SHEGER FM 102.1 RADIO

SHEGER FM 102.1 RADIO

Share

SHEGER 102.1FM 'Yenanetew Radio' is the first private radio station in Ethiopia. We are proud to be Ethiopian and we love our country more than anything!

Hear us live on www.ShegerFM.com, dedicated phone numbers, and mobile Apps. ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ መስከረም 23፣2000 ዓ.ም ሥራ የጀመረ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡

ይህ ከአዲስ አበባ በ250 ኪሎ ሜትር ክበብ ውስጥ ፕሮግራም እንዲያሰራጭ ፈቃድ አግኝቶ የረጅም ጊዜ የሬዲዮ ሥራ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተቋቋመው ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአድማጮች ዘንድ ተወዳጅነትን ሊያተርፍ ችሏል፡፡

ሸገር 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡

Sheger FM 102.1 Radio 04/05/2026

‘’አሁንም በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ነን’’ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን!

https://youtu.be/L6n6x7t5r00

ቴዎድሮስ ወርቁ

Sheger FM 102.1 Radio 1 like. " ''አሁንም በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ነን'' በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን"

04/05/2026

ሚያዝያ 26/2018

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ ያሉበት ውስብስበ ችግሮች ካልተፈቱለት ለግንባታ የፈጀውን የ341.1 ሚሊዮን ዶላር ብድርን ለመከፍል እንደሚቸገር ፓርላማው አሳሰበ፡፡

በህዝብ ተወካይዎች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2018 በጀት ዓመት የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1፣ 2 እና 3 የስኳር ፋብሪካዎች እና የኦሞ ኩራዝ 5 ፋብሪካ ግንባታ ፕሮጀክትን ተመልክቶ የግብረ መልስ ሪፖርት አሰናድቷል፡፡

በሪፖርቱ መሰረት የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ የተገነባው በብድር በተወሰደ የ341.1ሚልዮን ዶላር ሲሆን በቀን ፋብሪካው የሚፈጨው የአገዳ መጠን 12 ሺህ ቶን ነው፡፡

ይሁንና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች በመኖሪያ ቤት፣ በውሃ፣ በባንክና በኢንተርኔት አገልግሎት እጥረት እና በጥቅማጥቅምና በደመወዝ ማነስ ምክንያት ፋብሪካውን ለቀው እየሄዱ በመሆኑ የሚጠበቅበትን ያህል እያመረተ እንዳልሆነ ሪፖርቱ ጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም የፋይናንስ አቅርቦት እና የግብዓት አቅርቦትን የመሳሰሉ ከፍተት ችግሮች አሉበት ተብሏል፡፡

በመሆኑም ፋብሪካው ያለበትን የእዳ ጫና ተወጥቶ ትርፋማ እንዲሆን፣ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተጀመሩ የመስኖና የመብራት ኃይል የሰብስቴሽን ግንባታዎችን በፍጥነት እንዲጠናቀቅ አሳስቧል፡፡

የባለሙያዎችን ፍልሰት ለመግታት የበረሃ አበል፣ የደመወዝ ማሻሻያና መሰረታዊ አገልግሎቶችን ማለትም ውሃ፣ ባንክ፣ ኔትወርክ አገልግቶቶችን ማሟላትም ወሳኝ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ስኳር ፋብሪካ የግንባታ ፕሮጀክት ላይ ባደረገው የመስክ ምልከታም ከፍተኛ የሃበት ብክነት መመልከቱን አረጋግጧል ፡፡

በዚህም ለፋብሪካው ተብለው የተገዙ 75% የሚሆኑ ውድ ማሽነሪዎች ያለምንም መጠለያ በሜዳ ላይ ተበትነው እንደሚገኙ ቋሚ ኮሚቴው ተመልክቻለው ብሏል፡፡

በዚህም ምክንያት ከፍተኛ ወጪ ወጥቶባቸው የተጋዙ ማሽነሪዎች የዝገትና የብልሽት አደጋ እንደተጋረጠባቸው በሪፖርቱ መረጋገጡን ተመልክተናል፡፡

ፕሮጀክቱ ተገቢ የሆነ የቴክኒክና የኢኮኖሚ የአዋጭነት ጥናት ሳይከተል መጀመሩን የጠቀሰው ሪፖርቱ አሁን ላይ የግንባታው ሂደት ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል ሲል አስረድቷል፡፡

የፕሮጀክቱን የቀጣይ እጣ ፈንታ ለመወሰን ደግሞ ተገቢውን የቴክኒክ ምርመራ ለማድረግ የዘርፉ ባለሙያዎች ያሉበት ቡድን በማቋቋም በሜዳ ላይ የሚገኙ ማሽነሪዎች አሁን ላይ ያላቸውን የቴክኒክ ብቃትና የጉዳት መጠን በዝርዝር እንዲጠና አሳስቧል፡፡

የፋብሪካውን የአዋጭነት ክለሳ (Feasibility Review) በማካሄድ ፕሮጀክቱን አሁን ባለበት ሁኔታ ማስቀጠል ያለውን ሀገራዊ ፋይዳ እንዲጠናም አክሏል፡፡

ያሬድ እንዳሻው

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7

04/05/2026

ሚያዝያ 26/2018

በ2018 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት 103 አዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናገረ፡፡

አገልግሎቱ ከዋናው ግሪድና ከግሪድ የራቁ በርካታ አዳዲስ አካባቢዎችን ተጠቃሚ ማድረጉን እና ከጤናና ማህበራዊ ተቋማት በተጨማሪ ከ31 ሺህ በላይ አባዎራዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግሯል፡፡

በዚህም 82ቱ ከዋናው የኤሌክትሪክ መረብ (ግሪድ) እንዲሁም 21 የገጠር ከተሞችና መንደሮችን ደግሞ በፀሃይ ኃይል አማራጭ (ኦፍግሪድ) የተገናኙ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡

በተጨማሪም 423,200 አዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ያለ ሲሆን ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ18 ነጥብ 6 በመቶ ብልጫ አለው ተብሏል፡፡

ኃይል ከተገናኘላቸው አዳዲስ ደንበኞች ውስጥ 31 ሺህ 298 ያህሉ አዲስ የኤሌክትሪክ ተደራሽ በሆኑት የገጠር ከተሞችና መንደሮች ተጠቃሚ መሆናቸውን አስረድቷል፡፡

አዲስ ኤሌክትሪክ ካገኙ ደንበኞች መካከል 74.2 ከመቶ የድህረ ክፍያ እንዲሁም 25 ነጥብ 8 በመቶ የቅድመ ክፍያ ቆጣሪ ተጠቃሚ ናቸው፡፡

በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ ደንበኞች ቁጥር 5.64 ሚሊዮን ደርሷል መባሉን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያሳያል ፡፡

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

Sheger FM 102.1 Radio 04/05/2026

የሚያዝያ 26 /2018 የሸገር የቀትር ወሬዎችን በቀጥታ ይከታተሉ……

Sheger FM 102.1 Radio 1 like. "የቀትር ወሬዎች - ሚያዚያ 26 2018 "

Sheger FM 102.1 Radio 04/05/2026

ማንችስተር ዩናይትድ 3-2 ሊቨርፑል

Sheger FM 102.1 Radio 3 likes. "ማንችስተር ዩናይትድ 3-2 ሊቨርፑል "

Sheger FM 102.1 Radio 03/05/2026

"ሚያዝያ 27 የድል በዓል ሲታወስ" መዓዛ ብሩ ከዶ/ር ተካልኝ ወልደማርያም እና ዶ/ር ዮናስ አሽኔ ጋር የተደረገ ወግ

ሚያዝያ 25 / 2018

Sheger FM 102.1 Radio 2 likes. ""ሚያዝያ 27 የድል በዓል ሲታወስ" መዓዛ ብሩ ከዶ/ር ተካልኝ ወልደማርያም እና ዶ/ር ዮናስ አሽኔ ጋር የተደረገ ወግ - ሚያዝያ 25 / 2018"

Sheger FM 102.1 Radio 03/05/2026

መዓዛ ብሩ ከየኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማህበር የስራ ሃላፊዎች ጋር ያደረገችው ወግ

ሚያዝያ 25 / 2018

Sheger FM 102.1 Radio 1 like. "መዓዛ ብሩ ከየኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማህበር የስራ ሃላፊዎች ጋር ያደረገችው ወግ"

Sheger FM 102.1 Radio 02/05/2026

ከዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ መሥራች መቶ አለቃ ትዕዛዙ ኮሬ ጋር የተደረገ ጨዋታ 4ኛ ሳምንት ክፍል - 2
ሚያዝያ 24/2018

Sheger FM 102.1 Radio 1 like. "ከዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ መሥራች መቶ አለቃ ትዕዛዙ ኮሬ ጋር የተደረገ ጨዋታ 4ኛ ሳምንት ክፍል - 2"

Sheger FM 102.1 Radio 02/05/2026

ከዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ መሥራች መቶ አለቃ ትዕዛዙ ኮሬ ጋር የተደረገ ጨዋታ 4ኛ ሳምንት ክፍል - 1
ሚያዝያ 24/2018

Sheger FM 102.1 Radio 1 like. "ከዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ መሥራች መቶ አለቃ ትዕዛዙ ኮሬ ጋር የተደረገ ጨዋታ 4ኛ ሳምንት ክፍል - 1"

Sheger FM 102.1 Radio 02/05/2026

የጣሊያን ወረራ 90ኛ ዓመት ሲታወስ! - ሚያዝያ 24/2018 ዓ.ም

https://youtu.be/d_Aue0QhmjY?si=K5ffQMRYGvVhsVht

በተፈሪ አለሙ

Sheger FM 102.1 Radio ትዝታ ዘ አራዳ - የጣሊያን ወረራ 90ኛ ዓመት ሲታወስ

02/05/2026

ሚያዝያ 24/2018

የመንግስትን ጨምሮ በፋብሪካ እና የአገልግሎት ዘርፍ የሚሰሩ ሰራተኞች፣ የስራና የኢኮኖሚ ሁኔታዎችን ለማሻሻል በማህበር የመደራጀት ህገ መንግስታዊ መብት አላቸው።

የአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ ደግሞ ለመንግስት ሰራተኞች የመደራጀት መብት አይሰጣቸውም።

በዚህም የተነሳ ተደራጅተው መብቴ ተጣሰ ብለው ለመከራከርም ሆነ ለመታገል አልቻሉም ተብሎ ይነሳል።

የመንግስት ሰራተኞች የመደራጀት መብት መፍትሔ የሚያገኘው እንዴት ነው?

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…. https://youtu.be/nPhrUeUcrkk

ንጋት መኮንን

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7

02/05/2026

ሚያዝያ 24/2018

ዘንድሮ 34 የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታቸው ተጠናቅቆ እንደሚመረቁ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ተናገረ፡፡

ከ500 በላይ የመንገድ ፕሮጀክሮችን እየሰራ መሆኑን የሚጠቅሰው አስተዳደሩ ከግማሽ በላዩ እየተሰሩ ያለው በሃገር ውስጥ ስራ ተቋራጮች ነው ብሎናል፡፡

አንዱና አካባቢ ከሌላው ገጠሩን ከከተማው የሚያገኛኙ የመንገድ ግንባታዎች፣ ጥገናዎችና የዲዛይን ስራዎች እየተሰራባቸው ያሉ ከ500 በላይ ፕሮጀክቶች እንዳሉ የነገሩን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር መሃመድ አብዱራህማን፣ ከእነዚህ መካከል የፈጣን መንገዶችን፣ ክልሎችን እርስ በስርስ የሚያገናኙ፣ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ተነስተው በ5 አቅጣጫ የሚወጡ ፕሮጀክቶች ናቸው ብለውናል፡፡

ለመሆኑ የኢትዮጵያ የመንገድ ሽፋን ምን ያህል ደርሷል?ያልናቸው ሃላፊው ከ24ዓመታት በፊት 26 ሺህ ኪሎ ሜትር የነበረው የኢትዮጵያ የመንገድ ሸፋን አሁን 180 ሺህ ኪሎ ሜትር ደርሷል፤ከዚህም ውስጥ 30 ሺህ ኪሎ ሜትሩ በፌድራል ደረጃ ያለ ነው ብለዋል፡፡

በዘንድሮ ዓመትም በመላው ኢትዮጵያ እየተገነቡ ያሉ 34 የመንገድ ፕሮጀክቶች ስራቸው ተጠናቅቆ ይመረቃሉ ሲሉም ያስረዳሉ፡፡

ከዚህ ቀደም የመንገድ ግንባታን ጨምሮ በአጠቃላይ የግንባታው ዘርፍ የስራ ተቋራጮችና አማካሪ መሃንዲሶች በውጭ ምንዛሪ ከሌሎች ሃገራት መጥተው የሚሰሩ ነበሩ የሚሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሃገር ቤት ባለሙያዎቻችን አቅም በብዙ መንገድ እየተገነባ በመሆኑ ከግማሽ በላይ እስከ 55 በመቶ የሚሆኑ ስራዎቻችንን በእነዚሁ ባለሙያዎች ነው የምናሰራው፤እንደውም ሙሉ በሙሉ በራሳችን ባለሙያዎች የመስራት ውጥን አለን ሲሉም ያስረዳሉ፡፡

እየተገነቡ ያሉ እነዚህ የመንገድ ፕሮጀክቶች በወሰን ማስከበር ችግሮች፣ በግንባታ እቃዎች መወደድና፣ በግጭቶች ምክንያት ፈተና ውስጥ ቢሆንም ስራቸው ተቋርጦ የነበሩ 14 የመንገድ ፕሮጀክቶችን በዚህ ዓመት ስራቸውን እንደገና ማስጀመሩን መናገሩ ይታወሳል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…. https://tinyurl.com/2jxz5p7f

ምንታምር ፀጋው

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Addis Ababa Bahirdar Road
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 00:00
Tuesday 08:00 - 00:00
Wednesday 08:00 - 00:00
Thursday 08:00 - 00:00
Friday 08:00 - 00:00
Saturday 08:00 - 01:00
Sunday 08:00 - 00:00