CMTV

CMTV

Share

Our Mission: Helping people to reach their Glorious destiny in Christ.

24/06/2026

የመስፋፋት ፀጋ የምንካፈልበት ልዩ ጊዜ የፊታችን አርብና እሁድ ይኖረናል። ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
አርብ ከ9፡00 ሰዓት ጅምሮ
እሁድ የመጀመሪያው አገልግሎት ከ 1፡00 ሰዓት ጅምሮ
የሁለተኛ አገልግሎት ከ 4፡30 ጀምሮ

አድራሻ፡ ላምበረት ከአራራት አደባባይ ወደ ጉርድሾላ ቴሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብሎ https://goo.gl/maps/DN17Cszv2WRhfJjB9

Photos from CMTV's post 22/06/2026

በክርስቶስ ተልዕኮ ቤተክርስቲያን የእሁድ ሁለተኛው አገልግሎት

ርዕሰ :- ፍቅር ለእግዚአብሔር ራዕይ ለአለም

- ለእግዚአብሔር ደስታ፣ ለእግዚአብሔር ክብር ተፈጥረናል ትክክለኛ ህይወት መኖር የምንችለው ለክብሩ እና ለደስታው መኖር ስንችል ነው።

- ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር መለኪያው ቃላቶቻችን ስሜቶቻችን ሀይማኖታዊ እንቅስቃሴዎቻችን አይደለም።

- የፍቅር እውነተኛ ፈተና መልሱ የምንናገረው ሳይሆን የምንኖርበት ህይወት ነው። ዩሀ 14:21

- ታላቁ ትዕዛዝ : - ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን መውደድ ነው።

- እግዘብሔርን መውደድ የህይወት አላማ ነው።

- የተፈጠርነው የእርሱ ልንሆን ነው።

- ለእግዚአብሔር ያለን ፍቅር ለሰዎች የሚሆን ራዕይ እና ርህራሄ ይወልዳል

ታላቁ ተልዕኮ - ፍቅር በተግባር ማለት ነው።

-ፍቅር ስሜት ብቻ አይደለም ፍቅር ይንቀሳቀሳል ፣ይዘረጋል ፣ይሰዋል፣ ያገለግላል።

- ትልቁ የፍቅር ተግባር ክርስቶስን ለሰዎች ማስተዋወቅ ነው ማቴ 28:19

- ታላቁ መሰጠት መስዋትነት ነው ፍቅር ደግሞ ሁልጊዜ ወደ መስዋዕትነት ያመራል ዩሀ 3:16

-እግዚአብሔር ፍቅሩን ከሰማይ ሆኖ በቃል ብቻ አላወጀም ልጁን ሰደደ።

- እውነተኛ ፍቅር እውነተኛ ቁርጠኝነት መሰጠትን ይወልዳል።

- ታላቁ ቸልተኝነት ማድረግ የሚገባንን አለማድረግ ነው።

-ታላቁ ቸልተኝነት አማኞች የእግዚአብሔር በረከት ተቀብለው ነገር ግን ለሌሎች ሳያገለግሉበት ሲቀሩ ነው።

Photos from CMTV's post 22/06/2026

የእሁድ የቅባት ቀን የመጀመሪያ አገልግሎትአ

ርዕስ ለበረከት ሁን

- ለበረከት እንድንሆን ተጠረተናል
- ለበረከት ሁን ማለት ለሌሎች፣ ጥቅም ለእግዚአብሔር ቸርነት ፍቅር መተላለፊያ አንተ እራስህ ሁን ማለት ነው።
- ለበረከት ሁን ስንል እንደ ምርቃትም እንደ ትዕዛዝም የምንወስደው ነው።
- እንደ ምርቃት ስንለው አሜን፣ እንደ ትዕዛዝ ስንለው ደግሞ እሺ ወዴት ማለት ነው።
- መንፈስ ቅዱስ የተልዕኮ መንፈስ ነው።
- ህይወት በእኛ እና በእኛ ዙሪያ ሲሆን እንደክማለን።
- ህይወታችን የተልዕኮ ማዕከል ማድረግ ያስፈልጋል።
- ደስታ ያለው በእግዚአብሔር ውስጥ ነው።
- ለማጸናናት ለመታደግ ተጠርተናል።
- እኛ የአብርሀም ዘር ነን እንደተስፋውም ቃል ወረሾች ነን።
- ወደ ሌሎች ስንሆድ ለሌሎች ስንማልድ ወደሌሎች ስንዘረጋ የእግዚአብሔር ወዳጅ እንሆናለን ህወታችንም የተቀጣጠለ ይሆናል።
- በተልዕኮ ስንኖር እግዚአብሔር ሀይላችን ጉልበታችን ያድሳል መንፈስ ቅዱስን ያፈስልናል።

Photos from CMTV's post 20/06/2026

በክርስቶስ ተልዕኮ ቤተክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ምሽት አገልግሎት

ርዕሰ ፦ ወደ እግዚአብሔር ደስታ ግቡ

- እርሱ የተናገረውን አለመቀበል ማለት የእርሱን አምላክነት አለመቀበል ማለት ነው ።

- ወደ መንግስተ ሰማያት ወደ ፅድቁ መቅረቢያው ( መግቢያዉ ) ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ።

- ወደ አብ መግቢያ መንገዱ ኢየሱስ ነው ።

- ጌታ ኢየሱስን የሚሰማ የዘላለም ህይወት አለው ።

- እዉነት ተገልጧል እዉነትም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ።

- ጌታ ኢየሱስ ያለው ሰው ህይወት፣ እዉነት አለው ።

- ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው ።

- እዉነተኛው ሰው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው አምላክም ነው ።

- ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ የተገለጠ አምላክ ነው ።

- ኢየሱስን አለመዉደድ እርግማን ነው ።

- ጌታ ኢየሱስን ተከተሉት አምላክ ሰው ሆኖ በልቶ ጠጥቶ ተንቀሳቅሶ ኑሮ አሳይቶናል ።

- ኢየሱስ በሚያምኑት ፊት ህያው ነው ተረት አይደለም ።

- ኢየሱስ መድሀኒት ነው ።

- ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ራሱ አለም ሊያስገባን ወደ እኛ አለም ገባ ።

- ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ ሰላም እረፍት ሊያስገባን አምላክ ወደ ምድር መጣ ።

- አምላክ ወደ እርሱ ደስታ ሊያስገባን ኢየሱስ ወደ እኛ አለም መጣ።

- ራሱ እግዚአብሔር የሚኖርበት የእግዚአብሔር ደስታ አለ ።

- የእግዚአብሔር ደስታ ፍፁም ነው።

- ጌታ ኢየሱስን ለሚከተሉት ራሱ እግዚአብሔር የሚኖርበትን ሰላም እና ደስታ ያገኛሉ።

- እግዚአብሔር እዉነተኛ የደስታ ምንጭ ነው ።

- እግዚአብሔር የጋበዘን ወደ ደስታው ነዉ ።

- ኢየሱስን የሚሰማ ሰው የእግዚአብሔርን ፍፁም ደስታ ይቀበላል ።

- የሰማዩን ደስታ የተለማመደ ሰው የምድር ደስታ ምንም ይሆንበታል ።

- በእዚህ ምድር ሚታመን ብናጣ ኢየሱስ ግን መቶ እውነቱን ነግርናል።

- እኛ የተጠራነው ለድነት ብቻ አይደለም ለእግዚአብሔር ሰላም እረፍት ከእግዚአብሔር ጋር ለሚሆን ህብረት ነው።

15/06/2026

የመስፋፋት ኃይል የምንቀበለበት ልዩ የቅባት ቀን!!!
በዚህ በሰኔ ወር ወጥተን የምንወርስበት፣ ገደብ የሚነሳበት እና ወደ በረከታችን የምንዘረጋበትን መለኮታዊ ቅባት የምንካፈለበት ልዩ ጊዜ።
የፊታችን አርብ ሰኔ 12 ከ9፡00 ሰዓት ጀምሮ
እሁድ ሰኔ 14 በሁለቱም አገልግሎት ማለትም በመጀመሪያው አገልግሎት ከጠዋቱ 1፡00 እንዲሁም በሁለተኛው አገልግሎት ከረፋዱ 4፡30 ጀምሮ ልዩ የቅባት ቀኖች ይኖሩናል።

አድራሻ፡ ላምበረት ከአራራት አደባባይ ወደ ጉርድሾላ ቴሌ በሚወስደው መንገድ ወረድ ብሎ https://goo.gl/maps/DN17Cszv2WRhfJjB9

Photos from CMTV's post 15/06/2026

በክርስቶስ ተልዕኮ ቤተክርስቲያን የእሁድ አገልግሎት

ርዕሰ :- 5ቱ የአክሊል አይነቶች

እግዚአብሔር ለሚወዱት እና ለሚሹት ሁሉ ዋጋ አዘጋጅቶላቸዋል።

1- የህይወት አክሊል :- ህይወታቸውን ለሰጡ ሰዎች የሚሰጥ ነው

- እስከሞት ለመታመን ለጨከኑ ሰዎች የሚሰጥ የከበረ አክሊል ነው። (ራዕ 2:9-11)

2- የማይጠፋ አክሊል :- እያንዳንዱን ምድራዊ ነገር ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ብለን መስዋዕት ስናደርግ እግዚአብሔር ይሄ ስራችን እንዲከተል በመዝገብ ይመዘግበዋል

- ራሳቸውን ስለ ፍቅሩ ስለመንግሥቱ ስለ እርሱ ሲሉ የካዱ አምላካችን እግዚአብሔር ያዘጋጀላቸው የከበረ ሽልማት ነው። (1ቆሮ 9:25)

3- የደስታ አክሊል :- ሰዎችን ወደ ጌታ የሚያመጣ የሚያፀና የሚያገኘው አክሊል ነው።

- ሰዎችን በማገልገል የምናገኘው ነው። (ፊሊ 2:15)

4- የክብር አክሊል

- ክብሬን ጥቅሜ ሳይል ለሚያገለግል የሚሰጥ የክብር አክሊል ነው።

በእናንተ ኀላፊነት ሥር ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ የምትጠብቁትም ከእግዚአብሔር እንደሚጠበቅባችሁ በግድ ሳይሆን በፈቃደኝነት፣ ለጥቅም በመስገብገብ ሳይሆን ለማገልገል ባላችሁ ጽኑ ፍላጎት ይሁን፤ እንዲሁም በዐደራ ለተሰጣችሁ መንጋ መልካም ምሳሌ በመሆን እንጂ በላያቸው በመሠልጠን አይሁን። የእረኞች አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማይጠፋውን አክሊል ትቀበላላችሁ።
1 ጴጥሮስ 5፥2-4

5- የፅድቅ አክሊል :- የኢየሱስ ክርስቶስን ዳግም ምፅአት በጉጉት በመጠባበቅ ለሚኖሩ ሰዎች የሚሰጥ ነው።

- ሁሉን ነገር ጌታ ኢየሱስ እንደሚመጣ ታሳቢ በማድረግ በእውነት በፅድቅ ለሚኖሩ የተዘጋጀ ነው። (2ጢሞ 4:8)

Photos from CMTV's post 13/06/2026

በክርስቶስ ተልዕኮ ቤተክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ምሽት አገልግሎት

ርዕሰ ፦ ገደቡ ተነስቷል

📌 ወደ ቀኝ ወደ ግራ እንዳትስፋፉ የገደባችሁ ገደብ ተነስቷል ።

📌 እግዚአብሔር ወደ ሰፊ ስፍራ ያወጣችኃል ።

📌 ለመስፋፋት ህጋዊ መሰረት አለን ።

📌 ገደብ ማለት መንፈሳዊ እርግማን ማለት ነው ።

📌 እርግማን ማለት አንድን የተደረገ ወይም የተወረሰ ሀጢያትን ተከትሎ የሚሰራ ስዉር ገደብ ሀይል ነው ።

📌 እርግማን ከሰው ዉድቀት ማግስት በሰዉ ላይ እና የሰው በሆነው ነገር ሁሉ ላይ ከሰው ተቃራኒ የሚሰራ ስዉር እና ገዳቢ ሀይል ነው ።

📌 በህይወታችን ያለውን ገደብ አዉቀን በክርስቶስ የተሰራልንን ስራ አዉቀን ይህን እዉነት ልንቀበል ይገባል ።

09/06/2026

እግዚአብሔር አምላክ በዚህ ወር እደተናገረን በአገልግሎታችን በስራችን እንዲሁም በህይወታችን መስፋፋት ለታወጀበት ለሰኔ ወር እንኳን በሰላም አደረሰን!

የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 6 ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ በክርስቶስ ተልዕኮ ቤ/ክ ለCM ቴሌቪዥን የወንጌል ማህበረተኞች የተዘጋጀ ልዩ የትምህርትና የፀሎት ጊዜ ከፓስተር ዶ/ር ተስፋሁን ሙሉዓለም ጋር ይኖረናል።
እርሶም የፊታችን ቅዳሜ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ እንዲገኙና እግዚአብሔር ለአብሮ ሰራተኞች የያዘውን ልዩ የመስፋፋት ጸጋ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።

ማሳሰቢያ፡ ይህ ፕሮግራም ለCMTV ፓርትነሮች ብቻ የተዘጋጀ ነው!

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address


Ararat Round About To Gurd Sholla 1 Street
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 18:00
Tuesday 08:00 - 18:00
Wednesday 08:00 - 18:00
Thursday 08:00 - 18:00
Friday 08:00 - 19:00
Saturday 08:00 - 18:00
Sunday 07:00 - 15:00