Muroed-QR

Muroed-QR

Share

ይህ የግቢ ጉባኤ ተመራቂዎችገፅ ነው ቤተሰብ ይሁኑ !! Telegram channel https://t.me/victorygibiGC2010
ቤተሰብ ይሁኑ !!

31/07/2022

የመንግስት ዜና አገልግሎት ቅጥፈት
~~~~~~~~~~~~~~~~~~

ቅድስት ቤተክርስቲያን ያለአዋጅ የምታደርገው ጸሎተ ምህላ (የምስጋናም ይሁን የልመና) የላትም።

ቢኖራትም በመላው አለም ካላት አብያተክርስቲያናት በሙሉ ተነጥላ በአንዱ አጥቢያ ብቻ የምትፈጽመውም የምስጋናም መርኃግብር አካሂዳም ሆነ ፈጽማ አታውቅም። ነገም አታደርገውም።

እስከአሁኗ ሰዓት ድረስ በየትኛውም የቤተክህነት መዋቅርና ሆነ መንፈሳዊ አባት የታወጀ የምስጋናም ሆነ የጸሎተ ምህላ መርኃግብራት የሉም። አልታወጁም።

ይህቺ ቤት ስርዓት ህግ እና መንፈስቅዱስ ያለባት ቤት ናት። የቄሳር ቃል በክርስቶስ ቤት ውስጥ አይፈጸምም።

ቤተመንግስት እና ቤተ ክህነትን እየለየን ወገን

ልክ እንደ ከዚህ ቀድሞ ባሉት ሳምንታት ከሰንበትን በረከት ለማግኘት ፣ቅዱስ ቁርባንን ለመቀበል፣ከስርዓተ ቅዳሴው ኅብረት ለማድረግ፣ቅዱስ ቃሉን ሊማሩ የመጡትን ምዕመናንን የቄሳርን የግብዝነት የአዋጅ ምስጋና አስፈፃሚ አድርገው ማሳዬት ትልቅ ቅጥፈት ነው

መቅደሳችን ለሁለት ጌቶች አትገዛም።

31/07/2022

ዘወትር በቤትህ መጣልን እመርጣለሁ🙏

Photos from Muroed-QR's post 29/07/2022

ገዳዮቻችን ግን ሽንፈታቸውን ሲያስታውሱባት ይኖራሉ!

[ ብጹዕ አባታችን አቡነ ናትናኤል ያስተላለፉት መልዕክት]

| ሰማዕተ ጽድቅ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዘር ቀለም ሃይማኖት ሳይለየን ለኢትዮጵያውያን ሁሉ የመንፈስም የሥነ ልቡናም አሸናፊነት ተምሳሌት ናቸው

እንኳን ለ ብጹዕ አብነ ጴጥሮስ ሰማዕት ለተቀበሉበት መታሰብያ አደረሰን አደረሳቹ

በቅድሚያ የአሸናፊነት ሥነ ልቡናን ተላብሰን አሸናፊውን ሰማዕተ ጽድቅ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ለምናስብበት ለዚህ ዕለት ያደረሰን አምላካችን ይክበር ይመስገን።

ሰማዕተ ጽድቅ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዘር ቀለም ሃይማኖት ሳይለየን ለኢትዮጵያውያን ሁሉ የመንፈስም የሥነ ልቡናም አሸናፊነት ተምሳሌት ናቸው።

እኛ ይህቺን ዕለት ሞተንም በማሸነፋችን ስናስታውሳት ገዳዮቻችን ግን ሽንፈታቸውን ሲያስታውሱባት ይኖራሉ።

ብፁዕነታቸው ለጠላት ቢንበረከኩ ኖሮ ዛሬ እኛ ልጆቻቸው እንዲህ ቀና ብለን የጀግና አካሄድ ባልሄድን ነበር። ለአሸናፊዎች ይዘመራል እንጂ ስለማይለቀስ በሳቸው ሞት እኛ እንዘምራለን እንጂ አናለቅስም።

ይሁን እንጂ ዛሬ የኋልዮሽ የምንሄድ በሚመስል መልኩ እሳቸው በጠላት ጥይት ተደብድበው ቀና ያደረጉትን አንገታችንን እኛ እርበርስ በመደባደብ ስናጎነብስ እንደማየት ምን የሚያሳፍር ነገር አለ? ውድ ወገኖቼ ብፁዕነታቸውን ባሰብን ቁጥር ከሳቸው የምንማረው የሃይማናት፣ የሀገርንና የወገንን ፍቅር ነው ።

ስለሆነም በጥላቻ ወደኋላ ከመመለስ ይልቅ ብፁዕነታቸው እንደ አምላካቸው በደም ዋጋ ያወረሱንን ፍቅር ይዘን ወደፊት እንድንራመድ አምላከ ጴጥሮስ ይርዳን። የሞቱ ወገኖቻችንን ነፍስ ይማር የብፁዕነታቸው በረከት በሁላችንም ላይ ይደር አሜን።

ብጹዕ አብነ ናትናኤል
የምዕራብ ሸ የምሥራቅ ወለጋና የሆሮ ጉድሩ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

27/07/2022

ከቅዱስ አባቴ ጎን ነኝ!!! እናንተስ?💚💛❤😘😍

ለዻዻሳችሁ፣ ለቅዱስ አባታችሁ፣ ያላችሁን ድጋፍ አሳዩና ጠላት ይደንግጥ እስቲ! ከፊታቸው ቅዱስ መንፈስ፣ ከጀርባቸው 80 ሚሊየን ልጆቻቸው አለንላቸው!በውሸት ለተፈበረከ ቅራቅንቦ ጆሮ አንሰጥም!

ሚዲያ ኃይል አለው ባለማዕተቦች፣ ታዘዙ!

27/07/2022

ድምፁን ሳያሰማ እግዚአብሔርን ማስደሰት የቻለ መልካም ሰው ቢንያም መቄዶንያ 💚💛❤
እስኪ ለዚህ ጀግና ላይክ እና ኮመንት ግጩት

Photos from Muroed-QR's post 26/07/2022

ውድ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም፣በጤና፣በሰላም አደረሳችሁ።

ምስል:- ደብረብርሃን ጠባሴ ገብርኤል

25/07/2022

ሐዋሳ ቅዱስ ገብርኤል❤

24/07/2022

ቅድስት አርሴማ በዓለም አደባባይ !

አርሴማን በአንገት በልቧ ይዛ በዓለም አደባባይ በ5000 M የተወዳደረችው ጉዳፍ ጸጋዬ ወርቅ ለኢትዮጵያ አስመዝግባለች።

Photos from Muroed-QR's post 23/07/2022

የሐምሌ ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በአልን ምክንያት በማድረግ በሐዋሳ ገብርኤል ፅዳት ተከናወነ

23/07/2022

ከወለድሽው በኋላ ማኅተመ ድንግልናሽ እንዳይለወጥ አድርጎ የጠበቀሽን አማኑኤልን የወለድሽው እመቤቴ ማርይም ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡

Photos from Muroed-QR's post 23/07/2022

በስልጤ ዞን በአክራሪ ሙስሊሞች ከተቃጠሉ አብያተክርስቲያናት መሐከል አንዱ የሆነው..........

የፃዲቁ አባታችን ገብር ክርስቶስ ቤተክርስትያን ህንፃ መቅደስ የግንባታ ጽዳት ሥራ ተጀምሯል።

እግዚአብሔር ይመስገን!

22/07/2022

ይቅርታ ማድረግ ተሸናፊነት አይደለም!
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
👉ምናልባት ከበደሉ መደጋገም የተነሣ ስንት ጊዜ ይቅር ልበለው ይቅርታ ሳድርገላት አየባሰበት አየናቀኝ አይደለምን?ትል ይሆናል፣ ይህ የጴጥሮስም ጥያቄ ነበር ፣ወንድም ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ልተውለት፣ሰባት ጊው ነውን? ብሎ ሲጠይቅ ጌታችን ሳባ ጊዜ ሰባት ብሎ መልሶለት ነበር።
ማቴ ፩፰፥፳፱) አራት መቶ ዘጠና ጊዜ ብቻ ይቅር በለው ማለቱ ሳይሆን ፍጹም ቢበድልህ ፍጹም ይቅር በለው ሲል ነው። ይኸ ከበዛብህም ወንድምህን ፈጣሪ ይቅር እንዲልህ በምትፈልገው መጠን ብቻ ይቅር በለው። ብሞትም እንኳን ይቅር አልለውም የምትል ከሆነ ግን በሞቱ ይቅር ስላለህ አምላክ ሕማምና መከራ አስብ😢
👉የበደለህ ሰው ምን ቢበድልህ አንደ አይሁድ በመስቀል ላይ ቸንክሮ አልሰቀልህም ኸረ ቸንክሮ ከመስቀል አይተናንስም የምትል ከሆነ ደግሞ ጠላትህ አንደ አይሁድ ቢከፋብህም አንተ ግን አንደ ክርስቶስ ንፁሕ አይደለህም። ንፁህ ክርስቶስ ገና የእሺኸ አክሊሉ ከራሱ ላይ ሳይወርድ የቸንካሩ ምስማር ከእጆችሁ ውስጥ ሳይነቀል፦ አባቴ ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አያለ ሲጮኽ አይታይህምን?
ይቅርታ ማድረግ ተሸናፊነት አይደለም ፣አሸናፊው እግዚአብሔር በመስቀል ላይ ሆኖ ይቅርታን ያደረገውም ኃይል አጥቶ አልነበረም።
💝 አዎ ወዳጄ ለሰራ ኃጢአትህ ሁሉ እግዚአብሔር አምላክ ይቅር እንዲልህ በምትፈልገው መጠን የስቀይምኳቸው ሰዎች ሁሉ ይቅርታን ጠይቅ አንተም በፍጹም ልብህ ይቅር በለው።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
መስጋን ይሁን አንድ አምላክ ለሆነው ለእብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ዛሬም ዘወትር እስከ ዘላለሙ አሜንንን💒🙏💝💛💚
///////////// ቸር 💝 /////////////
/////////////////////////////////////////////////////

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Addis Ababa