Sheger mereja

Sheger mereja

Share

Info. This page is dedicated to all users... I will broadcast International and National news and articles for the users

Photos from Sheger mereja's post 16/06/2026

የባሕል ሙዚቃ ድምጻዊው ሰማኸኝ በለው ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ።
***
ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ውልደቱ በ1960 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ እንደኾነ የሕይወት ታሪኩ ያስረዳል።

አጼ ሠርፀ ድንግል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እና በፋሲሎ መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ተምሯል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በጣና ሐይቅ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምሯል።

በሙዚቃ ሥራው በግሽ ዓባይ ጀምሮ በ1982 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በታንጎ ሙዚቃ ቤት እና በኤሌክትራ ሙዚቃ ቤቶች አማካኝነት የሙዚቃ አልበሞችን ሠርቷል።

ከአንቱዬዋ እስከ ባላገሩ ዘፈኖቹ በሕዝብ ዘንድ የሚታወቀው ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው በካዛንቺስ የራሱን የባሕል ቤት ከፍቶ እንደነበርም ተነግሯል።

ከሙዚቃ በተጨማሪ በትወናው ሥራ ተሳትፎ የነበረው ድምጻዊው የባላገር ፍቅር፣ አላበድኩም/ ያዥኝ፣ ደቦት እንሥራ፣ ዲስካው፣ አውዳመት፣ አለሽ ነገር እና ዝናቡን የመሳሰሉ ዘፈኖችን ሠርቷል።

ሀገራዊ እና ማኅበራዊ ኀላፊነቶች ላይ ንቁ ተሳታፊ የነበረው የባሕል ድምጻዊው ሰማኸኝ በለው በ58 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ሥርዓተ ቀብሩ ለቤተ ክርስቲያኑ ብዙ አስተዋጽኦ ባበረከተበት እና ቀደም ብሎ ባዘጋጀው የቀብር ቦታ በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ወዳጆቹ፣ የሙያ አጋሮቹ እና ቤተሰቦቹ በተገኙበት ተፈጽሟል።

የአርቲስቱ የመታሰቢያ ፕሮግራምም የፌደራል እና የአዲስ አበባ ከተማ የባሕል፣ ስፖርት እና ኪነ-ጥበብ ተቋማት ኀላፊዎች ጋር በመነጋገር ይዘጋጃል ተብሏል።

Photos from Sheger mereja's post 15/06/2026

አሳዛኝ ዜና‼️
***
ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲሄድ በነበረ ተሽከርካሪ በደረሰ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታውቋል።

አደጋው የደረሰው ከደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች መካከል በሚገኘው የሐረጎ መንገድ ላይ ነው። ሰኔ 08/10/18 ዓ.ም ማለዳ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ የሕዝብ አውቶቡስ በተለምዶ ሐረጎ እየተባለ በሚጠራው መንገድ ላይ በደረሠበት አደጋ እስካሁን የ28 ሰው ሕይወት ሲያልፍ በርካቶች ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባተቸዋል።

የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው በግምት100 ሜትር ጥልቀት ወዳለው ገደል ገብቶ ነው አደጋው የደረሠው።
በሕይወት የተረፉትን ወደ ሕክምና ቦታ ለማድረስ አሁንም ርብርብ እየተደረገ መኾኑን የገለጸው ፓሊስ የአደጋውን ምክንያት በመጣራት ላይ ነው ብሏል።
# አሚኮ

13/06/2026

✨ ቅዴዎቼ እንዴት አደራችሁ✨
🌞☕️😁ተ.ሰ.ብ.ሰ.ቡ!!!🌞☕️😁
🤔"ሰው ሁሉም እያለው ምንም እንደሌለው ባክኖ የሚቀረው ትኩረት ሲያጣ ነው።"
✍️ እራስህን ሰብስብ፤ ትኩረትህ ላይ አተኩር፤ ትክክለኛውን፣ አስፈላጊውንና ወሳኙን ነገር ያለ እረፍት ፈልግ። ትኩረትህን የትም እየጣልክ፣ በተባለው ሁሉ እየደነገጥክ፣ ላየኸው ሁሉ አስተያየት እየሰጠህ፣ በማያገባህ ሁሉ ጣልቃ እየገባህ መባከንህን አቁም።
💫💫
አዎ! በመሩት መመራት ብርቅ አይደለም ይልቅ ብርቁ መምራት ነው፤ በተከፈተ በር መግባት አዲስ አይደለም ይልቅ አዲሱ በር እየከፈቱ ማስገባት ነው፤ አድናቂና ደጋፊ መሆን ብዙ ጥረት የሚፈልግ አይደለም ይልቅ ዋናው ጥረትና ትጋትን የሚፈልገው ተደናቂና ተወዳጅ መሆኑ ነው። ይህን አለኝ ያንን የለኝም ማለቱን አቁምና ባለህ ነገር ፍሬ ማፍራት ጀምር። ማንም ሲነዳህ እየተነዳህ፣ ማንም አውቅልሃለሁ ባይ ሁሉ የነገረህን ትርክት እያመንክ፣ አንዱ ከመሬት ተነስቶ ሌላውን የሚያጠለሽና የሚያጥላላ ነገር ሲያነሳ እያዳመጥክ፣ ትኩረትህን እዚህም እዛም እየበተንክ፣ ለደቂቃዎች እራስን ሰብስቦ፣ ውስጥን አረጋግቶ መኖር እያቃተህ የተለየ ነገር በህይወቴ ይከሰታል ብለህ እንዳትጠብቅ።

አዎ! ጀግናዬ..! ተሰብሰብ፤ እራስህን ሰብስብ፤ ትኩረትህ ላይ አተኩር፤ ትክክለኛውን፣ አስፈላጊውንና ዋሳኙን ነገር ያለእረፍት ፈልግ። ትኩረትህን የትም እየጣልክ፣ በተባለው ሁሉ እየደነገጥክ፣ ላየሀው ሁሉ አስተያየት እየሰጠህ፣ በማያገባህ ሁሉ ጣልቃ እየገባህ መባከንህን አቁም። ምርታማነትህ (productivity) የሚያሳስብህ ከሆነ ትኩረትህን አጥብቀህ ጠብቀው፤ የእውነት በህይወትህ ላይ ተጨባጭ ነገር ማምጣት የምትፈልግ ከሆነ ብክነትህን ቀንስ፣ እራስህን ወደ አንድ አቅጣጫ ሰብስበው፣ ሃሳብህን ፈር አስይዘው፣ ለእንቅስቃሴህ ትርጉም ፈልግለት። ቀላል ህይወት በምኞት ሳይሆን በከባድ ልፋትና ጥረት የሚመጣ ነው። ገና ከጅምሩ የትኩረት አቅጣጫውን በሚገባ ያልተረዳ ሰው ስለህይወቱ ቅለትና ክብደት ከመጨነቁ በፊት የትኩረቱን አቅጣጫ ማስተካከል ይኖርበታል።

አዎ! እስከመቼ በተበታተነ ሃሳብ፣ በተበታተነ መርህ ህይወትህን እንደምትመራ እራስህን ጠይቅ። እውቀቱ፣ ጥበቡ፣ ማስተዋሉ እያለህ ስለምን ከውጤት ጎዳና እንደራክ፣ ስለምንስ ህይወትህን በአግባቡ መምራት እንደተሳነህ እራስህን መርምር። እንደምትችል ማንም ያውቃል፣ ጉብዝናህን ማንም ይመሰክራል፣ ብዙ ችሎታ እንዳለህ ማንም ይናገራል፣ ነገር ግን በችሎታህና በጉብዝናህ ምንም የተለየ ውጤት ስታመጣ አትታይም። ትኩረትህን መሰብሰብ ባለመቻልህ ብቻ ሙሉ ህይወትህን እያባከንክ እንደሆነ አስተውል። ሁሉ ነገር እያለህ ምንም እንደሌለው ምስኪን ሰው መኖር ይብቃህ። ያለህን ሁሉ በትኩረት አሟጠህ ተጠቀመው፣ በስጦታህ ማሾፍ አቁምና አይንህን ወደ ጥራትና ውጤታማት አዙር። ትኩረትህን ሰብስብ፣ ስጦታህን ተጠቀም፣ የህይወት ደረጃህንም ከፍ አድርግ።
ምርጥ ጽሁፍ✍️
*
ቅዴዎቼ ተ.ሰ.ብ.ሰ.ቡ!!!🌞!!! ሰናይ ቅዴ፡፡🌞
ሰኔ 06 ቀን 2018 ዓ/ም
*

12/06/2026

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ
***
ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው ሰው በመሆን አዲስ የዓለም ታሪክ አስመዝግቧል።

ይህ ታሪካዊ ክስተት ሊመዘገብ የቻለው የስፔስ ኤክስ ኩባንያ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ የሕዝብ አክሲዮን (IPO) ሽያጭ በማድረጉና የኩባንያው ዋጋ ወደ 1.77 ትሪሊዮን ዶላር ከፍ በማለቱ ነው።

የኩባንያው ስኬት የኢሎን መስክን የግል ሀብት ከ1.1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ እንዲሻገር ያደረገው ሲሆን፥ የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋነቱንም በፅኑ አስጠብቆለታል።

ይህ ስኬት በንግዱ፣ በቴክኖሎጂውና በሀብት ፈጠራ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ የተከፈተበት ቅጽበት ሆኖ ተመዝግቧል።

Photos from Sheger mereja's post 11/06/2026

ዛሬ የሚጀምረው ተናፋቂው የዓለም ዋንጫ‼
***
በመላው ዓለም በጉጉት የሚጠበቀውና ከምድር ታላላቅ የስፖርት ሁነቶች አንዱ የሆነው የዓለም ዋንጫ ዛሬ በይፋ ይጀምራል።

ይህ ታላቅ መድረክ ልዩ ልዩ ሀገራትን፣ ባህሎችንና በቢሊዮን የሚቆጠሩ የእግር ኳስ አፍቃሪያንን በአንድነት የሚያስተሳስር ልዩ የደስታ በዓል ነው።

በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስት ሀገራት — አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጋራ ይህንን ውድድር ያስተናግዳሉ።

ይህ ታሪካዊ እትም፣ የእግር ኳስን ዓለም አቀፋዊ ዕድገትና ሰዎችን የማስተሳሰር አስደናቂ ኃይል የሚያሳይ፣ በታሪክ እጅግ ግዙፍ እና ታላቅ ዓላማ ያነገበ የዓለም ዋንጫ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ከቦነስ አይረስ ጎዳናዎች እስከ አዲስ አበባ መንደሮች፣ ከአውሮፓ ከተሞች እስከ አፍሪካና እስያ ገጠራማ አካባቢዎች፣ የመላው ዓለም እግር ኳስ አፍቃሪያን ዓይኖች አሁን ወደ አንዱ ታላቅ መድረክ አቅንተዋል።

ለሚቀጥሉት ሳምንታት፣ ሀገራት ለላቀው የእግር ኳስ ክብር በሚያደርጉት ፍልሚያ፣ መላው ዓለም በጋራ ይደሰታል፣ አብሮ ይጨነቃል፣ እንዲሁም አብሮ ያልማል።

የዓለም ዋንጫ ከእግር ኳስ ውድድር በላይ ነው፤ ጀግኖች የሚወለዱበት፣ ክብረ ወሰኖች የሚሰበሩበት እና ታሪክ የሚጻፍበት መድረክ ነው።

ውድድሩ ሲጀመር በቢሊዮን የሚቆጠሩ አድናቂዎች የሚጠይቁት አንድ ጥያቄ አለ፦

🏆 የዘንድሮውን የዓለም ዋንጫ ማን ያነሳ ይሆን?

Photos from Sheger mereja's post 07/06/2026

The Hermit የሚለውን የዶ/ር ራምፓን መጽሐፍ ያነበበ
👇
በቲቤት ሰማይ ላይ የታየው አስደናቂውና አስፈሪው የደመቀ ቀይ ብርሃን
***
ከሰማይ ወደ መሬት ሳይሆን ከመሬት ወደ ጠፈር የሚተኮሰው ያልተለመደው መብረቅ።

ቲቤት በደቡብ ምዕራብ ቻይና የምትገኝ፣ ከኔፓል፣ ህንድ እና ቡታን ጋር የምትካለልና እጅግ ሰፊ በሆነው የኪንግሃይ-ቲቤት እምብርት ላይ ያለች ከፍተኛ ተራራማ ቀጠና ናት።

በአማካይ ከባህር ጠለል በላይ ከ4,000 እስከ 5,000 ሜትር ከፍታ ላይ በመገኘቷ "የዓለም ጣሪያ" (Roof of the World) በሚል ስያሜ ትታወቃለች።

በዚሁ ልዩ ስፍራ በቅርቡ በቲቤት ሻናን ክልል በሚገኘውና ከባህር ጠለል በላይ ከ5,000 ሜትር በላይ ከፍታ ባለው ፑማ ዩምኮ ሐይቅ (Lake Puma Yumco) አቅራቢያ በተከሰተ ኃይለኛ የነጎድጓድ ማዕበል ላይ እጅግ አስደናቂ እና አስፈሪ የሆነ የበራ ቀይ የብርሃን ምሰሶ ብልጭታ በቪዲዮ ተቀርጾ ወጥቷል።

የሳይንስ ልብ-ወለድ ፊልም የሚመስለውና "ሬድ ስፕራይትስ" (Red Sprites) በመባል የሚታወቀው ይህ ክስተት፣ ልክ እንደ ግዙፍ የባህር እንስሳ ቅርፅ ያላቸው የብርሃን ዘንጎች ወደ ጠፈር ሲዘረጉ ታይቷል።

ክስተቱን በከፍተኛ ጥራት የቀረጸው ዶንግ ሹቻንግ የተባለ የቻይና የሥነ-ፈለክ ተመራማሪና ፎቶግራፍ አንሺ ሲሆን፤ ክስተቱ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።

ይህ ክስተት በተለምዶ እኛ ከምናየው መብረቅ እጅግ በጣም የተለየ ሲሆን የሚከሰተውም ከምድር ገጽ ከ50 እስከ 90 ኪሎ ሜትር ከፍታ ባለው የከባቢ አየር ክፍል ላይ ነው።

ከታች ባለው ደመና ውስጥ በጣም ኃይለኛ የሆነ የኤሌክትሪክ ብልጭታ ሲከሰትና ከደመናው በላይ ባለው የላይኛው ከባቢ አየር ላይ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ መስክ ሲፈጥር የሚመጣ ነው ተብሏል።

Photos from Sheger mereja's post 07/06/2026

"የሕክምና ልብሴ ልጄን ከስቃዩ አልሸፈነልኝም😭" ዶ/ር
***
"ዶ/ር የሮም ጌታቸው እባላለሁ።ከስድስት ዓመት በላይ በህክምና ሙያ ውስጥ ሕሙማንን በማከም፣ የተሰበሩ ቤተሰቦችን በማጽናናት እና ለብዙዎች ተስፋ በመሆን ኖሬያለሁ።በስራዬ ምክንያት ብዙ ወላጆች በልጆቻቸው አልጋ አጠገብ ሲያለቅሱ አይቻለሁ፣ብዙ ሰዎች ሕይወትን ለማትረፍ ሲታገሉ ተመልክቻለሁ። ዛሬ ግን ያ አባት እኔ ሆኛለሁ😭😭

የ3ዓመት ከ6 ወር ህፃን ልጄ በአጥንት ካንሰር ተጠቅቶ ከባድ የህክምና ፈተና ውስጥ ይገኛል። በየቀኑ ህመሙን ሲታገል ማየት፣ የልጄን ስቃይ እያየሁ ምንም ማድረግ አለመቻሌ ልቤን ይሰብረዋል።እንደ ሀኪም የበሽታውን ስም አውቃለሁ።እንደ አባት ግን የልጄን ህመም እሸከማለሁ😭

ልጄ ሕይወቱን ለማትረፍ ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ ልዩ የአጥንት ቀዶ ጥገና እና ተከታታይ ህክምና ማድረግ ያስፈልገዋል። ለዚህም ከ3.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተጠይቆብናል።

እኔ ሀኪም መሆኔ፣ ህዝቤን ለበርካታ አመታት በቅንነት ማገልገሌ ይህን ወጪ ለመሸፈን አላስቻለኝም።ሌሎችን የምናክም እጆቻችን፣ የራሳችንን ልጆች ለማዳን ሲያንሱ ማየት እጅግ ያማል!

የሕክምና ልብሴ ልጄን ከስቃዩ አልሸፈነልኝም። የዶክተርነት ማዕረጌም የልጄን ህመም አላስቆመውም።ዛሬ በፊታችሁ የቆምኩት እንደ ዶክተር ሳይሆን፣ልጁን ለማጣት የሚፈራ አባት ሆኜ ነው።

ውድ ወገኖቼ እባካችሁን ልጄ የመኖር እድል እንዲያገኝ፣በድጋሚ ሳቁን እንዳይ በአቅማችሁ የምትችሉትን እርዳታ እንድታደርጉልኝ እጠይቃለሁ።
ለእናንተ ትንሽ የሚመስለው አስተዋፅኦ ለልጄ ግን ሕይወት ሊሆን ይችላል።ሌሎችን ለማከም የቆምኩት እኔ ዛሬ ግን የራሴን ልጅ ለማዳን የወገኖቼን እጅ እጠብቃለሁ😭
ምንም ባታደርጉ እንኳ #ሼር በማድረግና በፀሎት አስቡት🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

#አካውንት ዶ/ር የሮም ጌታቸው
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ- 1000149557982
አባይ ባንክ - 2091011011819814
አዋሽ : 013201344371300
ቴሌ ብር: 0910119336
: https://www.gofundme.com/f/help-tsegabe-fight-cancer?lang=en_US&ts=1780047340

06/06/2026

✨ ቅዴዎቼ እንዴት አደራችሁ✨
🌞☕️😁መርዘኛውን አስወግዱ!!!🌞☕️😁
✍️ የማስተዋል ስንፈት ያለበት ሰው መርዘኛውንና አጋዡን ለይቶ የመኖር ብርታቱ ሊኖረው አይችልም። ከልክ በላይ መታገስ፣ ራስን ያለአግባብ መበደል፣ መርዘኞችንም እያዩ እንዳላዩ መሆን እያንዳንዳቸው የራሳቸው ጥልቀት ያለው አሉታዊ ውጤት አላቸው። ጀግናዬ! ራስን መግዛት መርዘኛውን ከመቁረጥ ይጀምራል፤ ዛሬውኑ መስመርህን አጥብቅና መርዘኛውን አስወግድ።
💫💫
በዙሪያችሁ ካለው መርዘኛ ሰው ጋር እየኖራችሁ፣ ንጹህና ጤናማ ህይወትን ለመኖር አትሞክሩ፤ ልባችሁ እንዲያርፍ አትመኙ። ለመጣላችሁ መርዛማ ቃልና ስሜት ሁሉ ቦታ አትስጡት። ትናንት በበደሏችሁ፣ ዛሬ አቅማችሁን በሚያዳክሙና ነገን በጨለማ በሚስሉባችሁ ሰዎች አትከበቡ። መርዘኛ ሰው ትልቁን አቅማችሁን የሚበላ፣ አስባችሁ እንዳታደርጉ፣ አቅዳችሁ እንዳታከናውኑ በጥርጣሬ ሰንሰለት የሚያስራችሁ የህይወት ጠንቅ ነው። እያስተዋላችሁ ወደፊት እንዳትራመዱ ወደኋላ የሚጎትታችሁ፣ በውጤት እንዳትከበቡ በውድቀትና በትችት ወሬ የሚያደነዝዛችሁ እባብ ነው። የማስተዋል ስንፈት ያለበት ሰው መርዘኛውንና አጋዡን ለይቶ የመኖር ብርታቱ ሊኖረው አይችልም። ከልክ በላይ መታገስ፣ ራስን ያለአግባብ መበደል፣ መርዘኞችንም እያዩ እንዳላዩ መሆን እያንዳንዳቸው የራሳቸው ጥልቀት ያለው አሉታዊ ውጤት አላቸው። ጀግናዬ! ራስን መግዛት መርዘኛውን ከመቁረጥ ይጀምራል፤ ዛሬውኑ መስመርህን አጥብቅና መርዘኛውን አስወግድ።

አዕምሯችሁን ከነሱ አሉታዊ ትንፋሽ ነፃ አውጡት፣ ከውስጥ ለሚመጣው ብርሃን የበረከት በር ክፈቱ። ሁላችንም የህይወታችን መጨረሻ ግብ የተሻለ ስፍራ መድረስ ነውና ውጤቱ ከመምጣቱ በፊት በሰዎች መርዛማ ወሬ አትድከሙ፤ ግባችሁን ሳትመቱ በተስፋ መቁረጥ ቅዠት ውስጥ አትውደቁ። ልባችሁን ግዙ፣ ፍላጎታችሁን ጨብጡ፣ የምትቀርቡትን ሰው እርከን አብጁለት። አንዳንዶች ከማበረታታት በላይ ማዳከም ይቀላቸዋል፣ አንዳንዶች ካንተ ስኬት በላይ ያንተን ስብራት ማየት ይናፍቃቸዋል። እናንተ ከማን ጋር ናችሁ? ከሚያሳድጓችሁ ወይስ ካላችሁበት ከሚያወርዷችሁ? መርዘኛን ሰው እያቆዩ ስኬትን መመኘት በሀሳብ ብቻ ቤት ለመገንባት የመሞከር ያህል ከንቱ ነው። ማብቂያ በሌለው የሰው አሉታዊ ወሬ አትዋጡ፣ እንደነገሩ በሆነ የውሸት ወዳጅነትም ራሳችሁን አታጥምዱ።

አዎ! ጀግናዬ..! ማሰብህ ካልቀረ በትልቁ አስብ፣ ለመርዘኞችም ምንም ገደብ ሳታበጅላቸው ከህይወትህ ገፅ ላይ ፍቃቸው። ከአንተ የሚወጣው በጎ ሀሳብ ማንም የማይሰጥህ ትልቁ ሀይልህ ነው፤ ይህንን ሀይልህን መርዘኞች እንዲበዝብዙት አትፍቀድ። በትላልቅ ሀሳቦች ተሞልተህ ሳለ መርዘኛ ሰው አጠገብህ ካለ፣ ሀሳብህ መሬት ላይ ሳይወርድ በጥርጣሬ የመቅበሩ እድሉ ሰፊ ነው። የነሱ የጥርጣሬ ሸክም ወደ ጥልቁ ሊጥልህ እንደሚችል አስተውል። ህይወትህን በጥርጣሬ ሳይሆን በእምነት ሙላው፣ ጉዞህን በርቀት ሳይሆን በቅርበት ተከታተለው። ደስታህን በራስህ ሀሳብ ፍጠረው፣ በአዕምሮህ ሰላምን አስፍን፣ ውስጥህን በመረጋጋት ሙላው። ያ ያማረው ትልቁ ሀሳብህና ህልምህ ውጤት ያመጣ ዘንድ ዛሬውኑ መርዘኛውን አስወግደህ ጉዞህን ቀጥል።
ምርጥ ጽሁፍ✍️
*
መርዘኛውን አስወግዱ!!! ሰናይ ቅዴ፡፡🌞
ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ/ም
*

Photos from Sheger mereja's post 05/06/2026

የእህታችንን ህይወት እንታደግ 😥
***
እህታችን ብርሀን ወ/ተንሳይ ተሠማ የተባለች የሁለት ልጆች እናት የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ልጆቿን ያለ አባት እያሳደገች ትገኛለች።

እህታችን ብርሀን ከዚህ ቀደም ባጋጠማት የኩላሊት ህመም ህክምና እየተከታተለች የምትገኝ ቢሆንም በአሁን ሠዓት ህመሙ ተባብሶ ሁለቱም ኩላሊቶቿ ፌል በማድረጋቸው ዳያሊስስ ማድረግ እንዳለባት በሀኪም ተወስኗል።

በአሁን ወቅት ካለው የዋጋ ውድነት አንጻር ለዳያሊስስ የሚሆን ገንዘብ ባለመገኘቱ ያለ አባት የአሳደኳቸው ልጆቼ ያለ እናትም ሊቀሩ በመሆኑ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያግዘኝ ስትል ጥሪ አቅርባለች።

✍️ ብርሀን ወ/ተንሳይ ተሠማ
👉ንግድ ባንክ 1000177197207
👉አቢሲኒያ ባንክ 22582507

02/06/2026

የሸዋልዑል መንግስቱ
***
የዛሬ 49 አመት በለጋ የወጣትነት ዘመኗ በተወለደች በ32 አመት በኢሕአፓ ነጭ ሽብር የግፍ ግድያ በጥ.ይ.ት ተደብድባ በሰባራ ባቡር ግንቦት 18,1969 ዓ/ም የተገ.ደ.ለችው ጋዜጠኛ : ገጣሚ : ደራሲ : ባለቅኔ : ፀሃፈ ተውኔትና የሴቶች መብት ተከራካሪ ሃረር ጃርሶ ( ኤጀርሳ ጎሮ) ያፈራቻት እንቁ የኪነጥበብ ባለሙያ የሸዋሉል መንግስቱ ለኢትዮጵያ የዘመናዊ ሙዚቃ እድገት ቁልፍ ፈር ቀዳጅ ባለሙያ ስትሆን የኢትዮጵያ ስመ ጥር አንጋፋ ተወዳጅ ድምፃዊያን በደራሲ የሸዋሉል መንግስቱ ምርጥ የዘፈን ግጥምና ዜማ ድርሰቶች ክብር እንዲያገኙ : እንዲወደዱ ሆነዋል። ለምሳሌ :-
☞ለድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ
♪ አካም ነጉማ
☞ለድምፃዊ ሙሉቀን መለሰ
♪ጀመረኝ
♪ትዝታ
♪ህልም ሆነሽ ቅሪ
♪ጉብል ቀዘባ
♪የምንጃር ሸጋ
♪በእኔ ሞት
♪ውብ አበባ
♪መውደድሽን ብታውቂው
♪ባይሽ ደስ ይለኛል
♪ከሴት እሷ ብቻ

☞ለድምፃዊ መሀሙድ አህመድ
♪አሸወይና
♪ትዝታ
♪ኦሆሆ ገዳማ
♪ስደተኛ ነኝ
♪እንዴት ነሽ ገዳዎ
♪መላ መላ
♪አታውሩልኝ ሌላ
♪መቼ ነው
♪ሳምራዬ

☞ለድምፃዊ አሊ ቢራ
♪ አዋሽ
♪ወይ ሆቢ ሆቢ

☞ለድምፃዊት አስናቀች ወርቁ
♪ እህ ልበል
♪ሰላ በልልኝ

☞ለድምፃዊ አያሌው መስፍን
♪ ሄደች ጋራ ዞራ
እና ሌሌችን ተጠቃሽ ስራዎቿ ናቸው። ገጣሚ ደራሲና ጋዜጠኛ የሽዋሉል መንግስቱ በኢትዮጵያ ሬዲዬ ሰጥታው ከነበረው ቃለመጠይቅ ውስጥ ከፊሉን ከራሷ አንደበት እናዳምጠው 📻
@ Negash Qemant

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Addis Ababa