Kambata Tube
👉የከምባታ ብሄረሰብ የባህል ፤ የወግ ፤ የቋንቋ እና የማንነት ገፅ ነው። ሼር ፤ ላይክ ኮሜንት በማድረግ ለሌሎችም እንዲደርስ በማድረግ ይተባበሩኝ።
03/05/2026
#ማንደራሜ
03/05/2026
03/05/2026
አቤል ብርሃኑ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ የጉዞ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሽልማትን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2018 በተለያዩ ሀገራት ጉብኝት በማድረግ እንቅስቃሴዎቹን በራሱ ዩቲዩብ የሚያጋራው አቤል ብርሃኑ (የወይኗ ልጅ) የአፍሪካን ጎልደን አዋርድስ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ የጉዞ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሽልማትን አሸንፏል፡፡
አቤል ብርሃኑ በዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ የጉዞ ተፅዕኖ ፈጣሪ ዘርፍ ለመጨረሻ የቀረቡትን ሶስት አፍሪካዊ ዩቲዩበሮችን በመበለጥ ነው ማሸነፍ የቻለው፡፡
ትናንት በኬኒያ መዲና ናይሮቢ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት በዩቲዩብ ከ2 ሚሊየን በላይ እንዲሁም በፌስቡክ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ ተከታዮች ያሉት አቤል ብርሃኑ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
አቤል ሽልማቱን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መልዕክት÷ ”ኢትዮጵያን ወክለን ተሸልመናል” ሲል ደስታውን አጋርቷል፡፡
በርካታ ሀገራትን አቋርጬ የራሴ አህጉር አፍሪካ እውቅና ስትሰጠኝ የሚሰማኝ ደስታ ወደር የለውም ብሏል።
በአሮጌ ስልክ ካሜራ የሀሳብ ውጥኑን ሲጀምር ዓለምን የማየት እና ታሪኮችን የማካፈል ህልም እንደነበረው አስታውሶ÷ ህልሙ እንዲሳካ ከጎኑ ለነበሩ ተባባሪዎቹ ምስጋና አቅርቧል፡፡
Kambata Tube @ዋና ደጋፊዎችደጋፊዎች
02/05/2026
ቃሉ ፑቲክ በኢንስታግራም (Instagram) ታሪክ አዲስ ሪከርድ ሰበረ!
ኢትዮጵያዊው ቃሉ ፑቲክ (Kalu Putic) በኢንተርኔት ዓለም ላይ አስገራሚና ታሪካዊ የተባለለትን ስኬት አስመዝግቧል።
ቃሉ በኢንስታግራም ገጹ 1 ሚሊዮን ተከታዮችን (1M Followers) ለማግኘትና ከደጋፊዎቹ ጋር ደስታውን ለማክበር በዝግጅት ላይ ሳለ፣ ነገሮች ግን ከእሱ እቅድና ግምት በላይ ሆነዋል።
ባሳለፍነው አንድ ለሊት ብቻ በለቀቃት አንዲት "Viral" የሆነች ቪድዮ ምክንያት፣ የገጹ ተከታዮች ቁጥር በከፍተኛ ፍጥነት በመጨመር ከ1 ሚሊዮን ተነስቶ 2.5 ሚሊዮን ላይ አልፏል።
በአሁኑ ሰዓትም ተከታዮቹ ቁጥር 2.8 ሚሊዮን ላይ ደርሷል።
እሱ ለ1 ሚሊዮን ተከታዮች የደስታ መግለጫ ዝግጅት ላይ እያለ፣ አድናቂዎቹ ግን በድንቅ የፈጠራ ጥበቡ ተማርከው ከ2.8 ሚሊዮን በላይ አድርሰውታል።
ይህ ስኬት ቃሉን በኢንስታግራም ገጽ ላይ ከ2.8 ሚሊዮን በላይ ተከታዮችን በማግኘት የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ ያደርገዋል።
በፈጠራ ስራዎቹ ዓለምን እያነጋገረ የሚገኘው ይህ ወጣት፣ የኢትዮጵያን ስም በዓለም አቀፍ የዲጂታል መድረክ ላይ በጉልህ እያስጠራ ይገኛል።
ለቃሉ ፑቲክ እና ለጥበብ አድናቂዎች በሙሉ
እንኳን ደስ አላችሁ!
👏👏👏
© ጉርሻ page
🌴🌴🌴
02/05/2026
30/04/2026
የእኛ የከምባታ 777 ወዳጅ የሆነው ምርጡ ወንድማችን Aklilu Tesfaye የ crown of humanity Award እጩ ነው ከታች የተቀመጠውን ሊNክ እየተጫናችሁ ምረጡ።
https://crownofhumanityawards.org/vote
30/04/2026
ውለታችን በጥይት ተከፈለን!
ታላቋ ኢትዮጵያ አፍሪካውያንን ነፃ አውጥታለች ቢባል ማጋነን አይሆንም። በባርነት ስር ላሉ ጥቁር ህዝቦች የገንዘብና የመሳሪያ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ ጣሊያንን መቀመጫውን ገርፋ ያባረረችው ነፃዋ ሐገራችን ለጥቁር ህዝብ ሁሉ በጨለማ ውስጥ የምትታይ የነፃነት ብርሃን ጭላንጭል ሆና ኖራለች።
ኢትዮጵያ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ማቋቋሟ ወይም ደቡብ አፍሪካን ከአፓርታይድ፣ ዙምባቤን ከሮዴዢያ Rhodesia) ስርአት ወዘተ ለማላቀቅ በከፈለችው ዋጋ ብቻ ታሪኳ አያበቃም። በአፍሪካ ለመጀመሪያ ግዜ የነጭን አምባገነናዊነት ይታገል ለነበረው ኔልሰን ማንዴላ ዜግነት በመስጠትም የመጀመሪያዋ ሐገር ነች።
ዛሬ የጥቁሮች የነፃነት symbol ሆኖ የሚታየው ኔልሰን ማንዴላ ያለ ኢትዮጵያ ምንም ነበር። አለም ፊቷን በደቡብ አፍሪካ ጥቁሮች ላይ ስታዞር፣ ምድር ስትከፋባቸው፣ በየመንገዱ ሲገደሉ፣ እንደባሪያ ሲረገጡ፣ በውሻ ሲበሉ፣ የነፃነት አርማዋ ኢትዮጵያ ጥቁር ልጇን ከደቡብ አፍሪካ አምጥታ፣ ሐገሩ ፊት በነሳችው ግዜ ክቡር የሆነውን የኢትዮጵያ ፓስፖርት ሰጥታ፣ አሰልጥናና አስታጥቃ ወደሐገሩ ልካዋለች።
ለዚህ ውለታችን የደቡብ አፍሪካ ዜጎች ዝቅ ብለው እጅ ሊነሱን ሲገባ ከሐገራችን ውጡ ብለው ተሰለፉብን። በየሜዳው ተኮሱብን። ውለታችን በጥይት ተከፈለን።
የኢትዮጵያ ኤምባሲም ሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይሄንን ታሪክ ለደቡብ አፍሪካውያኑ ሊያስታውሳቸው ይገባል። እኛ ነፃነትን ያጎናፀፍናቸው የዘመናት ባለውለታቸው እንጂ ጠላት አይደለንም።
Kambata Tube
ከMaster Abinet Kebede እና Meskelu Yohannis 2 የአድናቂ ባጆች ተቀብያለሁ።
30/04/2026
ይድረስ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት (United Nations)
እኛ የሰውነት ክብርን እና የሰብአዊ መብትን እንደ መሰረታዊ እሴት የምናክብር ሰዎች ሆነን፣ ዛሬ በልብ የሚያቃጥል ጥሪ ለመምጣት ተገደድን።
በደቡብ አፍሪካ ኑሮን ለማሸነፍ በተሰደዱ ንጹሃን ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግድያ፣ ዝርፍያ እና ግፍ ከሰውነት ወጥቶ የሚያስፈራ ደረጃ ደርሶአል። ሕይወታቸውን ለማዳን ኑሮን ለማሸነፍየተሰደዱ ሰዎች ዛሬ በፍርሃት ውስጥ እየኖሩ ናቸው፤ ቤታቸው ተቃጥሎ፣ ንብረታቸው ተዘርፎ፣ ሕይወታቸው በአደጋ ውስጥ ተጥሏል።
ይህ የሚፈጸመው ግፍ ፤ ሰው በሰው ላይ የሚያደርሰው እንደዚህ ያለ አሰቃቂ አደጋ በ21ኛው ክፍለ ዘመን መኖሩ የማይታገስ ነው። የተገደሉ ሰዎች ወንድሞቻችን ናቸው፣ እህቶቻችን ናቸው፣ ሕፃናት ናቸው እነሱ ቁጥር አይደሉም፤ ሕይወት ናቸው።
ስለዚህ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ እንዲህ ያለ ግፍ እንዲቆም በፍጥነት እና በግልጽ እርምጃ እንዲወስዱ እንጠይቃለን። የንጹሃን ደህንነት እንዲጠበቅ፣ የሰብአዊ መብት እንዲከበር፣ የፍትሕ ስርዓት እንዲሰራ ግዴታ አለብዎት።
ዝምታ በዚህ ጉዳይ ላይ ከግፍ ጋር መተባበር ነው። ዛሬ የሚያስፈልገው እርምጃ ነው።
የንጹሃን ደም እየፈሰሰ ነው፤ ዓለም ግን ዝም ብሎ ሊያይ አይገባም። እባክዎት ይህን ግፍ አቁሙ፤ ሰውነትን አድኑ፤ ፍትሕን አስመልሱ።
ከታላቅ ኀዘንና ከጽኑ ጥሪ ጋር።
To: UN
We, as individuals who deeply value human dignity and fundamental human rights, are compelled to raise an urgent and heartfelt appeal.
The violence currently being inflicted upon innocent migrants in has reached an alarming and inhumane level. Killings, looting, and acts of brutality have created an environment of fear and devastation. People who fled in search of safety and a better life are now living in terror—their homes burned, their property destroyed, and their lives placed at grave risk.
Such atrocities—humans inflicting this level of suffering upon others—are unacceptable in the 21st century. Those who have lost their lives are not statistics; they are our brothers, our sisters, and our children. They are human beings whose lives mattered.
Therefore, we urgently call upon the United Nations to take immediate and decisive action to stop these violations. It is your responsibility to ensure the protection of innocent lives, uphold human rights, and support the rule of law.
Silence in the face of such injustice is complicity. What is needed now is action.
Innocent blood is being shed, and the world must not stand by in silence. We implore you to act—stop the violence, ..
አን ጠምባርቹ
#የማዳምቅመም #ዱራሜ #ሐምበርቾ777 #ከምባታ #ማዕከላዊኢትዮጵያክልል
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Mekanisa
Addis Ababa
0000