Markos Tewodros - Mac

Markos Tewodros - Mac

Share

Not I, but Jesus �

12/08/2026

አንዳንዴ እግዚአብሔር ራሱ ያለንበትን ሁኔታ ይቀያይረዋል። መረጋጋት እንዳይኖረን አካባቢያችንን ሁሉ ወደ አልጠበቅነው ሁኔታ ቀይሮ ረግቶ የነበረውን ሁሉ እንዲተራመስ ያደርገዋል። ምናልባት ይሄ ሁሉ ነገር የሚሆነው እኛን ወደሚፈልገው ለመቀየር ይሆን?

11/08/2026

ሁሉም ሰው ምን ላይ አንዳለህ፣ ምን እየሰራህ እንደሆነ ማወቅ የለበትም። አንዳንድ ጊዜ የዝምታ ነው፤ ዝም ብለህ ራስህ ላይ የመስራት፣ የመማር፣ የማወቅ፣ ራስህን ማሳደግ እና የማሻሻል ጊዜ። ሁሉም እርምጃ ታዳሚ፤ እያንዳንዱ ስኬትም ማስታወቂያ አይፈልግም። አንድ ቀን ወደ ኋላ ዞር ብለህ ስታይ፣ አንተ ዝም ብትል እንኳን ስራህ የሚናገር ሆኖ እስክታየው አንገትህን ደፍተህ ስራ።
እድገት ጩኸት አይፈልግም። 🙏✨

08/08/2026

🌱 አንዳንድ መተው ማጣት አይደለም!
አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር የእኛ ብለን የምናስባቸውን ነገሮች እንድንተው ይጠይቀናል። የእኛ ያልሆነን ነገር መተው ቀላል ይሆን ይሆናል፤ የእኛ የሆነና ውድ የምንለዉን ነገር መተው ግን ፈታኝ ነው።
ከመተዋችን በፊት ከዛስ ብለን መጠየቅ፤ መራመድ ከመጀመራችንም በፊት መዳረሻውን መረዳት እንፈልጋለን። በመታዘዛችን ውስጥ ከምንተወዉ ሻል ያለን ነገር እንደምናገኝ ማወቅም እንፈልጋለን።
መፅሐፍ ግን እንዲህ ያስተምረናል፦
አብርሃም ወደ ተስፋው ከመግባቱ በፊት "ውጣ" በሚለው ቃል ላይ ብቻ ታምኖ፤ ከሚያዉቀዉ ነገር ሁሉ ተለይቶ መዉጣት ነበረበት።
ጼጥሮስ በውሃ ላይ መራመድ ምን እንደሆነ እንዲያውቅ፤ ከሚተማመንበት ታንኳው ላይ ወርዶ ዉሃዉ ላይ መቆም ነበረበት።
ሙሴ እስራኤልን ወደ ነፃነት ከምራቱ በፊት ምክንያቶቹን እና ፍርሃቶቹን ሁሉ ማሸነፍ ነበረበት።
ልክ እንደዚሁ እግዚአብሔር እኛንም አንዳንድ ነገሮችን በእምነት እንድንተው ይጠይቀናል።
ወዳጄ እግዚአብሔር እንድትተውለት እየጠየቀህ ያለው ነገር ምን ይሆን?
አጥብቀህ የያዝከውን ወዳጅነት ይሆን?
ነገ እንድትደርስበት የምትጓጓውን ህልምህን ይሆን?
ያለፈ ህመምና ቁስልህን ይሆን?
ፍርሃቶችህን ይሆን?
ወይስ ሁሉንም ነገር የመቆጣጠር ፍላጎትህን?
እውነት ለመናገር… መተው ከባድ ነው።
ግን ግን አንዳንድ ነገሮችን እኮ አጥብቀን የምንይዘው ስንለቀው ምን እንደሚሆን ስለምንፈራ ነው 😉 አይደለም እንዴ?
ወዳጄ አንዳንዴ እግዚአብሔር የበለጠ ጠንክረህ እንድትታገል ሳይሆን የበለጠ እንድታምነው እና እንድትተውለት ይፈልጋል።
በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ መሆን ትችላለህ 👉 ለእግዚአብሔር የምትሰጠው ነገር፣ በራስህ እጅ ካለው ነገር የበለጠ ደህንነት አለው። 🤍
“እርሱ ስለሚያስብላችሁ ጭንቀታችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉ።”
1ኛ ጴጥ 5፥7
ምናልባት ዛሬ እግዚአብሔር ለረጅም ጊዜ ተሸክመህ የቆየኸውን አንድ ነገር እንድትተው እየጠየቀህ ይሆናል። ምክንያቱን ላታውቅ ትችላለህ፤ ቀጥሎ ምን እንደሚሆንም ላታውቅ ትችላለህ። ነገር ግን ነገን በሚያውቀው አምላክ መተማመን ትችላለህ።
አጥብቀህ የያዝከውን ነገር ልቀቀው፤ በእግዚአብሔር ታመን፤ እተዋለሁ በል፣ ተውለት ❤️
አንዳንድ መተው ማጣት አይደለም ማትረፍ ነው!

05/08/2026

🌅 One Minute with God
እግዚአብሔር አይረሳህም!
ሰማይ ዝም ሲል 😊
በፀሎት ፀንተህ፣ በእምነት ጠብቀህ ሰማይ ግን ዝም ሲል ይሄንን እውነት አስታውስ፦
ሲሠራ ማየት ባትችል እንኳን፣ ሥራውን አቁሟል ማለት አይደለም። ዘር ከአፈር በታች ረጅም ጊዜ ካደገ በኋላ ወደ መሬት እንደሚወጣ አረንጓዴ ቅጠሉም እንደሚታይ፤ እግዚአብሔር የገባውን ተስፋ ለመፈጸም በስውር ይሰራል። በእኛ ሳይሆን በእርሱ ጊዜ ደግሞ ይበቅላል።
📖 "እርሱን ተስፋ ለሚያደርጉት፣ ለሚፈልገውም ሰው እግዚአብሔር መልካም ነው። ሰው የእግዚአብሔርን ማዳን፣ ዝም ብሎ ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው።"
ሰቆ ኤር 3፥25
ተወዳጅ ሆይ ለ10 ሰከንድ ይሄንን ጸሎት አብረን እንፀልይ
"አባት ሆይ፣ አንተ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ነህና አመሰግንሀለሁ። የእኔን ክፉ አትወድምና ተመስገን። በተስፋ ስደክም በሚያስችለው ፀጋህ አበርታኝ፣ ትዕግስትን አስታጥቀኝ፣ በእምነት መጠበቅን አስተምረኝ። ፍፁም የሆነውን የአንተን ጊዜ እንድረዳ መንገድህን አሳየኝ። ለእኔ መልካም አሳቢ ነህና ተመስገን። በኢየሱስ ስም፣ አሜን።"
እግዚአብሔር አይረሳንም!

04/08/2026

አንዳንድ ጉዳት ከጠላት ብቻ አይመጣም። አንዳንዴ ማንም በሌለበት ጊዜ ከጎኑ የቆምክ፤ ሲወድቅ ያነሳኸው፤ በጸሎት ያሰብከው እና የረዳኸው ወዳጅህ የህመምህ ምክንያት ይሆናል። በምስጋና ፋንታ ጉዳት፣ በፍቅርም ፋንታ ቁስል ይመለሳል። በእንደዚህ አይነቱ ጊዜ ውስጣችን መልካም በሆንባቸው ጊዜያት ለመቆጨት፤ ፍቅርን ደግሞ ለመጣል ይፈተናል።
መጽሐፍ ግን እንዲህ ያስተምረናል።
ህልመኛው ዮሴፍ በህልሙ መጀመሪያ በወንድሞቹ ቢከዳም፤ እግዚአብሔር ግን መከዳቱን ወደ በረከት ለውጦለታል። ዳዊትንም ደጋግሞ ምሕረትን ያደረገለት ሳኦል እስከመጨረሻ ድረስ አሳዶታል። ጌታ ኢየሱስ በሽተኞችን ፈወሰ፣ የተራቡትን መገበ፣ ደሆችን አፅናና፣ ፍቅርን ሰበከ፤ ሰዎች ግን የመለሱለት መስቀልን ነበር።
እና ወዳጄ ሰዎች መልካምን በክፉ ቢመልሱህ ምን ይገርማል?
ይልቅ ከእግዚአብሔር እንጂ ከሰዎች ምንም ነገር አትጠብቅ፤ መልካምነትህን ማንም አይንጠቅህ፤ አገልግሎትህን፣ መውደድህን፣ ይቅር ማለትህን አታቁም።
መልካም ያረክላቸው ሁሉ ቢረሱህ፤ ፍቅርህን በጥላቻ፣ መልካምነትህን በክፋት ቢመልሱ እንኳን እግዚአብሔር ግን ፈጽሞ አይረሳም። ለክፉ የተባለውን ሁሉ ለበጎ ይለውጥልሀልና አትድከም። የተሰወረውን መልካሙን ስራህን ሁሉ ያያል፤ ያፈሰስከውን እንባ ሁሉ ያውቃል፤ የምታልፍበትንም ሁሉ ያውቃል፤ በጊዜው ደግሞ ይክስሃል።
"በጎ ነገር ከማድረግ አንታክት፤ ተስፋ ካልቈረጥን ጊዜው ሲደርስ መከሩን እናጭዳለን። ስለዚህ ዕድሉ ካለን ለሰው ሁሉ፣ በተለይም ለእምነት ቤተ ሰቦች መልካም እናድርግ።"
(ገላትያ 6፥9)
ሰዎች ሊለወጡ ይችላሉ፤ እግዚአብሔር ግን ሁልጊዜ መልካም ነው።

01/08/2026

አንዳንዴ ህይወት ካልጠበቅናቸው ፈተናዎች ጋር ያጋፍጠናል። ፍርሃት፣ ጥርጣሬ፣ ኪሳራ፣ ተስፋ ማጣት፣ እና....ሌሎችም ከአቅማችን በላይ የሆኑ ፈተናዎች። እንደዚህ አይነቱ ጊዜ እውነት ግን እግዚአብሔር አለ? ያየኛል? ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል።
ዳንኤልም ተመሳሳይ ነገር ገጥሞት ነበር።
ወንጀለኛ ሆኖ ሳይሆን ለአምላኩ ታማኝ በመሆኑ ብቻ ወደ አንበሶች ጉድጓድ ተጥሎ ነበር። አንዳንዴ ሳስበው የወጣውን ህግ ፈርቶ ፀሎቱን ቢያቆም ምናልባትም ራስን የመጠበቅ አይነት Smart move ይመስል ነበር። እርሱ ግን ከፍርሃት ይልቅ እምነትን መረጠ።
እግዚአብሔርም አላሳፈረውም፤ ማንም ሊረዳው በማይችልበት ጊዜ ደረሰለት። መልአኩንም ልኮ የአንበሶቹን አፍ ዘጋ። ለሞት ከተደገሰለት ቦታ ውስጥ በደህና አወጣው። የርሱ ነገር አበቃ የተባለለት ቦታም ለምስክርነቱ መድረክ ሆነው።
ወዳጄ ትናንት የዳንኤልን መከራ ወደ ምስክርነት የቀየረው ጌታ ዛሬም ከእኛ ጋር አለ፤ ያየናል። ወደ ጉድጓድ ከመጣል ባያድነን እንኳን በጉድጓዱ ውስጥ ግን አብሮን አለ።
ከእግዚአብሔር ጋር በረሃም ቢሆን እንደ ኤደን ገነት ነው። 😊
Faith doesn't remove the lion. It reminds you that God is with you in the den."

29/07/2026

🌊 እምነት ከፍርሃት በላይ
ፍርሃት፦ ‘አይቻልም’ ሲል
እምነት ግን፦ ‘ከእግዚአብሔር ጋር ይቻላል’ ይላል።

በዘጸዓት 14 ላይ እስራኤላውያን በቀይ ባሕር ዳር በቆሙበት ጊዜ፣ በፍርሃት ተይዘው በጭንቅ ነበሩ። ከኋላ የፈርዖን ሠራዊት፤ ከፊት ደግሞ ቀይ ባሕር። የነበሩበት ሁኔታ በሰው ዓይን ሲታይ ተስፋ የሌለው ጨለማ ይመስል ነበር። እግዚአብሔር ግን ሰው ያላየውን መንገድ አስቀድሞ አዘጋጅቶ ነበር።

አንዳንዴ በእኛም ሕይወት እንዲህ ይሆናል። መውጫና ማምለጫ የሌላቸው ከሚመስሉ ትላልቅ ችግሮች ጋር ፊት ለፊት እንጋፈጣለን። በእንደዚህ አይነቱ ጊዜ ፍርሃት ችግር ችግሩን እንድናይ እና ተስፋ እንድንቆርጥ ይገፋፋናል። እምነት ግን ሁሌም ከችግሩ የሚበልጠውን እግዚአብሔር እንድናይ ይጋብዘናል።
ወዳጄ የእኛ እግዚአብሔር ልዩ ነው! ለእርሱ ዝግ የሚባል መንገድ የለም። ትናንት ቀይ ባሕርን ከፍሎ በባሕሩ መካከል መንገድን ያደረገው አምላክ ዛሬም ለልጆቹ መንገድን ያዘጋጃል።

ስለዚህ ፍርሃትን ሳይሆን እምነትን ምረጥ። እርሱ ነገን ቀድሞ እየሠራ ነውና። ችግርህ የተቀደመ ነው! ነገህ የተቀደመ ነው!

🙏 ይህ መልእክት ካበረታታህ፣ ተስፋን ለሚፈልግ ወዳጅህ አጋራው።

28/07/2026

#ማመን ይሻላል
Faith keeps you walking. Fear makes you sink. Keep your eyes on Jesus.
በዮሐንስ 14 ላይ ጴጥሮስ ምናልባት በታሪክ ውስጥ ማንም ሰው ያልሞከረውን ነገር አደረገ። በባህር መካከል ከታንኳው ወርዶ በውሃው ላይ በእምነት ተራመደ።
አይኑም በኢየሱስ ላይ በነበረበት ጊዜ ሁሉ ውሃው ሊያሰጥመው አልቻለም። የማይቻለውም ሁሉ ተቻለው። አይኖቹን ከጌታው ላይ አንስቶ ማዕበልና ነፋሱን ባየ ሰአት ግን ፍርሃት አሸነፈው፤ መስጠምም ጀመረ።
እናማ ወዳጄ የህይወት ፈተናዉ ብዙ ነው፤ ችግሩም አያልቅም፣ አይኖቹን በሚያልፈው ላይ ላደረገ ሰው በነገሮች እርግጠኛ መሆን፣ ነገን ማመን ከባድ ነው።
ግን ደግሞ የአማኝ ተስፋ መልካም በሆነው በእግዚአብሔር ላይ እንጂ በነገሮች መልካም መሆን ላይ የተመሰረተ አይደለም።
ዛሬ ያለንበት ሁኔታ ምንም ይሁን፤ ሁል ጊዜ ከሁሉ በላይ የሆነውን ጌታ እናስብ፣ ተስፋን የሰጠው የታመነ ነውና አይኖቻችን በእርሱ ላይ ይሁኑ። እግራችን በወጀቡ ላይ ቢሆንም ልባችን ግን በእርሱ ላይ ይሁን፤ ያን ጊዜ ብንወድቅም እንኳን እጃችንን ይዞ ያነሳናል፤ ከወጀቡም በላይ ያራምደናል።
ማቴ 14:31
ዛሬ የሚያስፈራንና የሚያስጨንቀንን ነገር በማሰብ ፈንታ ለጥቂት ጊዜ ስለ ታማኝነቱ አሰናሰላስል። ፍርሃትንም ሁሉ በእምነት እናሸንፍ
say "I choose faith."

27/07/2026

Your gaint have a name but so does your God 😊😍👌
እምነት እንደ ዳዊት! 😊
ፍርሃት ያንን ሁሉ ጀግና ወደ ኃላ ሲያስቀረው እምነት ግን ትንሹን ዳዊት አቆመው።
ሰው ሁሉ ግዙፉን ጎልያድ አይቶ ሲፈራ፤ ዳዊት ግን ትልቁን እግዚአብሔር አይቶ በረታ 😊
ፍርሃት፦ "አትችልም!" ሲል
እምነት ግን፦ "እግዚአብሔር ይችላል!" ይላል።
የአንተ ጎልያድ ምንድን ነው?
- ውድቀት እና አለመሳካት?
- ነገ?
- አዲስ ጅማሬ?
- የሰዎች አስተያየት?...
brother ከዳዊት ጋር የነበረው እግዚአብሔር ዛሬም ከአንተ ጋር ነውና አትፍራ፣ በርታ። ችግርህን በመጠኑ አትለካው፤ ይልቅ አምላክህን በታላቅነቱ እወቀው።
1ኛ ሳሙ 17፥45
🤔

27/02/2026

You may not know what tomorrow holds, but you know who holds tomorrow.

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Addis Ababa
1000