Addotcomplex
addotcomplex is design to be stock
of art, science,
music, video, graphics,
animations,
games and
HTML layout using tables
addotcomplex web design and software development
04/11/2025
18/08/2022
Ydengl mrym lg semu ytbrke yhun
✔ደብረ ታቦር የታሪክ ተራራ
በመጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ
በመላው ዓለም ያላችሁ ውድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች እንኳን ለበአለ ደብረ ታቦር አደረሳችሁ
ደብረ ታቦር ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ለሁለቱ ነቢያትና ለሶስቱ ሐዋርያት ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ታሪካዊ ተራራ ነው።
ጌታችንን መለኮታዊ ታሪክ የሰራባቸው ብዙ ታሪካዊ ተራራዎች አሉ።
ሀ/ ደብረ ሲና
ምሥጢረ ሥጋዌን የገለጠበት የምሥጢር ተራራ ነው
ለ/ ደብረ ቁስቋም
በስደቱ ጊዜ መላእክቱ ክንፋቸውን ዘርግተው ያመሰገኑበት የምስጋና ተራራ ነው።
ሐ/ ደብረ(ገዳመ )ቆሮንቶስ
ሶስቱ ፈተናዎችን እስከፈታኙ ድል ነስቶ አምላክነቱን የገለጠበት የድል ተራራ ነው።
መ/ ደብረ ዘይት
ለሐዋርያቱ ወደሰማይ ሲያርግ ባርኳቸው ያረገበት የወይራ ተራራ ነው።
ሰ / ደብረ ታቦር
ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት የለመለመ ተራራ ነው።
ወደዚህ ተራራ ከነቢያት ሙሴና ኤልያስን ከሐዋርያት ዮሐንስን ያእቆብን እና ጴጥሮስን ይዞቸው ወጥቶ ብርሃነ መለኮቱን ገልጦላቸዋል።
✔ ለምን ከነቢያት ሙሴና ኤልያስን መረጠ ቢሉ?
ነቢዩ ሙሴ በደብረ ሲና መልክህን ማየት እፈልጋለው ብሎ ጠይቆት ነበረና ዛሬ መልኬን አታይም በሇላ ጀርባየን ታያለህ ብሎት ነበረና ጥያቄውን ለመመለስ ነው በተራራ የተጠየቀውን በተራራ ለመመለስ ወደተራራው ወስዶታል።
✔ኤልያስም ተአምር አድራጊ ነቢይ ስለሆነ ጌታችን ታምራቱን አይተው ኤልያስ ነው ብለውት ነበርና ኤልያስ እንዳልሆነ እና የኤልያስ አምላክ መሆንን ለማስመስከር ኤልያስን ከብሄረ ህያዋን አመጣ።
✔ከሐዋርያት ዮሐንስ ያእቆብ ጴጥሮስ ለምን ይዞ ወጣ ቢሉ?
✔ጌታችን ወደተራራው ወጥቼ እነግሣለው ባለ ጊዜ የዮሐንስና የያእቆብ እናት ማርያም ልጆቸን በቀኝና በግራ አንግሥልኝ ብለው ነበረና የጠየቀችውን ጥያቄ ለመመለስ ያእቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወጥቷል
✔ጴጥሮስን ለምን ይዞ ወጣ ቢሉ?
ጌታችን ሰዎች ማን ይሉኛል ባለ ጊዜ ?
ጴጥሮስ አንተ የአብ የባህርይ ልጁ ኢየሱስ ነህ ብሎት ነበረና ብርሃነ መለኮቱን ገልጦ አምላክነቱን ሊያስረደው ወደተራራው ወስዶታል።
ሌሎችን ሐዋርያት ለምን ተዋቸው ቢሉ?
የሐትትዎ ለኀጥእ ከመ ኢይርዓይ
ስብሐተ እግዚአብሔር እንዲል
ኀጢአተኛውን የእግዚአብሔርን ብርሃን እንዳያይ ይከለክሉታል የተባለው ትንቢት ይፈፀም ዘንድ ይሁዳ ብረሃነ መለኮቱን እንዳያይ ነው።
በሱ ምክንያት ስምንቱም በእግረ ደብር ቀርተዋል ለሶስቱ ሐዋርያት የተገለጠው ምሥጢር ለስምንቱ ሐዋርያት ተገልጦላቸዋል ።
ይሁዳን ትቶ ሁሉን ይዞ እንዳይወጣ ከምሥጢሩ ቢለየኝ ከሞቱ ገባሁበት እንዳይል ነው።
ከነቢያት ካገቡትም ካላገቡትም
ከሐዋርያትም ካገቡትም ካላገቡትም ይዞ ወጥቷል።
* ከነቢያት ያገባው ሙሴ
ያላገባው ኤልያስ ነው።
* ከሐዋርያት ያገባው ጴጥሮስ
ያላገቡት ያእቆብና ዮሐንስ ናቸው።
የደናግል የሕጋዉያንም አምላክ እንደሆነ ለመግለፅ ህጋውያንን ደናግላንን ይዞ ወጥቷል
✔አንድም ደብረ ታቦር የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ ናት
መንግስተ ሰማያት የህጋውያንም የደናግልም እንደሆነች ለመግለጽ።
✔አምስት መሆናቸው ስለምን ነው ቢሉ?
ደብረ ታቦር የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ናት
በቤተ ክርስቲያን የሚቀድሱ ካህናት አምስት እንዲሆኑ ስርዓት ለመስራት ነው
✔አንድም በአምስቱ አእማደ ምሥጢር ምሳሌ ነው።
♦ከሞቱት አንስቶ ካሉት ጠርቶ ለህያዋንም ለሙታንም ብርሃነ መለኮቱን የገለፀው
የሙታንም የህያዋንም አምላክ መሆኑን ለመግለፅ ነው።
✔ደብረ ታቦር ከዘጠኙ ዓበይት የጌታችን በዓላት አንዱ ነው
ይህ በአል መለኮታዊ አምላካዊ ላእላዊ ሰማያዊ በአል ነው።
ደብረ ታቦር በእስራኤል ውስጥ የሚገኝ የለመለመ ተራራ ሲሆን በአሉ በተራረው ተሰይሞ ይከበራል
✔ከሌሎቹ ነቢያት ሙሴና ኤልያስን መርጦ ገልጦላቸዋል ምክንያቱም ሙሴ ፊትህን ማየት እፈልጋለው ብሎ ሲጠይቀዉ ገፅየሰ ኢያስተርኢ ለከ ወድህረሰ ትሬኢ ገፅየ ዛሬ ፊቴን አታይም ኋላ ታያለህ ባሎት ነበርና ቃሉን ለመፈፀም ከመቃብር አምጥቶ ደብረ ታቦር ላይ ገለጠለት
ሙሴ መሆኑ በምን ይታወቃል ቢባል በልቱትነቱ
ሙሴ በቤተ ፈርዖን ሲያድግ የፈርኦንን ግፍ አይቶ ንጉሡ ፈርዖንን በጥፊ ተማቶ የሞት ፍርድ ቢፈርድበት
የንጉሡ አማካሪዎቹ ልጅ ነው ምን ያውቃል ብለው እሳት እና ፍትፍት ይቅረብለት እና እሳቱን ትቶ ፍትፍቱን ከበላ ይገደል ክፉና በጎን ያውቃል ፍትፍቱን ትቶ እሳቱን ከጎረሰ ገና ስላላወቀ አይፈረድበት ብለው ፍትፍትና እሳት አቀረቡለት ፈትፍቱን ትቶ እሳቱን ጎርሶ ነበርና አፉ ተብታባ ነበር በዚህ ታውቋል አንድም ሙሴ ገና ሲወለድ ከፊቱ ላይ ብርሃን ተስሎበት ተወልዶ ነበርና በዚህ ታውቋል
ኤልያስ መሆኑ በምን ይታወቃል ቢሉ?
በጠጉሩ
ኤልያስን ዘፀጓር ብእሲሁ ይለዋልና አንድም
ኤልያስ ሲወለድ በእሳት ሰፋድል ተጠቅልሎ ነበር በዚህ ታውቃል
ኤልያስን የመረጠበት ምክንያት ኤልያስ ሲያርግ ከኤልሳዕ በቀር ያየው አልነበረመና በህይወት ማረጉን ለመግለፅ ነው ማቴ17+1
ከመጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ
ነሐሴ 12,/2014
ሆሣዕና ኢትዮጵያ
ETHIO FM 107.8 በፍቅር ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት እንዳይላላ ከልቡ ሊተጋ፣ መከባበርና መተሳሰብ የሚያስቀድም ኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ
28/02/2020
--- ስልካችን ስንጠቀም ማድረግ የሌለብን ነገሮች --
ያንብቡ ለሌላውም ያካፍሉ
♦♦♦
- በዝናብ ሰዓት Networking የሆኑ ነገሮች ማጥፋት( Airplane mode ላይ ማድረግ)
Bluetooth ,main network መብረቅ ይስባል)
- FM (ኤፍ ኤም) (በEarphone) አለማዳመጥ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ስማርት ስልኮች FM Antenna ስለሌላቸው ኢርፎኑን እንደአንቲና ነው የሚጠቀሙት ስለዚህ በኢርፎን ስናዳምጥ Electro magnetic ራዲየሸኑ ጭንቅላታችን ላይ ጉዳት ያደርሳል፡፡
- ስልክን ቻርጅ እያደረጉ ማንኛውንም ነገር አለመጠቀም በተለይ አለመደመጥ ( Wifi አለመጠቀም Gaming አለመጫወት፡፡
-Earphone ሙዚቃ ስናዳምጥ Equalizer በመጠቀም ድምፁን Bass ላይ ማድረግ ( ምክንያቱም Normal ድምፅ ስንጠቀም ያለው ለጆሯችን ቀጭን ድምፅ ስለሚያወጣ ያሳምመናል የHz አለመጣጣም፡፡
- ትልልቅ magnetic field ያላቸውን ነገሮች አቅራቢያ ስልካችሁ አለማስቀመጥ፡፡
- የስልክ እስክሪን Bluelight የሚባል አደገኛ ጨረር ይለቃል በተቻለ መጠን የስልካችንን Brigtness መቀነስ( Blue light Fiter APp መጠቀም)
- የባትሪ ቻርጅ በጣም low ሲሆን ወይም ሲቀንስ ስልኩን ያለመጠቀም ልማድ ይኑርዎ ምክንያቱም ቻርጅ ሲቀንስ የሚረጨው ጨረር መጠን ይጨምራል፡፡
-ሞባይል ሲነጋገሩ ከጆሮዎ የተወሰነ ሴንቲሜትር ራቅ ማድረግ Electromagnetic Radiation ከተባለ ጨረር ራስዎን ይጠብቁ፡፡
- የሞባይል ስልክ ታቅፈው አይተኙ ከአልጋ 1.8 meter ማራቅ ማታ ሲደወል ከሚለቀቀው ጨረር ራስዎን ይጠብቁ፡፡
- ነፍሰጡር ሞባይል ሲይዙና ሲጠቀሙ ይጠንቀቁ የጽንሱ ሕዋሳት ለ Electronics Radiation እጅግ በጣም አለርጅክ ናቸው ስለዚህ አጠቃቀሙ ከጽንሱ ራቅ ባለ ስፍራ ይሁን አላስፈላጊ አጠቃቀምን ለምሳሌ ረዥም ሰዓት ማውራት እና ቶሎ ቶሎ መደዋወል መቀነስ አለብዎ፡፡
- ብረት ነገር ባሉበት ቦታዎች ዙርያ ሞባይል አይጠቀሙ( ብረት የኤሌክትሪክ ማግኔቲክ ራድየሹን ወይም የጨረሩን ጉልበት ያጠነክረዋል( ስለዚህ መኪና ውስጥ አውሮፕላን ውስጥ ሊፍት ውስጥ፡ ባቡር ውስጥ ፡ ጋራጅ ውስጥ ወዘተ አስቸኳይ ወይም አጣዳፊ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር በተቻለ መጠን ሞባይል አይጠቀሙየሚጠቀሙም ከሆነ በአጭር ደቂቃ ብቻ ይሁን፡፡
በተለይ እድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ሞባይልን ባይጠቀሙ ወይም ባያዘወትሩ ይመረጣል፡፡ ጨረሩ የጭንቅላት ሴሎችን በእጅጉ ይጎዳል፡፡ በበለጸጉ ሃገሮች ከ15 ዓመት በታች የልጆች ሞት የሚከሰተው በጭንቅላት እጢ አማካኝነት ነው፡፡
አባክዎ በተቻለ መጠን ራስዎን ይጠብቁ
ሼር/Share
Click here to claim your Sponsored Listing.
Contact the business
Telephone
Address
Addis Ababa
Addis Ababa