Gebeya Media

Gebeya Media

Share

This is the official Gebeya Media page.

"Economic growth for social security"

Follow us on:
Telegram፦ t.me/gebeyanews
YouTube፦ youtube.com/@gebeyamedia
Gebeya Business፦ youtube.com/@gebeyabusiness
TikTok፦ vm.tiktok.com/ZMHKxXmEkuP8W-wJFBO/

በትምህርት ሚኒስትር ይፋ የተደረገው ሰው ሰራሽ አስተውሎት! 05/06/2026

ለመምህራን የትምህርት እቅድ የሚያዘጋጅ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የፈተና ጥያቄዎችንና አሳይመንቶችን የሚያመነጭ የሰው ሰራሽ አስተውሎት መተግበሪያ ተበልጽጎ በሙከራ ደረጃ ሥራ ላይ መዋሉን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ዝርዝሩን ያንብቡ!

በትምህርት ሚኒስትር ይፋ የተደረገው ሰው ሰራሽ አስተውሎት! በሙከራ ደረጃ ላይ የሚገኘው የዚህ መተግበሪያ ቀጣይ የማስፋፊያ ሥራዎች በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በሚንቀሳቀሰው “የኢትዮጵያ የትምህርት ለውጥ ኦፕሬሽን” ፕሮጀክት ድጋፍ እየተከ....

የ10 ዓመቱ የሒሳብ ምርመራ እና የግብር ከፋዮች አዲሱ መብት 05/06/2026

አነጋጋሪው አዲሱ የታክስ ህግ!

አዲሱ ረቂቅ አዋጅ የግብር ባለሥልጣኑ የታክስ ማጭበርበር መፈጸሙን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሲያገኝ፣ የግብር ከፋዮችን የሒሳብ ሰነድ እስከ 10 ዓመት ወደኋላ በመሄድ በድጋሚ የመመርመር (ኦዲት የማድረግ) ሰፊ ሥልጣን ይሰጠዋል። በተጨማሪም ደረሰኝ ባለመቁረጥ በሚፈጸሙ ግብይቶች ላይ ከባድ አስተዳደራዊና የወንጀል ቅጣቶችን ይጥላል።

በሌላ በኩል፣ በታክስ ባለሥልጣኑ እና በታክስ ከፋዮች መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን በገለልተኛ አስማሚ አማካኝነት በፍጥነትና በሚስጥራዊነት ለመፍታት የሚያስችል አዲስ ሥርዓት አስተዋውቋል። ይህ አሠራር ቀደም ሲል የነበረውን አድካሚና ረጅም የፍርድ ቤት ሂደት በማቃለል ግብር ከፋዮች መፍትሔ እንዲያገኙ ያግዛል ነው የተባለው።

ዝርዝር ያንብቡ!

የ10 ዓመቱ የሒሳብ ምርመራ እና የግብር ከፋዮች አዲሱ መብት ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ለኢትዮጵያ በሰጠው ማሳሰቢያ "የሀገር ውስጥ የታክስ እና ታክስ ያልሆኑ ገቢዎችን የመሰብሰብ አቅምን በከፍተኛ ደረጃ ማጠናከር ያስፈልጋል" ማለቱ መንግ....

05/06/2026

መልካም ቀን!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የኢቮላ ወረርሽኝ 04/06/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የኢቮላ ወረርሽኝ

በዚህ ወረርሽኝ ምክንያት ዋልያዎቹ ወደ አሜሪካ ተጉዘው ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ሊያደርጉት የነበረው የወዳጅነት ጨዋታ መሰረዙ ታውቋል።

ታዲያ ይህ የወዳጅነት ጨዋታ መሰረዙ ሳይሆን የተሰረዘበት ምክንያት ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል።

ዝርዝሩን ያንብቡ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የኢቮላ ወረርሽኝ በመካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ ዳግም ያገረሸው የኢቦላ ቫይረስ ስርጭት ዓለም አቀፍ ፍርሃትን የቀሰቀሰ ሲሆን በተለይ በአፍሪካ ደግሞ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል።

04/06/2026

ከ50 በላይ የልብ ሕክምና ባለሞያዎችን የያዘ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ ነው

ግንቦት 26/2018 (ገበያ ሚዲያ) ከ50 በላይ የልብ ሕክምና በጎ ፈቃደኛ ባለሞያዎችን የያዘ የሕክምና ቡድን ከአንድ ወር በኋላ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣ ተነግሯል።

ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት አራት መሰል ቡድኖች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የሕክምና አገልግሎት እንዲሰጡ ያደረገው 'ኸርት አታክ ኢትዮጵያ' የተሰኘው ግብረሰናይ ድርጅት፤ በቀጣዩ ሰኔ ወር መጨረሻ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣው ቡድን የልብ ሕክምና ለማግኘት ወረፋ እየተጠባበቁ ለሚገኙ ሕጻናት እና አዋቂዎች ሕክምና እንደሚሰጥ ገልጿል።

የሕክምና በጎ ፈቃደኛ ባለሞያዎች ቡድኑ የልብ ስፔሻሊስት ሃኪሞች እና ነርሶች፣ እንዲሁም ሌሎች ባለሞያዎችን ያካተተ መሆኑ ተነግሯል። የሕክምና በጎ ፈቃደኛ ባለሞያዎቹ ከህንድ፣ ካናዳ፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ሩዋንዳ እና ቦትስዋና የተወጣጡ መሆናቸውንም የኸርት አታክ ኢትዮጵያ መሥራች ዶክተር ተስፋዬ ተሊላ ገልጸዋል።

ኸርት አታክ ኢትዮጵያ በየጊዜው ተመሳሳይ ሥራዎችን በማከናወን የልብ ሕመም ህክምና ለማግኘት ወረፋ እየተጠባበቁ ለሚገኙ ሕጻናት ሕክምና መስጠቱን እንደሚቀጥልም ዶክተር ተስፋዬ አረጋግጠዋል።

IMF ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ባደረገው ስምምነት ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ሊለቅ ነው 04/06/2026

IMF ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ባደረገው ስምምነት ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ሊለቅ ነው

ድጋፉ የሚለቀቀው ሁለቱ ወገኖች በአምስተኛው ዙር ግምገማ ላይ በባለሙያዎች ደረጃ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ እንደሆነ ተገልጾዋል፡፡

እንደ አይ ኤም ኤፍ መግለጫ፤ ይህ አዲስ የገንዘብ ድጋፍ የተፈቀደው ኢትዮጵያ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳዋን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን እያሳየች ባለችበት ወቅት መሆኑን የጠቀሰ ሲሆን በተለይም የወጪ ንግድ፣ የውጭ ምንዛሬ ክምችት እና የመንግሥት ገቢ መሻሻል በማሳየታቸው እንደሆነ ጠቁሟል፡፡

ዝርዝሩን ያንብቡ!

IMF ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ባደረገው ስምምነት ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ሊለቅ ነው ይህ አዲስ የገንዘብ ድጋፍ የተፈቀደው ኢትዮጵያ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳዋን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን እያሳየች ባለችበት ወቅት መሆኑን የአይ ኤም ኤ....

ኢራን በኩዌት እና ባህሬን ላይ የድሮን ጥቃት ፈፀመች 03/06/2026

ኢራን በኩዌት እና ባህሬን ላይ የድሮን ጥቃት መፈጸሟ ተሰምቷል

የኩዌት መከላከያ ሚኒስቴር እንዳረጋገጠው በዚህ በኢራን የድሮን እና ሚሳኤል ጥቃት ሳቢያ የኩዌት ዋና ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት ለአጭር ጊዜ አገልግሎት አቋርጧል፡፡

ለዚሁ ጥቃትም የአሜሪካ ጦር በሰጠው ምላሽ በሆርሙዝ ሰርጥ አቅራቢያ በምትገኘው የኢራኗ ቃሺም ደሴት ላይ የአጸፋ እርምጃ መውሰዱ ተሰምቷል፡፡

ዝርዝሩን ያንብቡ!

ኢራን በኩዌት እና ባህሬን ላይ የድሮን ጥቃት ፈፀመች የአሜሪካ ጦርም ለዚሁ ጥቃት በሰጠው ምላሽ በሆርሙዝ ሰርጥ አቅራቢያ በምትገኘው የኢራኗ ቃሺም ደሴት ላይ የአጸፋ እርምጃ መውሰዱ ተሰምቷል፡፡

የኢትዮጵያዋ “አሶሳ” መርከብ በሆርሙዝ አቅራቢያ ታሪክ ሰራች 03/06/2026

የኢትዮጵያዋ “አሶሳ” መርከብ በሆርሙዝ አቅራቢያ ታሪክ ሰራች

መርከቧ በሆርሙዝ ሰርጥ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኝ ወደብ ላይ የሕክምና እና የንግድ ጭነቶችን በተሳካ ሁኔታ ጭና መመለሷ ተሰምቷል፡፡

የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ንብረት የሆነችው ይህቺ መርከብ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ባለበት የሆርሙዝ ሰርጥ አካባቢ ነው ደርሳ ጭና የተመለሰችው፡፡

ዝርዝሩን ያንብቡ!

የኢትዮጵያዋ “አሶሳ” መርከብ በሆርሙዝ አቅራቢያ ታሪክ ሰራች መርከቧ ከሆርሙዝ ሰርጥ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኝ ወደብ ላይ የሕክምና እና የንግድ ጭነቶችን በተሳካ ሁኔታ ጭና መመለሷ ተሰምቷል፡፡

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Addis Ababa
1000