HAQA BAAS
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from HAQA BAAS, Film/Television studio, Addis Ababa.
20/02/2026
በኢትዮጵያ ውስጥ ዋና ዋና ከሚባሉት ሜትሮፖሊታን ከተሞች አንዷ የሆነችው ውቢቷ መቀሌ፤ በአሁኑ ሰዓት ከምንግዜውም በላይ ከፍተኛ ስጋት እና ጭንቀት ውስጥ እንደምትገኝ መረጃዎች እያመለከቱ ነው። በመቀሌ ከተማ የሚገኘው ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ከደቂቃዎች በፊት ያጋራቸው እና በምስሉ ላይ የሚታዩት ትዕይንቶች፤ የከተማዋን አሳሳቢ ወቅታዊ ድባብ በግልጽ ያሳያሉ።
በእነዚህ መረጃዎች መሰረት የመቀሌ መንገዶች ፀጥ ብለዋል፣ ሱቆች ተዘጋግተዋል፣ እንዲሁም አጠቃላይ የከተማዋ ድባብ እጅግ ደብዛዛ እና ቀዝቃዛ ሆኗል። በሰሜኑ በኩል ያለው አስቸጋሪ የጦርነት ስጋት እና ውጥረት በከተማዋ ላይ ያጠላ ሲሆን፤ በቀጣይ ምን ሊፈጠር ይችላል የሚለው ጉዳይ በማይታወቅበት እና እርግጠኝነት በጠፋበት አስጨናቂ ቅጽበት ውስጥ እንደምትገኝ ተጠቁሟል።
የህዝባችን ጭንቀት አብቅቶ፤ ሰላም ለሀገራችን፣ ሰላም ለሰሜኑ የሀገራችን ክፍል እንዲሆን ከልብ እንመኛለን።
20/02/2026
19/02/2026
ልክ እንደ ታዋቂው 'Money Heist' (La Casa de Papel) ፊልም፤ በሀገራችንም እጅግ የተቀነባበረ እና የባንክ አሰራርን በሚገርም ሁኔታ የጣሰ ታላቅ የማጭበርበር ወንጀል ተፈጽሟል። የፌደራል ፖሊስ ባወጣው መረጃ መሰረት፤ በገዳ ባንክ፣ በኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በሌሎች ድርጅቶች ላይ ከ89 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት ያደረሱት ተጠርጣሪዎች ከነግብረ-አበሮቻቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል። ይህ ድርጊት የተፈጸመው ሀሰተኛ የባንክ ዋስትና ሰነዶችን በማዘጋጀት እና የውስጥ ሰዎችን በመጠቀም ህገወጥ የጥቅም ትስስር በመፍጠር ነው።
የዚህ ማጭበርበር "ፕሮፌሰር" ወይም ዋነኛ አስተባባሪ የተባለው የጎደር ዋይን ትሬዲንግ ስራ አስኪያጅ የሆነው ጌታሁን መለስ ልይህ ሲሆን፤ እቅዱን ከውስጥ ሆኖ ያሳለጠው "Inside Man" ደግሞ የገዳ ባንክ አገምሳ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አብዲሳ ቶሎሳ ደበሊ ነው። አብዲሳ የቅርንጫፉን ኃላፊነት፣ ፊርማ እና ማህተም ለዚህ ወንጀል ማስፈጸሚያነት ሲጠቀምበት መቆየቱን ፖሊስ ደርሶበታል። ይህንን ትልቅ የጥቅም ትስስር ያገናኘው፣ ያግባባው እና ሁኔታዎችን ያመቻቸው "Fixer" ደግሞ አበባው መኮንን አረጉ የተባለው ሌላኛው የቡድኑ አባል መሆኑ ተረጋግጧል።
ይህ የተደራጀ ቡድን ለወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን እና ለፈናን መሃመድ በሽር የቀለም ማምረቻ ድርጅት የሀሰት ዋስትና ሰነዶችን በማቅረብ ብቻ ከ43 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሷል። የቡድኑ መሪ ጌታሁን ከዚህ ቀደምም በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ላይ 28 ሚሊዮን ብር፣ እንዲሁም በፍርድ ቤት የታገደን ቤት በሀሰተኛ ሰነድ አሽጦ በንግድ ባንክ ላይ 18 ሚሊዮን ብር ጉዳት በማድረስ ክስ ተመስርቶበት ሲፈለግ የነበረ አደገኛ ተጠርጣሪ መሆኑን ፖሊስ አጋልጧል። በመጨረሻም ይህ የ"Money Heist" ህልም በፌደራል ፖሊስ ብርቱ ክትትል ከሽፏል። ፖሊስ ማህበረሰቡ እንዲህ አይነት ወንጀሎችን በ991 ነፃ የስልክ መስመር ወይም በ EFPApp መተግበሪያ እንዲጠቁም ጥሪውን አቅርቧል።
እናንተስ ይህንን ልክ እንደ ፊልም የተቀነባበረ የባንክ ማጭበርበር እንዴት አያችሁት?
With Hakim Hassen – I just got recognized as one of their top fans!
With Raaziyaa Abdo – I just got recognized as one of their top fans!
19/02/2026
የታላቁ የረመዳን ፆም መግባቱን ተከትሎ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ላይ ሁሌም የሚነሳ አንድ ትልቅ ቅሬታ አለ። በተለይም ህዝበ ሙስሊሙ ፆሙን በሚፈታበት የማፍጠሪያ እና ለሊት ለምግብ በሚነሳበት ሰዓት ላይ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ያጋጥማል።
ይህ ችግር አመት ከአመት የሚደገም በመሆኑ በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን አስነስቷል። ተቋሙ ይህንን የኃይል መቆራረጥ አስቀድሞ በማቀድ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ወይም ማመቻቸት ይችል የነበረ ቢሆንም፤ ሁሌም ግን ይህንን ሲያደርግ አይታይም። በተለይም በአዲስ አበባ፣ ናዝሬት፣ ድሬዳዋ፣ ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች ላይ በፆሙ ወቅት ከፍተኛ የኃይል መቆራረጥ እንደሚከሰት የደረሱን መረጃዎች ያሳያሉ። የሚመለከተው አካል ለዚህ ተደጋጋሚ ችግር አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ አበክረን እንጠቁማለን።
በእናንተ አካባቢስ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ምን ይመስላል?
19/02/2026
አይናለም ትባላለች፤ የትውልድ ቦታዋ ወላይታ ነው። ይህች ወጣት በዱባይ አየር መንገድ ላይ ትኬት ብቻ ተቆርጦላት ተጥላ የተገኘች ሲሆን፤ በወቅቱ የነበረችበት ሁኔታ እጅግ አሳዛኝ እና ልብ የሚነካ ነበር። ከፍተኛ የአእምሮ ህመም ምልክቶች የሚታዩባት አይናለም፤ በአውሮፕላን ጉዞዋ ወቅት ልብሷን እስከማውለቅ የደረሰ መረበሽ ውስጥ የነበረች ቢሆንም፤ አንዳንድ ደግ ኢትዮጵያውያን በጥሩ ሁኔታ ተግባብተውና አረጋግተው ከዱባይ ወደ አዲስ አበባ ቦሌ አየር መንገድ ይዘዋት መጥተዋል።
አይናለም በእጅዋ የያዘቻቸውን ሁለት ስልኮች ሰባብራቸው በመገኘቷ ቤተሰቦቿን በቀላሉ ለማግኘት አዳጋች ሆኗል። በጩኸት እና በእምባ የታጀበ ድምፅ እያወጣች "ደላሎች ጉድ ሰሩኝ፤ ስራ አለ ብለው አታለሉኝ" ስትል ትማጸናለች። እጅግ የሚገርመው ደግሞ ይህች ወጣት እንግሊዝኛ ቋንቋን እጅግ በሚገርም ሁኔታ ጥሩ እንግሊዘኛ መናገር መቻሏ ነው። በአሁኑ ሰዓት "ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ውሰዱኝ፤ እሳቸውን ማግኘት እፈልጋለሁ" በማለት ደጋግማ እየጠየቀች ትገኛለች።
በአሁኑ ሰዓት በቦሌ አየር መንገድ ሰራተኞች እንክብካቤ እየተደረገላት ይገኛል። በመሆኑም ይህችን ወጣት የምታውቁ ወይም ወላይታ አካባቢ የምትገኙ ወገኖች ቤተሰቦቿን እና ዘመዶቿን ፈልጋችሁ እንድታገኟቸው እና ከልጃቸው ጋር እንድታገናኟቸው በትህትና እንጠይቃለን። የሰው ልጅ በሰው ሀገር እንዲህ ሲገፋ እና ሲንከራተት ማየት እጅግ ያማል፤ ሁላችንም መረጃውን በማጋራት አጋርነታችንን እናሳይላት።
19/02/2026
የሱዳን ጦ-ርነት አልቋል ይባላል። RSF ተሸን-ፏል ይባላል። የሆነ ሌሊት ከእንቅልፍህ ስትነሳ ቡድኑ ሶስት አራት ከተሞችን መቆጣጠሩን በዜና ትሰማለህ። ይሄ የሆነው በጦ-ር ተሸከርካሪዎቹና በሶስት አራት ድ-ሮኖቹ ምክንያት ነው።
ሰሞኑን በኢትዮጵያ ከተሞች የመ-ከላከያ ሰራዊት የጦ-ር ተሽከርካሪዎች ሲጓጓዙ በተለያዩ የሶሻል ሚዲያ ተጠቃሚዎች ተጋርቷል። ይሄንን ተከትሎ ለኤርትራ መንግስት ቅርብ የሆኑ ፓለቲከኞች ስጋታቸውን ሲገልፁ ተመልክተናል። ኤርትራ ጦሯን በአግባቡ አለማደራጀቷን በመተቸት እየወቀሱ ነው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የጦ-ር ተሽከርካሪዎች አይነትና ብዛት በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa
28/11/2025