Ym

Ym

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ym, AIDS Resource Center, Addis Ababa.

Photos from Addis Ababa Prosperity Party - ብልፅግና's post 19/12/2024
26/11/2024
Photos from Prospertiy Party Kolfe Keraniyo Sc Branch - ብልፅግና 's post 05/11/2024
31/10/2024

ሀገራዊ ሪፎርምን በተመለከተ

በተለያዩ ዘርፎች ሲከናወኑ የነበሩ ሪፎርሞችን አጠናቀን ሀገራዊ ማንሰራራት የምንጀምርበት ዘመን የመጀመሪያ ምእራፍ ላይ ተገኝተናል፡፡ በመሆኑም በ2017 በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ለውጥ የምናስመዘግብ ይሆናል፡፡ ከዚህ አኳያ ከትናንት እሳቤ ወጥተን በጋራ ወደ ነገ መሻገር አለብን፡፡

Photos from Ym's post 02/10/2024

01/10/2024

ሰላማችንን በማጽናት ልማትን በማሳለጥ ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን በህብር እንተጋለን!

የአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እምርታ የሚለካው በሚኖረው የሰላምና የልማት ቅንጅት ነው። ልማት በሌለበት ሰላምን ማረጋገጥ እንደማይቻለው ሁሉ ያለሰላም ልማት ውጤታማ ሊሆን አይቻልም። ለዚህም ነው
ሰላምና ልማት የማይነጣጠሉ የሀገር የብልጽግና መሰረት ናቸው የምንለው።

ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የመበልጸግ ራዕይ አንግባ በመታተር ሰላምን ከልማት ጋር አቀናጅታ ወደ ከፍታ እየገሰገሰች ነው። ይህ ትውልድ ለለውጥ የሚሰራ ለነገ ዛሬ እየተጋ ምንዳን ለማሻገር በህብር ደምቆ በወል የሚሰራ አርበኛ ነው። ለዚህም በአንድ በኩል ለሰላም እየታተረ በሌላው ጎን ስለልማት አስቦ ለለውጥ ይሰራል።

ብሔራዊነት የአንድነት ምሰሶ መሆኑን በማመን የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በመጠበቅ ቃልን በተግባር እያፀና ምንዳን ለማሻገር ልማትና ሰላም ቁልፍ ሚና አለው። ሰላሟ የተረጋገጠ ሀገር መልማትና የህዝብን መሰረታዊ ጥያቄዎች መመለስ የሚያስችል አቅም ማጎልበት ወሳኝ ነው። ብልጽግና ፓርቲ ለተረጋጋ ሀገረ መንግስት ግንባታና ህብረብሔራዊ አንድነት ሰላም ብቸኛ መንገድ በመሆኑ ቅድሚያ ሰጥቶ ይሰራል።

ሰላም ሲኖር ልማትን ማሳላጥ እንደሚቻለው ሁሉ በበቂ ሁኔታ ልማት ባልተረጋገጠበትና መሰረታዊ ፍላጎቶች ባልተሟሉበት ሁኔታ ደሞ ሰላምን ማስፈን ይከብዳል። ለዚህ ነው ልማትና ሰላም የአንድሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው የምንለው። በዚህም በወንድማማችነትና እህትማማችነት ህብር ስለሰላም ቆመን ለልማታችን እየተጋን ከፍታችንን እናረጋግጣለን።

በወንድማማችነትና እህትማማችነት ህብረብሔራዊነትን አጽንተን በተደመረ አስተሳሰብና በወል እውነቶቻችን በጋራ ቆመን ስንተጋ በታሰበው ጥራትና ፍጥነት ካሰብንው የከፍታ ማማ ላይ በመውጣት ፤ ስለሰላም ለሀገራዊ ልዕልና በጋራ ቆመን ህልውናችንን በማስጠበቅ የህዝባችንን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ባከበረ ልማት ሁለንተናዊ ብልጽግናችንን እናበስራለን።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ ፅ/ ቤት

Want your practice to be the top-listed Clinic in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Addis Ababa