Glorious Life Church
The gospel of Jesus Christ is the only solution for man kind, so keep following us as we follow Jesus Christ. You are blessed.
“እርሱም፣ “እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?” አላቸው። ስምዖን ጴጥሮስም፣ “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” በማለት መለሰ።” ማቴ 16:15-16
“ he asked. “Who do you say I am?” Simon Peter answered, “You are the Messiah, the Son of the living God.”” Matt 16:15-16 NIV
26/06/2026
📢 የልዩ አምልኮና የቃል ፕሮግራም ግብዣ! 📣
የፊታችን እሁድ ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ፣ የተወደዱ የእግዚአብሔር ሰው መጋቢ ገረመው በቀለ ከሃገረ ስዊድን በስፍራው ተገኝተው በድንቅ የእግዚአብሔር ቃልና መንፈስ ያገለግሉናል።
የጌታ እጅና ጸጋ በታላቅ ሁኔታ በሚገለጥበት በዚህ ልዩ ዕለት፣ በአካል ተገኝተው የአምልኮቱና የበረከቱ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ በክብር እንጋብዝዎታለን!
📅 ቀን፦ እሁድ ሰኔ 21/2018 ዓ.ም
⏰ ሰዓት፦ ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ
📍 ቦታ፦ የክብር ሕይወት ቤተ ክርስቲያን
26/06/2026
🌟 « . . . አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ ብትፈልጉት ታገኙታላችሁ። »
— ዘዳግም 4:29
🙌 ሁላችሁም በክብር ተጋብዛችኋል! 🙌
የማለዳውን በረከት አብረን ለመቀበል፣ በጋራ የምንጸልይበትና የምንበረታበት ልዩ ሰዓት ተዘጋጅቶላችኋል።
📅 ቀን፦ ነገ ቅዳሜ፣ ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም
⏰ ሰዓት፦ ከጠዋቱ 12:00 - 2:00
📍 ቦታ፦ በኤክሰለንስ ዶም አዳራሽ
⚡️ >>>>>>>>>
25/06/2026
✍️ የእምነት መንፈስ (The Spirit of Faith) — ክፍል 17
🔥 የእምነት መንፈስ ምንጮች 🔥
"አመንሁ፤ ስለዚህም ተናገርሁ" (2ኛ ቆሮ. 4፥13) ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ እውነተኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት ዝም አይልም፤ ያምናል፣ ይናገራልም! ነገር ግን ይህ እምነት የሰው የፈጠራ ውጤት፣ አዎንታዊ አመለካከት (Positive attitude) ወይም ዝም ብሎ ግትር የሆነ የልብ ቁርጠኝነት አይደለም። እውነተኛ እምነት የሚመነጨው የእግዚአብሔር ቃል ወደ ልብ ሲገባ ከሚፈጠር መንፈሳዊ እርግጠኝነትና ከክርስቶስ ቃል ነው (ሮሜ 10፥17)። በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የእግዚአብሔርን ቃል "መስማት" ማለት ድምፅን ወደ ጆሮ ማስገባት ብቻ ሳይሆን፣ ቃሉን ማዳመጥ፣ መረዳት፣ በደስታ መቀበልና መታዘዝ ማለት ነው። የእግዚአብሔር ቃል የእርሱን ማንነት፣ ፈቃድና ኃይል የሚገልጥ በመሆኑ፣ ቃሉን ስንሰማና ስናሰላስል የቃሉ ትርጓሜ ያበራልናል፣ እምነትንም በልባችን ውስጥ ያነቃቃል (መዝ. 119፥130)። በመሆኑም በማንኛውም አስቸጋሪ ሁኔታና ፍርሃት ውስጥ እንኳ ብንሆን፣ የእግዚአብሔር ቃል በልባችን ሲኖር ጸንተን የእምነትን ቃል እንድንናገር ኃይል ይሆነናል (መዝ. 116፥10)። ዛሬ ልባችንን ለእግዚአብሔር ቃል እንክፈት፤ የእምነት መንፈስም በውስጣችን ይንገሥ! 🙌📖
#የእምነትመንፈስ #የእግዚአብሔርቃል #እምነት
24/06/2026
የፋውንዴሽን አንድ (Foundation 1) ተማሪዎች የምርቃት መርሐ ግብር በታላቅ ድምቀትና መንፈሳዊ ድባብ ተካሂዷል።
በዕለቱም የእምነት መንፈስ (The Spirit of Faith) — ክፍል 16ን እንዲህ ተምረናል:-
"አመንሁ፤ ስለዚህም ተናገርሁ" (2ኛ ቆሮ 4፥13) በሚለው መለኮታዊ እውነት ላይ የተመሠረተው የእምነት መንፈስ፤ በመከራና በተቃራኒ ሁኔታዎች መካከል እንኳ ሳይቀር መታመናችንን፣ መናገራችንን እና መጽናታችንን እንድንቀጥል የሚያደርግ የውስጥ ጽኑ ኃይል ነው ። እምነት ያለንበትን ተጨባጭ እውነታ ወይም ችግር በጭፍን አይክድም፤ ነገር ግን “እግዚአብሔር እኔ ከማየው ነገር ሁሉ በላይ ይበልጣል” ብሎ ያምናል ። ይህ መንፈስ እንደ ፍርሃታችን ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ቃል እንድንናገር ንግግራችንን የሚቆጣጠር ሲሆን ፤ እንደነ አብርሃም፣ ዳዊትና ደም ይፈሳት እንደነበረችው ሴት ሁኔታዎችን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ቃል እንድንመለከት ያደርገናል ። በመጨረሻም፣ ነገሮች በዘገዩና በቆዩበት ጊዜ ሁሉ ተስፋ ሳይቆርጥ በትዕግስትና በጽናት የሚያስኬድ በመሆኑ፣ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ የሚያልፍ የእምነት ሰው ሁልጊዜ ተስፋ ሳይቆርጥ ይናገራል፣ የተስፋውንም ቃል ይወርሳል ።
የፋውንዴሽን አንድ ተማሪዎች ምርቃት፣ ተመራቂዎቹ በቃሉ እውነት ታንጸው ለቀጣዩ መንፈሳዊ ዕድገትና አገልግሎት ራሳቸውን ያዘጋጁበት ታሪካዊ ዕለት ሆኖ አልፏል!
#የእምነትመንፈስ #የፋውንዴሽንአንድምርቃት #የእግዚአብሔርቃል #የምርቃትዘገባ #ጽናትናእምነት
22/06/2026
ነገ ማክሰኞ ሰኔ 16 2018 ከምሽቱ 11፡45 ጀምሮ ድንቅ ጊዜ ይኖረናል። በአካል ተገኝተው አብረውን ጌታን እንዲያመልኩ በክብር እንጋብዛለን።
21/06/2026
ቸርች እንዴት ነበር?
(How was Church?)
"...እምነት አይክድም..."
“ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ ...”
— 1ኛ ጴጥሮስ 4፥11
✍️ በሕይወት ዘመን ውስጥ ሁሉን ነገር የሚያንቀሳቅስ ኀይል የእምነት መንፈስ ነው። በእምነት ጉዞ ውስጥ ያለንበትን ሁኔታ ወይንም እውነታ መካድ አይደለም። እምነት ችግር የለም ብሎ በጭፍን አይዋሽም ይልቅስ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል የሚደቃ ነው።
እምነት የእኛን ንግግር መቆጣጠር ያለበት ሲሆን፤ አማኞች መናገር ካለባቸው የሚናገሩት መሆን ያለበት እንደ እግዚአብሔር ቃል ነው እንጂ እንደ ፍርሃቶቻችን መሆን የለበትም።
ታዲያ በእምነት ጉዞ ውስጥ እምነት በትዕግስት መቀጠል አለበት። እምነት ነገሮች በዘገዩበት እና በቆዩበት ጊዜ ሁሉ በጥንካሬ እና ተስፋ ሳይቆርጥ መቀጠል አለበት። በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ቢያልፍ ጽናት እና ትዕግስት አለው።
ለዚህ የእምነት ሕይወት ተምሳሌት አብርሃም የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል በማመን ተቃራኒ ሁኔታዎች ሳይመለከት ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር አመነ። እንዲሁም ዳዊት ደግሞ በእግዚአብሔር ኪዳን ላይ የነበረውን መታመን አሳየ፣ ደም ይፈሳት የነበረችው ሴት ያመነችውን እምነት ንግግር ቀጥሎም በተግባር ያመጣ ነበር።
በመጨረሻም የእምነት መንፈስ ከእግዚአብሔር እውነት የሚመነጭ የውስጥ ጽኑ እምነት ሲሆን፤ አማኞች በመከራና በተቃራኒ ሁኔታዎች መካከል እንኳ ሳይቀር መታመናችንን መናገራችንን መፅናታችንን አለማቆም ነው።
“የእግዚአብሔርን ቸርነት በሕያዋን ምድር አይ ዘንድ አምናለሁ።”
— መዝሙር 27፥13
ቀን እሁድ 14/10/2018
⛪️ የክብር ሕይወት ቤተክርስቲያን
አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ
መልካም የመነሳትና የማብራት ምሽት
21/06/2026
በክብር ሕይወት ቤተክርስቲያን የዱናሚስ የማላጅ እናቶች የጸሎት ሕብረት “ታላቋ ሴት” በሚል መሪ ቃል 7ኛ ዓመታዊ ክብረ በዓሉን በታላቅ ድምቀት አክብሯል!
ሴቶችንና እናቶችን ማዕከል ባደረገው በዚህ ፕሮግራም ላይ በርካታ እንግዶች የተገኙ ሲሆን፣ በመንፈሳዊ ዝማሬና በበረከት የተሞሉ ታላላቅ መልዕክቶች ተላልፈዋል ፦
የዕለቱ ዋና ዋና መልዕክቶች፦
- ሬቨረንድ ዶ/ር ተዘራ ያሬድ (የቤ/ክ መሪ)፦ በብሉይና በአዲስ ኪዳን እንዲሁም በታሪክ ውስጥ ማህበራዊና ባህላዊ አጥሮችን ሰብረው በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ተፅዕኖ የፈጠሩ ሴቶችን (እንደ ማርያም፣ ዲቦራ፣ አስቴርና ጵርስቅላ ያሉትን) በመጥቀስ፣ ሴቶች በጸሎት፣ በአመራርና በወንጌል አገልግሎት ያላቸውን ታላቅ ሚና አብራርተዋል ።
- መጋቢ ቁምነገር ተፈራ (የሕብረቱ መሪ)፦ ታላቅነት ከውስጥ ወደ ውጪ የሚገለጥ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ባለው ጥልቅ ግንኙነት፣ በማይናወጥ እምነትና እግዚአብሔርን በመፍራት የሚገነባ መሆኑንና ይህም ለቤተሰብ፣ ለቤተክርስቲያንና ለሀገር ጠቃሚ ሴት እንደሚያደርግ አስተምረዋል ።
- ዶ/ር ሚካል (ተጋባዥ እንግዳ)፦ “አገልግሎት ምን ይጠይቃል?” በሚል ርዕስ ሰዎችን ከጨለማ ወደ ብርሃን ለማምጣት እግዚአብሔርን ማወቅ፣ መታዘዝ፣ ምሳሌያዊ ሕይወት መኖርና ፈቃድን ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሔር መስጠት እንደሚገባ ገልጸዋል ።
- መጋቢ ትምኒት (ከደቡብ አፍሪካ)፦ “በታላቅነት መቀጠልና ማሸነፍ” በሚል ርዕስ ከቃሉና ከመንፈሱ ጋር ሕብረት በማድረግ ሕይወታችን ከአንዱ ክብር ወደ ሌላው ክብር እንደሚጨምር አጋርተዋል።
- ነብይት ብርሃን፦ የታላቋ ሴት ውበቷ ጌታን መፍራቷ፣ ብድራትን ሳትጠብቅ መልካም ማድረጓ፣ በመከራ መፅናቷና በትክክለኛ ቦታ ትክክለኛ መፍትሄ የምትመርጥ የነቃች ሴት መሆኗ እንደሆነ አስተምረዋል ።
ፕሮግራሙ በታላቅ የጸሎትና የጸጋ መካፈል ጊዜ፣ በምሳ ማዕድ እንዲሁም በማጠቃለያው የኬክ መቁረስ ስነ-ስርዓት ተካሂዶ በሰላም ተጠናቋል ።
19/06/2026
የፊታችን እሁድ ሰኔ 14 2018 ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ ከተወደደው መንፈሳዊ አባታችን ሬቨረንድ ዶ/ር ተዘራ ያሬድ ጋር ድንቅ ጊዜ ይኖረናል። በዕለቱም በአካል ተገኝተው አብረውን ጌታን እንዲካፈሉ በክብር እንጋብዛለን።
19/06/2026
🌟 « . . . አምላካችሁን እግዚአብሔርን በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ ብትፈልጉት ታገኙታላችሁ። »
— ዘዳግም 4:29
🙌 ሁላችሁም በክብር ተጋብዛችኋል! 🙌
የማለዳውን በረከት አብረን ለመቀበል፣ በጋራ የምንጸልይበትና የምንበረታበት ልዩ ሰዓት ተዘጋጅቶላችኋል።
📅 ቀን፦ ነገ ቅዳሜ፣ ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ.ም
⏰ ሰዓት፦ ከጠዋቱ 12:00 - 2:00
📍 ቦታ፦ በኤክሰለንስ ዶም አዳራሽ
⚡️ >>>>>>>>>
18/06/2026
✍️የእምነት መንፈስ፦ ማመን እና መናገር! (ክፍል - 15)✍️
“አመንሁ፤ ስለዚህም ተናገርሁ” (2 ቆሮ 4፥13) ተብሎ እንደ ተጻፈ ፣ እውነተኛ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት በልብ ከመረዳት አልፎ በአፍ የሚነገር ሕያው ኃይል አለው። ይህ የእምነት መንፈስ ትኩረታችንን ከጊዜያዊው መከራ ወደ ዘላለማዊው የእግዚአብሔር ክብር በማዞር በድካምና በጭንቀት ውስጥ ደግፎ ያቆመናል ። መተማመኛችን በራሳችን ላይ ሳይሆን በክርስቶስ ትንሣኤና በእግዚአብሔር ታማኝነት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ፣ ሙሉው የእምነት ፍሰት ከቃሉ መገለጥ (መስማት) ይነሳና በልብ መረዳት፣ በእምነት መናገርና በጭንቀት ውስጥ በመጽናት አልፎ የእግዚአብሔር ኃይልና የኢየሱስ ሕይወት በግልጽ እንዲታይ ያደርጋል ። ስለዚህ ሁኔታዎችን ሳይሆን የማይታየውን ዘላለማዊ እውነት እየተመለከትን ሁልጊዜ የእምነትን ቃል እንናገር!
#እምነት #የእምነትመንፈስ #የእግዚአብሔርቃል #የክርስቶስትንሣኤ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the place of worship
Telephone
Website
Address
Haile G/Selasie Street
Addis Ababa
GLC