Brhanu

Brhanu

Share

ethiopia

Photos from Brhanu's post 15/06/2025

ኮሩ ያሰለጠናቸውን የመቶና የጓድ አመራሮች አስመረቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት 08 ቀን 2017 ዓ.ም

በ6ኛ ዕዝ ስር የሚገኝ አዋሽ ኮር ለወራት ያሰለጠናቸውን የመቶና የጓድ አመራሮች አስመርቋል።

በምረቃ ሰነ-ስርዓቱ ላይ በመገኘት ብልጫ ውጤት ላመጡ ሰልጣኞች ሽልማት ያበረከቱትና የስራ መመሪያ የሠጡት የ6ኛ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ነገሪ ቶሊና ኮሩ በተሰለፈባቸው አወደ ውጊያዋች ፅናትና ቁርጠኝነት የተላበሰ አመራር ለመፍጠርና አቅሙን ለማዳበር እያካሄደ ያለው እቅስቃሴ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል።

ከግዳጅ ጎን ለጎን ታችኛውን አመራር አቅሙን መገንባት ለተሻለ ውጤት እንደሚያበቃ በመረዳት በተገኘው ክፍተት ሁሉ ራስን የማብቃት ተግባር ላይ በማተኮር ለተሰለፈበት ዓላማና ለተሰጠው ሃገራዊ ተልዕኮ ውጤታማ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልፀዋል።

የመቶና የጓድ አመራሩ ዉጊያ ጨራሽ እደመሆኑ መጠን ለተዋጊው ሀይል ከፍተኛ ጉልበት በመሆን የተሰጣቸውን የፀረ-ሽምቅ ውጊያዎች በአጭር ጊዜ ለማከናወን የሚያስችል አቅም መፈጠር መቻሉንና አስተማማኝ የማድረግ አቅም ላይ እደሚገኝ የተረጋገጠበት ስልጠና እደሆነ ተናግረዋል።

ተመራቂዎችም በወሰዱት ስልጠና ውጤታማ ተግባራትን በማከናወን በውጤት የሚለካ ስራዎችን መስራት እንደማጠበቅባቸው አሳስበዋል።

የስልጠናውን ሪፖርት ያቀረቡት የኮሩ የሠራዊት ሰነ-ልቦና ግንባታ ሃላፊ ሌተናል ኮሎኔል አበባው አይቸው በተሰጠው ስልጠና ሰልጣኞች መያዝ ያለባቸውን እውቀትና አቅም መጨበጥ እንደቻሉ ገልፀዋል።

ዘጋቢ ውበቴ አማረ
ፎቶ ግራፍ አያልቅበት ገዛሃኝ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

11/06/2025

"ሰላም የሚፈልግ ካለ በእኛ በኩል ሁሌም ዝግጁ ነን"
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

መንግስት በሰላም የሚመጡ አካላትን ተቀብሎ ለማወያየት ዝግጁ ነው::ከዚህም ባሻገር ህግ ማስከበር የመንግስት ስራ በመሆኑ መቀጣት ያለበትን አካል መቅጣት ይገባል፥ ሰላም በጣም አስፈላጊ በመሆኑ ተባብረን መስራት አለብን፡፡ሰላምን በተመለከተ የሚቀርቡ ጥያቄዎች ትክክለኛ ናቸው::ነገር ግን ሰላም እንዲሰፍን የሚጠይቁ አካላት ራሳቸውን በማግለል የመንግስት ብቻ ጉዳይ የማድረግ ልምምዶች ተገቢ አይደለም::

10/06/2025

ከከተማችን ሴቶች ጋር የተደረገ ዉይይት

Photos from Brhanu's post 07/06/2025

የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ በአጭር ኮርስ ያሰለጠናቸውን የክፍለ ጦር አመራሮች አስመርቋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 30 ቀን 2017 ዓ.ም

በምረቃው ላይ የሥልጠናውን ሪፖርት ያቀረቡት የኮሌጁ አዛዥ ብርጋዲየር ጀነራል ሙሉጌታ አምባቸው ፣ የተቋሙን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ በልዩ ሁኔታ የሰለጠኑት የክፍለ ጦር አመራሮች ውጤታማ በሆነ መልኩ ስልጠናቸውን አጠናቀው ለምረቃ መብቃታቸውን ገልፀዋል።

የሰራዊቱንና የአመራሩን አቅም ለመጨመር እየተደረገ ያለው ጥረት ማሳያ የሆነ ስልጠና መሰጠቱን የገለፁት አዛዡ ተግባራዊ ልምድ ላላቸው ከፍተኛ አመራሮቹ ተግባር ተኮር የሆነ ስልጠና መሰጠቱ ቀጣይ ለሚገጥማቸው ግዳጅ የሚኖረው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ስልጠናው በጊዜ በአቀራረብና በዓይነቱ ልዩ የነበረና የተቋሙን ፍላጎት ያሳካ መሆኑንም ገልፀዋል።

በምረቃው ላይ የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ሀላፊ ሌተናል ጀነራል ይመር መኮንንን ጨምሮ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮችና የኮሌጁ ማህበረሰብ ተገኝተዋል።

ዘጋቢ ብዙአየሁ ተሾመ
ፎቶግራፍ ገነት አወቀ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

03/06/2025

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከተማ የተጀመሩ የክረምት በጎ ፈቃድ ልማት ስራዎችን ከገጠሩ ክፍል ጋር የማስተሳስር አካል የሆነውን የገጠር የኮሪደር ልማት አሰጀመሩ ፡፡

AMN - ግንቦት 26/2017 ዓ.ም

Photos from Brhanu's post 03/06/2025

በክልሉ የተገኘው ሠላም የሠራዊታችን ክቡር መስዋዕትነት ውጤት ነው።
ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

በአማራ ክልል የተገኘው ሠላም የሠራዊታችን ክቡር መስዋዕትነት ውጤት ነው ሲሉ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ተናገሩ።

ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ በሰሜን ጎንደር ዞን ከደባርቅ ወረዳ አስተዳደር የፀጥታ አካላት ጋር በዞኑ አሁናዊ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ሠራዊታችን በማይበገረው የዓላማ ፅናቱ እንዲሁም ጀግንነቱ ክልሉን ከፅንፈኛው መፈንጪያነት ወደ አስተማማኝ ሠላምና ልማት እንዲመለስ አድርጓል ብለዋል።

ፅንፈኛው ኃይል ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስና ስልጣንን ኢ-ህገ መንግስታዊ በሆነ መንገድ ለመያዝ በታሪካዊ ጠላቶቻችን እየተነዳ ያደረገው የቀቢፀ ተስፋ ሙከራ ከባድ ዋጋ አስከፍሎታልም ብለዋል ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ።

እኛ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስና ስልጣን በአቋራጭ ለመያዝ የሚመጡ ኃይሎችን ስርዓት እናስይዛለን እያደርግን ያለንውም ይሄንኑ ነው ያሉት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ዋጋ የከፈልንበትን ሠላም ማፅናትና በቁርጠኝነት መስራት ከአስተዳደር እንዲሁም ከፀጥታ አካለቱ የሚጠበቅ ቁልፍ ተግባር ስለመሆኑም አሳስበዋል።

በክልሉ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ማስቀጠልና የአካባቢውን ሠላም መጠበቅ እንዲሁም ከአካባቢው ማህበረሰብ፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና የሐይማኖት አባቶች ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባም አቅጣጫ አመላክተዋል።

የዞኑ የፀጥታ ኃላፊዎችም ሚሊሺያ፣ ሠላም አስከባሪውና መደበኛ ፖሊስ ራሱን አደራጅቶ የክልሉን ብሎም የዞኑን ሠላም ለመጠበቅና ለማፅናት በትኩረት እየተሰራ ስመሆኑንም ተናግረዋል።

የአካባቢው ማህበረሰብ የፅንፈኛውን አድራጎት ተረድቷልም ተገንዝቧልም ያሉት የውይይቱ ተሳታፊዎች አሁንም ሠላሙን ለማፅናት ራሱን አደራጅቶ ስለ ሠላም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነው ብለዋል። ዘጋቢ አንዷለም ከፍያለው ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

01/06/2025

የሰላም ብቸኛ መንገድ መመካከር መሆኑ የገባቸው !!!
ትላንት በጦር ሜዳ ዛሬ በምክክር መድረክ፤ ለውጥማ አለ።እውነት ለውጥማ አለ። ትላንት በጦርነት ችግርን ካልፈታን ሲሉ የነበሩ ዛሬ ገብቷቸው፣ ተረድተው ለውይይት መድረክ ተቀምጠዋል። ይህ እጅግ ትልቅ ለውጥ፣ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ፣ ትልቅ ምሳሌም ነው። ተመስገን፣ ኢትዮጵያ እውነተኛ እርምጃ እያደረገች ነው።

Photos from Brhanu's post 01/06/2025

አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን የባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን በሚገባ መወጣት ይኖርባቸዋል
ሌተናል ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም

ሠራዊቱ በአካባቢው ሰላምን በማስጠበቅ የህብረተሰቡን የልማት ተግባራት ያለ እንቅፋት እንዲቀጥል የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት እየተወጣ መሆነን የደቡብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ ገለፁ።

ሌተናል ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ ይህንን ያሉት በኦሮሚያና በሲዳማ ክልል የዞን የመስተዳድር እና የፀጥታ በለድርሻ አካላት ጋር በአካባቢው ሰላምና ፀጥታ እንዲሁም በሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ወይይት ባደረጉበት መድረክ ነው።

በውይይቱ ላይ የደቡብ ዕዝ በተሰማራበት አካባቢ ህዝብና መንግስት የሰጡትን ሰላም የማስፈን ተግባሩን ከመቸውም ጊዜ በላይ በአስተማማኝ ብቃት እየተወጣ ነው ለዚህም በየደረጃው ያለው የፀጥታ መዋቅሩ ቅንጅት ሠራዊቱ ተልዕኮን በሚፈፅምበት አካባቢ ውጤታማ ስምሪት ለማከናወን በአካባቢው ከሚገኙ የፀጥታ መዋቅሮችና የሥራ ሃላፊዎች ጋር በቅንጅት በመስራት አስተማማኝ ሰላም ማምጣት መቻሉን ሌተናል ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ ገልፀዋል።

አብሮ የመኖር እሴቶችን የመሸርሽሩና በአጎራባች አካባቢዎች ለግል የፖለቲካ ትርፍ ሲሉ በህብረተሰቡ ውስጥ መጠራጠር እና ጥቃቅን ግጭቶችን ለመፈጠር የሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የፀጥታ መዋቅሩ የህዝቡን ሰላም ለማስጠበቅ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣትና የልማት እንቅስቃሴውን ማቀላጠፍ እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል ።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በበኩላቸው የመከላከያ ሠራዊታችን ያለ እረፍት በምንም የማይተካ ውድ ህይወቱን እየሰጠ የአካባቢያችንን ሰላም በመጠበቅ የህዝብ አልኝታነቱን እያስመሰከረ ነው ምንግዜም ኩራታችን ነው ብለዋል።

ሠራዊቱ ለህዝብ ደህንነት ሲል ዋጋ እየከፈለ የአካባቢውን ሰላም ለማፅናት ቀን ከሌሊት የሰላማችን ዘብ ነው ያሉት የፀጥታ ሃላፊዎች ሰላም የማስፈን ጉዳይ ለመከላከያ ሠራዊቱ ብቻ የሚተው ሳይሆን የሁሉም ዜጋ ሃላፊነት መሆኑንና በተለይ የባለድርሻ አካላት የፀጥታ መዋቅሩን በማጠናከር የሠራዊታችንን ተልዕኮ መደገፍ እንደሚገባቸው አንስተዋል። ዘገባው የዕዙ የሠራዊት ሥነ-ልቦና ግንባታ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

31/05/2025

ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና ማማ የምታደርገው ጉዞዋን ቀጥላለች!!
ሃገራችን ኢትዮጵያ በብዙ ነገር ጉዞዋ ወደ ፊት ሆኗል። ወደ ልማት፡ ወደ ብልጽግና፡ ወደ ቀድሞ ከፍታ ብቻ ነው ጉዞው። ምንም እንኳን ፈተናዎች ቢበዙም መሰናክሎች በመንገዷ ቢደረደሩም ሃገራችን ኢትዮጵያን ከጀመረችው የለውጥ ጉዞ የሚገታት የለም። ኢትዮጵያ ድህነትን ታሪክ አድርጋ ለማስቀረትና የተያዘዉን የልማት ጉዞን አጠናክራ ትቀጥላለች። የትንሳኤዋ ጊዜም እጅግ በጣም የቀረበና ወደ በለጸጉት ሃገራት መቀላቀሏም የማይቀር ነዉ።

Photos from Brhanu's post 30/05/2025

ተልዕኮን አደራጅቶ በመምራት የአመራር የመሪነት ጥበብ ማሳየት መቻል አለበት!
አቶ ተወዳጅ ኃ/ማርያም

በብልፅግና ፓርቲ አራዳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት መደበኛ የፓርቲ ተግራቶችና ወቅታዊ ተልዕኮዎች ላይ ውይይት አደረገ።

የአመራር የመሪነት ጥበብ በመላበስ ተልዕኮ በብቃት የመፈፀም አቅም በመጨመር የተቋም ግንባታ ስራ አጠናክሮ በመያዝ የተደራጀ የአመራር ስምሪት መስጠት እንደሚገባ በብልፅግና ፓርቲ አራዳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ተወዳጅ ኃ/ማርያም ገልጿል።

የአመራር የመፈፀም አቅም ከፍ እንዲል ሁለንተናዊ የድጋፍ አግባቦች አጠናክረን በመቀጠል ተልዕኮ ያለ ምንም መንጠባጠብ በመምራት የፓርቲያችን ተልዕኮ በአመራር ዲስኘሊን መፈፀም እንደሚገባ በብልፅግና ፓርቲ አራዳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ምክትልና የፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍራኖል ሞሲሳ አስገንዝቧል።

የተደራጀ የአመራር ስምሪት መስጠት የጠንካራ መሪ መገለጫ ነው ያሉት በብልፅግና ፓርቲ አራዳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ተልዕኮዎችን በእቅድ በመምራት አንፀባራቂ ድሎች ማስመዝገብ ይገባል ብሏል።

በመጨረሻም በመደበኛ የፓርቲ ተግባራቶችና በወቅታዊ ተልዕኮዎች ላይ አቅጣጫና የጋራ መግባባት በመስጠት ተጠቃለዋል።

Photos from Brhanu's post 30/05/2025

በመከላከያ ዋር ኮሌጅ የስትራቴጂክ አመራር ተማሪዎች የኢትዮጵያ አየር ሃይልን ጎበኙ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 22 ቀን 20 17 ዓ.ም

ጉብኝቱ በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን ትምህርት ከተግባር ጋር ለማቀናጀት የሚያስችልና የመማር ማስተማር ሂደቱን የሚያጠናክር መሆኑም ተገልጿል፡፡

ጎብኝቱ በተቀናጀ ዘመቻ በስትራቴጂክ እና በፀጥታ ደህንነት ላይ በንድፈ ሃሳብ ያገኘነውን እውቀት ለመተግበር በሚያስችል መልኩ የተካሄደ ነው ያሉት ተማሪዎቹ የዘመኑን ዲጅታላይዜሽን ቴክኖሎጂ በመጠቀም የሰው ሀይልና ሎጂስቲክስን አስተሳስሮ ለመምራት እንዳሁም በተግባር የታገዘ የፅንሰ-ሃሳብ ትሞህርት መማር ለመከላከል ሠራዊታችንና ለሀገራችን ያለው ፋይዳ የጐላ ነው ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ከኢትዮጵያ አየር ኃይል ባሻገር የተለያዩ የሀገሪቱን የመሰረተ ልማትና የመከላከያ ኢንዱስትሪ ተቋማት የጎበኙት ተማሪዎቹ በንድፈ ሃሳብ ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስችል አቅም እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።

ዘጋቢ አሰፉ ግርማይ
ፎቶግራፍ ኢፍቱ ቢራቱ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

27/05/2025

ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያንን ያስተሳሰረ የአንድነት ሐረግ ነው

ህዳሴ ግድብ የመላው ኢትዮጵያውያን የአንድነታቸው ምልክት የመቻላቸውም ምስጥር ነው::ህዳሴ ካለው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባሻገር ኢትዮጵያውያንን እርሰ በርስ ያስተሳሰረ ሀገራዊ ሀብት ነው።ፕሮጀክቱ አሁን የፍጻሜው ዋዜማው ላይ የደረሰው በዜጎች ዕውቀት፣ ገንዘብ እና ጉልበት ነው::ሁሉም ዜጋ በብሔር፣ ሃይማኖት እና ቋንቋ ሳይለያይ በአራቱም አቅጣጫ ርብርብ ያደረገ ሲሆን ይህም ከፕሮጀክቱ መገንባት ባለፈ የዜጎችን የእርስ በርስ ትስስር የሚያጠናክር ነው።በዜጎች ሁለንተናዊ ድጋፍ እየተገነባ ያለው ግድብ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ይገኛል::ግድቡ በኢትዮጵያውያን ትብብር መገንባቱ ለሀገር አንድነት መጠናከር ሚናው ከፍተኛ ነው::
#ከእዳወደምንዳ
#ዲፕሎማሲ
#ህዳሴ

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa