባሕርዩ የተነሣ፥ ሮጠን ያልቀደምነውን፣ ጠልፈን ያልጣልነውን፣ አጠልሽተን ያልደበዘዘውን፣ ቀጥቅጠን ያልሰበርነውን ሰብእና… የዘላፊ መንጋ አሰማርቶ ለመውቀጥ የተመቸ 'የባለጌ መማቻ' እንደኾነ አያከራክርም፡፡

‎ሰሞነኛዋ 'ባለተራ' ደግሞ ሳያት ኾናለች፡፡ ያውም ቢያስመሰግን እንጂ፣ ሊያስተች በማይችል ጉዳይ፡፡ በሻሽ የተገኘ ውበት የእናት ምሳሌ በመኾኑ መወደስና መወደድ ይገባው ነበር። ቤት አልባዎችን ጨምሮ ሻሽ የሚያስሩቱ የተዋርዶ ምልክት ተደርገው መታየት አልነበረባቸውም።

በርግጥ፣ በሳያት ላይ የተያዘው የስም ማጥፋቱ ዘመቻ ከጅምሩ ቢከሽፍም፣ በአጋጣሚ በግሌ ስለ ሳያት ማንነትና አኗኗር ከማወቀው ጥቂቱን መመስከሩ ተገቢ ይመስለኛልና ላውጋችኹ፡፡
‎ሞያዊ ስኬቷና ተፈጥሯዊ ውበቷ በስፋት የተነገረለት ስለኾነ እዚኽ በመድገም አላሰለቻችኹም፡፡

‎ያልተነገሩ መገለጫዎቿ ላይ ብቻ አተኩራለሁ፡፡
‎በሳያት ሚዛን(በሕግ ፊት አላልኹም!) ኹሉም ሰው እኩል ነው፡፡ ለሰው ኹሉ ተገቢውን አክብሮት መስጠት መለዮዋ እንደኾነ በቅርበት ከአወቅኋት ጀምሮ የታዘብኹት ነው።

‎ሳያት በብዙ መልኩ ለምሳሌነት የሚበቃ ሰብእና እንዳላት፣ ነቃፊዎቿም ደፍረው አይናገሩት እንጂ፤ አይክዱትም፡፡ እጅግ በሚያስገርም ደረጃ ለሰዎች ደራሽ ናት፤ “ውብዬ ትሙት፣ ማንም ሰው እንዳይሰማ!” ብላ በወላጅ እናቷ ምላ፣ የወዳጆቿን ጎዶሎ ትሞላለች። በእርሷ ዘንድ “ቀኝኽ የሚሰጠውን ግራኽ አይየው፤” የሚለውን ቃለ ወንጌል በንባቡም በትርጓሜውም ኑሮዋ አድርጋዋለች፡፡ “ለነገዬ” የሚል ስስት በመዝገበ ቃላቷ አልሰፈረም። ከቤተሰብ እና ከወዳጆቿ በዘለለ፣ ለማኀበረሰብ ያላት አረዳድ ለፍጽምና የቀረበ ነው። ሰው ቤተሰብ ሲመሠርት ያስደስታታል። “እኛ በሰላም የምንኖረው ጨዋ ቤተሰብ በብዛት ሲመሠረት ነው፤” የሚለው እምነቷ አብሮ አደጓ ነው።

ሥራን ‘ቀላል ወይም ከባድ’ ብላ የማታማርጥ ጠንካራ ሠራተኛ ናት፡፡ ጊዜዋን በሥራ ከማሳለፍ አትቦዝንም። ትዳርን ለሴት ልጅ እንደ “ሥራ ፈጠራ” አድርጎ በደነገገ ሀገር ውስጥ በላጤነቷ ብርቱ ኾና የወጣች ናት፡፡

ምናልባት፣ አንድ ቀን እግዚአብሔር ፈቅዶ የሥራ ባህሏን የሚፈትሽ ፕሮግራም ቢሰናዳ፣ ትጋቷ ከማስገረም አልፎ ለብዙዎች አርኣያ-ሰብ እንደሚኾን አልጠራጠርም። ዛሬ ሳያትን በቅርብ አውቃችኋትም ኾነ ብዙም ሳታውቋት በሩቁ ከጎኗ የቆማችኹ፣ ለሰጣችኋት ድጋፍ መቼም እንደማታፍሩ አረጋግጥላችኋለኹ።

‎ሳያት፣ ውበቷን በተፈጥሯዊ መንገድ የምትጠብቅ ንጹሕ እና ጽድት ያለች ልጅ ናትና፣ የተለያዩ ማስዋቢያዎችን (Makeup) አትቀባም። ቅንድቧን ኦምብሬም ኾነ ማይክሮ ብሊዲንግ አትሠራም፤ እግዚአብሔር ከሰጣት ውጪ አንድም ሰው ሠራሽ አካል አትቀጣጥልም። ኾኖም ደግሞ፣ በአደባባይም ኾነ ከጓደኞቿ ጋራ ስትጫወት፡- “ሌሎች ለምን ይቀባሉ? ይዋባሉ ወይም ለምን እንዲኽ ያደርጋሉ?” የሚል ትችትና ወቀሳ ከአንደበቷ ፈጽሞ አይወጣም፡፡

ይህም ኾኖ፣ ከወጣቶች ጋራ ፕሮግራም ሲኖራት እንደ እነርሱ ለብሳ፣ በአለባበስ እነርሱን መስላ ምቾት መስጠት ትችልበታለች። ሰርግ፣ ልደት፣ ምረቃ… ቦታዎች ስትጠራም ተገቢውን ልብስ ለብሳ አክብሮቷን ማሳየት ታውቅበታለች። ለፀጉሯም ቢኾን ከፈለገች ፍሪዝ ታደርጋለች፣ ሹሩባ አሠራሩንም ታውቅበታለች፣ ዘመናዊ አሠራሩም አልጠፋባትም ወይም ሻሽ ታስራለች።

‎በተረፈ፣ በዚኽ በዲጂታል ሚዲያ ዘመን፥ ጥቂት የማይባሉ ወጣቶች፣ በስክሪን የሚያዩትን ነገር ኹሉ አድርገው ለመታየት አላስፈላጊ ትንቅንቅ ውስጥ ከሚገቡ፣ ሥራቸውን እስከ ሠሩ ድረስ በሻሽም ማማር እንደሚቻል ከሳያት ደምሴ ቢማሩ በእጅጉ ያተርፋሉ።

‎በተጨማሪ፣ የሴቶች ቆዳ በቀላሉ እንደሚጎዳ ልብ ይሏል፡፡ ገና በልጅነት ኬሚካል ባላቸው የተለያዩ ነገሮች ቆዳን ከማሣሣት ይልቅ፣ በተፈጥሯዊ ገጽታው ለመንከባከብ ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ ሳያት ምሳሌ ናት። ሳይንሱም ቢኾን የሚመክረው የእርሷን መንገድ ነው - “ክልሱን ሳይኾን ቱባውን መጠበቅ”።

‎ሳያት የፋሽን ባለሞያ ስለኾነች ‘መዘነጥ ይጠፋባታል’ ተብሎ አይታሰብም። ከሚገባው በላይ ለመዘነጥ ዕድሉም፣ እውቀቱም ዐቅሙም አላት። ግን ከልክ ያለፈ 'ኦቨርድሬስድ' መኾን ምቾት የሚሰጣት አይመስለኝም። በነገራችኹ ላይ፣ ልብስ፥ ጫማ፥ ቦርሳ እና ጌጣጌጥ በእጇ መሥራት የጀመረችው ገና ልጅ ኾና በቤተሰቦቿ ግቢ ውስጥ ነው። ፊልም እና ሙዚቃም ስትሠራ ‘ተገቢ ነው’ ከተባለው ባለፈ፣ ዲሬክተር እና ኮስቲዩም ዲዛይነር አታስቸግርም። አምናበት ከገባች የተባለችውን ለማድረግ ታዛዥ ናት።

‎ይኹንና፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ለወጣቶች ጥሩ አርኣያ የሚኾን ሰው እንዳይኖር የተባለ ይመስል፣ እንከን ቢያጡ ምክንያትና ሰበብ እየፈለጉ ሰዎችን መዝለፍ የተለመደ ቢኾንም የሰሞነኛው ዘመቻ አጋፋሪዎች አልተሳካላቸውም።

‎በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ከሰጡት የሚበዙት ለሳያት ያላቸውን ፍቅር የገለጹበትን መንገድ ስመለከት፣ “ሻሿ” ብለው ለዘለፋ ጣታቸውን የጠቆሙ ግለሰቦች ለሳያት የበለጠ ድምቀት መንገድ ኾነውላታል። በተጨማሪም፣ ሳያትን ከመልኳና ከአለባበሷ ጋራ ብቻ በማያያዝ የድጋፍም የተቃውሞም መለኪያ ማድረጉ ተገቢ አይደለም። እንዲሁም ሳያትን በአለባበሷ ሲያደንቁ፣ ሌሉችን በአለባበሳቸው እየተቃወሙ አድርጎ ማቅረቡም ስሕተት ነው። ለሳያት ድጋፋቸውን የሰጡ ወንዶች ብቻ እንደኾኑ አስመስሎ ማቅረብም አጭበርባሪነት ነው። ሳያትን "በማያስወቅሳት ጉዳይ ስሟን አንሥታችኋል፤” ብለው የተቃወሙ እልፍ ናቸው።

ይህ እንደተጠበቀ ኾኖ፣ ሳያት በትጋቷና በብርታቷ ዛሬ የደረሰችበት (ኢኮኖሚያዊውን ጨምሮ) ስኬት፣ አውሮፓዊ ወይም አሜሪካዊ ብትኾን፣ ዐያሌ ዶክመንተሪ ፊልሞች የሚሠሩላት፣ መጻሕፍት የሚጻፉላት፣ የክብር መነሳንሶች የሚያሸበሽቡላት ማማዊ ምልክት ትኾናለች ቢባል ማጋነን አይኾንም፡፡ አለመታደል ኾነና በእኛ ዘንድ እርሷን የመሳሰሉ ብርቱዎችን ለማሰናከል የሚታትሩ ይበዛሉ።

"ሻሽዬ፤ ሻሽ አበባ" የዕንቁጣጣሽ ዕለት ልጃገረዶቾ የሚዘፍኑት ዘፈን አዝማች ነው። አበባ የሚያብበው ከዕፀዋቱ ግንድ፥ ቅርንጫፍ እና ቅጠል በላይ ነው። ከአበባው በላይ የሚገኝ ፍሬ ብቻ ነው። እናም፣ ሴቶችዬ! ለሳያት አማናዊ ውበቷ በኾነው ትጋቷ እና ብርታቷ እጅግ ብዙ ያልተነገረ ፍሬ-ምግባር ያላት ናትና፣ ደፈር ብላችኹ፡- “እናከብርሻለን! ብርቱዋ እመቤት!” በሏት፡፡

‎በመጨረሻም፣ ብርቱዋ ሳያት ደምሴ ሆይ፡- መጪው ዐዲሱ የአውሮፓውያን ዓመት፣ ብዙ ሥራዎችሽ አደባባይ ወጥተው፣ ማንነትሽ የበለጠ ደምቆ የሚታይበትና የምትመሰገኝበት ይኾን ዘንድ እመኛለኹ።

‎በጣም ከቅርብ ወዳጅሽ (ያው እህት በይኝ) የተጻፈ ማስታወሻ ነው።

/በሥራ ላይ ሥነ ምግባር ምክንያት ስሜን በይፋ ከአለመግለጼ በቀር፣ የጻፍኹትን ነገር አፌን ሞልቼ ለመናገር የማላፍር እንደኾነ ልብ ይባልልኝ/

16/10/2025

እጅግ አድርጌ የማከበረዋት አባታችን ፈጣሪ ይድረስለዋት! በጸሎት ከጎኖዋ ነን :: የምህረት አምላክ የሆነው ፈጣሪ ይማሮዋት! #ሀጅዑመርእድሪስ ( ሙፍቲ)💛 #ኢትዮጵያ

28/09/2025

#አስቴርአወቀ ሁሌም እደምለዉ የሙዚቃ ልኳ ! የመድረክ ንግስቷ የበሀል አባሳደራ ፣ የፍቅር እና የሀገር መልክተኛዋ፣ የዜማ፣ ግጥም ደራሲዋ፣ የሙዚቃ ባለሙየዋ፣ ድንቅ ድምጻዉዊያ! ሳይዛባብሽ ለዘመናት ለሰጠሽን የጥበብ ውጤቶች እናመሠግናለን!! ፈጣሪ ይጠብቅልን!!
ትላንት ቅዳሜ በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀዉ የሙዚቃ ዝግጅትሽ ላይ እጅግ አስደንቀሽናል!! አስለቅሰሽናል። የጥበብ አምላክ ይክፈልሽ! #የኢትዮጵያዬ ልጅ በመሆንሽ ሁሌም እኮራለሁ!! 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
Aster Aweke #ኢትዮጵያ #ኢትዬጵያሙዚቃ #ኢትዮጵያሙዚቃ 💚💛❤

28/09/2025
Photos from Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)'s post 27/09/2025
Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Addis Ababa