Auto Safe Vehicle Inspection Center

Auto Safe Vehicle Inspection Center

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Auto Safe Vehicle Inspection Center, Motor Vehicle Company, kirkos k/ketema wereda 06, Addis Ababa.

12/10/2025
Photos from Ministry of Transport and Logistics - Ethiopia's post 10/10/2025
Photos from Ethiopian News Agency's post 08/10/2025
11/09/2025

Happy new year!!!2018 E.C.🌼🌼🌼 አዲሱ ዓመት🌼🌼🌼
✔የጤንነት
✔ የሠላም
✔ የፍቅር
🤝 ✔ የአንድነትና
✔ የመከባበር ዓመት ያድርግልን!
መልካም አዲስ ዓመት !!!🌼እ🌻ን🌼ቁ🌻🌼ጣ🌻ጣ🌻ሽ🌼🌼🌼

26/06/2025

1ዐዐ የከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አውቶብሶች ሊገዙ ነው
የፐብሊክ ትራንስፖርት አገልግሎትን ለማሻሻልና ተጨማሪ አውቶብሶችን ለመግዛት የጨረታ ሂደት መጠናቀቁን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚንስቴር አስታውቋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚንስቴር የ2017 በጀት ዓመት የ11 ወራት የዕቅድ አፈፃጸም አድምጧል።

የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚንስትር ዶክተር ዓለሙ ስሜ እንደተናገሩት፤ በአዲስ አበባ ከተማ የሚስተዋለውን ከፍተኛ የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡን ከማዘን ባለፈ ተጨማሪ 100 አውቶብሶችን ወደ ሥራ ለመሰማራት የጨረታ ሂደት ተጠናቋል ብለዋል።

የትራፊክ አደጋን በዘላቂነት ለመቀነስ በአሽከርካሪዎች ስነምግባር ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ የገለፁት ሚኒስትሩ፤ አሽከርካሪዎች ከሙያ ብቃት በተጨማሪ በስነምግባር የታነፁ እንዲሆኑ፤ ለሀገር አቋራጭ አውቶብስ አሽከርካሪዎች የስነምግባር ስልጠና ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የህገወጥ ኬላዎች መበራከት ከፍተኛ ችግር ሆኖ ቆይቷል ያሉት ዶክተር ዓለሙ፤ ይህንን ማነቆ ለመፍታት በቀጣይነት የተጠናከረ ሥራ ይሰራል ብለዋል።

የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመን በቴክኖሎጂ ልማትና የተቋማት የአቅም ግንባታ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

የአዲሱ የመኪና ሰሌዳ ምን አዲስ ነገር ይዞ መጥቷል? | BBC News አማርኛ #bbcamharic #bbc #ethiopia 24/06/2025

የአዲሱ የመኪና ሰሌዳ ምን አዲስ ነገር ይዞ መጥቷል? | BBC News አማርኛ #bbcamharic #bbc #ethiopia ላለፉት አስርት ዓመታት ጥቅም ላይ ሲውል የነበረው የተሽከርካሪዎች ሠሌዳ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥ በሆነ አዲስ ሠሌዳ ሊቀየር እንደሆነ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታ.....

06/06/2025

ኢድ ሙባረክ !!!

Photos from የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለሥልጣን AA Driver and Vehicle Authority's post 19/05/2025
20/04/2025

እንኳን ለብርሀነ ትንሣኤው በሠላም ያደረሳችሁ

18/01/2025

እንኳን ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ጥምቀት ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ኅብረ ብሔራዊ በዓላችን ነው። በሃይማኖታዊነቱ የኢየሱስ ክርስቶስን ከሰማያት ወርዶ፣ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ወንዝ መጠመቅ እናስብበታለን። ይሄም የጠፋውን አዳም ለመፈለግ የተደረገ ጉዞ ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ አዳም በወደቀበት በእያንዳንዱ ዱካ ከቤተልሔም እስከ ቀራንዮ ተከትሎ ዋጅቶታል። በዚህም አዳምን ወደ ጥንት ክብሩ መመለስ ብቻ ሳይሆን ከጥንቱ የበለጠ ክብር ሰጥቶታል።

ይሄም ለዛሬዋ ኢትዮጵያ የሚያስተምረን ብዙ ነው። ሀገራችን ኢትዮጵያ ከቤተልሔም እስከ ቀራንዮ የወደቀችበት ብዙ ነው። በእያንዳንዱ በወደቀችበት ውድቀት ተከትለን ማንሣት አለብን። የትርክት፣ የሀገረ መንግሥት፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የመግባባት ውድቀቶቿን ወደ ትንሣኤዋ መቀየር አለብን።

ክርስቶስ አዳምን ሲያድነው እንዲህ ወይም እንዲያ ማድረግ አለብህ አላለውም። አዳም ዐቅም እንደሌለው ያውቃልና። መዳኑን እርሱ ራሱ ሊያደርገው እንደማይችል ያውቃል። ስለዚህ ክርስቶስ ተገብቶ ፈጸመለት።

ኢትዮጵያችን በዘመናት መከራዎች ደክማለች። በዘመናት ድህነትና ኋላ ቀርነት ተጎድታ ዐቅም አጥታለች። እንዲህ ወይም እንዲያ ማድረግ ነበረባት የሚለው አሁን ለውጥ አያመጣም። መደረግ ያለበትን እኛ ልጆቿ ዛሬ እናድርገው። ስለ ሀገራችን እኛ ቤዛ እንሁን። ቤተልሔም መወለድ ካለብን እንወለድ። በባሕር መካከል መቆም ካለብን እንቁም። መሰደብ ካለብን እንሰደብ፣ መሰቀል ካለብንም እንሰቀል። ነገር ግን ይህ ሁሉ የኢትዮጵያን ትንሣኤ የሚያመጣ ይሁን። ዛሬ እያደረግነው ያለነውም ይሄንኑ ነው።

ጥምቀት ባህላዊ በዓላችንም ነው። የኢትዮጵያ የመስክ ላይ ትዕይንት ማቅረቢያ በዓል ነው። መስኩና ወንዙ ይታይበታል። ልብሳችን እና የወግ ዕቃዎቻችን ለዓለም እናሳያለን። የፀጉር አሠራራችንን እና ዜማዎቻችንን እናቀርባለን። ጥምቀት የኢትዮጵያ ባህል የአደባባይ ሙዝየም ነው።

ብዙ ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ይሄንን ወቅት ከሚመርጡበት ምክንያቶች አንዱ ይሄ የአደባባይ ሙዝየም ነው። ከገጠር እስከ ከተማ ፤ ከዳር እስከ መሐል፤ ከውጭ እስከ ሀገር የጥምቀት በዓል የእኛነታችን መገለጫ ነው።

ጥምቀት ኅብረ ብሔራዊ በዓልም ነው። የኢትዮጵያን ብሔሮች፣ ቋንቋዎች፣ ባህሎች ለማየት የፈለገ ሰው አንዱ አማራጩ የጥምቀት አደባባይ ነው። በአንድ አደባባይ ሺህ ዓይነቱን ኀብረ ብሔራዊ ማንነታችንን ማየት ይቻላል። የክት የተባለው የባህል ልብሳችን ይወጣል፤ ታይተው የማያውቁ ጌጣጌጦች ብቅ ይላሉ፤ በጥምቀት የኢትዮጵያን መልከ ብዙ ገጽታ ማየት ይቻላል።

እነዚህን የመሰሉ ዕሴቶቻችንን ስላስረከቡን ቀደምቶቻችንን እናመሰግናቸዋለን። ጥምቀት ከተማን ከገጠር ያገናኛል። ብዙዎች ወገኖቻቸውን ለማግኘት ገጠር ይወርዳሉ። የውጭውንም ከሀገር ቤት ያስተሣሥራል። ሚልዮን ወገኖቻችን ጥምቀትን አብረውን ለማክበር ከውጭ ገብተዋል። ይሄም ኅብረ ብሔራዊ ትሥሥራችንን ይበልጥ የሚያጠናክር ነው።

የጥምቀትን አስተምህሮ ለሀገር ግንባታ በመጠቀም፤ ባህላዊ እሴቱን በማጎልበት እና ኅብረ ብሔራዊነቱን በማጠናከር በዓሉን እንድናከብር አደራ እላለሁ።

በድጋሚ መልካም የጥምቀት በዓል ይሁን።


ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ጥር 10፣ 2017 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ( ዶ/ር)

18/01/2025

🚘🚖🚘🚖አመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ ሣያደርጉ መንገድ ላይ ማሽከርከር የሶስት ሺህ ብር ቅጣት አንዳለው ያውቃሉ?🚘🚘🚘አውቶ ሴፍ ቁጥር1/** ሜክሲኮ አደባባይ (ሴፌሪያን ግቢ በጀርባ በር) 🚘🚘ቁጥር 2/** ሀና ማርያም (ወደ ሣሪስ 58) 🚘🚘ቁጥር 3/** ቄራ ቡልጋሪያ (አርባ ምንጭ አሣ አጠገብ) ተሽከርካሪዎትን በወቅቱ ያስመርምሩ🙏🚘🙏🚖🙏🚘🙏🚖

Want your business to be the top-listed Autos & Automotive Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Kirkos K/ketema Wereda 06
Addis Ababa