Divers Media Network - DMN

Divers Media Network - DMN

Share

This is promoter center....

01/06/2026

የማይታመን! በፒኤስጂ ደጋፊ እግር ላይ የተቀረጸው “የታሪክ አሻራ”!

የጋብሬልን የፔናልቲ ስህተት በሰውነቱ ላይ ያስነቀሰው የፒኤስጂ ደጋፊ አስገራሚ እርምጃ!

የእግር ኳስ ፍቅር ወሰን የለው! አንድ የፓሪስ ሴንት ጀርመን (PSG) ደጋፊ በቻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ጨዋታ ላይ ጋብሬል ማጋሌሽ የሳታትን የፍጹም ቅጣት ምት (ፔናልቲ) ለዘላለም ለማስታወስ የወሰደው እርምጃ የአድናቂዎችን ቀልብ እየሳበ ይገኛል።

ደጋፊው የጋብሬል ማጋሌሽ የቅጣት ምት ሲመታ የሚያሳየውን ገጽታ በግራ እግሩ ላይ ንቅሳት (Tattoo) በማድረግ፣ የዚያን ታሪካዊ ቅጽበት ስሜት በቆዳው ላይ አትሞታል።

በስታዲየም ውስጥ የነበረውን ስሜት በቀጥታ ወደ አካሉ ማዛወሩ የእግር ኳስ አክራሪነት ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ ያሳያል።

ይህ ድርጊት “ከደጋፊነት በላይ የሆነ ፍቅር” የሚባለውን አባባል በተግባር ያሳየ ሆኗል።

የእግር ኳስን ውበት የሚያጣጥሙት የጉርሻ ፔጅ ቤተሰቦች ይህን አጋጣሚ እንዴት ታዩታላችሁ ግን ?

📷ዳጉ ጆርናል

Via: ጉርሻ ፔጅ

01/06/2026

የድምፅ መስጫ ሰዓት እስከ ሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ተራዘመ
***************************

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከማለዳ 12:00 ሰዓት ጀምሮ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ የማስፈጸም ሂደት ላይ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ቦርዱ በሥምሪት ላይ ያለው የክትትል ቡድኑ ያቀረበለትን ሪፖርት መነሻ በማድረግ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በዚህም መሠረት በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 49(4) በተደነገገው መሠረት፤ የምርጫው ነፃና ፍትሐዊነት ይበልጥ ያሰፍናል ተብሎ በመታመኑ የድምፅ መስጫ ሂደት ባልተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እስከ እኩለ ሌሊት 6:00 ሰዓት ድረስ የተራዘመ መሆኑን ቦርዱ አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም የተመዘገቡ መራጮች መርጠው በተጠናቀቁባቸው ጣቢያዎች ላይ አስፈጻሚዎች የድምፅ ቆጠራ ሂደቱን እንዲያከናውኑ ቦርዱ አሳስቧል፡፡

#የኢትዮጵያምርጫ #ምርጫ2018 #የምርጫቦርድ #ኢትዮጵያ

01/06/2026

የደስታ እና የእምባ ምሽት! የአርሰናል እና የ PSG ፍልሚያ ✍️

ይበልጥ በወዳጅነት ለመዝለቅ ኑ የዩቱብ አድራሻችንን ይጎበኙ Subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ 🙏
https://youtube.com/?si=J1UZ76Q4-6KxvbqC

Divers Media Network - DMN

Photos from Divers Media Network - DMN's post 01/06/2026

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

Divers Media Network - DMN

Photos from Divers Media Network - DMN's post 01/06/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በበሻሻ ድምፅ ሰጡ
*******************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በትውልድ ቀያቸው በሻሻ ድምፅ ሰጥተዋል።

31/05/2026

ቲክቶክ ለነገው ምርጫ መዘጋጀቱን ገለጸ

| ቲክቶክ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ የሚናፈሱ ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመግታት እና የፕላትፎርሙን ደህንነት ለመጠበቅ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ይፋ አደረገ።

ማህበራዊ ሚዲያው ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ (NEBE) እና ከተለያዩ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ያስታወቀ ሲሆን፤ የዚሁ ስራ አካል በሆነው የማጣራት እርምጃ በ2025 ማጠናቀቂያ ላይ ብቻ ደንቡን የጣሱ ከ1.8 ሚሊዮን በላይ ከኢትዮጵያ የተቀረጹ ቪዲዮዎችን ማስወገዱን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገልጿል።


​ #ቅዳሜገበያ

Photos from Divers Media Network - DMN's post 31/05/2026

‎በ1950ቹ የተለያዩ አገልግሎቶችን ይሰጥ የነበረው የቴፒ መለስተኛ የአየር ማረፊያ ለብዙ አመታት ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም ከአቬሽን ባለስልጣንና ለሎች አካላት ጋር በመሆን የሸካ ዞን ዳግም ወደ ስራ ማስገባት ችሏል ።

‎በዚህም የመጀመሪያ በረራ ተጠቃሚዎች እንደገለፁት
‎በትራንስፖርት ዘርፍ በሸካ ዞን ከዚህ በፊት ከፍተኛ ችግር መኖሩን ገልፀው አሁን የተጀመረው በረራ ያለውን እንግልት የቀነሰና ለተገልጋዩ ምቹና ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት የሰጠ ነው ብለዋል።

‎በተመጣጣኝ ዋጋ የትራንስፖርት አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውን የተናገሩት መንገደኞች የመጀመሪያ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ በመሆናቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ጠቁመዋል ።

‎የሸካ ዞን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ያለበት በመሆኑ ይህን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግና አካባቢ ላይ ያለውን ምርት ለማስተዋወቅ በረራ አገልግሎት መጀመሩ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ካፕቴን አብረሃም ጆሴፍ ተናግረዋል።

‎የበረራ አገልግሎት መጀመሩ ለሸካ ዞን ብቻ ሳይሆን በአካባቢ ላይ ትልቅ እድል የፈጠረና ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲኖር ያስቻለ መሆኑን የገለፁት ካፒተን አብረሃም ይህም በተመጣጣኝ ዋጋ የቀረበ በመሆኑ መጠቀም አለባችሁ ብለዋል።

‎የፍላይት ቡክንግ አስተባባሪ አቶ ብሩክ በለጠ በበኩላቸው የትራንስፖርት አገልግሎት ለማግኘት booking app የተሰኘውን መተግበሪያ ከአፕስቶር በማውረድ ባሉበት ሆነው ቲኬት መቁረጥ የሚችሉ መሆኑን ተገልጿል ።

‎በዚህም ተገልጋዮች ያለምንም እንግልት መጠቀም መጀመራቸውን የገለፁት አቶ ብሩክ የአካባቢው ማህበረሰብ ይህን አገልግሎት መጠቀም እንዳለበት አሳውቀዋል ።

‎ከዚህ በተጨማሪ ቴፒ ግሪን ኮፊ የፌስቡክ እና ቴሌግራም ገፆች ላይ መረጃዎችን ማግኘት እንደሚቻል ገልፀው ተጠቃሚዎች የሚኖራቸውን አስተያየት በዚህ ላይ ማስቀመጥ እንደሚችሉም ተናግረዋል ።

‎በረራው ሰኞ እና አርብ ከሳምንት ሁለት ጊዜ
‎ዘወትር እንደሚኖር ገልፀው ይህም አካባቢውን ለማስተዋወቅና የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ ትልቅ አቅም አለው ብለዋል።

‎Masha FM

31/05/2026
30/05/2026

#ፒኤስጂ አሸናፊ ሆኗል

Photos from Divers Media Network - DMN's post 30/05/2026

የፍጻሜ ጨዋታው ወደ ፍጹም ቅጣት ምት አምርቷል
**********************

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ አርሰናል እና ፒኤስጂ 1 ለ 1 አቻ በመሆናቸው ወደፍጸፁም ቅጣት ምት አምርተዋል።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa