abyssinialaw.com
የኢትዮጵያ ሕጎችን፣ የፍርድ ውሳኔዎችን፣ የሕግ ጡመራዎችን፣ የሕግ ፎርሞችንና ጠቃሚ የሆኑ የሕግ መረጃዎችን ከአቢሲኒያ ሎው ይከታተሉ!
abyssinialaw.com is an open source for Ethiopian Lawyers, Students, Lecturers, Judges, Prosecutors, Advocates, Draft person and Researchers. It is dedicated not only to making Ethiopian Laws freely available in an electronic format but also to provide the status of the laws. This site is not affiliated in any way with any government entity; it is an independent, an effort to foster the learning of
17/10/2025
The Ethiopian Startup Proclamation No. 1396/2025: A Guide to Incentives and Legal Framework | Legal Analysis | Liku Worku Law Office Legal analysis: “The Ethiopian Startup Proclamation No. 1396/2025: A Guide to Incentives and Legal Framework”. Insight from Liku Worku Law Office, a premier law f…
በግልግል ዳኝነት የፍርድ ቤቶች ሚና
ጸሐፊ፡ ፍቃዱ አንዳርጌ መኮንን (ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ)
ይህ ጽሑፍ፣ ከፍርድ ቤት ውጪ በግልግል ዳኝነት በሚፈቱ አለመግባባቶች ውስጥ መደበኛ ፍርድ ቤቶች ያላቸውን ወሳኝ ሚና ይተነትናል። የግልግል ዳኝነት ራሱን የቻለ ሥርዓት ቢሆንም፣ የግልግል ጉባዔን በማቋቋም፣ ጊዜያዊ ትዕዛዞችን በመስጠት፣ በማስረጃ አሰባሰብ ላይ ድጋፍ በማድረግ፣ እንዲሁም በግልግል የተሰጡ ውሳኔዎችን በማስፈጸምና በይግባኝ በመመርመር ረገድ የፍርድ ቤቶች ድጋፍ የግድ አስፈላጊ መሆኑን ጽሑፉ በዝርዝር ያስረዳል።
https://www.abyssinialaw.com/blog/the-role-of-courts-in-arbitration
09/09/2025
A Legal Guide to Ethiopian Security Listings: A Roadmap for Banks | Legal Analysis | Liku Worku Law Office A legal analysis on 'A Legal Guide to Ethiopian Security Listings: A Roadmap for Banks.' Insight from Liku Worku Law Office, a premier law firm in Addis Ababa, Et…
02/08/2025
ቅጽ 27 የሰበር ውሳኔዎች ታትሟል
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቅጽ 27 የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች አትሞ ለተጠቃሚዎች አውጥቷል፡፡
ውሳኔውን ከቴሌግራም ግሩፓችን ወይም ከዚህ በታች ባለው ሊንክ ማውረድ ይችላሉ
Federal Supreme Court Cassation Decisions Volume 27 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቅጽ 27 የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች አትሞ ለተጠቃሚዎች አውጥቷል፡፡ ውሳኔውን ከዚህ ማግኘት ይችላሉ
https://t.me/abyssinialaw/411
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የ2017 ዓ.ም የግብር ዘመን ግብር አወሳሰንና አሰባሰብ አሠራር መላክን ይመለከታል በሚል ርዕስ ጠበቆች ለ2017 በጀት ዓመት ከግብር ዓመቱ አጠቃላይ ገቢ 35% እንደ ወጪ 65% ግብር የሚከፈልበት ገቢ ሆኖ በሠንጠረዥ "ሐ" መሠረት ግብሩን በማስላት ተሰውኖ ገቢውን እንዲሰበሰብ በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። ውሳኔውን ከዚህ ያግኙ
ደረጃ ሀ እና ለ የሒሳብ መዝገብ በለመያዛቸው ምክንያት የግብር ማስከፈያ የማትሪፈያ ህዳጉ እጥፍ ተወስዶ እና የታክስ ጉዳቱን 40 በመቶ እና የታክሱን እጥፍ በመቅጣት ሕጉን ተፈጻሚ እንዲደረግ ብሏል፤
የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017 አውጥቷል።
ይህ መመሪያ ከጥቅምት 1 2006 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ የነበረውን የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ በማሻሻል የወጣ ሲሆን ፍርድ ቤቱ መመሪያውን እና ማብራሪያውን ለተጠቃሚዎች ዛሬ አሰራጭቷል።
መመሪያው እና ማብራሪያውን ከዚህ ማግኘት ይችላሉ።
09/06/2025
ከዚህ ቀደም አዲሱ የዳኝነት ክፍያ ስሌትን አስመልክቶ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ክፍያ ማስያ (calculator) የአሰላል ስህተት እንዳለው መጠቆማችን ይታወሳል። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጉዳዩ ላይ ማስተካክያ እሲያደርግ ድርስ Negari App ለተጠቃሚዎች ሳንለቅ ቆይተናል።
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አሁን አሰላሉን ያስተካከለ በመሆኑ (ምንም እንኳን አሁንም የተወሰነ ስህተት ቢኖረውም)፣ ከዚህ በታች ያለውን የNegari App ማሻሽያ ለቀናል።
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነት ክፍያ ስሌቱን ማስያ በትክክል እንደሚያደርግ ርግጠኞች ነን።
የNegari App መተግበሪያን ከቴሌግራም ገጻችን ዳውንሎድ ያድርጉ። telegram.me/abyssinialaw
የ iPhone ተጠቃሚዎች በአቢሲኒያሎው ድረገጽ በዚህ ሊንክ ማስያውን ማግኘት ይችላሉ፡
https://abyssinialaw.com/court-fee-calculator
30/05/2025
የመድህን እና የማጓጓዣ ሕግ ይርጋ
በ፦ ካሴ መልካም
የንግድ ሕግ ይርጋዎች ማለትም የንግድ ጉዳዮችን በሚመለከት የሚቀርቡ የይርጋ መቃዎሚያዎች ማለትም፡-
1. በዳይሬክተሮች ቦርድ ላይ የሚቀርብ ክስ ይርጋ
2. የሚተላለፍ የገንዘብ ሰነድ (የሐዋላ ወረቀት እና የቼክ) 3 ዓይነት ይርጋዎች
3. በባለአክሲዮኖች ጉባዔ የተሰጠ ውሳኔን የማሰረዣ ክስ የማቅረቢያ የይርጋ ጊዜ
4. በአክሲዮን ማህበር አደራጆች ላይ የሚቀርብ ክስ ይርጋ
5. የንግድ ማህበራት የሀብትና ዕዳ መግለጫን የመቃወሚያ ክስ ማቅረቢያ የይርጋ ጊዜ
6. በዓይነት መዋጮ በተጋነነ ግምት ለደረሰ ጉዳት ክስን ለማቅረብ የይርጋ ጊዜ
7. ሀሰተኛ የትርፍ ክፍያን ለማስመለስ የሚቀርብ ክስ የይርጋ ጊዜ
ከሕጉ እና ከሰበር አስገዳጅ የሕግ ትርጉም አንጻር ተዳሰዋል። የእነዚህ ጉዳዮች የይርጋ ጊዜ ሰፊ ትንታኔ ከፈለጉ መጽሐፉን እንዲያነቡ እነሆ ጀባ ብለናል።
መልካም ንባብ
የመድህን እና የማጓጓዣ ሕግ ይርጋ - Blog ይህ ጽሑፍ በቀጥታ የተወሰደው በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያዎች ከሚለው ተሻሽሎ ከታተመው መጽሐፍ ላይ ነው። ሆኖም ለዚህ የበየነ-መረብ ጽሑፍ ለንባብ እንዲመ....
29/05/2025
ይድረስ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት - የፌደራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን የወጣ ደንብ ቁጥር 1/2017 መሰረት የተሰራው ማስሊያ (calculator) ስህተት ያለበት ስለመሆኑ
ካልኩሌተሩ የዳኝነት ክፍያ ጣሪያን ግምት ሳያስገባ በፐርሰንት/በመቶኛ ብቻ በማስላቱ የሚከተለው ዓይነት ስህተት አለው፤
ለምሳሌ
ለ20ሺ ብር የዳኝነት ጥያቄ የዳኝነት ክፍያው 2ሺ ሲሆን ለ21ሺ ብር ደግሞ 1,890.00 ነው። ለ20 ሺ ብር ዳኝነት 2ሺ የሚከፈል ከሆነ እንዴት ለ21ሺ ብር ዳኝነት 1,890.00 ይከፈላል። ይህ ግልጽ ስህተት ነው። ይህ ስህተት የተገኘው በግልጽ አሰላሉን ደንቡ ስለማያሳይ ነው።
በእኛ አረዳድ
እስከ ብር 20 ሺ ላለ የዳኝነት ጥያቄ ጣሪያው 10 በመቶ ማለትም 2ሺ ብር ተይዞ ከ20ሺ ብር በላይ ላለው ደግሞ ቀጣይ ያለው 9 በመቶ ይሰላል ማለት ነው። በመሆኑም፡
ለ20,000.00 ብር ዳኝነት ጥያቄ የዳኝነት ክፍያ 2,000.00 ብር ሲሆን
ለ21,000.00 ብር ደግሞ ብር 2,089.91 ይሆናል።
ተክክለኛውን አሰላል ከዚህ ይመልከቱ
https://www.abyssinialaw.com/court-fee-calculator
በቀጣይ የነጋሪ አፕን ማሻሻያ እንለቃለን። ይጠብቁን ይህንን ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያድርሱልን።
11/04/2025
በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ላይ ትኩረት የሚሹ አወዛጋቢ ነጥቦችና መፍትሔዎቻቸው
በ፡ ካሴ መልካም
ይህ ጽሑፍ የተወሰደው በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያዎች በሚል ከታተመው በ2017 ዓ.ም ተሻሻሎ በቀረበው መጽሐፌ ላይ ሲሆን የግርጌ ማስታዎሻዎቹ እና ማጣቀሻዎቹ ለዚህ ጽሑፍ ሲባል ለንባብ በሚመች አግባብ እንደገና ተቀናጅተው ተሰርተዋል፡፡ በዚህ ጽሑፍ የተካተቱት አብዛኛዎቹ ነጥቦች አወዛጋቢ ሆኖም በሕግ ባለሙያው ብዥታ እና ልዩነት የሚፈጥሩ ነጥቦች በመጽሐፉ የመጀመሪያ ዕትም ያልነበሩ አሁን ላይ በችሎት በሚገጥሙ ክርክሮች ሰበር ጭምር መፍትሔ የሰጣቸውን እና ሰበር መፍትሔ ያልሰጠባቸውን ደግሞ የመጽሐፉ አዘጋጅም የራሱን ምልከታ እና መፍትሔ የሚላቸውን ሃሳቦች ያሰቀመጠባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡
በዚህ በተሻሻለው ዕትም ከ400 በላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያን የሚመለከቱ በ5 እና በ7 ዳኞች የተሰጠ የሰበር ችሎቱ አስገዳጅ የሕግ ትርጉ እና በርካታ የፌዴራሽን ምክር ቤቶች የተካተቱበት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በመጀመሪያ ደረጃ እና በከፍተኛ ፍርድ ቤት በችሎት አከራካሪ የሆኑ ጉዳዮች እና ፍ/ቤቶቹ የሰጡት ፍርድን መነሻ በማድረግ መፍትሔ የሚሆኑ ነጥቦችን ለማስቀመጥ ተሞክሯል፡፡
በዚህ ጽሑፍ የሚከተሉትን ያገኛሉ።
1. በጽሑፍ ያልቀረበን የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያን ከሳሹ በቃል ክርክር የማቅረብ መብት ያለው ስለመሆኑ
2. በመቃወሚያ ላይ ማስረጃ የመስማት አስፈላጊነት
3. በብዙ መቃወሚያዎች ላይ የውሳኔ አሰጣጥ ስነ-ስርዓት
4. በመቃወሚያዎች ላይ ከሳሽ በክሱ ያልዘረዘራቸውን ማስረጃዎች የማቅረብ መብት
5. በተጣመሩ ተከሳሾች አንዱ በሌላኛው ላይ መቃዎሚያዎችን የሚያነሱበት አግባብ
6. በመቃዎሚያዎች ላይ ይግባኝ የሚባልበት አግባብ
7. በመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያ ላይ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ የክስ መሻሻል ውጤት
8. የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያና እሱን ለመወሰን መሰረት የሚሆነው ሕግ
9. በፍርድ ቤት በራሱ እና በተከራከሪዎች ብቻ የሚነሱ መቃዎሚያዎችን
10. በተከራካሪዎች ብቻ የሚነሱ የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያዎች
11. ፍርድ ቤቱ በራሱ ሊያነሳቸው የሚችሉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃዎሚያዎች
https://www.abyssinialaw.com/blog/controversial-points-and-their-solutions-for-preliminary-objections
መልካም ንባብ!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the practice
Telephone
Website
Address
Bole, Gulf Aziz Building
Addis Ababa
23113
Opening Hours
| Monday | 09:00 - 17:00 |
| Tuesday | 09:00 - 17:00 |
| Wednesday | 09:00 - 17:00 |
| Thursday | 09:00 - 17:00 |
| Friday | 09:00 - 17:00 |