DireTube

DireTube

Share

DireTube.com is the #1 Ethiopian Video Sharing Site. DireTube is an Ethiopian media and entertainment website founded on October 26, 2008.

11/06/2026

"ጦርነትን ሳይጀመር ማስቆም የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ የቤት ሥራ ሊሆን ይገባል!!" - ኢዜማ

ሀገራችን በታሪኳ እስከአሁን ድረስ በተለያዩ የኃይል አማራጮች ችግሮችን ለመፍታት እንዲሁም የመንግሥት ሥልጣንን ለመቀየር ስትባዝን አለች፤ ሆኖም የረጅም ዓመት ሀገረ መንግሥት ታሪኳን በማይመጥን መልኩ እስከአሁን ኋላቀር ከሚባሉት ሀገራት ግንባር ቀደም ከመሆን የዘለለ አንዳች ነገር አላገኘችም።

ላለፉት ከ 30 ዓመታት በላይ በሀገሪቱ ውስጥ ላሉ ችግሮች፣ ግጭቶች፣ ጥቃቶች እንዲሁም ሌሎች በርካታ ችግሮች በዋነኛነት ምክንያቱ ደግሞ ሕወሓት ሥልጣነ መንበሩን በኃይል ካረጋገጠ በኋላ ያሠፈነው የብሔር ፖለቲካ ነው። ይኽ የፖለቲካ ሥርዓት ከፍተኛ ችግር ያስከተለ ቢሆንም በሕወሓት ተንኳሽነት የተጀመረው እና ከሁለት ዓመታት በላይ የፈጀው የሰሜኑ ጦርነት ያስከተለውን የሰው ህይወትና የንብረት ውድመት በከፍተኛነቱ የሚስተካከለው የለም።

ከዚህ ጥፋት መልስ በፕሪቶሪያ ስምምነት ከጦርነት መውጣት የተቻለ ቢሆንም ይህ በዘላቂነት እንዳይቀጥል በተለይ ሕጋዊ ማንነቱን ባጣው ሕወሓት በኩል እንደሥምምነቱ እንዳይፈፀም የታዩ ዳተኝነቶች እና እንደ አጠቃላይ የፖለቲካ ሥሪቱ ላይ ውጤት ሊያመጣ የሚችለውን ሀገራዊ ምክክር፣ የ2018 ዓ.ም ምርጫ በትግራይ ክልል እንዳይከናውን በማድረግ፣ በክልሉ የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው እንዳይመለሱ በታጋችነት በመያዝ በአጠቃላይ በክልሉ ያለው ችግር እንዳይፈታ በማድረግ ይኸው ችግር መልሶ ይፈጠር ይሆን የሚል ስጋትን እንደያዘ አለ።

ለትግራይ ማኅበረሰብ እቆረቆራለሁ የሚለው ይህ ቡድን ከእሰጠዓገባ ውጪ መኖር የማይችል በሚመስል መልኩ የተለያዩ ችግሮችን ለመፍጠር እየሞከረ የከረመ ሲሆን ሰኔ 02/2018 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ እና በክልሉ አፀደቀ በተባለው አዋጅ ግልጽ የጦርነት አዋጅን ለፍፏል። በተለይም በአዋጁ ያካተተው አስገዳጅ የወታደር ምልመላ፤ የተለዩ ድምፆች በትግራይ እንዳይሰሙ ያስቀመጠው ልጓም፤ ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር የሚመስለው የፕሮፖጋንዳ ልፈፋ ይኽንን ተፈጥሯዊ ጠበኛ ባሕርዩን እና ፍላጎቱ አሁንም የትግራይን እና አጠቃላይ የኢትዮጵያን ህዝብ በስንት ልፋት ወዳስቆመው ጦርነት እና እልቂት መክተት መሆኑን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው።

በመሰረቱ አዋጁን ማውጣቱ እና በተለይም ከወታደር ምልመላ እና ጦርነቱን ካለመደገፍ ጋር በተገናኘ የተካተቱት ቅጣቶች ማኅበረሰቡ በጦርነቱ ለመሣተፍ ፍላጎት እንደሌለው እና በዚህም ቡድኑ ስጋት ያደረበት መሆኑን በግልፅ የሚያሣይ ነው፤ ይህ ተስፋ የቆረጠ እድሜያቸው የገፋ የሥልጣን ጥመኞች ስብስብ አሁንም በግጭት ውስጥ አፍላ ወጣቶችን የመማገድ ዓላማ አድርጎ ከዚህ ቀደም ልጆቻቸውን ያጡትን እናቶች፤ በስለት ከጦርነቱ የተረፈ የቀረ ልጅ ያላቸውን ጧሪ ቀባሪያቸውን ሊነጥቃቸው አሰፍስፎ መምጣቱ ለትግራይ ህዝብም ሆነ ለሰው ልጆች ሁሉ እንጥፍጣፊ ርህራሄ እንደሌለው ያሳያል። ይህንን ኃይል በቃህ ማለት እና በትግራይ ያሉ ወገኖቻችንን ከማያባራ መከራ መታደግ የሁላችንም ኢትዮጵያውያን የጋራ የቤት ሥራ ሊሆን ይገባል፤ ጦርነትን ሳይጀመር በፊት ማስቆም ይገባናል።

ኢዜማ የትኛውም ፖለቲካዊ ችግር በውይይት መፈታት አለበት ብሎ በጽኑ የሚያምን ሲሆን ይህንን ለማድረግ ፈቃደኛ ያልሆነን እንደ ሕወሓት ዓይነት ደም የማይጠረቃ አካል እና እሱን የሚዘውሩ ጥቂት ግለሰቦች በቃችሁ ብሎ ለማስቆም እና የትግራይ ህዝብን ካላስፈላጊ መከራ ለመታደግ በህዝብ ላይ ምንም አይነት መስዋዕትነት በማያስከትል መልኩ በሕገወጥ ቡድኑ ላይ ብቻ ያነጣጠረ አስፈላጊ ሕጋዊ እርምጃ በመንግሥት እና ከመንግሥት ጋር በጋራ በሚቆሙ ማንኛውም ለትግራይ ማኅበረሰብ በሚቆረቆር አካል ሊወሰድ እንደሚገባ ያምናል፤ ማኅበረሰቡም አሁን ለጦርነት ዕያሣየ ያለውን እምቢተኝነት በተጠናከረ መልኩ እንዲገፋበት ጥሪ እናቀርባለን።

በመጨረሻም በዚህ ሒደት ውስጥ ፓርቲያችን ማኅበረሰቡ እያለፈበት ያለውን ጭንቀት እየኖረበት ያለውን አሰቃቂ ሁኔታ ለመቅረፍ ባለው አቅም ሁሉ በቀጥታ ለማገዝ ከማንኛውም ሀገራዊ ኃይል ጋር በጋራ ለመሥራትና የበኩሉን ለማበርከት ዝግጁ መሆኑን ያረጋግጣል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)
ግንቦት 04/ 2018 ዓ.ም.

Photos from DireTube's post 11/06/2026

1ኛው የኢትዮጵያ 10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር የፊታችን እሁድ በባህርዳር ይካሄዳል

1ኛው የኢትዮጵያ 10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር የፊታችን እሁድ ሰኔ 07 ቀን 2018 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ በታላቅ ድምቀት ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በውድድሩ ቅዶመ ዝግጅት ዙሪያ ለመገናኛ በዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ ቴክኒክ ባለሙያዎች ወደ ባህርዳር በማቅናት አስፈላጊውን ስራ እያከናወኑ ሲሆን ተተኪ አትሌቶችና የውድድር እድል ለመፍጠር ዓላማ ያደረገ መሆኑን በመግለጫው ተገልጿል ።

በውድድሩ ላይ የግል ተወዳዳሪዎችን ጨምሮ ከ6 ክለቦች የተውጣጡ 91 አትሌቶች ይሳተፋሉ ።

በውድድሩ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ለሚወጡ አትሌቶች የገንዘብ ሽልማት የሚበረከት ይሆናል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የውድድርና ተሳትፎ ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ጊዜ አድነው እና አቶ መሐሪ ነጋሽ መግለጫውን በጋራ ሰጥቷል።

ውድድሩ በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን /አሚኮ/ በቀጥታ ይተላለፋል።
(ኢአፌ)

11/06/2026

በ"ቪቫ ሶፍት" የንግድ ምልክት መብት ጥሰት የተጠረጠሩት ግለሰብ ላይ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ የ7 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቀደ

በ"ቪቫ ሶፍት" ምርት ላይ ተፈጽሟል በተባለ የንግድ ምልክት መብት ጥሰት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት አቶ ሰይድ መሐመድኑር ዑመር ላይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት ዛሬ ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተጨማሪ የ7 ቀናት የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ፈቅዷል።

ፍርድ ቤቱ ቀደም ሲል ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ለፖሊስ የ7 ቀናት የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ፈቅዶ ለዛሬ ሰኔ 4/2018 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ በዋለው ችሎት የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ እስካሁን ያከናወናቸውን ተግባራትና የቀሩትን የምርመራ ሂደቶች ለችሎቱ አቅርቧል።

ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ማብራሪያ፣ ድርጊቱ "ፒዩር ዉድ ፐልፕ ኤንድ ፔፐር ፓኬጂንግ" ኃላ/የተ/የግ/ማህበር በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ሕጋዊ የምዝገባ ሰርተፍኬት ቁጥር LTM/3249/2017 የተሰጠውንና በዓለም አቀፍ ምድብ 16 ሥር የሚገኘውን የ"VIVa" (ቪቫ ሶፍት) የንግድ ምልክት ያለ ባለቤቱ ዕውቅና መጠቀምን የሚመለከት መሆኑን አስታውሷል። ተጠርጣሪው ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ የቪቫ ሶፍትን ማሸጊያ ፕላስቲክ ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ አመሳስለው በመሥራት፣ ጥራቱን ያልጠበቀ፣ ፎርጅድ የሶፍት ምርት በአዲስ አበባና በተለያዩ ክልሎች በድብቅ ሲያሰራጩ እንደነበር በመግለጽ፣ ድርጊቱ ሸማቹን የማታለል፣ ጤናማ የገበያ ውድድርን የማዛባትና በመንግስት ታክስ እንዲሁም በኢኮኖሚው ላይ ቀውስ ለመፍጠር ሆን ተብሎ የተፈጸመ ውስብስብ ወንጀል መሆኑን በድጋሚ አስረድቷል።

ባለፉት ቀናት ውስጥ የ4 ሰዎችን ምስክርነት መቀበሉን ያመለከተው ፖሊስ፣ ለኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን፣ ለኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት፣ ለኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ለኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ፣ ለኦሮሚያ ንግድ ቢሮና ለሌሎች ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ተቋማት ወንጀሉን ሊያስረዱ የሚችሉ መረጃዎች እንዲሰጡት ጠይቆ ውጤቱን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

በተጨማሪም ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን እና ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት የባለሙያ አስተያየት ወይም ምስክርነት መቀበል እንደሚቀረው እንዲሁም በክልል መጋዘን ውስጥ ተከማችቶ የሚገኝ ፎርጅድ የሶፍት ምርትን ለመመርመር ጊዜ እንደሚያስፈልገው ፖሊስ አስረድቷል። ተጠርጣሪው በዋስትና ቢወጡ ከባለሙያዎቹ የሚሰጡ ምስክርነቶችን ሊያስቱና ገና ካልተያዙ ግብረአበሮቻቸው ጋር በመሆንም የምርመራ ሥራውን ሊያደናቅፉ ስለሚችሉ፣ የምርመራ መዝገቡን በባለሙያዎች ምስክርነት እና በሰነድ አሟልቶ ለመጨረስ የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።

የግራ ቀኙን ክርክር የመረመረው የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ የጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት፣ የፖሊስን ጥያቄ መርምሮ የ7 ቀናት የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ የፈቀደ ሲሆን፣ በቀጣይ የምርመራ ውጤቱን ለመጨረሻ ጊዜ ለመስማት ለሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
#ድሬቲዩብ

11/06/2026

የአዲስ አበባ ከተማ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ከዛሬ ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአዳዲስ ተሽከርካሪዎች ብቻ እየሰጠ የሚገኘው የአዲሱ ሰሌዳ (ታርጋ) ዋጋ እስከ 56 ሺ ብር እንደሚደርስ ተነግሯል።

​የዋጋ ዝርዝሩ እነኾ:-

​🚗 ለግል (የቤት)፣ ለንግድ፣ ለዲፕሎማት እና ለዕርዳታ ድርጅቶች፦

​በነዳጅ ለሚሰሩ፦ 56,000 ብር

​በኤሌክትሪክ/ጋዝ ለሚሰሩ፦ 44,500 ብር

​🚚 ለድንበር ተሻጋሪ ጭነት፦

​በነዳጅ ለሚሰሩ፦ 28,500 ብር

​በኤሌክትሪክ/ጋዝ ለሚሰሩ፦ 15,200 ብር

​🚕 ለሕዝብ ታክሲ፦

​በነዳጅ ለሚሰሩ፦ 11,700 ብር

​በኤሌክትሪክ/ጋዝ ለሚሰሩ፦ 9,400 ብር

​🚌 ለአውቶቡስ፣ መንግሥት፣ አካል ጉዳተኛ እና ባጃጅ፦

​በነዳጅ ለሚሰሩ፦ 9,400 ብር

​በኤሌክትሪክ/ጋዝ ለሚሰሩ፦ 7,100 ብር

​🏍 ለሞተርሳይክል፦

​በነዳጅ ለሚሰሩ፦ 4,700 ብር

​በኤሌክትሪክ/ጋዝ ለሚሰሩ፦ 3,550 ብር

#ጥያቄ

የአዲሱን ሰሌዳ ተመን (ክፍያ) እንዴት አገኙት?

11/06/2026

በሳዑዲ ዓረቢያ ታሰረው የነበሩ አንድ ሺህ 655 ኢትዮጵያውያን በምህረት እንዲፈቱ ተደረገ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪያድ የሚገኘውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሚሲዮን እና ጂዳ የሚገኘውን ቆንስላ ጽ/ቤት በማስተባበር ባደረገው የዲፕሎማሲ ጥረት በሳዑዲ አረቢያ ለእስር ተዳርገው የነበሩ 1655 ዜጎቻችን የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ እንዲሰጣቸው ተደርጓል።

ይህ ውጤት መንግሥት በውጭ ግንኙነቱ ለዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በሰጠው ትኩረት የተገኘ ነው።

ከዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ አኳያ በሳዑዲ አረቢያ ቀሪ የዲፕሎማሲ ጥረት የሚሹ ጉዳዮችን በተመለከተም ክትትል እያደረገ ነው።

በዚሁ አጋጣሚ መንግሥት ሕብረተሰቡ ከሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በማኅበራዊ ሚዲያ የታጀበ ሀሰተኛ ማታለያ ድርጊት የውጭ አገር ጉዞ ራሱን እንዲጠብቅ እያሳሰበ፤ ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን የሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ደሞዝ እና አዲሱ በጀት? ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ 11/06/2026

ደሞዝ እና አዲሱ በጀት? ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ

ደሞዝ እና አዲሱ በጀት? ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በዛሬው ዕለት ሰኔ 4/2018 ዓ/ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ 2019 ዓ/ም በአዲሱ በጀት ዙሪያ የ...

Photos from DireTube's post 11/06/2026

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት የእርስ በርስ የቁጥጥር ስርዓት መጠናከሩን ገለጸ። በአባላቱ መካከል ያለው የእርስ በርስ የቁጥጥር ስርዓት ሙያዊ የስነ-ምግባር ጥሰቶች በምክር ቤቱ የግልግል ዳኝነት እንዲታዩ እድልም ፈጥሯል።

ምከር ቤቱ የመገናኛ ብዙሃን የእርስ በርስ የቁጥጥር ስርዓትን ይበልጥ ለማጠናከር እና ተደራሽነቱን ለማስፋት ከጂአይዜድ ኢትዮጵያ (GIZ Ethiopia) ጋር በመተባበር በርካታ ውጤታማ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል። በዛሬው ዕለትም በጂአይዜድ ኢትዮጵያ ድጋፍ የተዝጋጀ ምከር ቤቱንና ስራዎቹን ለማስተዋወቅ የሚያግለግሉ የመልቲ ሚዲያ ውጤቶች ርከከብ ተካሂዷል፡፡

በጀርመን መንግሥት ስም እና የጀርመን የልማት ትብብርን (German Cooperation) በመወከል ጂአይዜድ ኢትዮጵያ (GIZ Ethiopia) የመገናኛ ብዙሃን የእርስ በርስ የቁጥጥር ስርዓት እንዲጎለብትና የግልግል ዳኝነት አካል ዋና ተግባራትን ለህብረተሰቡ ለማስተዋወቅ የሚረዱ በርካታ ድጋፎችን አድርጓል፡፡ ከድጋፎቹ መካከልም ህብረተሰቡ በተላለፊ ዜና:ማስታዎቂያና ፕሮግራም ላይ የሚስተዋሉ የሚዲያ የስነ-ምግባር ጥሰቶችን ለምከር ቤቱ ሪፖርት የሚያደረግባቸውን አማራጮች ማስተዋወቅና ተደራሽ ማድረግ ይገኙበታል፡፡

የዚህ አጋርነት አካል የሆነው እና የምክር ቤቱ _ አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆን እንዲሁም የተቋሙን አቅም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚረዳ ድረ-ገጽ በአዲስ መልክ የማዘመን ስራም በስኬት ተጠናቋል።

ምክር ቤቱ ከጂአይዜድ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ከሚዲያ የስነ-ምግባር ጥሰት ጋር የተገናኙ ቅሬታዎች ለምከር ቤቱ የግልግል ዳኝነት አካል በቀላሉ የሚቀርቡበትን አሰራር ለህብረተሰቡ ለማስተዋወቅ በ32 የማህበረሰብ ሬዲዮ እና በአምስት የማህበረሰብ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ማስታወቂያዎችን በተለያዩ ቋንቋዎች ሲያስራጭ ቆይቷል።

የምከር ቤቱን የሰው ሃይል በማጠናከር፣ የቅሬታ ማቅረቢያ ዘዴዎችን በማዘመንና በተለያዩ ቋንቋዎች ተደራሽ በማድረግ፣ የተቋሙን ሎጎና ብራንድ በማሻሻል እንዲሁም የግልግል ዳኝነት አካሉን በማጠናከር ረገድ ከጂአይዜድ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር አመርቂ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

በተሰሩት የሚዲያ ዘመቻዎች ምክንያት ህብረተሰቡ በመገናኛ ብዙሃን ይዘቶች ላይ የታዩ የስነ-ምግባር ጥሰቶችን ለምክር ቤቱ እያመለከተ ሲሆን፤ ምከር ቤቱም በቀረቡት ቅሬታዎች ላይ ውሳኔ እየሰጠባቸው ይገኛል፡፡

በዚህ መሠረት ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 25 ከጋዜጠኝነት የስነ-ምግባር ጥሰት ጋር የተገናኙ ቅሬታዎች ለምክር ቤቱ የግልግል ዳኝነት አካል ቀርበው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ህብረተሰቡ እነዚህን ቅሬታዎች ያቀረበው በህዝብ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች:በንግድ የሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች:በህዝብ የህትመት ጋዜጦች እና በበይነ-መረብ ሚዲያዎች ላይ ነው።

ምክር ቤቱ የግልግል ዳኝነት ስራዎችን በማጠናከር በመገናኛ ብዙሃን ስራዎች ላይ የሚስተዋሉ የሰነ-ምግባር ጥሰቶች እንዲታረሙና ሙያዊ አሰራሮች እንዲጉለብቱ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምከር ቤት የግልግል ዳኝነት አካል ከተለያዩ የሙያ ማህበራት እና የህብረተሰብ ከፍሎች የተወጣጡ 18 አባላት ያሉት ፓናል ነው፡፡

የርክክብ ፕሮግራሙ የተዘጋጀው በጀርመን መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ እና በጂአይዜድ (GIZ) የመልካም አስተዳደር በኢትዮጵያ ፕሮግራም አስተባባሪነት ነው፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት በሥነ ምግባር የታነጸና በሃላፊነት ስሜት ህዝብን የሚያገለግል ሚዲያ በሀገራችን እንዲጎለብት የሚሰራ ተቋም ሲሆን፤ በሕግ ተመዝግበው ፈቃድ የወሰዱ ከ120 በላይ የህዝብ ፤የንግድ፤ የማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃንን፤ የበይነ መረብ ሚዲያንና የጋዜጠኞች ሙያ ማህበራትን በአባልነት በማቀፍ የእርስ በርስ የቁጥጥር ስርዓትን ተግባራዊ እያደረገ የሚገኝ ተቋም ነው።
#ድሬቲዩብ

Photos from DireTube's post 11/06/2026

በ2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የ10.2 በመቶ ዕድገት ያስመዘግባል - አቶ አሕመድ ሺዴ

ኢትዮጵያ ከይፋዊ አበዳሪዎች ጋር የተጀመረው የውጭ ዕዳ ሽግሽግ ስምምነት ወደ ማጠናቀቂያው ምዕራፍ ላይ መድረሱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 25ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የ2019 በጀት ዓመት መነሻ ዕቅድን ለውይይት ባቀረቡበት ወቅት ነው።

የመንግሥትን የውጭ ብድር ጤናማ ለማድረግ በቡድን 20 የጋራ ማዕቀፍ ስር የተጀመረው የዕዳ ሽግሽግ ሂደት በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡበት መሆኑን ጠቅሰዋል።

እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ በዋና ዋና የፋይናንስ መለኪያዎች ላይ የተደረሰውን ስምምነት መሠረት በማድረግ የመግባቢያ ሰነድ የተፈረመ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ከአብዛኞቹ አበዳሪዎች ጋር የሁለትዮሽ የዕዳ ሽግሽግ ስምምነቶች ተፈርሟል።

ከዩሮቦንድ እና ከሌሎች አበዳሪዎች ጋር የሚደረገው ድርድርም ስምምነት ላይ ለመድረስ መቃረቡን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ይህም በየዓመቱ ለዕዳ ክፍያ የሚውለውን የውጭ ምንዛሬ ጫና በመቀነሱ ለኢትዮጵያ የልማት ፋይናንስ ተጨማሪ ሀብት ለማዋል ማገዙን እና የሀገራችን የዕዳ ጫና ስጋት ወደ መካከለኛ ደረጃ ዝቅ እንደሚያደርገው አስረድተዋል።

በመጠናቀቅ ላይ ባለዉ 2018 በጀት ዓመት የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ምርታማነት እና ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን አቶ አሕመድ ጠቅሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አማካኝነት ከግሉ ዘርፍ ጋር በመቀናጀት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ፕሮጀክት መጀመሩን እና በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚከናወነውን የቢሾፍቱ ኢንተርናሽናል አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ፕሮጀክትን በዋነኛነት ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ እየታየ ያለው አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ካለፉት ዓመታት እጅግ የተሻለ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፣ በዚህም መሰረት በ2019 በጀት ዓመትም የ10.2 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት እንደሚመዘገብ ግምት መወሰዱን ተናግረዋል፡፡

11/06/2026

መንግስት ሐምሌ 1/2018 ዓ.ም በሚጀምረው በጀት ዓመት፤ ከታክስ ገቢ ወደ 1.5 ትሪሊዮን ብር ለመሰብሰብ ማቀዱ ታወቀ፡፡

በበጀት ዓመቱ መንግስት ለጠቅላላ ገቢ የውጪ ብድርን ጨምሮ ከ2 ትሪሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ እንዳቀደ ዛሬ ወደ ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎ የሚጠበቀው የፌደራል መንግስት የ2019 የገቢ በጀት ረቂቅ ሰነድ ያሳያል፡፡

በ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት ጠቅላላ ገቢ የውጪ ዕርዳታን ጨምሮ 1.8 ትሪሊዮን ብር እንደሚሆን ተገምቷል የሚለው ሰነዱ ይህም በ2018 በጀት ዓመት ይሰበሰባል ተብሎ ከተገመተው ጠቅላላ ገቢ አንጻር የ17.4 በመቶ እድገት ያለው እንደሆነ ዘርዝሯል፡፡

ከዚህ ውስጥ 1.5 ትሪሊዮን ብር ወይም 82 በመቶው ከታክስ ገቢ እንደሚሆን አስረድቷል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

ጠቅላላ ገቢና ዕርዳታ 1,816,550,478,151 ብር፣

ከምንዳና ደመወዝ 97,346,528,758 ብር ፣

የአገር ውስጥ ቀጥታ ታክሶች 427,487,817,419 ብር፣

ከኪራይ ገቢ ግብር 2,589,596,337 ብር፣

ከኮርፖሬት ድርጅቶች የንግድ ሥራ ገቢ ግብር 263,009,567,243 ብር፣

ከገቢ ዕቃዎች የቅድሚያ ገቢ ግብር 26,627,285,968 ብር፣

ከአገር ውስጥ ቀጥታ ያልሆኑ ታክሶች 277,988,904,983 ብር፣

በአገር ውስጥ ከሚመረቱ ዕቃዎችና አገልግሎቶች የተጨማሪ እሴት ታክስ 225,535,497,927 ብር፣

በአገር ውስጥ ከሚመረቱ ዕቃዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ 113,422,746,069 ብር፣

ነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች 3,639,722,663 ብር፣

ከስኳር 2,362,600,874 ብር መንግስተ ለመሰብሰብ ማቀዱን የ2019 በጀት ረቂቅ ሰነድ ያሳያል።

አጠቃላይ የፌዴራል መንግስት የ2019 ጠቅላላ ወጪ በጀት ብር 2.3 ትሪሊዮን ሲሆን፣ ይህም በ2018 በጀት ዓመት ከፀደቀው የወጪ በጀት አንጻር የብር 411.5 ቢሊዮን ብር ጭማሪ ወይም የ21.3 በመቶ ዕድገት አለው፡፡

የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት ወጪ እቅድን በተመለከተ ደግሞ ለመደበኛ ወጪ 1.2 ትሪሊዮን ብር ፣ለካፒታል ወጪ 568 ቢሊዮን ብር ተመድቧል፡፡

የካፒታል ወጪ በጀቱ ከመደበኛ በጀቱ በግማሽ ያንሳል፡፡

ከቀረበው ጠቅላላ የፌዴራል መንግስት የወጪ በጀት ውስጥ 52.9 በመቶ የሚሆነው ከፍተኛው ድርሻ ለመደበኛ በጀት የተመደበ ነው፡፡

ይህም በ2018 በጀት ዓመት ለመደበኛ በጀት ከተመደበው አንጻር የ16.5 በመቶ ዕድገት አለው።

ከዚህ ጠቅላላ የመደበኛ ወጪ ውስጥ ብር 542.1 ቢሊዮን ወይም 43.8 በመቶ የሚሆነው ከፍተኛው ድርሻ የተደለደለው ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ዕዳ ክፍያ ሲሆን፣ 236.4 ቢሊዮን ብር ወይንም 19.1 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ለማዳበሪያና ለነዳጅ ድጎማ እንዲሁም የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅትን ካፒታል ለማሳደግ የተመደበ በጀት እንደሆነ ሰነዱ አመላክቷል፡፡

520.6 ቢሊዮን ብር ለብሔራዊና ክልላዊ መንግሥታት የበጀት ድጋፍ እንዲሁም 14 ቢሊዮን ብር ለክልሎች ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ የተመደበ በጀት እንደሆነ ተጠቅሷል

የቀጣዩ የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት የተጣራ የበጀት ጉድለት 308.6 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 5.7 ቢሊዮን ብሩ ከውጭ እና 302.9 ቢሊዮን ብሩ ከሀገር ውስጥ የተጣራ ብድር በመውሰድ እንዲሸፈን የታቀደ ነው፡፡

ይህም የተጣራ የበጀት ጉድለት ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ 1.4 በመቶ እንደሆነ ያሳያል፡፡

(ያሬድ እንዳሻው - ሸገር ኤፍኤም)

Photos from DireTube's post 11/06/2026

አዲሱ የተሽከርካሪ ሰሌዳ - ለአዲስ ተሽከርካሪዎች ብቻ ከዛሬ ጀምሮ እየተሰጠ ነው

🔴 የነባር ተሽከርካሪዎች መውሰጃ ጊዜ አልታወቀም፣

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከዛሬ ጀምሮ አዲሱ የተሽከርካሪ ሰሌዳ መሰጠት ጀምሯል።

የከተማዋ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ዘገየ በላይነህ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ፥ ከሴኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ አዲሱ ሰሌዳ ለከተማዋ ተሽከርካሪዎች መሰጠት ተጀምሯል።

በዚህ መሰረትም ተመዝግበው ሲጠባበቁ የነበሩ አሽከርካሪዎች በተመዘገቡበት ቅርንጫፍ በኩል ስልክ ተደውሎ እንዲወስዱ ይደረጋል ብለዋል።

አዲሱ ሰሌዳ የሚሰጠው ለአዳዲስ ተሽከርካሪዎች ብቻ መሆኑንም ነው ዋና ሥራ አስኪያጁ ያስገነዘቡት፡፡

ነባሩን የተሽከርካሪ ሰሌዳ የሚጠቀሙትን በተመለከተ ወደፊት በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በኩል ይፋ እንደሚደረግ አመልክተዋል፡፡

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Addis Ababa